Historical Books 2 Kings

The Beginning of Revival

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 279 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 2ነገስት መፅሀፍት ዉስጥ እንደ ሰራነው አንድ ጭብጥ የሚለመድ ይመስላል - አብዛኞቹ ነገስታቶች በእግዚአብሄር እይታ ክፉ ነገር አደረጉ ፡፡ በሁሉም ትንሽ በእግዚአብሄር እይታ መልካም ነገር ወዳደረጉት ወደ መቀላቀል ንጉሶች ይበተናሉ ነገር ግን ብዙ አልነበሩም ፡፡ በ 2ነገስት 21 የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በ 12 አመቱ ንጉስ ሆነ ፤ በቁጥር 1 መሰረት ከሁሉም በጣም ክፉ ንጉስ ነበር ፤ የምናሴ ልጅ አሞጽ ንጉስ በሆነ ዜ ነገሮች መጥፎ ሆኑ በጣም ክፉም ስለነበረ አገልጋዮቹ በመግደል የአሞፅ ልጅ ኢዮስያስን እንደ ንጉስ በዙፋኑ ላይ አስቀመጡት (ቁጥር 26) ፡፡

በጠቅላላበይሁዳ ላይ 20 ነገስታቶች ነበሩ (ንግስት ጎቶልያን ጨምሮ) ፤ ከእነዚህ ከ20ዎቹ ዉስጥ ስምንቱ በእግዚአብሄር ፊት መልካም ነገር አደረጉ፡ አሳ፣ ኢዮሳፍጥ፣ ዮአስ፣ አሜሲያስ፣ ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ ሕዝቅያስ እና ኢዮስያስ ፡፡ እነዚህ ነገስታቶች ወደ ዳነዉ ዘር ያመለክታሉ ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (22፡ 1-2)፡ ኢዮስያስ ንጉስ በሆነ ጊዜ ስምንት አመቱ ብቻ ነበር 31 አመት አስተዳደረ ፡፡ ኢዮስያስ በእግዚአብሄር ፊት መልካም የሆነዉን በማድረግ በዳዊት መንገድ ተጓዘ (ቁጥር 1-2) ፤ ምዕራፍ 22 ለእግዚአብሄር የኢዮስያስን ጥረት ይመዘግባል ፡፡

2-ነገስት (22፡ 3-7)፡ ቤተ መቅደሱ መልሶ ጠገነ(ሰበሰበ) (ቁጥር 3-7)፡ በአገዛዙ በ18ተኛዉ አመት (በ26 አመቱ) ኢዮስያስ ንጉስ አካዝ ቤተ መቅደሱ ላይ አድርጎት የነበረዉን ዉድመት ለመጠገን በሚል ትዕዛዝ ወደ ቤተ መቅደሱ ወደ ካህኑ ኬልቅያስ ፀሀፊዉን ላከ (ቁጥር 3-6) ፡፡ ኢዮስያስ ኬልቅያስን ገንዘቡን ያለመዝገብ እንዲቆጣጠር አመነው ምክንያቱም ሰራተኞቹ በሀቀኝነት ስለሚሰሩ (ቁጥር 7) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ኬልቅያስን “ ወጣቱ ኢዮስያስ በፈፀመዉ በእዉነተኛዉ ኃይማኖት መነቃቃት እንደ ዋና አንቀሳቃሽ “ ይገልፀዋል ፡፡

2-ነገስት (22፡ 8-20)፡ የህጉ መፅሀፍ ተገኘ (ቁጥር 8-20)፡ በቤተ መቅደሱ ጥገና ጊዜ የህጉ መፅሀፍ ተገኘ (ቁጥር 8) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የህጉ መፅሀፍ “ ግማሹን ወይም ሙሉ ኦሪትን እንደያዘ “ ይገልፃል በተጨማሪም “ ጠፍቶ፣ ተለይቶ ተቀምጦ ወይም በምናሴ ወይም በአሞፅ ክፉ ዘመን ተደብቆ እንደ ሚሆን “ ያመለክቷሉ ፡፡ ኮንስታብል “ ምናልባትምምናሴ ወይም ደግሞ አሞፅ የነበረዉን የእስራኤልን የኪዳን ህግ አጥፈተዉት እንደ ነበር ይመስላል ለማመን ሁሉም ምክንያት ስላለ ኬልቅያስ የሙሴን ህግ እንደ ሚያውቀው ፤ ይህ አስቸጋሪ አይሆንም ምክንያቱም በቀድሞዉ ጊዜ የሚታወቁ ማስረጃዎችም እንኳን ጥቂት ኮፖዋች እንደ ነበሩ “ ይናገራል ፡፡ ኬልቅያስ የህጉን መፅሀፍ እራሱ አንብቡ ለኢዮስያስ ለሚያነብለት ወደ ኢዮስያስ ፀሀፊ ሳፋን አስተላለፈው (ቁጥር 9-10) ፡፡

ስነ መለኮታዊያን ሳፋን ለኢዮስያስ የትኛዉን የህግ መፅሀፍት ክፍል እንዳነበበለት ለመበጋገር ይፈልጋሉ ፤ ብዙዎች ከዘዳግም መፅሀፍ እንደሆነ ያስባሉ ለምሳሌ፡ የእስራኤል ሰዎች እንዴት ክፉዎች እንደ ነበሩ (ዘዳግም 4-13)፣ እግዚአብሄር ጠይቆ እስራኤል ያላደረገዉን ነገርን (ዘዳግም 14-18) ወይም ደግሞ እግዚአብሄር የሚደርገዉን ማስጠንቀቂያ (ዘዳግም 27-30) ፡፡ ለኢዮስያስ መፅሀፍን ሲሰማ የመጀመሪያ ጊዜዉ ስለ ነበር ወደ ፍርሀት ወሰደው ፤ ታላቅ (ፍፁም) የሆነዉን ፀፀቱን ለማሳየት ልብሱን ቀደደ (ቁጥር 11) ፡፡

ኢዮስያስ ከእግዚአብሄር ትንቢታዊ እይታ ስለፈለገ አምስት ሰዎችን ስለ እርሱ ሄደው ከእግዚአብሄር እንዲጠይቁ ፡ ካህኑ ኬልቅያስ፣ ጸሀፊዉን ሳፋን፣ የሳፋንን ልጅ አኪቃምን፣ የሚክያስን ልጅ ዓክቦርን እና የንጉሱን አገልጋይ ዓሳያን አዘዛቸው (ቁጥር 12-13) ፡፡ ሳፋን በዚህ ላይ ለየት ያለ ሚና ተጫወተ ቤተሰቡ(ከአንድ ልጁ ዉጪ) ለብዙ አመታት የእግዚአብሄርን ቃል ጠብቀዉ እና አጋርተዉ ስለነበር ( 1ነገ 22፡ 12-28፣ ኤር 26፡ 16-24፣ 29፡ 1-23፣ 36፡ 11፣ ሕዝ 8፡ 11-12) ፡፡ ሰዎቹ ነቢይቱ ሕልዳና በመሄድ ተፈጥሮ የነበረዉን ገለፁ (ቁጥር 14 ) ፡፡ አስታዉሉ በመፅሀፍ ሌሎች ሴት ነቢዮችእንደ ነበሩ ለምሳሌ ማሪያም (ዘጸ 15፡ 20) እና ድቦራ (መሳ 4፡ 4) ፡፡

ሕልዳና የእግዚአብሄርን መልዕክት በትንቢታዊ ግልፅነት ነገረቻቸው ፤ መልዕክቱ ወደ ሁለት ክፍል የተከፈለ ነበር እያንዳንዳቸዉ ኢዮስያስን “ እናንተን የላካችሁ ሰዉ “(ቁጥር 15-17) እና “ እናንተና የላካችሁ የይሁዳ ንጉስ “ በመባል ደርሰዉታል (አድርሰዉታል) (ቁጥር 18-20) ፡፡ በቁጥር (15-17) እግዚአብሄር ባለመታዘዛቸዉ ምክንያት በይሁዳ ላይ ጥፋት እንደሚያመጣ ልኳቸዉ ለነበረዉ ሰዉዬ እግዚአብሄር ንገሩት አለ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቤተ መቅደሱ ሲታደስ እና ለንጉሱ ሲነበብለት በተገኘ ጊዜ ንጉሱ የሰማዉ የህጉን መፅሀፍ ክፍል መልዕክት ለማስፈፀም የተገባ ለሀይማኖት መካድ ማስፈራሪያ መቅሰፍት እንደ ሆነ “ ያመለክታል ፡፡ በቁጥር (18-20) እግዚአብሄር ንጉሱ የህጉን መፅሀፍ በሰማ ጊዜ እራሱን በማዋረዱ እና በኃይል በመፀፀቱ ምክንያት በእርሱ ዘመን በይሁዳ ጥፋት እንደ ማይሆን ንገሩት አለ ፤ ኢዮስያስ በሰላም እንደሚሞት ቃል ተገባለት ፡፡

መደምደሚያ

በዚህ ምዕራፍ ላይ መነቃቃቱ የቱ ጋር ነው ? በኢዮስያስ ልብ መልስ ላይ የታዬ ነው ፤ የእግዚአብሄርን ቃል በመያዝ ዉስጥ የታዬ ነው ፤ የእግዚአብሄርን መንገድ በመከተል ዉስጥ የታዬ ነው ፤ ብዙ ለማወቅ በመዋረድ ዉስጥ የጀመረ ነው ፡፡ 2ጢሞ (3፡ 16-17) የሚለው “ የእግዚአብሄር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበት መፅሀፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለዉ ምክር ደግሞ ይጠቅማል “ ፡፡ ኢዮስያስ እነዚህን ሁሉ ዝቅ በማለት እና በመዋረድ የእግዚአብሄርን ቃል በመያዝ አደረገ (መዝ 119፡ 105) ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 488.

  2. Nelson’s Commentary, pp. 488–489.

  3. Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: 2 Kings, p. 58; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2kings.pdf.

  4. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 587.

  5. Wiersbe, p. 587.

  6. Nelson’s Commentary, pp. 489

ጥያቄዎች

  1. ምናሴ በእግዚአብሄር ፊት ያደረጋቸዉ ጥቂት ክፉ ነገሮች ምንድን ነበሩ (ዘዳ 12፡ 31፣ 17፡ 3፣ 18፡ 10) ? በዚህ ክፋት ምክንያት የእግዚአብሄር ፍርድ ምን ነበር ?
  2. እግዚአብሄር ህዝቡን በፍፁም እንደ ማይተው ተስፋ ሰጥቷል (ዘሌ 26፡ 11፣ 1 ሳሙ 12፡ 22) ፤ በ 2ነገ (21፡ 14) ምን እያለ ነበር ? (2 ሳሙ 7፡ 14፣ ምሳ 3፡ 12፣ ዕብ 12፡ 6)
  3. በ 2ዜና (33፡ 11-13) መሰረት በህይወቱ መጨረሻ ላይ ምናሴ ምን አደረገ ? ይህ እግዚአብሄር ሁሉንም ለማዳን መፈለጉ ከእግዚአብሄር የራቁትን ቤተሰቦችችሁን እና ጓደኞቻችሁንም እንኳን እንደ ሚፈልግ ተስፋ እና መበረታታት ይሰጣችኋል ? ( 2 ሳሙ 14፡ 14፣ 2 ዜና 7፡ 14፣ 2ጴጥ 3፡ 9)
  4. ንጉስ ኢዮስያስ እግዚአብሄርን ማክበር ይፈልግ እንደ ነበር ለማመልከት የወሰዳቸዉ ጥቂት አርምጃዎች ምንድን ናቸው ?
  5. በ 2ነገስት (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 22:13

“Go and inquire of the LORD for me, the people, and all Judah about the instruction in this book that has been found. For great is the LORD’s wrath that is kindled against us because our ancestors have not obeyed the words of this book in order to do everything written about us.”

ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ስምንት አመቱ ነበረ ለሰላሳ አንድ አመትም ነገሠ ፡፡ በእግዚአብሔርም ፊት ቅን የሆነውን ነገር አደረገ ቀኝም ግራም አላለም ፡፡ ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ቤተ መቅደሱ በመታደስ ላይ ነበር በዚህም ጊዜ የህጉ መጽሀፍ ተገኝቶ ንጉሡ ባለበት ተነበበ ፡፡ ንጉሡ ኢዮስያስም የህጉን ቃል በሰማ ጊዜ ራሱን አዋረደ ለበለጠ መረዳትም እግዚአብሔርን እርዳታ ጠየቀ ፡፡ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ልብ ስለ ህዝቡ ለማወቅ ናፈቀ በተጨማሪም የእግዚአብሔር ፍላጎት የሆነው የህጉን መጽሀፍ መከተል በትውልዱ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለማወቅ ፈለገ ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል የሚኖርና የሚሰራ ነው ፡፡ እርሱም ለበጎ ስራ ሁሉ ብቁና የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ በጽድቅ ለማስተማር ፣ ለተግሳጽ ፣ ለመሻሻልና ለማሰልጠን ይጠቅማል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ለእግርህ መብራት ለመንገድህም ብርሃን ነው ፡፡ መቼም በፈለከው ቦታና ጊዜ ለመጠቀም የእግዚአብሔርን ቃል ይኖርሃል ፡፡ አሁንም ግን ለምን ይሆን በየቀኑ ለማነበብ ከባድ የሆነብህ ? ዛሬ ቃሉን ግለጥና አንብብ ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ከማንበብ ሊያግድህ ያለውን የጠላት እቅድና ሴራ እወቅ ፡፡ በሴራው ውስጥ ታገል የእግዚአብሔርንም ቃል ለመግለጥ ጊዜ ውሰድ ፡፡ ህይወትህም ይለወጣል ፡፡

“ አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሰሩ ዘንድ የዚህችን መጽሀፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቁጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ህዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ የዚህችን የተገኘችውን መጽሀፍ ቃል እግዚአብሔርን ጠይቁ ብሎ አዘዛቸው ፡፡ “

  • 2ኛ ነገሥት 22፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 118(119)፡105 –“ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው ፡፡ “

2ኛ ጢሞቲዎስ 3፡16-17 –“ የእግዚብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሀፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ፡፡ “

ዕብራውያን 4፡12 –“ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሰራም ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል ፡፡ “