Defiling The Temple
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የ 2ነገስትን እብደት(እንከን የተሞላበትን) የሆነ የዘር ግንድ ስንመለከት የዳነ ዘር ስላለን እግዚአብሄርን ማመስገን እንችላለን ፡፡ አብዛኞቹ ነገስታት የሰሜኑ መንግስት የእስራኤል እና የደቡቡ መንግስት የይሁዳ ሁለቱም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነበረ ፤ አልፎ አልፎ በይሁዳ ንጉሶች በእግዚአብሄር ፊት ትክክል የሆነዉን ያደርጋሉ ፡፡ ምዕራፍ 15 በሁለቱም መንግስት በነገስታቶች መካከል ይዘላል ነገር ግን ዘመናቸዉ አጭር ነበር ምክንያቱም ሁሉም በንጉስ ኢዮሮብዓም ኃጢዓት ስለተከተሉ ፡፡ በቁጥር 32 ኢዮአታም እንደ ይሁዳ ንጉስ ተዋወቀ ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (16፡ 1-4)፡ በእስራኤል በፉቁሔ ዘመን በአስራ ሰባተኛዉ አመት አካዝ በ 20 አመቱ የይሁዳ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 1-2) ፡፡ አካዝም ከንጉስ ዳዊት መንገድ ይልቅ በኢዮሮብዓም መንገድ መጓዝን መረጠ ፤ በዚህ ጊዜ ሁለት አዲስ ነቢያቶች ወደ ይሁዳ ገቡ፡ ኢሳያስ እና ሚክያስ ፡፡ ይህ ሁሉ እንዴት እንደ ሆነ እርግጠኞች አይደለም ነገር ግን እዚህ ጊዜ ላይ የአካዝ አባት ንጉስ ኢዮአታም በህይወት ነበር ፡፡ አካዝ ልጁን ለሞሎክ አምላክ በእሳት ሰዋው (ቁጥር 3)(ዘሌ 18፡ 21) ፤ በተጨማሪም አካዝ በህዝቡ ዉስጥ ይሰዋና በማቃጠል ያጥናን ነበር (ቁጥር 4) ፡፡
2-ነገስት (16፡ 5-9)፡ የሶሪያ ንጉስ ረአሶንና የእስራኤል ንጉስ ፋቁሄ በኢየሩሳሌም እና በንጉስ አካዝ ላይ ሊዋጉ በመዝመት ኃይላቸዉን አጣመሩ ፤ ከተማዋን ከበቧት ነግር ግን ሊይዟት አልቻሉም (ቁጥር 5) ፡፡ በ 2ዜና (28፡ 5-8) መሰረት በኃጢዓቱ ምክንያት አካዝ ለእስራኤል ንጉስ ተላልፎ ተሰጠ ፤ በሂደቱ የንጉስ አካዝ ልጅ ተገድሎ ነበር ብዙዎችም ተገድለዉ እና ተማርከዉ ነበር ፡፡ ኃጢዓት ያለማቋረጥ ወደ ዉጤቱ ይመራል ፡፡ እስከዛዉ የሶሪያ ንጉስ ለይሁዳ ኢኮኖሚያ ዋና የነበረችዉን አስፈላጊ ወደብ ኤላትን መልሶ ወሰደ አይሁዳዊያንንም ከእርሷ አሳደደ (ቁጥር 6) ፡፡ አካዝ በሶሪያ እና በእስራኤል ንጉስ ላይ ለእርዳታ በመጠየቅ ለአሶር ንጉስ መልዕክተኞችን ላከበት ለእርሱም ታማኝነቱን ማለለት (ቁጥር 7) ፡፡ እንዲሁም አካዝ ለአሶር ከቤተ መቅደሱ እና ከቤቱ እንደ ግብር ብር እና ወርቁንለአሶር ንጉስ ላከ (ቁጥር 8) ፡፡ አሶር በመርዳት ዘመተ የሶሪያንም ህዛብ አሳደደ ረአሶንንም ገደለው (ቁጥር 9) ፡፡
2-ነገስት (16፡ 10-18)፡ አካዝ የአሶርን ንጉስ ሊገናኘው ሄደ ፤ በዚያ የደማስቆን መሰዊያ አየ የመሰዊያዉንም ቅርፅ እና የህንፃዉን እቅድ ለካህኑ ኦሪያ ላከው (ቁጥር 10) ፡፡ “ በዚህ ኃይለኛዉ ኃጢዓት ( ታማኝነት ማጉደል) ጣልቃ በመግባት በግላዊ ሙከራ በእግዚአብሄር ተሰጥቶ የነበረዉን የቤተ መቅደሱን እቃዎች እና ዲዛይን መቀየር ነበር “ ፤ (ዘጸ 25፡ 40፣ 26፡ 30፣ 27፡ 1-8፣ 1ዜና 28፡ 19) ፡፡ የአካዝ ድርጊት የራሱን አምላክ ከማስደሰት ይልቅ የአሶርን ንጉስ ለማስደሰት መፈለጉን ያሳያል ፡፡
ለእግዚአብሄር ታዛዥ ሆኖ ከመቆየት ይልቅ በዚህ አለም ጓደኞችን ለማድረግ የምንሞክረዉን ሚከራ ማስወገድ አለብን ፡፡ አካዝ በአለም ጓደኛ ለመሆን ተመለከተ (ያዕ 4፡ 4)፣ በአለም የተበላሸ ሆነ (ያዕ 1፡ 27)፣ አለምን ወደ መዉደድ መጣ (1ዮሐ 2፡ 15-17) እና ለአለም የተመቸ ለመሆን መረጠ (ሮሜ 12፡ 2) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በብዙ አለምን እየመሰለች ነው ?
ካህኑ ኦሪያ ለእግዚአብሄር የታዘዘ ሆኖ ከመቀጠል ይልቅ ለመሰዊያዉ የአካዝን ትዕዛዝ ተከተለ (ቁጥር 11) ፡፡ አካዝ በተመለሰ ጊዜ በአዲሱ መሰዊያ አመለከ ሰዋም (ቁጥር 12-13) ፡፡ ከዚያም አካዝ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን የናሱን መሰዊያ ፈቀቅ አደረገው (ቁጥር 14) ፡፡ አካዝ ኦሪያን በአዲሱ መሰዊያ ላይ ሁሉንም መስዋዕት እንዲያደርግ አዘዘው ንጉሱ ብቻ በናሱ መሰዊያ ላይ ይሰዋል ስለዚህም የእግዚአብሄርን ምሪት ይፈልግበታል (ቁጥር 15) ፡፡ የእግዚአብሄር ካህኑ ኦሪያም ያለዉን አደረገ (ቁጥር 16) ፡፡ አካዝም የአሶርን ንጉስ ለማስደሰት በቤተ መቅደሱ ላይ የዉሃ ኩሬዎቹን እና የናሱን ሳህን በማስቀመጥ ከቤተ መቅደሱ ከፈፍ አስወገደ (ቁጥር 17-18) ፡፡ ዋይርስቤ ፅሁፍ “ አካዝ በዚህ በሚያምር አዲስ ቤተ መቅደስ መስዋዕት ሲቀርብለት እግዚአብሄር ደስ እንደ ሚለዉ አሰበ ነገር ግን ስህተት እንደ ነበር ፤ እግዚአብሄር መታዘዝን እንጂ መስዋዕትን አይፈልግም “ ፡፡
ዴል ራልፍ ዳቪስ አካዝ ያደረጋቸዉን አራት ለዉጦች ጠቅሷል ፤ አካዝ 1) አዲስ መሰዊያዎችን ሰራ (ቁጥር 10-12)፣ 2) አዲስ አደራደር አደረገ (ቁጥር 12-14)፣ 3) አዲስ ደንብ አረቀቀ(አወጣ) (ቁጥር 15-16) እና 4) አዲስ ምክንያት አመጣ (ቁጥር 17-18) ፡፡ መፅሀፍ በኢየሩሳሌም አካዝ ያመጣቸዉን አራት ዋና ለዉጦች ይገልፃል፡
- ከሚንቀሳቀስ መቀመጫዎች ላይ የጎን ክንፎቹን እና መታጠቢያዎቹን አስወገደ (1 ነገ 7፡ 27-29) ፡፡
- “ ባህር “ ተብሎ የሚጠራዉን ትልቁን ጌጠኛ ኩሬዉን ከላይ አስራ ሁለት የናስ በሬዎች ወደ አንድ አዲስ የድንጋይ መቀመጫ አስወገደው (1 ነገ 7፡ 23-26) ፡፡
- በሰንበት በንጉሱ ጥቅም ላይ የሚዉለዉን የሰንበት ጥላ አስወገደ ፡፡
- በሰንበት እና በፆም ቀን ንጉሱ የሚጠቀምበት ወደ ቤተ መቅደሱ የተለየዉን አንዱን መግቢያ የንጉሱን ዉጫዊ መግቢያ አስወገደው ፡፡
እነዚህ ለዉጦች ንጉሱ ወደ እግዚአብሄር ፊት በሚመጣበት ጊዜ ንጉሱን የሚሸፍነዉን አድል አስወገዱ ፡፡ አካዝ እነዚህን አልፈለጋቸዉም ምክንያቱም የአሶር ንጉስን ማረጋገጫ(ሀሳብ ማድረግ) ስለተመኝ ፡፡ አካዝ በእግዚአብሄር ላይ ፊቱን አዞረ ፡፡
መደምደሚያ
ከዋይርስቤ በእነዚህ ቃሎች መዝጋት እፈላጋለሁ፡
“ አንድ ጊዜ አለማዊነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲገባ ከፈቀድንለት በፀጥታ በማደግ ህብረቱን ይበክላል በመጨረሻም ይቆጣጠራል ፤ አካዝያስ አርክሶት የነበረዉ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት መቀደስ እና እንደ ገና መከፈት ልጁ ሕዝቅያስ እስከሚያስተዳድር ድረስ አልነበረም ( 2ዜና 29፡ 1-29) “ ፡፡
1ቆሮ (5፡ 6) ስለ ንጉስ አካዝ፡ “ መመካታችሁ መልካም አይደለም ፡፡ ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታዉቁምን ? “ የሚለዉን እንዳስብ ያደርገኛል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers,2005), p. 458.
MacArthur, p. 458.
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 566.
Dale Ralph Davis, Focus on the Bible: 2 Kings (Great Britain: Christian Focus Publications, 2011), n.p.
Wiersbe, p. 566.
ጥያቄዎች
-
በ 2ነገ (15፡ 19) የወቅቱ የእስራኤል ንጉስ እርዳታዉን ለማግኘት ለአሶር ንጉስ 1,000 ብር መክሊት ከፈለ ፤ ይህ ብር ከየት ነበር የመጣው ?
-
በ 2ነገስት 15 ከእስራኤል ነገስታቶች ሁለቱ እንዴት እንደ ሚሞቱ ተጠቀሰ ? ስለዚህ መንግስት ሁኔታ ምን ይነግረናል ? (ሮሜ 1፡ 28-32)
-
የይሁዳ ንጉስ አካዝ “ በእሳት ዉስጥ ያለፈ “ ልጅ ነበረው ፤ ይህ ምን ማለት ነው ? ( ዘሌ 20፡ 2-3፣ ዘዳ 18፡ 9-10፣ ሕዝ 16፡ 21)
-
ከአሶር ንጉስ ጋር በተገናኘ ጊዜ ንጉስ አካዝ የንጉሱን መሰዊያ አዬ በኢየሩሳሌምም ለማምለኪያ ይህን የሚመስል እንደሚሰራ ተናገረ ፤ እግዚአብሄር በዚህ ደስተኛ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ (ዘጸ 39፡ 32፣ 39፣ 42-43) ? ህዝቡ እንዴት በቤተ መቅደሱ እንደሚሰግዱ ንጉስ አካዝ ምን ለዉጦች አደረገ (2ነገ 16፡ 14-18) ? ይህ የሰዉ ልጅ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ከመታዘዝ ይልቅ በራስ መንገድ እንዴት ድዛይን እንደሚያደርጉ የሚያሳይ ነው ?
-
በ 2ነገስት (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 16:18
“To satisfy the king of Assyria, he removed from the LORD’s temple the Sabbath canopy they had built in the palace, and he closed the outer entrance for the king.”
ንጉሥ አካዝ ይሁዳን ከመምራቱ ከአመታት በፊት እግዚአብሔር ንጉሥ ሰለሞንን ስለ ቤተ መቅደሱ ህግጋት ፣ የእግዚአብሔር መገኘት ሁልጊዜ ስለሚያርፍበት ቦታ ፣ ህዝቡም ሄደው እርሱን ስለሚያመልኩበት ቦታ ትዕዛዝ ሰጥቶት ነበር ፡፡ ቢሆንም ግን ንጉሥ አካዝ ራሱን ከአሶር ንጉሥ ጋር አወዳጀ በቤተ መቅደሱም ላይ ለውጦችን ማድረግ ጀመረ ፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የቀድሞውን ተዕዛዝም ተው ፡፡ የመቀመጫውን ከፈፍ ቆረጠ ፣ ኩሬውን ፣ የዙፋኑንም መሰረት አሰወገደ እንድሁም በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ አዞረው ፡፡ ንጉሥ አካዝ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ይልቀ የአሶርን ነጉሥ ማስደሰትን ፈለገ ፡፡
አለምን ለማስደሰት ስትሻ ያንተ የሆኑ ነገሮችን መቀየር ትጀምራለህ ፡፡ አለም ሊስብህ ፣ ሊፈትንህና በጌታ ላይ ከማትኮር አሳብህን ሊሰርቅ ይሞክራል ፡፡ ምናልባት አንተም ክርስቶስን የሚወክሉ የህይወት ክፍሎችህን ቀስ በቀስ ልታስወግድ ትችላለህ ፡፡ ምናልባት ለወጡ መጀመሪያ ላይ ትንስ ይመስል ይሆናል ነገር ግን በውጭ ማድረግ የጀመርከው ነገር በወስጥ ያለውን የልብህን ሁኔታ ያመለክታል ፡፡ ከርስቶስን የሚወክሉ ነገሮችን ካስወገድክ ከዚያ በኋላ እነዚህን የክርስቶስ ባልሆኑ ነገሮች መተካትህ አይቀርም ፡፡ ዛሬ ራስህን ጠይቅ ፡- የአለምን መስፈርት ለማሟላት ነው የምትኖረው ወይስ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ ለመሄድ ?
“ በእግዚአበሔርም ቤት የዙፋኑን መሰረት ሰራ ስለ አሶርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 16፡18
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 83(84)፡10 –“ ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንድት ቀን ትሻላለች በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ ፡፡ “
ገላትያ 1፡10 –“ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን ? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን ? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም ፡፡ “
1ኛ ተሰሎንቄ 2፡4 –“ ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን እንድሁ እንናገራለን ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔር እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።