Waiting on the Lord's Timing
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁላችንም የመንገድ ብስጭትን እንዴት አንድ ድርጊት ከሌላዉ ሰዉ ኃላ ጎማ ሌለኛዉ አሽከርካሪዉን ሁኔታዉን በማባባስ ከቁጥጥር ዉጪ አንዴት ማድረግ እንደ ሚችል ሰምተናል ፡፡ ክፉን ለክፉ ስለ መመለስ በምናወራ ጊዜ እንዲአይነቱን ነገር በፍፁም አናደርግም ለማለት ቀላል ነው ፤ ነገር ግን የብስጭት ጡዘቶች ከቁጥጥር ዉጪ በሚሆን ጊዜ ቀላል ነው ፡፡ የእስራኤል ንጉስ ኢዩ የይሁዳን ንጉስ አካዚያስን ገድሎታል ፤ እናቱ ጎቶልያም ለዙፋኑ ወራሾቹን ሁሉ በመግደል የልጇን ዙፋን ትወስዳለች ፤ ነገር ግን ይህም የዳነ ዘር ታሪክ ነው ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (11፡ 1-3)፡ የንኩስ አካዚያስ እናት ጎቶሊያ ልጇ ሞቶ ባገኘችዉ ጊዜ የመንግስታትን ዘር ወራሽ ሁሉ ገደለች (ቁጥር 1) ፤ ነገር ግን የአካዚያስ እህት ዮሳቤት የአካዚያስን ህፃን ወንድ ልጅ ኢዮአስን በማዳን እርሱን እና ሞግዚቱን ከአካዚያስ እናት ደበቀቻቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ኢዮአስ ሴት አያቱ ይሁዳን እስክታስተዳድር ድረስ ለስድስት አመት በመደበቅ ቆየ (ቁጥር 3) ፡፡ ዋይርስቤ የኢዮአስን መደበቂያ ስፍራ “ አሮጌ የአልጋ ልብስ በሚጠራቀምበት ከዚያም በቤተ መቅደስ ዉስጥ በአንድ ክፍል እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ይህ የይሁዳ ቀጣዩ ንጉስ የእግዚአብሄር ጊዜ እስኪመጣለት ድረስ ጠበቀ ፡፡
2-ነገስት (11፡ 4-16)፡ ዮሳቤት የታላቁ ካህን ዮዳሄ ሚስት ነበረች፡፡ በጎቶልያ አስተዳደር በሰባተኛዉ አመት ዮዳሄ በአንድ ላይ እያንዳንዳቸዉ በመቶ ሰዎች ላይ የተሾሙ አምስት አዛዦችን እና አምስት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን አመጣ ፤ ለእነርሱም ወጣቱን ንጉስ በማስቀመጥ ኢዮአስን እንዲጠብቁት በመኃላ አስማላቸው ፡፡
ዮዳሄ የዚህን የ510 ሰዎች ቡድን የኢዮአስን ህይወት እንዴት አድርገዉ ያለሟቋረጥ እንደሚጠብቁት ትዕዛዝ ሰጣቸው (ቁጥር 4-8) ፤ እያንዳንዳቸዉ መቶ የሆኑትን ሰሰዎስት ክፍሎች በንጉሱ ቤት ዙሪያ መግቢያ እንዲቀመጡ አዘዛቸው ፤ ሌሎቹ ሁለቱ ክፍሎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ተቀመጡ (ተሰየሙ) ፡፡ ክፍሎቹ በቤቱ እና በቤተ መቅደሱ ላይ ይዟዟራሉ ፤ በተጨማሪም የወታዶሮቹን ጦር እንዲጠብቁ ተነገራቸው ንጉሱንም የቀረበዉን ማንኛዉንም ሰዉ እንዲገሉ ታዘዙ ፡፡
አዛዦቹ ዮዳሄ ያዘዛቸዉን ሁሉንም ነገር አደረጉ (ቁጥር 9) ፤ አዛዦቹም ኢዮአስን ለመጠበቅ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ተለይቶ ተቀምጦ የነበረዉን የንጉስ ዳዊትን ጋሻ እና ሰይፍ ተሰጣቸው (ቁጥር 10-11) ፤ እነዚህ መሳሪያዎች በአድርአዛር ላይ ከተዘመተ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ተለይተዉ ተቀምጠዉ ነበር (2ሳሙ 8፡ 11) ፡፡ ዮዳሄም ኢዮአስን በማዉጣት ዘዉዱን በእርሱ ላይ በማስቀመጥ እንደ ንጉስ አወጀዉ (ንጉስ አደረገው) (ቁጥር 12) (ዕብ 6፡ 12) ፡፡
ንግስቲቱ ከቤተ መቅደስ ጩኸቱን በሰማች ጊዜ እየተካሄደ የነበረዉን ለማየት ሄደች (ቁጥር 13) ፤ ወደ ቤተ መቅደሱም ስትመለከት እንደ ተለመደዉ አዲሱ ዘዉድ ያደረገዉ ንጉስ ከአምዱ አጠገብ ቆሞ አየች (ቁጥር 14) ፡፡ ጎቶልያ ግን ክህደት እያለች ጮኸች ዮዳሄም አዛዦቹን አስረዉ ከቤተ መቅደሱ ዉጪ እንዲወስዷት እና የሚከተላትን ሁሉ እንዲገድሉ አዘዛቸው (ቁጥር 15) ፡፡ ከንጉሱ ቤት ዉጪ ተገደለች (ቁጥር 16) (ወደ ንጉሱ ቤት ተወስዳ በዚያ ተገደለች) ፡፡
2-ነገስት (11፡ 17-21)፡ ከዚያም ዮዳሄ በእግዚአብሄር፣ በንጉሱ እና በህዝቡ መካከል ኪዳንን አደረገ በተጨማሪም ሌላ በንጉሱ እና በህዝቡ መካከል በማድረግ ተሰብሮ የነበረዉን ኪዳን አደሰ (ቁጥር 17) ፡፡ ህዝቡ የባዖል መስገጃዎችን(ቤቶችን) በማፈራረስ ሁሉንም መሰዊያዎች እና ምስሎች ሰባበሩ (ቁጥር 18) ፡፡ ንጉስ ኢዮአስም በቤቱ በንጉስ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር (ቁጥር 19) ፤ የዳዊት ኪዳንም እንደ ገና ተመሰረተ ህዝቡም ተደሰተ (ቁጥር 20) ፡፡ ኢዮአስ በሰባት አመቱ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 21) ፡፡
መደምደሚያ
ዮዳሄ በአንድ ላይ ያመጣቸዉ ቡድኖች በእግዚአብሄር ተስፋ የሚያምኑ ቅሬታዎች ነበሩ ፡፡ ድርጊታቸዉ በይሁዳ ላይ መነቃቃት አመጣ ፤ ዋይርስቤ “ መነቃቃት ማለት በቀላሉ የእግዚአብሄርን ቃል ማክበር እና አባቶቻችን እንዲያደርጉት ያዘዛቸዉን ማድረግ ነው ፤ የአሁኑ አዲስነት አያስፈልገንም የቀደመዉ እዉነታ እንጂ በማለት “ ፅፏል፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 546.
Wiersbe, p. 548
ጥያቄዎች
-
ጎቶልያ ልጇ ከሞተ ጀምሮ ንግስት ለመሆን ሁሉንም ቤተሰብ እንዳጠፋች ታስባላችሁ ? ዮሳቤት ኢዮአስን ለምን ሰረቀች ? (2 ነገ 11፡ 1-3)
-
በ 2ነገ (12፡ 6) የቤተ መቅደሱ መጠገን እስካሁን አልተደረገም ነበር ፤ ለምን እንዳልተደረገ ምን ታስባላችሁ?
-
በ 2ነገ (12፡ 17-18) ኢዮአስ በንብረት ክፍል ያገኘዉን የተቀደሰዉን ሁሉንም ነገር ለምን ለንጉስ አዛሄል እንደላከ ምን ታስባላችሁ ?
-
በ 2ነገስት (11-12) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 11:3
“Joash was in hiding with Jehosheba in the LORD’s temple six years while Athaliah ruled over the land.”
የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጅዋ እንደ ሞቱ ባየች ጊዜ ተነስታ የመንግስትን ዘር ሁሉ አጠፋች ፡፡ ከዚያም ዙፋኑን ለራስዋ ወሰደች በይሁዳም ለስድስት አመት ንግሥት ሆነች ፡፡ ነገር ግን ዮሳቤት የተባለች ጎበዝ ሴት ከአካዝያስ ልጆች መካከል አንዱ የሆነውን ኢዮአስን በድብቅ በማዳን ደበቀችው ፡፡ በሰባተኛው አመት ካህኑ ዮዳሄ የዳዊት ዘር መትረፉን የሰባት አመቱ ኢዮአስ በህይወት መኖሩን ገለጠ ፡፡ ኢዮአስንም ዘውድ ጭነው ቀቡት እርሱም የሚገባውን ቦታ ዙፋኑን ተቀበለ ፡፡ ህዝቡም ሁሉ ደስ አላቸው ፣ ጎቶልያም ተገደለች ፡፡
ለሰባት አመታት ኢዮአስ ከይሁዳ ህዝብ ሁሉ ተደብቆ ቆየ ፡፡ ይህንን ጊዜ ተደብቆ ባያሳልፍ ኖሮ ምናልባት እርሱ በይሁዳ ላይ ፈዕሞ ባልነገሰ ነበር ፡፡ በመደበቅ ያሳለፍካቸው ጊዜያት አሉ ይሆን ? ምናልባት ዛሬ እግዚአብሔር ለሆነ ነገር እንደጠራህ ታውቅ ይሆናል ነገር ግን ጊዜው እንዳልደረሰ ትረዳለህ ፡፡ በመደበቂያ ቦታ ፣ በመጠበቂያ ቦታ ፣ በጥሞና ጊዜ ላይ ነህ ፡፡ ከውጭ ማንም ላያይ ወይም ላይረዳ ይችላል ነገር ግን በልብህ ታውቃለህ እግዚአብሔር ወደ ፊት ላለው ነገር እያዘጋጀህ እንደሆነ ፡፡ በእርሱ እረፍ ፡፡ አታስገድደው አትግፋው ፡፡ እመን እግዚአብሔር በስውር ስራ ላይ እንዳለ ፡፡ ስትጠብቅም ወደ እግዚአብሔር ቅረብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል ፡፡
“ በእርስዋም ዘንድ ተሸሽጎ በእግዚአብሔር ቤት ስድስት አመት ያህል ተቀመጠ ፡፡ ጎቶልያም በምድር ላይ ነገሠች ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 11፡3
ተጨማሪ ጥቅስ
መክብብ 3፡11 –“ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሰራውን ስራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው ፡፡ “
ሰቆቃው ኤርምያስ 3፡25-27 –“ እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው ፡፡ ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው፡፡ ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው ፡፡ “
ዕብራውያን 6፡12 –“ በእምነትና በትዕግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።