Historical Books 2 Kings

Doing Evil in God's Sight

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 277 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ሁሉንም ሳምንት እንዳየነው በደንብ ክፉ ተግባራትን ለማየት እንቀጥላለን ፡፡ ንጉስ ሕዝቅያስ ይመጣል ነገር ግን እስካሁን አልመጣም ፡፡ በምዕራፍ 17 ወደ መጨረሻዎቹ ነገስታት እንገባለን ፤ የዳነዉ ዘር ከእስራኤል ሳይሆን ከይሁዳ የዘር መስመር ይመጣል ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (17፡ 1-6)፡ የይሁዳ ንጉስ አካዝ ክፉ ንጉስ ነበር ፤ በአስተዳደሩ በ12ተኛዉ አመት ሆሴዕ በእስራኤል ላይ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 1) ፡፡ ሆሴዕ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ ነገር ግን ሌሎቹ የእስራኤል ነገስታቶች እንዳደረጉት የከፋ አልነበረም (ቁጥር 2) ፡፡ የአሶር ንጉስ ስልምናሶር እስራኤልን አጠቃ ፤ በምላሹም ሆሴዕ የስልማናሶር አገልጋይ በመሆን ለመደህንነት ግብር ከፈለው (ቁጥር 3) ፡፡ ሆሴዕ በአሶር ላይ እርዳታ በመፈለግ ለግብፅ ንጉስ ሴጎር መልዕክተኞችን ልኮ ነበር ፤ ስልምናሶር በሰማ ጊዜ ሆሴዕን በማሰር በእስር ቤት አስቀመጣው (ቁጥር 4) ፡፡ የአሶርም ንጉስ ለሰዎስት አመታት ጠቅላላ ምድሪቱን ከበባት (ቁጥር 5) ፡፡ እስራኤል የመጨረሻዋን ንጉስ አጥታ ነበር ፤ የሰማሪያም ምድር ከእስራኤል ተወሰደች እስራኤላዊያንም ወደ አሦር ተሰደዱ በዚያም ደግሞ ተቀመጡ (ቁጥር 6)፡፡

2-ነገስት (17፡ 7-20)፡ እስራኤል ለመቀጣት እየጀመረ ነበር ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ ባለመታዘዛቸው (ቁጥር 7) ፡፡ ሌሎች አማልዕክቶችን ማምለክ ቢመርጡም እግዚአብሄር ሕዝቡን ዋጅቷቸዉ ነበር ፤ ዴል ራልፍ ዳቪስ በእዉነቱ የእስራኤል ኃጢዓት ዉለታ ቢስነት እንደ ነበር ይናገራል ፡፡

በህይወት ግማሹ ዉጊያ እግዚአብሄርን ምስጋና በመሰጠት የሚሸነፍ ሁኔታ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ምስጋና መስጠት በማቆም ብዙ ስለ ፈለጉ ፡፡ የእስራኤል ነገስታቶች ባመጡላቸዉ በሌሎች ህዝቦች ልምድ መሰረት ኖሩ (ቁጥር 8) ፡፡ ዳቪስ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ለማድረግ ምንም ያልነበረዉን መያዝ የሚችሉትን ለቀጣዩ ታላቅ ነገር ያለማቋረጥ እየተመለከቱ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ ባህሎቹን ብቻ አልያዙም ነገር ግን በሁሉም ኮረብቶች ላይ እና በሁሉም አረንጓዴ ዛፎች ስር የጣኦት አምላኮችን አምልኮ አስፋፉ (ቁጥር 9-11) ፤ ከተስፋይቱ ምድር ወጥተዉ የነበሩት ህዝቦች አድረገዉት የነበረዉን እያደረጉ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ከክፉ መንገዳቸዉ ለማስጠንቀቅ ነቢያትን እና ትንቢት ተናጋሪዎችን ላከላቸው (ቁጥር 13)(ዕብ 12፡ 25) ፡፡

ህዝቡም የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ ለመስማት እምቢ አሉ (ቁጥር 14) ፡፡ ግትር በመሆናቸው መጨረሻቸዉ በአሶር ስደት ሆነ ፡፡ እስራኤላዊያን በአስር የአለመታዘዝ ድርጊቶች ጥፋተኞች ነበሩ - ዳቪስ “ የ200 አመት ቃል ኪዳን ማፍረስ “ በማለት ይጠራዋል ፡፡

  1. ስርዓቱን እና ኪዳኑን ዘነጉ(አልተቀበሉም) (ቁጥር 15) ፡፡
  2. ምናምንቴ ጣዖቶችን ተከተሉ (ቁጥር 15) ፡፡
  3. የእግዚአብሄርን ትዕዛዝት ተዉ (ቁጥር 16) ፡፡
  4. ለራሳቸዉ የተቀረፁ ምስሎችን አዘጋጁ (አደረጉ) (ቁጥር 16) ፡፡
  5. የአሼር አምዶችን (በወሲባዊ ስርዓት አልበኝነት የሚደረግበትን) አደረገ (ቁጥር 16) ፡፡
  6. ለሰማያዊ ሰራዊት ሰገዱ (ቁጥር 16) ፡፡
  7. ባዖልን አገለገሉ (ቁጥር 16) ፡፡
  8. ወንድ ልጆቻቸዉን እና ሴት ልጆቻቸዉን በእሳት እንዲያልፉ አደረጉ (ሰዉአቸው) (ቁጥር 17) ፡፡
  9. ምዋርት እና ሞራ ገላጭነትን ተለማመዱ(አደረጉ) (ቁጥር 17) ፡፡
  10. በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸዉን በመስጠት አደረጉ (አናደዱት) (ቁጥር 17) ፡፡

እግዚአብሄር “ በእስራኤላዊያን በጣም ተበሳጨ “ ምክንያቱም ሙሉ በሆነዉ አለመታዘዛቸው ስለሆነም “ ከፊቱም ጣላቸው ፤ ከይሁዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አልቀረም “ (ቁጥር 18) ፡፡ ይሁዳባለመታዘዝ እንደ እስራኤል የተጓዘ ቢሆንም እንኳን የዳነዉ ዘር ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር (ቁጥር 19) ፤ እግዚአብሄር ሁሉንም እስራኤላዊያንን ጠላ፣ አስወገዳቸው እንዲሁም ደግሞ ከፊቱ አጠፋቸው (ቁጥር 20) ፡፡

2-ነገስት (17፡ 21-23)፡ ቁጥር 21-23 ወደ ግዞት የመራቸዉን የእስራኤል ያለመታዘዝ ታሪክ ማጠቃለያ ይሰጣል ፡፡ የዚህ ያለመታዘዝ መንገድ መጀመሪያ የእስራኤል መንግስት ወደ ሁለት ህዝብ መከፈል እና ወደ እስራኤል ንጉስ ኢዮሮብዓም በእቅድ የእስራኤልን ህዝብ እግዚአብሄር ከመከተል መርቶ ወደ ነበረው ወደ ኃላ ይወስዳል (ቁጥር 21)፡፡ ኢዮሮባዓም ከሞተ በኋልም እስራኤላዊያን በእነዚህ ኃጢዓቶች ቀጠሉ (ቁጥር 22) ፡፡ በመጨረሻም በአለመታዘዛቸው እግዚአብሄር ወደ አሶር አሰደዳቸው (ቁጥር 23) ፡፡

መደምደሚያ

በአሁኑ ስዓትብዙዎቻችን በባርነት ነን ለተስፋ ወደ ይሁዳ መመልከት አለብን ፤ ካልሆነ በባርነት እንቆያለን ፡፡ ፀሎቴ ቀላል ነው “ እግዚአብሄር ሆይ በባርነት የሆንባቸዉ ስፍራዎች የቶቹ ናቸዉ ? አንተን ገፍተን ምናምንቴ ጣዖቶችን የተከተልንበት ስፋራ የቱ ነው አሳዬን ፤ መንፈስ ቅዱስ ተናገረን “ የሚል ነው ፡፡

ኢየሱስ ከምርኮ ነፃ ሊያወጣ መጣ ፤ ወደ ኋላ የሚመልሱንን ነገሮች የምንተዉ ከሆነ ይህን ነፃነት ማጣጣም እንችላለን ፡፡

  1. Dale Ralph Davis, Focus on the Bible: 2 Kings (Great Britain: Christian Focus Publications, 2011), n.p.

  2. Davis, n.p.

  3. Davis, n.p.

ጥያቄዎች

  1. 2 ነገስት 17 የእስራኤል መንግስት ተይዞ እንዴት ወደ ምርኮ እንደ ተወሰደ ይገልፃል ፤ በ 2ነገ (17፡ 7-23) መሰረት ለምን ይህ ሆነ ? (ዘዳ 31፡ 16-18፣ ኢያ 24፡ 20፣ ሮሜ 1፡ 21-25)
  2. በሰማሪያ ከተሞች ለመኖር መጥተዉ የነበሩት እግዚአብሄርን መፍራት ባለመኖራቸዉ ምክንያት እግዚአብሄር ምን አደረገ (2 ነገ 17፡ 25) ? የእስራኤልን አምላክ ለመለመን እንዴት ሞከሩ (2ነገ 17፡ 27-28) ? አንድ ካህን እንዴት እግዚአብሄርን እንደሚፈሩ ካስተማራቸዉ በኋላ በትክክል አገኙት ? ( 2 ነገ 17፡ 33፣ 41)
  3. ሙሴ ሰርቶት የነበረዉን ንጉስ ሕዝቅያስ ምንድን ሰባበረ (ዘኁ 21፡ 9) ? የነኃሱ እባብ ወደ ምንድን አመለከተ (ዮሐ 3፡ 14-15፣ 12፡ 32) ? እንዴት ያለአግባብ ተጠቀሙት ?
  4. በ 2ነገ (18፡ 5-6) የንጉስ ሕዝቅያስን መግለጫ አንብቡ ፤ በዚህ መግለጫ ለእናንተ የቀረላችሁ(የተለዬ ነገር) ነገር አለ ? የክርስቶስ አይነት ነው ?
  5. በ 2ነገ (18፡ 22) የአሶር ሰዎች ንጉስ ንጉስ ሕዝቅያስ የአምላክን መስገጃ ኮረብታዎችን በማፈራረስ መሰዊያዎቹን ወሰደ በማለት ተናገረ ፤ ይህ ትክክል ነበር ? (2 ነገ 18፡ 3-4)
  6. በእዉነት የአሶር ንጉስ በይሁዳ ላይ የተላከዉ በእግዚአብሄር ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ (2ነገ 18፡ 25) ? በይሁዳ ላሉት ሰዎች እግዚአብሄር እንደ ማያወጣቸዉ በመናገር ምን ስልት እየተጠቀመ ነበር (2 ነገ 18፡ 32) ? በ 2ነገ (18፡ 27-35) ያለዉ ሁሉም ነገር እዉነት ነበር ? እናንተን ለማሸነፍ ጠላቶቻችሁ እንደዚህ አይነት ዘዴ(ዉሸት እና ፍራት) ይጠቀማሉ ?
  7. በ 2ነገስት (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 17:17b–18

“They devoted themselves to do what was evil in the LORD’s sight and provoked Him. Therefore, the LORD was very angry with Israel, and He removed them from His presence. Only the tribe of Judah remained.”

መግቢያ

ዛሬ ሁሉንም ሳምንት እንዳየነው በደንብ ክፉ ተግባራትን ለማየት እንቀጥላለን ፡፡ ንጉስ ሕዝቅያስ ይመጣል ነገር ግን እስካሁን አልመጣም ፡፡ በምዕራፍ 17 ወደ መጨረሻዎቹ ነገስታት እንገባለን ፤ የዳነዉ ዘር ከእስራኤል ሳይሆን ከይሁዳ የዘር መስመር ይመጣል ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (17፡ 1-6)፡ የይሁዳ ንጉስ አካዝ ክፉ ንጉስ ነበር ፤ በአስተዳደሩ በ12ተኛዉ አመት ሆሴዕ በእስራኤል ላይ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 1) ፡፡ ሆሴዕ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ ነገር ግን ሌሎቹ የእስራኤል ነገስታቶች እንዳደረጉት የከፋ አልነበረም (ቁጥር 2) ፡፡ የአሶር ንጉስ ስልምናሶር እስራኤልን አጠቃ ፤ በምላሹም ሆሴዕ የስልማናሶር አገልጋይ በመሆን ለመደህንነት ግብር ከፈለው (ቁጥር 3) ፡፡ ሆሴዕ በአሶር ላይ እርዳታ በመፈለግ ለግብፅ ንጉስ ሴጎር መልዕክተኞችን ልኮ ነበር ፤ ስልምናሶር በሰማ ጊዜ ሆሴዕን በማሰር በእስር ቤት አስቀመጣው (ቁጥር 4) ፡፡ የአሶርም ንጉስ ለሰዎስት አመታት ጠቅላላ ምድሪቱን ከበባት (ቁጥር 5) ፡፡ እስራኤል የመጨረሻዋን ንጉስ አጥታ ነበር ፤ የሰማሪያም ምድር ከእስራኤል ተወሰደች እስራኤላዊያንም ወደ አሦር ተሰደዱ በዚያም ደግሞ ተቀመጡ (ቁጥር 6)፡፡

2-ነገስት (17፡ 7-20)፡ እስራኤል ለመቀጣት እየጀመረ ነበር ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ ባለመታዘዛቸው (ቁጥር 7) ፡፡ ሌሎች አማልዕክቶችን ማምለክ ቢመርጡም እግዚአብሄር ሕዝቡን ዋጅቷቸዉ ነበር ፤ ዴል ራልፍ ዳቪስ በእዉነቱ የእስራኤል ኃጢዓት ዉለታ ቢስነት እንደ ነበር ይናገራል ፡፡

በህይወት ግማሹ ዉጊያ እግዚአብሄርን ምስጋና በመሰጠት የሚሸነፍ ሁኔታ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ምስጋና መስጠት በማቆም ብዙ ስለ ፈለጉ ፡፡ የእስራኤል ነገስታቶች ባመጡላቸዉ በሌሎች ህዝቦች ልምድ መሰረት ኖሩ (ቁጥር 8) ፡፡ ዳቪስ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ለማድረግ ምንም ያልነበረዉን መያዝ የሚችሉትን ለቀጣዩ ታላቅ ነገር ያለማቋረጥ እየተመለከቱ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ ባህሎቹን ብቻ አልያዙም ነገር ግን በሁሉም ኮረብቶች ላይ እና በሁሉም አረንጓዴ ዛፎች ስር የጣኦት አምላኮችን አምልኮ አስፋፉ (ቁጥር 9-11) ፤ ከተስፋይቱ ምድር ወጥተዉ የነበሩት ህዝቦች አድረገዉት የነበረዉን እያደረጉ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ከክፉ መንገዳቸዉ ለማስጠንቀቅ ነቢያትን እና ትንቢት ተናጋሪዎችን ላከላቸው (ቁጥር 13)(ዕብ 12፡ 25) ፡፡

ህዝቡም የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ ለመስማት እምቢ አሉ (ቁጥር 14) ፡፡ ግትር በመሆናቸው መጨረሻቸዉ በአሶር ስደት ሆነ ፡፡ እስራኤላዊያን በአስር የአለመታዘዝ ድርጊቶች ጥፋተኞች ነበሩ - ዳቪስ “ የ200 አመት ቃል ኪዳን ማፍረስ “ በማለት ይጠራዋል ፡፡

  1. ስርዓቱን እና ኪዳኑን ዘነጉ(አልተቀበሉም) (ቁጥር 15) ፡፡
  2. ምናምንቴ ጣዖቶችን ተከተሉ (ቁጥር 15) ፡፡
  3. የእግዚአብሄርን ትዕዛዝት ተዉ (ቁጥር 16) ፡፡
  4. ለራሳቸዉ የተቀረፁ ምስሎችን አዘጋጁ (አደረጉ) (ቁጥር 16) ፡፡
  5. የአሼር አምዶችን (በወሲባዊ ስርዓት አልበኝነት የሚደረግበትን) አደረገ (ቁጥር 16) ፡፡
  6. ለሰማያዊ ሰራዊት ሰገዱ (ቁጥር 16) ፡፡
  7. ባዖልን አገለገሉ (ቁጥር 16) ፡፡
  8. ወንድ ልጆቻቸዉን እና ሴት ልጆቻቸዉን በእሳት እንዲያልፉ አደረጉ (ሰዉአቸው) (ቁጥር 17) ፡፡
  9. ምዋርት እና ሞራ ገላጭነትን ተለማመዱ(አደረጉ) (ቁጥር 17) ፡፡
  10. በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸዉን በመስጠት አደረጉ (አናደዱት) (ቁጥር 17) ፡፡

እግዚአብሄር “ በእስራኤላዊያን በጣም ተበሳጨ “ ምክንያቱም ሙሉ በሆነዉ አለመታዘዛቸው ስለሆነም “ ከፊቱም ጣላቸው ፤ ከይሁዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አልቀረም “ (ቁጥር 18) ፡፡ ይሁዳ ባለመታዘዝ እንደ እስራኤል የተጓዘ ቢሆንም እንኳን የዳነዉ ዘር ከይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር (ቁጥር 19) ፤ እግዚአብሄር ሁሉንም እስራኤላዊያንን ጠላ፣ አስወገዳቸው እንዲሁም ደግሞ ከፊቱ አጠፋቸው (ቁጥር 20) ፡፡

2-ነገስት (17፡ 21-23)፡ ቁጥር 21-23 ወደ ግዞት የመራቸዉን የእስራኤል ያለመታዘዝ ታሪክ ማጠቃለያ ይሰጣል ፡፡ የዚህ ያለመታዘዝ መንገድ መጀመሪያ የእስራኤል መንግስት ወደ ሁለት ህዝብ መከፈል እና ወደ እስራኤል ንጉስ ኢዮሮብዓም በእቅድ የእስራኤልን ህዝብ እግዚአብሄር ከመከተል መርቶ ወደ ነበረው ወደ ኃላ ይወስዳል (ቁጥር 21)፡፡ ኢዮሮባዓም ከሞተ በኋልም እስራኤላዊያን በእነዚህ ኃጢዓቶች ቀጠሉ (ቁጥር 22) ፡፡ በመጨረሻም በአለመታዘዛቸው እግዚአብሄር ወደ አሶር አሰደዳቸው (ቁጥር 23) ፡፡

መደምደሚያ

በአሁኑ ስዓትብዙዎቻችን በባርነት ነን ለተስፋ ወደ ይሁዳ መመልከት አለብን ፤ ካልሆነ በባርነት እንቆያለን ፡፡ ፀሎቴ ቀላል ነው “ እግዚአብሄር ሆይ በባርነት የሆንባቸዉ ስፍራዎች የቶቹ ናቸዉ ? አንተን ገፍተን ምናምንቴ ጣዖቶችን የተከተልንበት ስፋራ የቱ ነው አሳዬን ፤ መንፈስ ቅዱስ ተናገረን “ የሚል ነው ፡፡

ኢየሱስ ከምርኮ ነፃ ሊያወጣ መጣ ፤ ወደ ኋላ የሚመልሱንን ነገሮች የምንተዉ ከሆነ ይህን ነፃነት ማጣጣም እንችላለን ፡፡

1 Dale Ralph Davis, Focus on the Bible: 2 Kings (Great Britain: Christian Focus Publications, 2011), n.p.

2 Davis, n.p.

3 Davis, n.p.