Flood of Victory
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዛሬዉ ትምህርት ለእስራኤል፣ ለይሁዳ እና ለኤዶምያስ ንጉስ የእግዚአብሄርን አቅርቦት(ስጦታ) በእልሳዕ በተሰጠዉ በእግዚአብሄር ቃል በኩል እናያለን ፡፡ ዋይርስቤ “ የኤልሳዕ ተዓምራት በመጀመሪያ የእግዚአብሄር ቸርነት እና ምህረት መገለጥ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ የኤልሳዕ ህይወት እንደ ሚኖር ዘር ወደ ሚመጣዉ መሲህ ያመለክታል ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (3፡ 1-3)፡ አክዓብ እስራኤል ላይ ንጉስ ነበር ኤልዛቤል ደግሞ ንግስቱ ነበረች ፡፡ ኤልዛቤል እና አክዓብ ሁለት ልጆች ነበሯቸው፡ አካዝያስ እና ኢዮራም ፤ አካዝያስ ከኢዮራም በፊት ንጉስ ነበር ነገር ግን ለሁለት አመት ብቻ አስተዳደረ (1 ነገ 22፡ 51) ፡፡
2-ነገስት (3፡ 4-5)፡ የመሞዓብ ንጉስ ሞሳ በንጉስ አካዝያስ ላይ አመፀ ፤ ንጉስ አካዝያስም አመፁን በመቀበል ከሞዓብ ሞሳ ግብር መክፈሉን እንዲቀጥል ለማስገደድ ምንም አላደረገም ፤ ነገር ግን የአካዝያስ ወንድም ኢዮራም ንጉስ በሆነ ጊዜ ግብሩን እንደ ገና መክፈል እንዲጀምር ሞዓብን ለማስገደድ ወሰነ ፡፡
2-ነገስት (3፡ 6-9)፡ የሰሜን መንግስት ንጉስ ኢዮራም የደቡቡን መንግስት ኢዮሳፍጥን በሞዓብ ላይ እንዲጣመሩ ጠየቀው ፤ ጥያቄዉ በመካከላቸዉ በነበረዉ ዝምድና ላይ የተመሰረተ ነበር - ከኢዮሳፍጥ ልጆች አንዱ ኢዮሮአም ከኢዮራም እህት ጎቶሊያ ጋር የተጋባ ነበር ፡፡ ከአመቱ በፊት በእግዚአብሄር እርዳታ ሞዓባዊያንን አሸንፏቸው የነበረው ኢዮሳፍጥ ተስማማ ፡፡
የእስራኤል እና የይሁዳ ንጉሶች ለማጥቃት ቀጥተኛ ባልሆነዉ መንገድ ከጀርባ በኩል ሞዓብን ቀረቡ ፤ ንጉስ ሞሳ ከዚህ አቅጣጫ ጥቃት ይመጣብኛል ብሎ አይጠብቅም ፤ በኤዶም በኩል ሲጓዙ የኤዶምም ንጉስ በሞዓብ ላይ በመነሳት ለመዋጋት ተጣምሯል ፡፡ ጥሩ እቅድ ነበር ነገር ግን ኢዮራም እና ኢዮሳፍጥ የምግብ አቅርቦት መኖሩን ግምት ዉስጥ አላስገቡም ፡፡ ቀስ በቀስ ወንዙን ተሸግረዉ እንደሚሄዱ ብቻ አስበዋል ነገር ግን ከሰባት ቀን በኋላ ዉኃዉን ተሸግረዉ መምጣት ስለአልቻሉ ምግባቸዉ አለቀ ፡፡
2-ነገስት (3፡ 10-12)፡ ኢዮሳፍጥ እግዚአብሄር ምን እንዲያደርጉ እንደ ሚፈልግ ለመስማት ነቢዩን ኤልሳን መፈለግ እንዳለባቸዉ የምክር ሀሳብ አመጣ ፡፡ ኢዮራም እልሳዕን አይወደዉም ምክንያቱም ስለ እርሱ ኤልሳዕ ያለዉ መልካም ነገር ምንም ስላልነበር ነገር ግን ኢዮራም ከኤልሳዕ ጋር ለማዉራት ለመሄድ ወደ ኢዮሳፍጥ ምክር አደመጠ፡፡ ኢዮራም ወደ ክፉዉ ሁኔታ አስተሳሰብ ካላከበሩት ሰዎች መካከል አንድኛዉን መስሏል ፤ ምንም አይነት አቅርቦት በሌላቸዉ ጊዜ ወዲያዉኑ እግዚአብሄር ሞዓባዊያን እንዲያሸንፉዓቸዉ እንደ ሰጣቸዉ ደመደመ ፡፡
2-ነገስት (3፡ 13-14)፡ ኤልሳዕም ኢዮራምን ከመጀመሪያዉ ከእናቱ እና ከአባቱ ነቢያት ጋር ለማዉራት እንዲሄድ ነገረው ፤ የኢዮራም ቤተሰቦች ከኤልያስ ጋር ብዙ ነገር ተነጋግረዉ የነበሩት ንጉስ አክዓብ እና ንግስት ኤልዛቤል ነበሩ ፡፡ ኢዮራም ምናልባትም ከአክዓብ ትንሽ የተሸለ በመሆን በይሁዳ ወይም በእስራኤል መንግስት ካሉት በጣም ክፉዉ ንጉስ ነበር ፡፡ ኢዮሳፍጥ በሌላኛዉ ጫፍ ህብረ ቀለም ነበር ፤ ኢዮሳፍጥ እንደ ዳዊት በጣም መልካም(ጥሩ) አልነበረም ነገር ግን አሁንም እግዚአብሄርን ያገለገለ ንጉስ ፃድቅ ንጉስ ነበር ፡፡ እዚህ ኤልሳዕ እንደ ድልዳል አገለገለ ፤ በነገሮች ላይ በመንገስ ንጉሱን በመስመሩ ላይ ለማቆም ሞከረ ፡፡
2-ነገስት (3፡ 15)፡ የኤልሳዕ ጥያቄ ባለበገናን ዳዊት ሳዖልን ለማሳረፍ በገና የመጫወቱ ትዝታ(ትዉስታ0 ነበር፡ “ የእግዚአብሄርም መንፈስ ከሳዖል ራቀ ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሄር ዘንድ አሰቃየው ፡፡ የሳዖልም ባሪያዎች እነሆ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሄር ዘንድ ያሰቃይሃል ፤ በገና መልካም አድርጎ የሚመታ ሰው ይሹ ዘንድ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን ባሪያዎቹን ይዘዝ ፤ ከእግዚአብሄርም ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ በእጁ ሲመታ አንተ ደህና ትሆናለህና አሉት ፡፡ ሳዖልም ባሪያዎቹን መልካም አድርጎ በገና መምታት የሚችል ሰዉ አምጡልኝ አላቸው ፡፡ ከብላቴኖቹም አንዱ መልሶ እነሆ መልካም አድርጎ በገና የሚመታ የቤቴ ልሔማዊዉን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ ፤ እርሱም ጽኑ ኃያል ነው በነገርም ብልህ መልኩም ያማረ ነው እግዚአብሄርም ከእርሱ ጋር ነው አለ ….እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሄር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳዖል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር ፤ ሳዖልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈዉም ነበር ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር “ (1 ሳሙ 16፡ 14-18, 23) ፡፡ መንፈሱን መጉዳት የሚችል በጆሮ ላይ ስለ ጣዕመ ዜማዉ ጨዋታ የሆነ ነገር አለ ፡፡
2-ነገስት (3፡ 16-20)፡ ኤልሳዕ ንጉሶቹን ጉዱጓዶች እንዲቆፍረ በማዘዝ ጥማቸዉን በማርካት በፍጥነት ለፍላጎታቸዉ እግዚአብሄር ጉድጓዶቹን ዉሃ በመሙላት እንደ ሚሰጣቸዉ አወጀ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ሞዓባዊያንን በእጃቸዉ አሳልፎ በመስጠት ቀድሞ አንድ እርምጃ ይሄዳል ፡፡ ለጦሩ(ለሰራዊቱ) ይህ ርሃብ ምን ያክል አደገኛ እንደ ነበር አናዉቅም ነገር ግን በኤልሳዕ በኩል ከእግዚአብሄር ጣልቃ ገብነት ዉጪ ሞት ይገጥማቸዋል ፡፡
2-ነገስት (3፡ 21-23)፡ የሞዓብ ሰራዊት ከመሳሪያቸዉ ወይም ከጦር ልብሳቸዉ ዉጪ ወደ ይሁዳ ሰፍር ሄዱ ምክንያቱም እየመጣ የነበር ዉጊያ እንደ ሌለ በማሰብ ፡፡ በይሁዳ ሰፈር ሰዎስቱ ንጉሶች አንዱ በሌለኛዉ ላይ አዞረዉ እንደ ነበር በማሰብ ከዉጊያዉ ምርኮን ለመሰብሰብ በቀላሉ እየሄዱ ነበር ፡፡
2-ነገስት (3፡ 24-26)፡ የኤዶም ንጉስ የሞዓብን ንጉስ ወደ ድንበሩ ያለዉን መስበር ለመስበር 700 ሰይፍ በወጋባቸዉ ላይ የታጠቁትን ሰዎች እንዲወስድ በመምራት በጥቂቱ ገለልተኛ ሆኗል ፡፡ ኤዶም እና ሞዓብ ጎረቤቶች ነበሩ ስለዚህ ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው ፡፡ ምናልባትም ሞዓባዊያን ሰላም ወዳድ ህዝቦች ነበሩ ፤ በጎች በማርባት የታወቁ ነበሩ ፤ እረኞችን እንደ ጦር አድራጊ አታስቧቸዉም ፡፡
2-ነገስት (3፡ 27)፡ የሞዓብ ንጉስ የመጀመሪያ ወንድ ልጁን እንደ ሚቃጠል መስዋዕት በሚሰዋ ጊዜ ሌለኛዉ ንጉስ አንዱን ሌለኛዉን ባለማክበር “ ምን እያደረገ ነው ? “ ብሎ የሚጠይቀዉ ነው ፡፡ “ አዲሱ እንግሊዘኛ መፅሀፍ ቅዱስ ንባብ በዚህ እይታ ሰፈሩን በማጥቃት ወደ ምድራቸዉ በመመለስ እስራኤላዊያን በድንጋጤ ተሞልተዉ ነበር “ ፡፡
መደምደሚያ
የእስራኤል ንጉስ ኢዮራም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ያደረገ ሌለኛዉ ንጉስ ነበር ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር በሞዓብያዊያን ላይ ድል ማድረግን ፈቀደለት ምክንያቱም የይሁዳ ንጉስ ኢዮሳፍጥ ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ፡፡ እንደ ገና እግዚአብሄር የዳዊትን ዘር በይሁዳ ንጉስ በኩል አቆየ(አስቀጠለ) ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 513.
Wiersbe, p. 515.
ጥያቄዎች
-
በ 2ነገ (3፡ 3) ኢዮራም በናባጥ ልጅ በኢዮሮብዓም ኃጢዓት ተያዘ ባለ ጊዜ ጥቅሱ ምን ኃጢዓት እየጠቀሰ ነበር ? (1ነገ 12፡ 28-31)
-
በቁጥር 15 ኤልሳዕ ለምን ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ለምን ጠራ ? ( 1ዜና 25፡ 1)
-
በንጉስ ኤዶምያስ ጥሶ መግባት እንደማይችል ባወቀ ጊዜ የሞዓብ ንጉስ ልጁን እንደ ቃጠል መስዋዕት እንዲያቀርብ ስለ ተቆጣጣረው ነገር ምን ታስባላችሁ ? ይህ እንደሚያሳካለት በምን አሰበ ? (2 ነገ 3፡ 27)
-
በ 2ነገስት 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 3:11–12
“But Jehoshaphat said, ‘Isn’t there a prophet of the LORD here? Let’s inquire of Yahweh through him.’ One of the servants of the king of Israel answered, ‘Elisha son of Shaphat, who used to pour water on Elijah’s hands, is here.’ Jehoshaphat affirmed, ‘The LORD’s words are with him.’ So the king of Israel and Jehoshaphat and the king of Edom went to him.”
የይሁዳ ፣ የእስራኤልና የኤዶምያስ ነገሥታት ከሞአብ ጋር ለጦርነት በወጡ ጊዜ ሲጠሩት ኤልሳ ከእግዚአብሔር ጋር ስለተራመደ በቃል ዝግጁ ነበር ፡፡ የእግዚአብሔርም እጅ በኤልሳ ላይ መጣችበት በድፍረትም ተናገረ ፡፡ ነገር ግን ወታደሮቹ የእግዚአብሔርን ቃል ሙሉ በሙሉ አልሰሙም ፡፡ ስለዚህም የተነገረውን ሁሉንም በረከት ብቻ አልነበረም ያልተቀበሉት ነገር ግን እግዚአብሔር ቁጣውንም ሊያሳያቸው ወድዶም ነበረ ፡፡
ከጌታ ጋር እየተራመድክ ነው ? ስለዚህም ውሳኔ መወሰን ሲያስፈልግህ ወይም ስለ ኢየሱስ ከሆነ ሰው ጋር ማውራት ስትፈልግ እውነቱን ለማወጅ ዝግጁ ትሆናለህ ፡፡ ልክ እንደ ኤልሳዕም የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ትሆናለች ፡፡ እርሱ ሁልጊዜም ካንተ ጋር ነው ኃይሉም በውስጥህ ይኖራል ፡፡ በክርስቶስ ሁልጊዜም የነቃህ ትሆናለህ ፡፡ ዛሬ ከጌታ ጋር ጊዜ ውሰድ ቃሉንም አንብብ ስለዚህም ዝግጁ ትሆናለህ ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ስለሚመራህ ደፋር ሁን ስለ እርሱም ለመናገር ለራስህ እድሎችን ፍጠር ፡፡
“ ኢዮሳፍጥም በእርሱ እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የእግዚአብሔር ነቢይ በዚህ አይገኝምን ? አለ ፡፡ ከእስራኤልም ንጉሥ ባሪያዎች አንዱ በኤልያስ እጅ ላይ ውኃ ያፈስስ የነበረው የሳፍጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ ብሎ መለሰ ፡፡ ኢዮሳፍጥም የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል አለ ፡፡ የእስራኤል ንጉሥና ኢዮሳፍጥ የኤዶምያስም ንጉሥ ወደ እርሱ ወረዱ ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 3፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳይያስ 64፡8 –“ አሁን ግን አቤቱ አንተ አባታችን ነህ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሰሪያችን ነህ እኛም ሁላችን የእጅህ ስራ ነን ፡፡ “
- ሉቃስ 21፡36 –“ እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ ፡፡ “
- 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15 –“ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት ፡፡ በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።