Historical Books 2 Kings

Not Having a Complete Heart for God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 273 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኬልይ እንደ ሚለዉ የዛሬዉ ትምህርት በትንሹ የሚያስገርም ነገር ነው ፡፡ በምዕራፍ 8 በሚገኘዉ በዚህ ፅሁፍ መነሻ እጀምር ፤ ሁለተኛ ነገስት ከአካዚያስ አስተዳደር (ከእስራኤል ዘጠነኛዉ ንጉስ) ከ863 ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ እስራኤል በሶሪያ በወደቀችበት በ722 ከክርስቶስ ልደት በፊት እና እስራኤል እና ይሁዳ በባይሎን እስከ ወደቁበት እስከ 586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሰዎስት መቶ አመት ርዝመት ያክል ይሸፍናል ፡፡ በእግዚአብሄር ሰዎች ታሪክ ይህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር ፡፡

እነዚህን ነገስታቶች በመመልከት መደናገር ቀላል ነው ምክንያቱም ሁለት አካዝያስን ንጉሶች ነበሩ በተጨማሪም ሁለት ኢዮራም ንጉሶች ነበሩ ከእያንዳንዳቸዉ በእንዳንዱ መንግስት ነበሩ ፡፡ ሁለቱም አካዚያሶች እያንዳንዳቸዉ አንድ አመት አስተዳደሩ ነገር ግን አስተዳደራቸዉ በተመሳሳይ ጊዜ(የተደራረበ) አልነበረም ፡፡ የሁለቱ ኢዮራም አስተዳደር ተደራርቧል ፡፡ የእስራኤል አካዚያስ ከይሁዳዉ አካዚያስ 11 አመት ቀድሞ አስተዳደረ ፡፡ በይሁዳ ኢዮራም (853-841 ከክርስቶስ ልደት በፊት) አካዚያስን (841 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ይቀድማል ነገር ግን በእስራኤል አካዚያስ (853-852 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ኢዮራምን (852-841 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ይቀድማል ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (9፡ 1-10)፡ ኤልሳዕ የንጉሱን የኢዮራምን አዛዥ ኢዩን እንደ አዲስ ንጉስ በእስራኤል ቤቱን ለማጥራት እንዲቀባዉ አንድ ነቢይ ላከ (ቁጥር 1-4) ፡፡ ነቢዩ የተላከበትን ለማድረግ የራሱን ህይወት አደጋ ላይ ጣለ ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ መሰረት “ ኢዩ በእግዚአብሄር በተሸመ አገልጋይ የተቀባ ብቸኛዉ የእስራኤል ንጉስ ነው “ ፡፡ የኢዩ እንደ ንጉስ መቀባትከጥቂት 20 አመታት በፊት የተሰጠዉ የኤልያስ ትንቢት መፈፀም ነው (1ነገ 19፡ 15-16) ፡፡ በእነዚህ ሁለት ምዕራፎች የተፈፀሙ ብዙ ትንቢቶች አሉ ምክንያቱም በጣም ለረጅም ጊዜ ክፉ ብቻ መጠራቀም ስለቻለ ፡፡ ሲቀባ ኢዩ የአክዓብን እና የኤልዛቤልን ቤት ሁሉ እንዲያጠፋ ተነግሮታል (ቁጥር 7-10) ፡፡

2-ነገስት (9፡ 11-13)፡ የእርሱ ሰዎች ምን እንደ ተፈጠረ በጠየቁት ጊዜ ኢዩ ላለመመለስ ሞከረ ነገር ግን በመጨረሻም እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ንጉስ አድርጎ እንደ ቀባው ተቀበለ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ሰዎቹም ኢዩን እንደ ንጉስ አወጁት(አወሩለት) (ቁጥር 13) ፡፡

2-ነገስት (9፡ 14-16)፡ ኢዩ ንጉሱን ለመግደል በማቀድ ጊዜ አላጠፋም (ቁጥር 14-16) ፡፡ ኢዮራም የሰዓቱ የእስራኤል ንጉስ ለአክዓብ እና ለኤልዛቤል ልጅ የነበረው በዉጊያ ተጎድቶ ስለ ነበር ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ ነበር ፤ የይሁዳ ንጉስ አካዝያስም ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ ነበር (2 ነገ 8፡ 28-29) ፡፡ ኢዩ አዛዦቹን ከእነርሱ 25 ማይል ርቃ ከምትገኘዉ ከኢይዝራኤል ማንም እንዳያመልጥ አዘዛቸው ትዕዛዙም የእስራኤልን እና የይሁዳን የሁለቱንም ንጉሶች አካቷል ፡፡

2-ነገስት (9፡ 17-29)፡ በኢይዝራኤል ግንብ ላይ ያለ አንድ ጠባቂ የኢዩ ወታደሮች እየቀረቡ እንደ ነበር ተናገረ ኢዮራምም በሰላም እንደ መጡ ለመጠየቅ አንድ ፈረሰኛ ላከ (ቁጥር 17) ፤ ይሁን እንጂ መልዕክተኛዉ ሳይመለስ የኢዩን ሰራዊት ተቀላቀለ ፡፡ ኢዮራምም በተመሳሳይ ጥያቄ ሌላ ፈረሰኛ ላከ እርሱም ደግሞ የኢዩንም ሰራዊት ተቀላቀለ (ቁጥር 19-20) ፡፡

የእስራኤል እና የይሁዳ ንጉሶች ኢዩን ለመገናኘት ወጥተዉ በመሄድ በሰላም እንደ መጣ ጠየቁት (ቁጥር 21-22) ፤ ናቡቴ ተገድሎበት በነበረዉ አክዓብ የወይን ስፍራዉ ባደረገው በናቡቴ መሬት ላይ ኢዩን አገኙት ( 1ነገ 21፡ 116) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለዝናዉ(ለስሙ) ዉጊያዉ የደከመዉን ንጉስ በማምጣት ተጋጣሚዉን አገናኘዉ ፤ ከግልፍተኛ አዛዡ የጦርን ጥቃት ፈራ ፤ ምናልባትም በህጋዊ ንጉሱ ላይ የህዝብ ማሳመፅ ተግባር እንደ ሆነ ለማወቅ ሊያገኘዉ እንደ ፈለገ “ ይናገራል ፡፡ ኢዩም በኤልዛቤል ድርጊት ምክንያት ሰላም ሊኖር እንደ ማይችል መለሰላቸው (ቁጥር 22) ፤ “ የኤልዛቤል መንፈሳዊ ምንዝርና ወደ መንግስቱ አሰቃቂ ሰይጣናዊ ድርጊቶችን በማምጣት ፍርዳቸዉን አትመዋል ፤ እግዚአብሄር አስፈራርቶ እንደ ነበረው እንዲዚህ አይነቶቹ ተግባራት በሚገባ ስለ ህዝቡ ዉርስ ይመጣሉ “ ፡፡ (ዘዳ 28፡ 15፣ 25-26) ፡፡

ይህ የማጨድ እና የመዝራትን መርህ ያሳያል - የተተከለዉ ያድጋል አምላካዊ ወይም አለማዊ ቢሆንም ፡፡ ኢዮራም ለማምለጥ እንደሞከረ ኢዩ በቀስት ወጋዉ ኢዮራምም ሞተ (ቁጥር 24) ፤ ኢዩ የነበረዉን የኢዮራምን ሰዉነት ወደ ናቡቴ እርሻ ወረወረው በ 1ነገስት 21 ከእግዚአብሄር የኤልያስ ትንቢት ተፈፀመ ፡፡ ንጉስ አካዝያስም ሸሸ ነገር ግን ተወጋ በመጊዶም ሞተ (ቁጥር 27) ፡፡ ዋይርስቤ አካዝያስ በመጊዶ ሊሸሸግ እንደ ሞከረ ነገር ግን የኢዩ ሰዎች በዚያ ደርሰዉ እንደ ገደሉትም ይናገራል ፡፡ የአካዝያስ አካል ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ በዳዊት ነገስታት ስፍራ ቀበሩት ፡፡

“ በኢዮራም፣ በባዖል አምልኮ እና የእናቱን የጎቶሊያን የአጎት ልጅ በመከተል ስላላመቻመቸ ከዚህ ሁሉ እፍረት እና ሽንፈት ዳነ “ ፡፡ ሁልጊዜ ኃጢዓት ወደ ሞት ይመራል ነገር ግን ኢየሱስ ከዚያ ኡደት ሊያወጣን መጣ ፡፡

2- ነገስት (9፡ 30-37)፡ ኤልዛቤል የተፈጠረዉን ሰማች አይኖቿን በመኳል ፀጉሯን አስጌጠች እስከ መጨረሻ እምቢተኝ እንደ ሆነች ቀረች (ቁጥር 30) ፡፡ ኢዩ ብቅ ባለ ጊዜ በማንጓጠጥ ዙፋኑን ለመያዝ ጌታዉን የገደለ አንድ ከሀዲ በሆነዉ ስም ዘምሪ ብላ ጠራቸው (ቁጥር 31) (1 ነገ 16፡ 11-12) ፡፡ ኢዩ ከጃንደረባዎቹ ድጋፍ ባገኘ ጊዜ በመስኮቱ አዉጥተዉ እንዲወረዉሯት አዘዛቸው ፤ ደሟም በግንቡ ላይ እና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ ኢዩም በእርሷላይ ሄደባት (ቁጥር 32-33) ፡፡ ይህ የሌለኛዉ ትንቢት መፈፀም ነው (1ነገ 21፡ 22-23) ፡፡ አካሏ ወደ አንድ ማሳ ተወረወረ እንደ ቆሻሻም ተቆጠረ (ቁጥር 37) ፡፡

2-ነገስት (10)፡ ኢዩ የአክዓብን ቤት ማስወገድ ቀጠለ ፡፡ የአክዓብን ሰባ ወንድ ልጆች ( ቁጥር 1-11)፣ የአካዚያስን አርባ ሁለት ወንድሞች(ቁጥር 12-14)፣ የቀረዉን የአክዓብን ቤተሰብ (ቁጥር 15-17) እና የባዖልን አማላኪዎችን (ቁጥር 18-27) ገደለ ፡፡ ኢዩ ቅናቱን ለእግዚአብሄር አፈሰሰ (ቁጥር 16) ፤ ነገር ግን በእግዚአብሄር መንገድ አልተጓዘም ( ቁጥር 29-31) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኢዩ የባዕል መስገጃዎችን ማጥፋት ፖለቲካዊ ድርጊት ነበር ፤ የቀጠለዉ የአምልኮ አወቃቀር ፖሊሲዉ በእስራኤል ከእዉነተኛ መንፈሳዊ መነቃቃት ዉጪ እንደ ሆነ በግል በሚታየዉ በኢዮራም 1 የተመሰረተ ነበር ይልል “ ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ ከኃጢዓት ነፃ ሊያወጣን መጣ ፤ ይህን ነፃነት ለማግኘት ብቸኛዉ መንገድ ኢየሱስን የህይወታችን ጌታ ማድረግ ነዉ - ማለትም ሁሉንም ነገር ለእርሱ መስጠት ፡፡ ኢዩ ጣዖቶቹን ስላላስወገድ ስርዓቱን ጎዳበት ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለእኛ በምድር ላይ ጊዜአችን በጣም አጭር ነው ፤ ከዘላለም ጋር ስናወዳድረዉ እንደ አንድ እርግብ ግብ ነው ፡፡ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር እንድትሰጡ አበረታታችኋለሁ ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ምንም የለም ጥቅም የሚያስገኝ ማጭበርበር ወይም ማንኛዉም አይነት ኃጢዓት የለም ፡፡ በእግዚአብሄር በሙሉ ነፃነት በመጓዝ እንዲጠቀምባችሁ ፍቀዱለት ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 538.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 472.

  3. Nelson’s Commentary, p. 472.

  4. Wiersbe, p. 539.

  5. Wiersbe, p. 539.

  6. Nelson’s Commentary, p. 474.

ጥያቄዎች

  1. በመጀመሪያ እግዚአብሄር ኢዩን እንዲቀባ ምንን ነገረው (1ነገ 19፡ 16) ? አንድን ሰዉ መቀባት ማለት ምን ማለት ነው ? (1 ሳሙ 10፡ 1፣ ሉቃ 4፡ 18-19)
  2. ኢዩ የአክዓብን ቤተሰብ እንዲያጠፋ ለምን ነበር የተጠየቀው ( 1ነገ 21፡ 21-24) ? ከእግዚአብሄር የሆነዉን ይህን ቃል ፈፅሟል ? ( 2 ነገ 10፡ 17)
  3. በ 2ነገ (9፡ 11) የኢዩ ማህበር ሰራተኞች ወጣቱን ነቢይ እብድ ብለዉ ጠሩት ፤ በመፅሀፍ ላይ አማኞች እብድ ብለዉ የከሰሱበትን ስፍራ ማሰብ ትችላላችሁ ( 1ሳሙ 21፡ 12-14፣ ማር 3፡ 20-21፣ ዮሐ 10፡ 20፣ ሐዋ 26፡ 24፣ 2ቆሮ 5፡ 13) ? ስለ ወንጌል እንደ እብድ ተከሳችሁ(ተብላችሁ) ታውቃላችሁ ?
  4. ኤልዛቤል በእግዚአብሄር ፊት ምን ክፉ ነገር አደረገች (1 ነገ 16፡ 31፣ 18፡ 19) ? በራሳችሁ ህይወት የኤልዛቤል የሆነን ነገር በፍጥነት ለማጥፋት ምን ማድረግ ያስፈልጋችኋል ?
  5. ኢዩ አድርጎት ስለ ነበረዉ ስራ እግዚአብሄር እንዴት ሸለመው ? ኢዩ መልካም አድርጎ ከነበር ወደ ሆሴ (1፡ 4) መግለጫ(መዝገብ) እንዴት ትወስዱታላችሁ ( 2ነገ 9፡ 15) ? ኢዩ የእግዚአብሄር ቃል አመቻምቾ ነበር ?
  6. በ 2 ነገስት (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 10:28–29

“So Jehu destroyed Baal worship in Israel. However, he did not turn away from the sins of Jeroboam son of Nebat, which he had caused Israel to commit—the worship of the golden calves at Bethel and Dan.”

ኤልሳዕ በእስራኤል ላይ ንጉስ እንዲሆን ኢዩን ቀባው ፡፡ ንጉስ ኢዩም ንጉስ ኢዮራምን ፣ ንጉስ አካዝያስንና ኤልዛቤልን ከገደለ በኋላ የአክዓብን ቤተሰብ ሁሉና የበኣልን ተከታዮች ይገድል ዘንድ ሄደ ፡፡ ምንም እንኳ ንጉስ ኢዩ ለእግዚአብሔር እንደቀና ቢናገርም ደግሞም አብዛኛውን ክፋት መግደልና ማስወገድ ላይ ቢሳካለትም ነገር ግን አንድን ኃጢአት ፈጽሞ አላጠፋም እርሱም ፡- የወርቅ እምቦሶች አምልኮ ነበር ፡፡ ይህ ኃጢአት በእስራኤል ቀርቶ ነበር ፡፡

ኢየሱስ ከኃጢአት ባርነት ሊያወጣን መቷል ፡፡ ህይወትህን ሙሉ ለእርሱ አሳልፈህ እንድትሰጥ ይሻል ፡፡ የጌታ ጸጋ ይሸፍንሃል ፍቅሩም ከአንተ አይለይም ፡፡ ነገር ግን ወደ ኃጢአት ከረጢት ዘልቀህ ስትገባ በክርስቶስ ካለው ፍጹም ነጻነት ትወጣለህ ፡፡ ምክንያቱም በክርስቶስ ልንለማመደው የተገባ ኃጢአት የለም ፡፡ ዛሬ ምን ይሆን ከህይወትህ ሙሉ በሙሉ ልታስወግደው የሚያስፈልግህ ? “ ጌታ ሆይ ሁሉ ያንተ ነው “ በል ፡፡ ጸጋውን ተቀበል ፤ በየቀኑም በመንፈሱ ተመላለስ የስጋንም ስራ አትፈጽምም ፡፡

“ እንድሁም ኢዩ በኣልን ከእስራኤል አጠፋ ፡፡ ነገር ግን እስራኤልን ካሳተው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኃጢአት በቤቴልና በዳን ከነበሩት ከወርቁ እምቦሶች ኢዩ አልራቀም ፡፡ “

  • 2ኛ ነገሥት 10፡28-29

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 3፡36 –“ በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው በልጁ የማያምን ግን የእግዚአበሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ህይወትን አያይም ፡፡ “

ዮሐንስ 8፡36 –“ እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ ፡፡ “

ገላትያ 5፡1 –“ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ ፡፡ “