Historical Books 2 Kings

Limited Only By Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 270 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለ 1ነገስት ሀረጉ የሚበልጠዉ ነገር ነበር ለ 2ነገስት ደግሞ ሀረጉ የዳነ ዘር ነው ፡፡ በሁለቱም መፅሀፍት ላይ የተመለከት ነው በክርስቶስ ተፈፅሟል ፤ የነቢያቶች፣ የካህናቶች እና የእግዚአብሄር ህዝቦች ነገስታቶች መዉደቅ ወደ ክርስቶስ አስፈላጊነት ያመለክታል ፡፡ ክርስቶስ የእነዚህ የሰዎስቱ ክፍሎች ጥሩነት ጥምረት ነበር ፤ እንደ ነቢይ የክርስቶስ ቃል ከታላቁ ነቢይ ከኤልያስ በብዙ ይበልጣል (ማቴ 17፡ 1-5፣ ዕብ 1፡ 1-2) ፤ ኢየሱስ በነገስት ከተመዘገቡት ማንኞቹም የላቀ ነው ( ዕብ 7፡ 22-27) ፡፡ በ 2 ነገስት ለክርስቶስ እኛን እንደ ሚገዛ ንጉስ በግልፅ የሚያስፈልጉትን ያሳያል ፡፡ የአይሁድ ንጉስ እንደ ነበር በተጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ እንደ ነበር አረጋግጧል (ማቴ 27፡ 11) ፤ ኢየሱስ ከታላቅ ንጉሳቸዉ የሚበልጥ ንጉስ ነው ፡፡ የ 26 ገዢዎች ዘመን ወደ መጨረሻዉ መጥቷል ነገር ግን ክርስቶስ በዳዊት ዙፋን ለዘላለም ይገዛል (1ዜና 17፡ 14፣ ኢሳ 9፡ 6-7) ፤ “ የነገስታት ንጉስ እና የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው “ (ራዕ 19፡ 11-16) ፡፡ ክርስቶስ ለአገልግሎት ስራ፣ ለማነቃቃት፣ የክርስቶስን አካል ለመገንባት ቅዱሳንን ለማነሳሳት በቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ የሚሆኑ ስጦታዎችን ሰጥቷል (ኤፌ 4፡ 7-8፣ 11-16) ፤ ክርስቶስ እነዚህን ይሰጣል ምክንያቱም በአምስቱ ስጦታዎች ሙሉ ስለሆነ አንዳንዶችን፡ ሐዋሪያት፣ ነቢያት፣ ወንጌል ሰባኪዎች፣ ፓስተሮች እና አስተማሪዎች ናቸው ፡፡

ሌለኛዉ አንዱ ስዕል ከ 1እና 2 ነገስት የአባቶችን እምነት ነው ፡፡ ሙሴ ኢያሱን እንዳሰለጠነዉ እና ጳዉሎስ ጢሞቲዎስን እንዳሰለጠነው ኤልያስ ኤልሳዕን አሰለጠነው ፡፡ በቤተ ክርስቲያን እናቶች እና አባቶች ያስፈልጉናል !

ትምህርት

ምዕራፍ 4 አራት ተዓምራቶችን ይይዛል፡ የመበለቲቱ ዘይት ተመልሶ መሙላት፣ የሱናማዊቱ ሴት ወንድ ልጅ መነሳት፣ የድስቱ ወጥ መንፃት እና የ መቶ ሰዎች መመገብ ፡፡

2-ነገስት (4፡ 1-7)፡ ከነቢያት ልጆች ሚስቶች አንዷ ልጇን ከባርነት በማዳን እንዲረዳት ወደ ኤልሳዕ ጮኸች (ቁጥር 1) ፤ ጆሴፍ ሴቲቱ የነቢዩ አብዲዩ ሚስት እንደ ነበረች ብሏል ፡፡ ኤልሳዕ ምን እንዲያደርግላት እና በቤቷ ምን እንደ ነበር ጠየቃት ፤ አንድ ማሰሮ ዘይት ብቻ ነበራት (ቁጥር 2) ፤ ኤልሳዕ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ባዶ እንስራዎችን እንድትሰበስብ ነገራት ( ቁጥር 3) ፡፡ በዙሪያዋ ያሉትን ሰዎች እርሷን ለመርዳት እግዚአብሄር እንዴት እንደ ተጠቀመባቸዉ አስታዉሉ ፤ ዋይርስቤ “ ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር ቀድሞዉኑ ባለን ነገር እንደ ሚጀምር “ ያመለክታል( ዘጸ 4፡ 2፣ ሉቃስ 5፣ ዮሐንስ 6) ፡፡

ዮሐንስ ማክስዌል “ የእግዚአብሄርን እጅ ስለሚያንቀሳቅስ ባዶ ነገር የሆነ ነገር እንዳለ ፤ በስጦታዉ ላይ እንጂ በምንም ነገር ላይ መደገፍ ወደ ማንችልበት ስፍራ ሊመራን ይወድዳል ይላል “ ፡፡ ሴቲቱም ኤልሳዕ እንዳላት አደረገች የተዋሰቻቸዉን ሁሉንም በዘይት ሞላች (ቁጥር 4-5) ፤ ዘይቱ ባዶ ማድጋዎች በሌሉ ጊዜ መፍሰሱን አቆመ (ቁጥር 6)፡፡ ኮንስታብል “ ማድጋዎቹ የዘይት መለኪያ ነበሩ ፤ በሌላ ቋንቋ መለኮታዊ ኃይል በእምነት ተጠበቀ - እምነት በክስተቱ ላይ የእግዚአብሄርን የሚንቀሳቀስ ምንጭ እንደ ለካ “ ተናግሯል ፡፡ የተቀበለችዉ የዘይቱ መጠን በነበራት ማድጋዎች ቁጥር የተወሰነ ነበር ያም በእምነቱ የተገደበ ነበር (2 ነገ 13፡ 18-19) ፡፡ ምናልባት ለትልቅ ማለም እና ለብዙ ማመን ያስፈልገናል ፤ እግዚአብሄር ባመነዉ እና በተዘጋጀነዉ መጥን ይሞላናል (ሮሜ 4፡ 17) ! የኔልሰን ማብራሪያ “ ኤልሳዕ ወዲያዉኑ(በፍጥነት) የሚያስፈልጋትን ብቻ አልነበረም ያረጅም ጊዜዉንም እንጂ እንዳገኘ “ ይገልፃል ፡፡ ይህ እዳችንን ለመክፈል ሁሉንም የሰጠዉ የክርስቶስ ጥላ ነው ስለሆነም መኖር እንችላለን ፡፡

2-ነገስት (4፡ 8-26)፡ ኤልሳዕ እንዲቆይበት ስፍራ የሰጠችዉን ሱናማዊት ሴት አገኘ ልጅም እንደሚኖራት ትንቢት ተናገረ ፤ ቆይቶም ልጇ ሞተ እንዲረዳትም ኤልሳዕን ለማግኘት ሮጠች ፡፡

2-ነገስት (4፡ 27)፡ ኤልሳዕ ከእግዚአብሄር ብዙ ጊዜ የሰማ ቢሆንም ሴቲቱ ምን እንደሚያስፈልጋት እግዚአብሄር ከእርሱ ደበቀው ፡፡ በአዲስ ኪዳን መንፈሳዊ ስጦታዎችን በቅንነት እንድንፈልግ አበረታቶናል (1 ቆሮ 14፡ 1) ፤ እግዚአብሄር እንድናጠናዉ ብቻ አይፈልግም እንድንቀምሰውም (እንድንኖርበትም) እንጂ ፡፡ የእግዚአብሄርን ድምፅ መስማት እና ማዳመጥ ተለማመዱ ፤ በአደባባይ እድሎችን በመዉሰድ በግል ወደ እግዚአብሄር ተመልሶ መምጣት፡፡ እንደ ተማራችሁት፣ በመተከል፣ በማደግ እና በመከተል መጓዝን ቀጥሉ ፡፡

መደምደሚያ

በቃል በኩል የእግዚአብሄርን ድምፅ ማወቅ ያስፈልገናል በተጨማሪም የእግዚአብሄርን ድምፅ “ መስማትም “ ያስፈልገናል ፡፡ ሁሉም ነገር በመፅሀፍት የተፃፈ አይደለም ፡፡ በማቴዎስ 28 ደቀ መዛሙርቱ ሄደዉ ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል ፤ ያ ማለት ከእግዚአብሄር እንደ ሰማነዉ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ዋልማርት ላይ አራት መተላለፊያ ላይ ለምናገኛቸዉ ሰዎች ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል ማለት ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 516.

  2. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): 2 Kings, p. 18; available online at planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2kings.pdf.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 466.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ነገ (4፡ 1-7) ዘይቱ የዚችን ሴት ቤተሰብ በማዳን ትልቅ ሚና ተጫዎቷል ፤ በታላቅ መንገድ የዘይትን ጥቅም ሌላ የት ላይ እናገኛለን (ዘጸ 27፡ 20፣ መዝ 45፡ 7) ? ዘይቱ መንፈስ ቅዱስን ይወክላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይወክልም ? (ሐዋ 10፡ 38)
  2. ሀብታሟ ሴት ለኤልሳዕ የሰጠችዉ እንግዳ ተቀባይነት እንዴት ሸልሟት (ከፍሏት) ነበር (2 ነገ 4፡ 16) ? ሌላ የት ላይ እንግዳ ተቀባይነት ሲታይ ታያላችሁ ? ( ዘሌ 19፡ 33-34፣ ማቴ 25፡ 34-36)
  3. በሁለት በተለያዩ ክስተቶች ሱናማዊቱ ሴትደህና እንደ ነበር እና መልካም እንደ ሚሆን ተናገረች ፤ ይህን ለምን እንዳለች ምን ታስባላችሁ ? ( ምሳ 18፡ 21፣ ማር 11፡ 23)
  4. ኤልሳዕ ለልጇ ያደረገዉ (2ነገ 4፡ 34-35) እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? ( ማር 5፡ 22-43፣ ሉቃ 7፡ 11-15፣ ዮሐ 11፡ 1-44)
  5. በ 2ነገ (4፡ 42-44) ኤልሳዕ አገልጋዩን የአቁማዳዉን እሸት እና የገብስ እንጀራዎቹን ህዝቡን እንዲመግባቸዉ ነገረው ፤ አገልጋዩም ምግቡ የሚበቃ አልነበረም ነገር ግን ሁሉም በልተዋል ፤ ይህን ተዓምራት ሌላ የት ታዩታላችሁ ? (ማቴ 14፡ 13-21፣ ማር 8፡ 1-8)
  6. በ 2ነገስት 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 4:17

“The woman conceived and gave birth to a son at the same time the following year, as Elisha had promised her.”

እግዚአብሔር ታምራዊ ኃይሉን ያሳይ ዘንድ ነቢዩ ኤላሳዕን ተጠቀሟል ፡፡ እግዚአብሔር ማድጋን በማድጋ ላይ ዘይትን በመሙላት ባሏ ለሞተባት ሴትና ለልጆቿ ታምራዊ ስጦታን አድርጓል ፡፡ እግዚአብሔር የሱናማዊቷን ሴት እንግዳ ተቀባይነት አይቶ እሷና ሸማግሌ ባሏ ወንድ ልጅን እንድያገኙ አድርጓል ፡፡ እንድሁም ደግሞ ልጁ በሞተ ጊዜ እስትንፋሱ ወደ ልጁ ይመለስ ዘንድ ኤልሳ ወደ እግዚአበሔር ጮኸ ልጁንም ከሞት አስነሳው ፡፡ ከዚያም ኤልሳዕ በእግዚአብሔር ኃይል መጥፎውን ምንቸት ወደ ጤናማና ህይወት ሰጭ ቀይሯል ፡፡ በእግዚአብሔር ኤልሳዕ ለመቶ ሰዎች እንጀራን ይበሉ ዘንድ አብዥቷል ከዚያም አልፎ በልተው ተርፏል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ምንም መንገድ የሌለ ሲመስል እግዚአብሔር ታምራትን አድርጓል ፡፡

እግዚአብሔር ትላንትናም ፣ ዛሬም ነገም የተአምራት አምላክ ነው ፡፡ አማኞች ስሙን ልትጠሩና ኃይሉ ልታስቡት በማትችሉት መንገድ በራሱ ጊዜና መንገድ ሊሰራ እንደሚችል ልታምኑ ይገባል ፡፡ እምነትህን አትብቀህ ያዝ ደግሞም ምልክትን ባታይ እንኳ እርሱ በስራ ላይ እንዳለ እመን ፡፡ ምናልባት ዛሬ ተስፋህ ይቀጥል ዘንድ ይህን እውነት መስማት ይኖርብህ ይሆናል ፡፡ ጽና ደግሞም ይፈውስህ ፣ ይሰጥህ ፣ ያስተካክልልህና ያበረታህ ዘንድ እንድችል እመን ፡፡ እርሱ ፈጽሞ አይተውህምና በእርሱ ላይ በእምነት ጽና ፡፡

“ ሴቲቱም ፀነሰች በዚያም ወራት በአዲሱ ዓመት ኤልሳዕ እንዳላት ወንድ ልጅ ወለደች ፡፡ “

  • 2ኛ ነገሥት 4፡17

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤርምያስ 32፡27 –“ እንዲህ ሲል መጣ እነሆ እኔ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምለክ እግዚአብሔር ነኝ ፡፡ “

ማቴዎስ 17፡20 –“ ኢየሱስም ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል የሚሳናችሁም ነገር የለም ፡፡ “

ሐዋርያት ስራ 3፡16 –“ በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው ፡፡ “