God Gave Hezekiah a Second Chance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዚህ ሙሉ ሳምንት መልዕክቱ ስለ እስራኤል ነገስታቶች አለመታዘዝ ነው ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ወደ አሶር ግዞት ላካቸው ፡፡ ዛሬ ተመልሰን ወደ ይሁዳ ዘር እንጓዛለን(እንሄዳለን) ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (20፡ 1-3)፡ ንጉስ ሕዝቅያስ እስከ ሞት በሚያደርስ በሽታ ታመመ ፤ ነቢዩ ኢሳያስ ንጉሱን ጉዳዮቹን በስርዓት እንዲያስቀምጥ ነገረዉ ምክንያቱም ስለማይድን (ቁጥር 1) ፡፡ ሕዝቅያስ በ 25 ዓመቱ ንጉስ በመሆን ለ 29 አመታት አስተዳደረ (2ነገ 18፡ 1-2) ፡፡ በመጨረሻም ልጁ ምናሴ በ 22 አመቱ በ687 ከክርስቶስ ልደት በፊት ንጉስ ይሆናል ፤ ኢሳያስ አባቱን ስለ መሞቱ በነገረዉ ጊዜ ምናሴ ሰባት አመቱ ነበር ፡፡ የሕዝቅያስ የመጀመሪያዉ ምላሽ ለኢሳያስ ማሳወቅ በፀሎት ወደ እግዚአብሄር እንዲመልስለት ነበር (ቁጥር 2-3) ፡፡ ( ኢሳ 38፡ 2 ስለ ሕዝቅያስ ፀሎት እና ኢሳ 38፡ 10-20 ስለዚህ ልምምድ ስለ ኢሳያስ ዜማ አንብቡ ) ፤ ሕዝቅያስ የሰለሞን ፀሎት ሞደል የሆነዉ ይመስላል ፡፡ ( ስለ ሰለሞን ፀሎት ድርሻ 2ዜና 6፡ 16-17 አንብቡ ) ፡፡
2-ነገስት (20፡ 4-11)፡ እግዚአብሄር የሕዝቅያስን ፀሎት ከሰማ በኋላ የሆነ ነገር ተቀየረ(ነገሩ ተቀየረ) ፤ እግዚአብሄር ወዲያዉኑ በመመለስ ኢሳያስን አደባባዩን ከማለፉ በፊት አስቆመዉ (ቁጥር 4) ፤ እግዚአብሄር ኢሳያስን ትድናለህ በሚል ዜና ወደ ሕዝቅያስ መልሶ ላከው ፡፡ በምላሹም ሕዝቅያስ በሰዎስተኛዉ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እንዲሄድ ተነገረው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር ለሕዝቅያስ በሕይወቱ ላይ ሌላ 15 አመታት በመስጠት የኢየሩሳሌምን ከተሞች እንደሚከላከል ተስፋ ገባ (ቁጥር 6) ፡፡ ጸሎት በፍጥነት ነገሮችን መቀየር ይችላል ! ኢሳያስ የሕዝቅያስን የተጠቃ ቆዳን ለማከም ስለ ሚጠቀምበት የበሉጥ ዛፍ ጠየቀ ፤ ሕዝቅያስ ሙሉ በሙሉ ዳነ (ቁጥር 7) ፡፡
ሕዝቅያስ ኢሳያስን ሙሉ በሙሉ ስለ መዳኑ(መፈወሱ) ምልክትን ጠየቀው (ቁጥር 8) ፤ ኢሳያስም “ ጥላው አስር ደረጃ ወደ ፊት ይሄድ ዘንድ ወይም አስር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ ዘንድ ትወዳለህን ? አለ “ ፡፡ የኢሳያስ ጥያቄ የነበረው ሕዝቅያስ የጥላ መለኮታዊ እርዝመት ወይስ እጥረት ለማየት ይፈልግ እንደሆን ነበር ፤ ሕዝቅያስም ጥላዉ ወደ ኃላ አስር እርምጃ እንዲመለስ(እንዲያጥር) አለ (ቁጥር 10) ፡፡ ኢሳያስ እግዚአብሄርን ሕዝቅያስ የፈለገዉን ምልክት ነገረው እግዚአብሄርም ጥላዉን አስር እርምጃ መልሶ አመጣው (ቁጥር 11) ፡፡ ስነ መለኮታዊያን እግዚአብሄር ይህ እንዲሆን የህዋን ምህዋር ገለበጠ ወይስ የምህዋርን ዙሪት አቆመ በማለት ይጠይቃሉ ነገር ግን በግልፅ ማንም አላወቀዉም ፡፡
2-ነገስት (20፡ 12-19)፡ ሕዝቅያስ ከታመመ ጀምሮ ደብዳቤ እና ስጦታዎችን ይዞ የመጣዉን ከባቢሎን ንጉስ የተላከን ጎብኚ ተቀበለ (ቁጥር 12) ፤ ሕዝቅያስ ለንጉሱ ልጅ በግምዣ ቤት እና በጦር መሳሪያ ካዝና ቤት የነበረዉን ሁሉንም ነገር በማሳየት በእንግዳ ተቀባይነት ምላሽ አደረገለት (ቁጥር 13) ፡፡ ኢሳያስ ሕዝቅያስን የጎበኙትን እንግዶች ባገኛቸዉ ጊዜ ሰዎቹ ከየት እንደ መጡ ጠየቀ ፤ ሕዝቅያስም ከባቢሎን እንደ ነበሩ መለሰለት (ቁጥር 14) ፤ ኢሳያስም በቤቱ ምን አይተዉ እንደ ነበር ጠየቀ ሕዝቅያስም ኢሳያስን ሁሉንም ነገር እንዳሳያቸዉ ነገረው (ቁጥር 15) ፡፡
ከዚያም ኢሳያስ ይሁዳ የነበረዉ ሁሉም ነገር ወደ ባቢሎን ይወሰዳል የሚለዉን የእግዚአብሄርን ቃል ሰጠ(ተናገረ) (ቁጥር 15) ፤ በተጨማሪም ጥቂት የሕዝቅያስ ልጆችም ይወሰዳሉ (ቁጥር 18) ፡፡ ልጁም ምናሴ በ586ከክርስቶስ ልደት በፊት ከኢየሩሳሌም መፍረስ በፊት ወደ ባቢሎን ይወሰዳል ፡፡
ሕዝቅያስ በኩራቱ የነበረዉን ለማሳየት ደስተኛ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የመፅሀፍ ቅዱስ የሚያስደንቅ ገፅታ በምርጥ ጀግኖቹ እና ሴት ጀግኖች ዉድቀት ላይ የሚያዋዛ አይደለም ፤ የሕዝቅያስ ሞኝነት በእግዚአብሄር ላይ ያለዉ ፈጣን መተማመንን ተከትሎ የሚተር እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ዋይርስቤ “ ኩራት ለእግዚአብሄር ብቻ የሆነዉን ክብር እንድንሰርቅ እንደሚያደርግ ፤ ኩራት የሀሰት ደህንነት ስሜት በመስጠት ወደ ኃጢዓት እና ሽንፈት እንደሚመራን “ አመልክቷል ፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሄር ላይ እንዲያምፅ ያደረገዉ ኩራት ነበር ፤ ጠላታችን (እባብ) ሊያስተን ይመጣል - አንበሳ ደግሞ ሊበላን ያስበናል ፡፡
2-ነገስት (20፡ 20-21)፡ ቁጥር 20 እንደ ንጉስ የሕዝቅያስን ታላቅ ስኬቶችን አጉልቶ ያሳያል ፤ ከኢየሩሳሌም ቅጥሮች ዉጪ የሚገኝ በሲሆን ምንጭ መካከል የሚያልፍ አንድ የተቆፈረ ዋሻ ነበረው እንዲሁም በቅጥሩ ዉስጥ የሚገኝ የሴሎ መዋኛ ገንዳም ነበረው ፡፡ ዋሻዉ በከተማዉ ዉስጥ ያሉትን ሰዎች በከበባ ጊዜ ይረዳል ፤ ዋሻዉ የሕዝቅያስ ዋሻ በመባል እየተጠራ አለ የሚያስደንቅም የምህንድስና ሙያ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ሕዝቅያስ ከይሁዳ ነገዶች በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ያደረገ አንዱ ንጉስ ነበር ፤ ዋሻዉ ብቻዉን እንደ ንጉስ የነበረዉን ጥበብ እና አርቆ አሳቢነት ያሳያል ፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ ኩራቱ ወደ ይሁዳ ዉድቀት መራ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 574
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 487.
Nelson’s Commentary, p. 487.
Wiersbe, p. 576.
Nelson’s Commentary, p. 487.
ጥያቄዎች
-
ንጉስ ሕዝቅያስ ሰምቶት የነበረዉ ሪፖርት ምን ነበር ? ከሕዝቅያስ ምላሾቹ ምን ነበሩ ? እነዚህ ጥሩ ምላሾች ነበሩ ?
-
ንጉስ ሕዝቅያስ ስለ ይሁዳ ሰዎች ምን ተረዳ (2 ነገ 19፡ 4፣ 30) ?
-
የአሶር ንጉስ ምንም እግዚአብሄርን መፍራት ያልነበረዉ የመሰለዉ ለምን ነበር ? እግዚአብሄር ሕዝቅያስን እንደ ማይረዳዉ ለምን አሰበ ?
-
ለእርሱ ተልኮለት የነበረዉን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የሕዝቅያስ ድርጊት እና ምላሽ ምን ነበር ? ለሕዝቅያስ ፀሎት የእግዚአብሄር ምላሽ ምን ነበር ? ለፀሎታችሁ እንደ ምላሽ እግዚአብሄር ለእናንተ ሲዋጋ መቼ አያችሁት ?
-
እግዚአብሄር ስለ ሕዝቅያስ ሞት ያለዉን ለምን እንደተወ(እንደ ቀነሰ) ምን ታስባላችሁ (2 ነገ 20፡ 1፣ 5-6) ? በመፅሀፍት በሌሎች ሰዎች ላይ እንዲህ አይነት ከእግዚአብሄርን የሆነ ምህረት የት ታያላችሁ ? (ዘጸ 32፡ 9-14፣ ዮና 3፡ 10፣ ሮሜ 5፡ 8)
-
በ 2ነገስት (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅደሱ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 20:2–3
“Then Hezekiah turned his face to the wall and prayed to the LORD, ‘Please LORD, remember how I have walked before You faithfully and wholeheartedly and have done what pleases You.’ And Hezekiah wept bitterly.”
ንጉሠ ሕዝቅያስ በጠና ታመመ ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም ሕዝቅያስን ስለማትድን ቤትህን አስተካክል አለው ፡፡ በዚህ ጊዜም ሐዝቅያስ ወደ እግዚአብሔር አምርሮ አለቀሰ ፡፡ እንድሀም ብሎ ጸለየ በፊትህ በአውነትና በፍጹመ ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ ፡፡ ወድያውኑም ከዚህ ጸሎት በኋላ እግዚአብሔር የሕዝቅያስን የህይወት አቅጣጫ ቀየረ ፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ መጣ ሕዝቅያስንም በሶስት ቀን ወስጥ ትፈወሳለህ በለው አለው ፡፡ እግዚአብሔርም ለሕዝቅያስ የአሶርን ንጉሥ ውድቀት የሚያይባቸወን አስራ አምስት አመታት በእድሜው ላይ ጨመረለት ፡፡ እግዚአብሔር የሕዝቅያስን ጸሎት ሰምቶ መለሰለት ፡፡
በህይወትህ በአስቸጋሪ የህይወት አጋጣሚ ተጎድተህ በጸሎት እግዚአብሔርን ያየህባቸው ጊዜያት አሉ ? ድንገተኛ የጤን መረጃ ? የስራ መጣት ? ስለ ልጀህ ያልተጠበቀ ዜና ? እግዚአብሔር እንባህን ያያል ፣ ጸሎትህን ይሰማል ፡፡ በማትገምተው በማታስበው መነገድ እርሱ መስራት ይችላል ፡፡ ዛሬ በጸሎት እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ እርሱ ወደ እርሱ እንድትጮኽ ይፈልጋል ጆሮዎቹም ዘወትር ክፍት ናቸው ፡፡ የሚያስፈልግህ ትንስም ይሁን ትልቅ ችግር የለውም ፤ ለአንተ ጠቃሚ ከሆነ ለእግዚአብሔርም ጠቃሚ ነው ፡፡ እርሱ ሊያነሳህና ሊያድንህ በዚያ አለ ፡፡ እግዚአብሔር ሊታደግህ መጥቷል እርሱ የእንደገና አምላክ ነውና ፡፡
“ ፊቱንም ወደ ግድግዳው መልሶ እንድህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አቤቱ በፊትህ በእውኔትና በፍጹምልብ እንደ ሄደሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ ፡፡ ሕዝቅያስም እጅግ አደርጎ አለቀሰ ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 20፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 65(66)፡17-18 –“ በአፌ ወደ እርሱ ጮኸሁ በአንደበቴም አመሰገንሁት በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አየሰማኝም ነበር ፡፡ “
- 1ኛ ጴጥሮስ 3፡11-12 –“ መለካምንም ያድርግ ሰላምንም ይሻ ይከተለውም የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል የጌታ ፊት ግን ከፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው ፡፡ “
- 1ኛ ዮሐንስ 5፡14 –“በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።