Historical Books 2 Kings

Radical Transformation

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 271 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 2ነገስት ታሪኮቹ በሆነ ሰዉ ላይ የሚመጣን የአዲስ ነገር ኡደትን የተሸለ ይሆናል ብሎ በማሰብ እና በሁሉም ጊዜ እግዚአብሄር እንዴት ጣልቃ እንደ ገባ ያሳያል ፡፡ ዛሬ እንደ ገና በ 2ነገስት 5 ዉስጥ በአንዲት ሴት ብላቴና ጣልቃ ገብነት እናየዋለን ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (5፡ 1)፡ ንዕማን ለሶሪያ ንጉስ አዛዥ እና አለቃ (ቀዳሚ ሰዉ) ነበር ፡፡ ንዕማን ሁልጊዜ ለንጉሱ መንገድ ያዘጋጃል ፤ ንዕማን በኃላፊነት ያለ ሰዉ ነበር ልታልፉት የምትፈልጉት ሰዉ አልነበረም ፤ ነገር ግን ንዕማን እንደ ቆዳ አይነት በሽታ ትልቅ ችግር አድጎበታል ፡፡ ብዙዎች በሽታዉ ለምፅ እንደ ነበር ያስባሉ ነገር ግን በግልፅ በፁሁፉ ላይ አልተገለፀም ፡፡ የተበላሸ እንደ ነበር እና ቀስ በቀስ ወደ ንዕማን ሞት እንደ ሚመራዉ እናዉቃለን ፡፡ በእስራኤል ለምፃሞች ከሌላዉ ማህበረሰብ ይለያሉ ነገር ግን ንዕማን እስከዚህ ስዓት ድረስ በተግባሩ መቀጠል የቻለ ነበር ፤ በመጨረሻም የንዕማን በሽታ በመለየት ያጠፋዋል ፡፡ የንዕማን የቆዳ በሽታ ልክ እንደ ኃጢዓት ነበር ፡፡

2-ነገስት (5፡ 2-3)፡ በቁጥር 2 ይቺ እስራኤላዊ ሴት ብላቴና የንዕማን ጠላት ትሆናለች ፤ ንዕማን ቤቷን በማጥፋት ወደ ምርኮ ወስዷታል ፤ በሁሉም ነገር በሚያስብል ደረጃ የነዕማን ተቃራኒ ነበረች ፡፡ ነዕማን ኃይለኛ(ኃል) ሰዉ ነበር እርሷ ደግሞ አገልጋይ ነበረች ፤ ንዕማን የብዙ ሰዎች ኃላፊነት ያለበት ሰዉ ነበር እርሷ ደግሞ የንዕማን ሚስት አገልጋይ ነበረች ፤ ይሁነ እንጂ በሰማሪያ ሄዶ ነቢዩን እንዲጎበኝ ለንዕማን የንዕማንን ሚስት ምበረታቷ የፍፁም እምነቷ ማስረጃ ነው ፡፡ አገልጋይቱ ሴትጠላቷ የሆነዉን ሰዉዬ ንዕማን የተፈወሰ እንዲሆን ፈለገች ፡፡

2-ነገስት (5፡ 4-10)፡ ንዕማን ከእግዚአብሄር አስፈላጊነት ወደ እግዚአብሄርን መፈለግ ተንቀሳቀሰ ፡፡ ንዕማን ሰማሪያን እንዲጎበኝ የንጉሱን ፍቃድ ተመለከተ ፤ ንጉሱም ንዕማንን ከደብዳቤ፣ ከወርቅ ጋር፣ ከብር እና ከመቀየሪ ልብሶች ጋር ሊልከዉ ተስማማ ፡፡ ምናልባትም ሁሉም ስጦታዎች ንዕማን እንዲፈወስ ከንጉሱ ሞገስን ለመግዛት መሞከሪያዎች ነበሩ ፡፡

የእስራኤል ንጉስ ኢዮራም የሶሪያን ንገስ ደብዳቤ በተቀበለ ጊዜ የፖለቲካ መሸወጃ እንደ ነበር አሰበ ፤ ልብሶቹንም በመቅደድ የንዕማንን የቆዳ በሽታ የመፈወስ ተግባር ለምንድን ይሰጠኛል በማለት ተገረመ ፡፡ ኤልሳዕ ስለ ንጉሱ አመኔታ ሲሰማ ንዕማንን ወደ እርሱ ላከዉ በማለት ቃል ላከለት ፤ ኤልሳዕ ንዕማን ወደ እርሱ ሲመጣ በእስራኤል አንድ ነቢይ እንዳለ ያዉቃል በማለት በእግዚአብሄር ያለዉን ሙሉ እምነት አሳዬ ፡፡ ኤልሳዕ መልሱ ስለ ነበረው በጥሪዉ ተጓዘ ፤ እጥፍ ቅባት እንዳለዉ ተጓዘ ፤ ለማዳን በእግዚአብሄር ኃይል መማመኑን አሳዬ ፡፡ ንዕማን እግዚአብሄርን ሲመለከት ኤልሳዕ መልስ እንደ ነበረው አዉቋል ፡፡ ንዕማን ፈዉሱን በመመልከት ሁሉንም ወደ ገበታዉ በማምጣት ኃብቱን እና ኃይሉን ለማሳየት ሁሉንም ፈረሶቹን እና ሰረገሎቹን ወደ ኤልሳዕ ቤት አመጣ ፤ ነገር ግን ኤልሳዕ ለንዕማን ለመመለስ ወደ በሩ እንኳን አልሄደም ፤ ይልቁንም ኤልሳዕ አንድ አገልጋይ ላከ ፡፡ ኤልሳዕ በዚህ መንገድ ድርጊቱን አደረገ ምክንያቱም ህጉ ርኩስ ከሆነ ሰዉ እስራኤላዊያን እንዳይቀርቡ ስለ ሚከለክል (ዘኁ 5፡ 1-4) ፡፡ ኤልሳዕ ለንዕማን ራሱን ዝቅ እንዲያደርግ መልዕክት ላከበት ፤ የኤልሳዕ መልዕክት አንድ ብቻ ነበር በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ታጠብ የሚል ፡፡ ምናልባትም ይህ ማለት ንዕማን ወደ ወንዙ በመሄድ ሁሉንም ራሱን በማርጠብ(ዉሃ በማስነካት) ከዚያም ይህን ሰባት ጊዜ ማድረግ ማለት ነበር ፡፡ ለንዕማን ዉርደት(ዝቅ ማለት) እንዴት ነው !

2-ነገስት (5፡ 11-12)፡ ንዕማን እግዚአብሄርን መፈለግ ከጀመረ በኋላ እግዚአብሄርን መቋቋም ጀመረ ፤ የኤልሳዕ ትዕዛዝ ቀላል ነበር ነገር ግን ንዕማንን ሞኝ የመሰለ ያደርጉታል ፤ ንዕማን ዝቅ ያለ መሆን አስፈለገው (1ጴጥ 5፡ 5) ፡፡ ፈረሶች፣ መልዕክተኞች ወይም ሰረገሎች አያስፈልጉም ፤ እነዚህ ነገሮች እርሱን አያነፁትም በእግዚአብሄር ፊት ቅዱስም አያደርጉትም ፡፡ ባደረግነዉ ነገር መሰረት ወይም ወደ እርሱ ባመጣነዉ ነገር መሰረት አልዳንንም ፤ ቲቶ (3፡ 5) የሚለው “ እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ስራ አይደለም “ ፡፡ ንዕማን ማድረግ የሚያስፈልገዉ ነገር ራሱን በማዋረድ ወደ ኤልሳዕ ማደማጥ ነበር ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በመፅሀፍት ከለምፅ የነፃ(የተፈወሰ) ሰዉ አልነበረም ፡፡ ንዕማን እንዴት ሊፈወስበት እንደሚችል የኤልሳዕን ትዕዛዝ ለመስማት የተበሳጨ ነበር - ከለምፅ በመንፃት እንዴት የመጀመሪያዉ ሰዉ እንደ ሚሆን - እና የኤልሳዕን መልስ ስላልወደደው ተናደደ ፡፡ ንዕማን የራሱ የጨዋታ እቅድ ነበረው ፤ እግዚአብሄርን መቃወሙን ከቀጠለ ንዕማን በእግዚአብሄር ፊት መንፈሳዊ መናዊ ልምፁን ሲያሳየዉ አገኘው ፡፡ የንዕማን አካላዊ ሁኔታ በሽታዉ ወደ ሚገድለዉ ደረጃ ዝቅ ማድረጉን ይቀጥላል - በጣም በተመሳሳይ መንፈሱ በኃጢዓት ይሸረሸራል ከእግዚአብሄር በመለየቱም በመንፈሳዊነት ይሞታል ፡፡

2-ነገስት (5፡ 13-14)፡ ንዕማን እግዚአብሄርን መታመን ጀመረ ፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ ንጉስ ወይም አንድ አዛዥ እግዚአብሄርን መቋቋም ከጀመረ እግዚአብሄርን መቋቋም ይቀጥላሉ ፤ ነገር ግን የንዕማን ታሪክ የተለየ ነበር በአንድ አገልጋዩ ምክንያት መቀየር ጀመረ ፡፡ አገልጋዩ ነቢዩ እንዲያደርግ የፈለገዉን ተናግሮት የነበረዉን ነቢዩ እንዳለዉ ንዕማን ወደ ሚፈፅመዉ አመለከተ ፤ አገልጋዩ ንዕማንን ነቢዩ የነገረዉን ትንሽ ነገር በማድረግ ራሱን ዝቅ እንዲያደርግ አሳመነው ፡፡ ንዕማን ሰዉነቱን በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ከታጠበ በኋላ ቆዳዎ ተፈወሰ ፤ የነፃ ነበር ፤ ሙሉ የሆነው የህፃን ልጅ እምነት የሚመስለዉ አዳነው (ማቴ 18፡ 3) ፡፡ ንዕማን ድንጋይ ራስ (ራሱን አደንድኖ) በመቀመጥ ተኩራርቶ ቢሆን አይፈወስም ነበር ፤ ነገር ግን ልክ እንደ ህፃን ልጅ እምነት በመተግበሩ ዳነ ፡፡

ኢየሱስ በሉቃ (4፡ 23-29) 2 ነገስትን ጠቅሶታል ፡፡ የኢየሱስ አድማጮች ተበሳጭተዉ ነበር ምክንያቱምአህዛቦች እግዚአብሄርን ለማወቅ ስለ ሚመጡ ፤ ነገር ግንንዕማን እግዚአብሄርን ለማወቅ እንዲመጣ የረዳችዉ ብላቴናይቱ እስራኤላዊት ነበረች ፡፡

2-ነገስት (5፡ 15-19)፡ ንዕማን ለእግዚአብሄር ስጦታ ለማቅረብ ፈለገ ነገር ግን ኤልሳዕ ከለከለዉ ምክንያቱም የንዕማን ፈዉስ ለሽያጭ አልነበረም ፡፡ ኤልሳዕ በመታዘዝ ብቻ ያደረግ የእግዚአብሄር ሰዉ ነበር ፡፡ ንዕማንም ከእስራኤል ለአፈር ጠየቀ ይህ ከሆነም በሀሰት አመልክ ቤተ መቅደስ እንዲሰግድ በተገደደ ጊዜ ለመደፋት በጉልበቱ ስር ያስቀምጠዋል ፡፡ ንዕማን መሰረቱን በእግዚአብሄር ላይ ማድረግ ፈለገ ፤ በአለም ቢሆንም እንኳን መሰረቱ ያህዌ እንደ ነበር አዉቋል ፡፡ አሕዛቡ ንዕማን እግዚአብሄርን ወደ ማወቅ መጣ ምክንያቱም አንድ እስራኤላዊት ስለረዳችው፡፡

2-ነገስት (5፡ 19-24)፡ የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር ለማግኘት ስልጣኑን (ስራዉን) ለመጠቀም ፈለገ ፡፡ ኤልሳዕን ለመጎብኘት ስለመጣ አንድ ሰዉ ለገንዘብ እና ለልብሶችን ጥያቄ በማድረግ በሚል ታሪክ መጣ ፡፡ ንዕማን ለመርዳት በመጓጓት ከጠየቀዉ ገንዘብ ሁለት እጥፍ ከልብሶች ጋር እና ሁሉንም ነገር እንዲሸከሙ ከሁለት አገልጋዮች ጋር ለግያዝ ሰጠው ፡፡ በደረሱ ጊዜ ግያዝ ሁሉንም ነገር በመደበቅ አገልጋዮችን ወደ ኋላ ላካቸው ፡፡

2-ነገስት (5፡ 25-27)፡ ግያዝ የእግዚአብሄርን መንግስት ከማስቀደም በላይ በብዙ ስለ ራሱ ነበር ፤ ስራዉን የራሱን አጀንዳ በጥልቅ ለመሄድ እንደ መንገድ ተጠቀመበት ስለዚህም ነገር ኤልሳዕን ዋሸው ፡፡ በዚህም ምክንያት ግያዝ ንዕማን ተፈዉሶት ከነበረዉ የቆዳ በሽታ በኃይል ተረገመ ፡፡

መደምደሚያ

ለጌታዋ ስለ እግዚአብሄር ለመናገር እድል በወሰደችዉ አንዲት እስራኤላዊ ቀላል እምነት የአንድ አሕዛብ መዳንን አመጣ ፤ እግዚአብሄር ለማን ነዉ የላካችሁ ?

  1. Warren Weirsbe, Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 521.

  2. Wiersbe, p. 522.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ነገ (5፡ 11) ንዕማን ከለምፁ የሚነፃበትን አገልጋዩ መጥቶ በነገረዉ ጊዜ ለምን ተበሳጨ ? (ምሳ 26፡ 12)
  2. በ 2ነገ (6፡ 16-17) ኤልሳዕ የአገልጋዩ አይኖች እንዲከፈቱ በጸለዬ ጊዜ አልሳዕ አገልጋዩን “ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው “ ፤ ይህ ስለ እግዚአብሄር ምን ይናገራል ? ( መዝ 46፡ 1-2፣ ሮሜ 8፡ 31)
  3. በ 2ነገ (6፡ 22-23) ኤልሳዕ በድርጊቱ ኢየሱስን እንዴት ገለፀዉ(አሳየዉ) ? (ማቴ 5፡ 39፣ 14፡ 13-21)
  4. በ 2ነገ (6፡ 26-29) አንድ ሴት ለእርዳታ ወደ ንጉሱ የእርሷን ልጅ እንደ በሉት እና አሁን ደግሞ ሌለኛዋ ሴትም የእርሷም እንዳይበላ ለመከላከል እነደ ደበቀችዉ በመናገር ጮኸች ፤ ህዝቡ(ሰዎቹ) ጀርባቸዉን በእግዚአብሄር ላይ ካዞሮ ይህ እንደሚሆን የተነበየዉ የት ላይ ማን ነበር ? (ዘዳ 28፡ 53-57)
  5. በ 2ነገስት (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 5:13–14

“But his servants approached and said to him, ‘My father, if the prophet had told you to do some great thing, would you not have done it? How much more should you do it when he tells you: wash and be clean?’ So Naaman went down and dipped himself in the Jordan seven times, according to the command of the man of God. Then his skin was restored and became like the skin of a small boy, and he was clean.”

የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት አለቃ ንዕማን ጽኑዕ ኃያል ነበረ ነገር ግን ለምጻም ነበረ ፡፡ የንዕማን ሚስት አገልጋይ የነበረችው እስራኤላዊት ብላቴና በእምነት በግልጽ ንዕማንን መፈወስ ስለሚችለው በሰማሪያ ስለሚገኘው ነቢይ ትናገርና ታወራ ነበር ፡፡ ስለዚህም ንዕማን ኤልሳዕ የተባለውን ነቢይ ለማየት ሄደ ፡፡ ኤልሳዕም ንዕማንን “ ሂድ በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ታጠብ ስጋህም ይፈወሳል አንተም ንጹህ ትሆናለህ “ ብሎ አዘዘው ፡፡ በመጀመሪያ የኤልሳዕን ትዕዛዝ ለመከተል እምቢ ካለ በኋላ ፤ ንዕማን ራሱን ዝቅ አደረገ ፣ኩራቱንም ተወ በመታዘዝም በእምነት ሄደ ፡፡ ይህንን በማድረጉም ሙሉ በሙሉ ተፈወሰ ፡፡ ኤልሳዕም በሰላም ሂድ አለው ፡፡ ንዕማን በትህትና መታዘዝ ብቻ እንጂ ለፈውሱ ለኤልሳ ክፍያ መፈጸም አላስፈለገውም ፡፡

በህይወትህ ኩራትህን በመተው ፣ በትህትና መራመድ እንድሁም እግዚአብሔርን መታዘዝ የሚያስፈልግህ ሁኔታዎች አሉ ይሆን ፡፡ ምናልባት ዛሬ ይህን መስማት ይኖርብህ ይሆናል “ ራስህን ትሁት አድርግ በቃ አድርገው ” ፡፡ ምንም ነገር ይሰማህ እግዚአብሔር እንድታደርገው የነገረህን ነገር በእምነት አድርገው ፡፡ ምናልባት ከባድ ፣ የጀብዱ ወይም የተወሳሰበ ላይሆን ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር ብልጭልጭ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው በትህትና እንድትታዘዝ ብቻ እንጂ ፡፡ በእምነትና እግዚአብሔርን በመታዘዝ ስትራመድ ሰላሙ በአንተ ላይ ይፈሳል እንድሁም እርሱ ይከብራል ፡፡

“ ባሪያዎቹም ቀርበው አባት ሆይ ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር ይልቁንስ ታጠብና ንጹህ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ ብለው ተናገሩት ፡፡ ወረደም የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ ስጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ስጋ ሆኖ ተመለሰ ንጹህም ሆነ ፡፡ “

  • 2ኛ ነገሥት 5፡13-14

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 24(25)፡8-9 –“ እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል ገሮችን በፍርድ ይመራል ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል ፡፡ “

መዝሙር 114(115)፡1 –“ እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድኩት ፡፡ “

ሚክያስ 6፡8 –“ ሰው ሆይ መልካሙን ነግሮሃል እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው ? ፍርድን ታደርግ ዘንድ ምህረትንም ትወድድ ዘንድ ፣ ከአምላክህም ጋር በትህትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ? “