The Sin of Disobedience
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬም ጥናታችንን በ 2ነገስት 7 እንቀጥላለን ፡፡ ለዚህ ትምህርት መነሻ ለመሳል ሰማሪያ በርሀብ ስር እንደ ነበረች እና ከምግብ ዉጪ እንደ ነበሩ በ 2ነገስት 6 የተመዘገበዉን ያስታዉሳል ፡፡ በተስፋ መቁረጥ አንዲት ሴት ወደ ንጉሱ ተጠርታ ነበር ምክንያቱም ሌለኛይቱ ሴት የራሷን ልጅ ለመግደል ፈልጋ ስለ ነበር ለዚያ ቀን ምግብ ይኖራቸዋል እናም ለቀጣዩ ቀን የሌለኛኝቱን ልጅ ሊበሉ ቃል ስለተገባቡ ፡፡ ሴቲቱ የመጀመሪያዉን ልጅ በላች ነገር ግን የሁለተኛዉ ልጅ እናት ልጇን ደበቀችዉ (ቁጥር 28-29) ፡፡ ንጉሱም በተፈጠረዉ ነገር በማፈር ሀዘኑን ለማሳየት የማቅ ልብስ ለበሰ (ቁጥር 30) ፤ ይህ ለምዕራፍ 7 መነሻ ነው ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (7፡ 1-20)፡ ይህን ክፍል “ ኤልሳዕ ወደ ማዳን “ የሚል ርዕስ መስጠት እንችላለን ምክንያቱም በመደጋገም ኤልሳ በመዝለል ጥቂት ማዳኖችን ስላደረገ ፡፡ ኤልሳዕ በማግስቱ (በቀጣዩ) ቀን በሰማሪያ በር ላይ እግዚአብሄር ምግብ እንደ ሚሸጥ ቃል እንደ ገባለት አወጀ (ቁጥር 1) ፤ ነገር ግን ንጉሱ የተደገፈዉ የንጉስ ሰራተኛ የኤልሳዕን ቃል ተጠራጠረው (ቁጥር 2) ፤ ኤልሳዕም ሰራተኛዉን ምግቡን እንደሚያየዉ ግን እንደማይበላዉ መለሰለት (ቁጥር 2) ፡፡ ለምፅ ያለባቸዉ አራት ሰዎች ወደ ከተማዋ ዉስጥ መሄድ እንደ ማይችሉ በማወቅ ይሞቱበት በነበረዉ ከከተማዋ ዉጪ ተቀመጡ ፤ ሶሪያዉያን ምግብ ይሰጡናል ብለዉ ተስፋ በማድረግ ወደ ሶሪያዉያን ሰፈር ሄዱ (ቁጥር 3-4) ፤ ይሁን እንጂ ሶሪያዊያን ሸሽተዉ ስለ ነበር ሰፈሩ ምድረበዳ(በርሃ) ሆኖ ነበር (ቁጥር 5-13) ፡፡ ንጉሱ ዜናዉን በተቀበለ ጊዜ ህዝቡ ሄደዉ ሰፈሩን ዘረፉ (ቁጥር 14-16) ፡፡ ንጉሱ የኤልሳዕን ቃል ተጠራጥሮ የነበረዉን ሰራተኛ የበሩን ኃላፊነት እንዲወስድ ሾመው ነገር ግን ምግብ ለማግኘት በጥድፊያቸዉ ህዝቡ ረግጦት ሞተ (ቁጥር 17-20) ፡፡
እንደ ክርስቲያን ይህ የኛ ታሪክ ነው ፡፡ እነዚያን ኃጢዓተኞች ለምፃሞችን ነበር ፤ የታመምን እና ከእግዚአብሄር አቅርቦት ዉጪ የተራብን ነበርን ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ ላለን አመፅ ሞት ይገባንል ፤ በትህትና ወደ እግዚአብሄር መገኘት ተደፋን ፡፡ በሞትና በባርነት ፋንታ ፀጋን አገኘን ፤ ህይወትን አገኘን ፤ የእግዚአብሄርን መልካምነት በላንም ጠጣንም ፡፡ ታላቅ ኃብት እና ንብረት በማግኘት ወስደን በልባችን ደበቅናቸው (መዝ 34፡ 8) ፡፡ በእኛ ዉስጥ የድነት መንገድ አለን (ራዕ 3፡ 17) ፡፡ ከአጥራችሁ(ከግንባችሁ) እንድትወጡ እጋብዛችኋለሁ ፤ ከደህንነታችሁ ዉጡ ፤ ምቹ የሆነዉን በመተዉ ህይወትን ፈልጉ ፡፡
2-ነገስት (8፡ 1-6)፡ ኤልሳዕ ወደ ህይወት መልሶ ያመጣዉን የሞተዉን የሱናማዊቱን ሴት ልጅ ታስታዉሱታላችሁ (2 ነገስት4) ? ኤልሳዕ ሴቲቱን እንደገና በመናገር ርሀብ እየመጣ እንደ ነበር አስጠነቀቃት (ቁጥር 1) ፡፡ የእናንተ የሆነዉን ነገር በመሸከፍ ርቆ መንቀሳቀስ ምክንያቱም የሚመጣዉ ርሃብ ከፍተኛ ትህትናና እምነት ይወስዳል ፤ ይሁን እንጂ ይቺ ሴት ከኤልሳዕ ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት ነበራት ፤ በዚያ አካባቢ በሚጓዝ ጊዜ በእርሷ ፎቅ ላይ ያርፍ ነበር ፤ ልጅ እንደ ምትወልድ ነግሯታል ከዚያም ልጁን ወደ ህይወት መልሶታል ፡፡ እርሱን በማመን ለሰባት አመታት ወደ ፍልስጤማዊያን ምድር ሄደች (ቁጥር 2) ፡፡ ሰባተኛዉ አመት መጨረሻ ላይ ወደ ቤት ተመለሰች (ቁጥር ቁጥር 3) ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሰባት አመታት ህዝቡን ለመፈተን እንዴት እንደ ተጠቀመባቸዉ የሚያስደንቅ አይደለም (ዘፍ 41፡ 17-30) ? ሰባት አመት ሙሉነትን ያመለክታል ፡፡ ምናልባትም በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር ለመቅጣት ወይም ለማንፃት ድርቁን ተጠቀመው ፡፡
ሴቲቱ ቤቷ እና እርሻዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሱ ትሄዳላች (ቁጥር 3) ፤ በንጉሱ ፊት በመጣች ጊዜ ንጉሱ ኤልሳዕ አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር ከኤልሳዕ አገልጋይ ከግያዝ ጋር ቃለ ምልልስ እያደረገ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ የእስራኤል ንጉስ ኤልስዓ ስላደረገዉ ነገር ለመስማት የሚጠይቁ መሆኑ አስደናቂ ነው ፡፡ ግያዝ እንደ መለሰለት ሴቲቱ ደረሰች ግያዝም ኤልሳዕ ልጇን ወደ ህይወት የመለሰላት እንደ ነበረች ገለፀለት (ቁጥር 5) ፡፡ ይህ አጋጣሚ ነበር ወይስ መለኮታዊ ቀጠሮ ? በግሌ አጋጣሚ እንደሆነ አላምንም ፡፡ ንጉሱም ታሪኳን ሰማ ትታዉ የሄደችዉን ሁሉንም ነገር መለሰላት (ቁጥር 6) ፡፡
2-ነገስት (8፡ 7-15)፡ የሶሪያ ንጉስ ታሞ ነበር ፤ ኤልሳዕ በአቅራቢያ እንደ ነበር በሰማ ጊዜ ከበሽታዉ እንዲያገግም ደርገዉ እንደ ሆን መዳን ለማግኘት ስጦታ ከተጫኑ አርባ ግመሎች ጋር አገልጋዩን አዛሄልን ላከው (ቁጥር 7-9) ፡፡ ኤልሳዕም ንጉሱ ከበሽታዉ እንደ ሚድን ነገር ግን በቅርብ እንደ ሚሞት ቃል ገባለት (ቁጥር 10) ፤ ከዚያም ኤልሳዕ አዛሄል ላይ አይኖቹን ትኩር በማድረግኤልሳዕ አለቀሰ (ቁጥር 11) ፡፡ ኤልሳዕ አዛሄል የሶሪያ ንጉስ በመሆን በእስራኤል ህዝብ ላይ አስከፊ ነገር ያደርጋል አለ (ቁጥር 12-13) ፤ ይህ እግዚአብሄር የሚያስት መንፈስ የተጠቀመበት ሌላ ምሳሌ ነው (1 ነገ 22፡ 20) ፡፡ ጌታዉን ንጉሱን እንዲገድለው ይህ ትንቢት ከኤልሳዕ አዛሄልን በቀላሉ የሳበ ነው ? አዛሄል ወደ ንጉሱ በተመለሰ ጊዜ ኤልሳዕ ያለዉን ግማሹን ብቻ ነገረው (ቁጥር 14) ፡፡ በቀጣዩ ቀን አዛሄል ንጉሱን ገደለው (ቁጥር 15) ፡፡
2-ነገስት (8፡ 16-24)፡ እንደ እስራኤል ንጉስ በኢዮራም ዘመን አምስተኛው አመት ላይ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ ላይ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 16) ፡፡ በጊዜዉ ኢዮራም 32 አመት ላይ ነበር ስምንት አመትም አስተዳደረ የንጉስ አክዓብን እና የንግስት ኤልዛቤልን ሴት ልጅ አገባ በእግዚአብሄርም አይን ክፉ ንጉስ ነበር (ቁጥር 1-18) ፡፡ ኤልዛቤል የሰዶም ንጉስ ሴት ልጅ ነበረች ፡፡ የተፈጠረዉ ስዕል የሰዶም ንጉስ በሁሉም በእስራኤል እና በይሁዳ መንገድ እያዳረሰ ነበር ስለሆነም ተፅዕኖ በጣም ኃይለኛ ነበር (ዘዳ 7፡ 3-4፣ 2ቆሮ 6፡ 14) ፡፡ እዚህ ቦታ ላይ ኤልዛቤል በህይወት ነበረች ፤ ሆኖም ግን እግዚአብሄር በዳዊት ኪዳን ምክንያት ይሁዳን ለመቅጣት ፍቃደኛ አልነበረም (ቁጥር 19) ፡፡ ኤዶምያስ በኤዮራም ላይ አመፀ ከዚያም ሊብና አመፀ (ቁጥር 20-23) ፤ ኢዮራም ሞተ በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ ፡፡ ልጁም አካዝያስ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 24) ፡፡
2-ነገስት (8፡ 25-29)፡ አካዚያስ ንጉስ በሆነ ጊዜ ሀያ ሁለት አመቱ ነበር አንድ አመትም ብቻ አስተዳደረ (ቁጥር 25-26) ፤ በእግዚአብሄርም ፊት በብዙ ክፉ ነገር አደረገ (ቁጥር 27) ፡፡ ከአጎቱ ከንጉስ ኢዮራም ጋር በሶሪያ ንጉስ በአዛሄል ላይ ለጦርነት ሄደ ፤ ኢዮራምም በመቁሰል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል (ኤልዛቤል ወደ ምትኖርበት) ተወሰደ (ቁጥር 28-29) ፤ አዛሄል ኢዮራምን ወደ ኢይዛራኤል ተከተለው (ቁጥር 29) ፡፡
መደምደሚያ
በመልካም እና በክፉ መካከል ያለዉ ዉጊያ፣ በእግዚአብሄር አመራርነት እና በክፉ አመራርነት እስራኤልና ይሁዳ ሁለቱም በወረርሽኝ ተመቱ ፡፡ ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ለመጓዝ የመረጡ ነገስታቶች ጥቂቶች እና ሩቅ መካከል ነበሩ ፤ በመታዘዝ ለመጓዝ እምቢ ያሉት ከሀገራዊ አንፃር እና እንዲሁም ህዝቡ በሀገሩ ዉስጥ በሀገራቸዉ ላይ ጥፋትን አስቀጠሉ ፡፡
ጥያቄዎች
-
2 ነገስት 7 መጀመሪያ ላይ ኤልሳዕ ምን ይሆናል እያለ ነበር ? ማንን እየተናገረ ነበር ምን እንደሚሆንስ ተናገረ ? በመጨረሻስ ሆኗል ? (2ነገ 7፡ 16)
-
ለምፃሞቹ በከተማዋ መግቢያ በር ላይ የነበሩት ለምን ነበር ? ( ዘሌ 13፡ 36፣ 45-46)
-
እግዚአብሄር ሞዓባዊያንን ለማሸነፍ ከአምስቱ ስሜቶቹ የትኛዉን ተጠቀመ (2ነገ 3፡ 21-23) ? ሶሪያዊያንን እግዚአብሄር እንዴት አሸነፋቸው ?
-
እንቲቱ እና ልጅየዉ ለንጉሱ ይግባኟን ለማድረስ በሄደች ጊዜ ምን እየሆነ ነበር ? ለእናንተ እግዚአብሄርበትክክለኛ ጊዜዉ ያደረገላችሁን ነገር ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
ኤልሳዕ ንጉሱ ይሞታል አይሞትም ለሚለዉ ጥያቄ በአደረገዉ መንገድ ለምን መለሰ ? እግዚአብሄር ኤላሳዕን ምንድን አሳየው ? እንዴት ነበር የተደረገው(የተፈፀመው) ?
-
በ 2ነገስት (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 7:9
“Then they said to each other, ‘We’re not doing what is right. Today is a day of good news. If we are silent and wait until morning light, our sin will catch up with us. Let’s go tell the king’s household.’”
በታለቁ ረሀብ ጊዜ በሰማርያ በር አራት ለምጻሞች ነበሩ ፡፡ እነርሱም ከመሞት ውጭ ምንም ምርጫ እንዳልነበራቸው አወቁ ፡፡ ነገር ግን አሳብ ነበራቸው እንድህ “ እስክንሞት ድረስ በዚህ ለምን እንቀመጣለን ? ወደ ከተማ እንገባ ዘንድ ብንወድድ ራብ በከተማ አለ በዚያም እንሞታለን በዚህም ብንቀመጥ እንሞታለን ፡፡ እንግዲህ ኑ ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሽሽ በህይወት ቢያኖሩን እንኖራለን ቢገድሉንም እንሞታለን “ ተባባሉ ፡፡ ስለዚህም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄዱ እግዚአብሔርም ሶርያውያንን ደንግጠው ሀብታቸውንና ያላቸውን ሁሉ ትተው እንድሸሹ አድርጎ ነበር ፡፡ ለምጻሞቹም ህሊናቸው እስኪወቅሳቸው ድረሰ ያገኙትን ሁሉ ሸሸጉ ፡፡ በመጨረሻም ሄደው ለንጉሡ ቤተሰብ የምስራቹን ይናገሩ ዘንድ ወሰኑ ፤ ስለዚህም አብልጠው መሰብሰብ ቻሉ ፡፡
ይህ የመዳን ታሪክ ነው ፡፡ በኃጢአታችሁ ብዛት ሙታኖች ናችሁ ፡፡ ከክርስቶስ ውጭ ተስፋ ቢስነትና ሞት ይገጥማቸኋል ፡፡ ምርጫ አላችሁ ልትቀመጡና በኃጢአታችሁ ልትሞቱ ወይም ልትነሱና ልትሄዱ የጸጋውን ፣ የተስፋውን ፣ የፍቅሩን ብዛት ልታዩ እንድሁም በኢየሱስ የሚገኘውን ዘላለማዊ ህይወት ልታገኙ ፡፡ የኢየሱስን ጸጋ ለማግኘት ከለመዳችሁት ቦታ ልትነሱና ሄዳችሁ እግዚአበሔር ለእናንተ ያዘጋጀውን ልታዩ ይገባል ፡፡ በኢየሱስ ያገኛችሁትን ስታምኑ በህይወት ትኖራላችሁ ፣ ሙሉ ትሆናላችሁ ደግሞም ትፈወሳላችሁ ፡፡ ይህ የምስራች ለእናንተ በቻ እንድትቀበሉት አይደለም ነገር ግን ለሌሎችም ጭምር እንጂ ፡፡ ሂዱና በክርስቶስ ብቻ ስለሚገኙት ሰለ እነዚህ ታላቅ ሀብቶች ተናገሩ ፡፡
“ ከዚያም ወዲያ አርስ በርሳቸው መልካም አላደረግንም ዛሬ የመልካም ምስራች ቀን ነው እኛም ዝም ብለናል አስኪነጋም ድረስ ብንቆይ በደለኞች እንሆናለን ኑ አንሂድ ለንጉሥ ቤተሰብ አንናገር ተባባሉ “
- 2ኛ ነገሥት 7፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
ማርቆስ 16፡15 –“ እንዲህም አላቸው ፡- ወደ አለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ፡፡
ሮሜ 6፡23 –“ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ህይወት ነው ፡፡ “
ኤፌሶን 2፡7 –“ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሳን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።