Walking Out Limited Faith
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በብሉይ ኪዳን በሰባተኛዉ መፅሀፍ ላይ ነን ሁሉም እነዚህ መፅሀፍት ወደ ሚመጣዉ መሲህ ያመለክታሉ ፡፡ ለ 2ነገስት ሀረጋችን የዳነዉ ዘር የሚል ነው ፡፡ በምዕራፍ 11 በዳዊት ኪዳን የሚያምኑ ጥቂት ቡድኖችን እና የይሁዳ ንጉስ እና የዳነ ዘር የሆነዉን አንድ የሰባት አመት ልጅ ስሙ ኢዮአስ የተባለዉን ላይ ተመልክተናል ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (13፡ 1-3)፡ የይሁዳ ንጉስ በመሆን በኢዮአስ 23አመት አስተዳደር ላይ የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ የእስራኤል ንጉስ ሆነ (ቁጥር 1) ፡፡ ሁሉም የእስራኤል ንጉስ እንዳደረጉት ኢዮአካዝም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ መጀመሪያ ኢዮሮብዓም አድርጎት በነበረዉ ኃጢዓት ቀጠለ (ቁጥር 2) ፡፡ ኢዮአካዝ የኢዮሮብዓምን ኃጢዓት መከተል የሚያመጣዉ መዘዝ እንደለ ጥቂት አሳቡ እንዳለዉ ታስባላችሁ ነገር ግን “ ከእነርሱም አልራቀም “ (ቁጥር 2) ፡፡ “ ኢዮሮብዓም ያደረገዉን ኃጢዓት…እስራኤል እንዲያደርገዉ ምክንያት ሆነ “ የሚለዉን ሀረግ አስታዉሉ ፤ ሌሎች ነገስታቶችን 2 ነገስት (10፡ 29፣ 31፣ 13፡ 6፣ 11፣ 15፡ 9) ለመግለፅ ተመሳሳይ ሀረግ ጥቅም ላይ ዉሏል ፡፡ ይህ ሀረግ በ 2ነገስት ቢያንስ 17 ጊዜ ተጠቅሟል ፡፡ ሞደሉ ዳዊት ያደርግ የነበረዉን የሚያደርግ እንጂ ክፉዉ ንጉስ ኢዮሮብዓም የሚያደርገዉ እንደ ሆነ አስቡ ? በሚያናድድ ሁኔታ ይህ ኢዮአካዝ ብቻ የሚያዉቀዉ ብቸኛዉ ሂደት ነበር ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር 2 ነገስት 13 በመሳፍንት መፅሀፍ የተዘረዘረዉን ኡደት እንደሚያንፀባርቅ ይናገራል፡
- ኢዮአካዝ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ (ቁጥር 2፣ መሳ 2፡ 11-13፣ 3፡ 7) ፡፡
- እግዚአብሄር በእስራኤል ተበሳጨ ለጠላቶቻቸዉም ሰጣቸው (ቁጥር 3፣ መሳ 2፡ 14-15፣ 3፡ 8) ፡፡
- ኢዮአካዝ ለእግዚአብሄር በጠላቶቹ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ጮኸ (ቁጥር 4፣ መሳ 2፡ 18፣ 3፡ 9) ፡፡
- እግዚአብሄር እስራኤልን ለማዳን ነፃ አዉጪ ጠራ (ቁጥር 5፣ መሳ 2፡ 16፣ 18፣ 3፡ 9) ፡፡
- ነፃ ከወጡ በኋላ እስራኤል ወደ ክፉ መንገዳቸዉ ተመለሱ ኡደቱም እንደ ገና ጀመረ (ቁጥር ቁጥር 6፣ መሳ 2፡ 19፣ 3፡ 1-14) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ የእግዚአብሄር ቁጣ ለመምጣት የዘገዬ ሊሆን የሚችል ነገር ግን ፍርዱን ለማምጣት የሚያነሳሳ ሊሆነ የሚችል እንደ ሆነ (ዘዳ 4፡ 24-25፣ መዝ 103፡ 8) ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ሩህሩህ ነው “ ኪዳኑን ለሚጥሱ ግን ቁጣዉ አለ “ (ዘዳ 13፡ 17፣ 29፡ 25-27፣ ኢያ 23፡ 16፣ መሳ 2፡ 20) “ የእግዚአብሄር ቁጣ ፅድቅ ነው የሰዉ ብስጭት ግን በመጥፎ ነገር የተመዘነ ነው “ (ዘፍ 49፡ 6፣ ምሳ 14፡ 17) ፡፡
2-ነገስት (13፡ 4-9)፡ ኢዮአካዝ ሰምቶት ለእስራኤል አዳኝ ወደ ላከላቸዉ ወደ እግዚአብሄር ተጣራ ፤ እስራኤልም ከሶሪያ ኃይል አመለጠ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ህዝቡ ወደ ድንኳናቸዉ ተመለሱ ነገር ግን የኢዮአካዝን ኃጢዓትን መከተል ቀጠሉ (ቁጥር 5-6) ፡፡ ኃጢዓት ማድረግ፣ የእግዚአብሄርን ፍርድ መቅመስ፣ ለእርዳታ መጮኽ፣ ነፃ መዉጣት ከዚያ ተመልሶ ወደ ኃጢዓት መሄድ በሆነዉ ኡደት ቀጠሉ ፡፡ ኢዮአካዝ ከእነርሱ ጋር በኃጢዓት ተጓዘ ፡፡ “ የከንዓን የለምነት ምናልባትም እንደ ጥቂት ወሲባዊ ተኮር የከነዓናዊያን የለምነት ምልክት እንደ ነበር በመረዳት የኃይማኖታዊ ዛፍ ወይም አምድ “ የአሴርንም አምዶች እንኳን እንዳሉ ነበሩ ፡፡ እስከዛዉ ኢዮአካዝ የቀረ ሰራዊት አልነበረዉም ጥቂት ወታደሮች እንጂ (ቁጥር 7) ፡፡ ኢዮአካዝ ሞተ በሰማሪያም ተቀበረ ፤ ልጁም ዮአስ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 8-9) ፡፡
2-ነገስት (13፡ 10-13)፡ ዮአስ በእስራኤል ላይ ንጉስ በሆነ ጊዜ ንጉስ ኢዮአስ በዙፋን ላይ ሰላሳ ሰባት አመት ላይ ነበር ዮአስም 16 አመት አስተዳደረ (ቁጥር 10) ፡፡ ዮአስም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ በኢዮሮብዓም ኃጢዓት ተጓዘ (ቁጥር 11) ፡፡ ዮአስ በይሁዳ ንጉስ በአሜሲያስ ላይ ጦሩን አዘመተ ፡፡ ዮአስ በሞተ ጊዜ ከሌሎች ከእስራኤል ነገስታት ጋር በሰማሪያ ተቀበረ (ቁጥር 12-13) ፡፡
2-ነገስት (13፡ 14-21)፡ ከ 40 አመታት በላይ ኤልሳዕ ስላደረገዉ ምንም አልተጠቀሰም እዚህ ቦታ ላይ 70 አመታትን አገልግሎ ነበር ፤ አልሳዕ ታመመ ቆይቶም በበሽታዉ ሞተ (ቁጥር 14) ፡፡ የእስራኤል ንጉስ ዮአስታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ በነበረዉ በኤልሳዕ አለቀሰ (ቁጥር 14) ፤ ኤልሳዕም ዮአስን ቀስቱንና ፍላፃዎቹን እንዲወስድ ነገረው በፍላፃዉም ላይ ኤልሳዕ በንጉሱ እጅ ላይ እጁን አደረገ “ ዮአስ በሶሪያዊያን ላይ በነብዩ በኩል ከእግዚአብሄር በመጣዉ ኃይል እንደ ሚያደርስባቸው “ ያመለክታል (ቁጥር 15-16) ፡፡ ኤልሳዕ ዮአስን የምስራቁን መስኮት በመክፈት ከመስኮቱ ዉጪ ቀስቱን እንዲተኩሰዉ ነገረው (ቁጥር 17) ፤ ዮአስ በተኮሰዉ ጊዜ ኤልሳዕ በሶሪያዊያን ላይ የድል ማድረግ ቀስት እንደ ሆነ ነገረው (ቁጥር 17) ፡፡ ኤልሳዕ ዮአስን የቀሩትን ቀስቶች በመዉሰድ መሬቱን እንዲወጋ ነገረው ፤ ዮአስ ሰዎስት ጊዜ መሬቱን ወጋዉ (ቁጥር 18) ፡፡ ኤልሳዕ ዮአስ ከአምስት ወይም ከስድስት ጊዜ ይልቅ ሰዎስት ጊዜ ብቻ መሬቱን በመወጋቱ በመበሳጨት ዮአስ ሶሪያዊያንን እስከ ሚበቃው እስከ መጨረሻዉ ድረስ ሳይሆን ሰዎስት ጊዜ ብቻ ትመታለህ የሚል ትንቢታዊ ቃል ሰጠው (ቁጥር 19) ፤ ከዚያም ኤልሳዕ ሞተ ተቀበረም (ቁጥር 20) ፡፡ የሞዓባዊያን ሰላዮች በፀደይ ወደ ምድሪቱ በመጡ ጊዜ አንድ ሰዉ ሊቀብሩ የነበሩት እስራኤላዊያን ሰዉዬዉን ወደ ኤልሳዕ መቃብር ላይ ወረወሩት ፤ አካሉ የኤልሳዕን አጥንት በነካ ጊዜ ሰዉዬዉ በመንቃት ቆመ (ቁጥር 21) ፡፡ የኤልሳዕ አጥንት ሳይሆን እግዚአብሄር ስራዉን ሰራ (ሕዝ 37፡ 4፣ ማቴ 27፡ 52) !
2-ነገስት (13፡ 22-25)፡ የሶሪያ ንጉስ አዛሄል በኢዮአካዝ ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስጨነቀ (ቁጥር 22) ፤ ነገር ግን አሁንም እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ እና ከያዕቆብ ጋር ስላደረገዉ ኪዳን ርህራሄ ነበረው (ቁጥር 23) ፡፡ ንጉስ አዛሄል በሞተ ጊዜ ልጁ ወልደ አዴር የሶሪያ ንጉስ ተደረገ ፤ ዮአስ በወልደ አዴር ላይ በጦርነት በመዝመት አዛሄል ከዮአስ አባት ከኢዮአካዝ ወስዷቸዉ የነበሩትን ከተሞች መልሶ ወሰደ ፡፡ ዮአስ ወልደ አዴርን ነቢዩ ኤልሳዕ እንደ ተነበየዉ በትክክል ሰዎስት ጊዜ ብቻ አሸነፈው (ቁጥር 24-25) ፡፡
መደምደሚያ
ዮአስ በሶሪያ እና በወልደ አዴር ላይ ከፊል ድል ብቻ ነበር የነበረዉ ምክንያቱም አምኖት በነበረዉ ልክ ብቻ ስለተጓዘ፡፡ በህይወታችን በሁሉም ስፍራ እንዲሁ በተመሳሳይ ይሄዳል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 450.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 477.
Nelson’s Commentary, p. 477.
John MacArthur, p. 451.
ጥያቄዎች
-
በ 2ነገ (13፡ 17) ቀስቱ ምን ይወክላል ? በቁጥር 19 የእግዚአብሄር ሰዉ በንጉሱ ላይ ለምን ነበር የተበሳጨው ?
-
በ 2ነገ (13፡ 23) እግዚአብሄር ስለ ኪዳኑ ቸር እና መሀሪ ነበር ፤ ኪዳኑ ምን ነበር ? (ዘፍ 15፡ 18-21፣ 26፡ 2-5፣ 28፡ 13-15)
-
በ 2ነገ (14፡ 3) አሜስያስ በእግዚአብሄር ፊት የሚያስደስት ነገር አደረገ ነገር ግን በሙሉ አልነበረም ፤ በአያቱ በዳዊንት ፋንታ የአባቱን መንገድ ተከተለ ፤ ከእግዚአብሄር ኋላ የተከተላችሁበትን ነገር ግን በሙሉ ያልነበረበትን ጊዜ ወይም ሁኔታ ማሰብ ትችላላችሁ ? በምን መንገድ ? ተፀፅታችሁበታል ? ለምን ወይስ ለምን አልተፀፀታችሁም ?
-
በ 2ነገስት (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 13:21
“Once, as the Israelites were burying a man, suddenly they saw a raiding party, so they threw the man into Elisha’s tomb. When he touched Elisha’s bones, the man revived and stood up!”
ኤልሳዕ በኤልያስ ላይ ከነበረው ሁለት እጥፍ ኃይል የተሰጠው እግዚአብሔር የመረጠው ነቢይ ነበር ፡፡ ለጥሪው የተቀባው ኤልሳዕ የእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል ታምራዊ በሆነ መንገድ በውስጡ ነበረ ፡፡ ኤልሳዕም በሞተ ጊዜ አካሉ ተቀብሮ ነበር ፡፡ በዚያም አመት በጸደይ እስራኤላውያን አንድን ሰው ሲቀብሩ የሞአብ አደጋ ጣዮችን አዩ ፡፡ ስለዚህም ሬሳውን በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት ፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ ? እግዚአብሔር በእልሳዕ ህይወትና ሞት ያለውን የእርሱን ኃይልና ጥንካሬ የሚገልጥበት ሌላ አንድ ተጨማሪ ታአምራት ነበረው ፡፡
እግዚአብሔር የሞቱ ነገሮችን እንደሚያስነሳ ደግሞም የደረቁ አጥንቶችንም እንደሚያስነሳ ይናገራል ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታይ በእናንተ ውስጥ ይህን የሚመስል የትንሳኤ ኃይል አለ ፡፡ የሆነ ሰው ወደ እናንተ ቢጣል ምን ይፈጠር ይሆን ? በክርስቶስ ህያው መሆናችሁን ያውቁ ይሆን ? ኢየሱስ ለሚቀበሉት ሁሉ ህይወትን ሊሰጥ መጥቷል ፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ፍቅር እየፈነደቃችሁ ኑሩ እንድሁም በውሎአችሁ ከእናንተ ጋር ለሚገናኙት ሁሉ እንድተላለፍባቸው አድርጉ ፡፡ ምናልባት ዛሬ በዙሪያችን ያሉትን የደረቁ አጥንቶች የማንቃት ቀን ይሆናል !
“ ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 13፡21
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢዮብ 33፡4 –“ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል አምላክ እስትንፋስ ህይወትን ሰጠኝ ፡፡ “
ሕዝቅኤል 37፡5 –“ ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንደዚህ ይላል እነሆ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በህይወትም ትኖራላችሁ ፡፡ “
ዮሐንስ 5፡21 – “ አብ ሙታንን እንደሚያነሳ ህይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ህይወትን ይሰጣቸዋል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።