Passing the Mantle
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ነገስት ፅሁፉ የተለመደ ነገር ያወራል ምክንያቱም 1 እና 2 ነገስት እንደ አንድ መፅሀፍ ተፅፈዉ ስለ ነበር ፡፡ የአይሁድ ባህል 2 ነገስትን ኤርምያስ እንደ ፀፋዉ ያምናል ፤ ያ ግን ትርጉም አይሰጥም ምክንያቱም ኤርምያስ በፍፁም በባቢሎን አልነበረም ፤ ስለዚህ 1 እና 2 ነገስትን ማን እንደፃፈው ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች አይደለንም ፡፡ እነዚህ መፅሀፎች ትክክል እና የተተረጎሙ ታሪካዊ መዝገብ ናቸው ማለትም ፀሀፊዉ እነዚህን መፅሀፎች ፃፈ እስራኤልም ከስህተት መማር ቻለ ፡፡ ጳዉሎስ ቫን ጎርደር “ 2 ነገስት የሁሉም አይሁዳዊያን የብስጭት መፅሀፍ እንደ ሆነ “ ፅፈዋል ፤ ለምን ? ምክንያቱም 2 ነገስት የእስራኤላዊያን ወደ ምርኮ የተወሰዱ በመሆን ስለ ተመዘገበ ፡፡
የ 2 ነገስት መፅኀፍ ወደ ሁለት ክፍል የተከፈለ ነው ፤ ከምዕራፍ 1 እስከ 17 እስከ ሰማሪያ መዉደቅ ድረስ ይሁዳን እና እስራኤልን ይሸፍናል ፤ ከምዕራፍ 18 እስከ 25 እስከ ኢየሩሳሌም መፍረስ ድረስ የይሁዳን ታሪክ ይሸፍናል ፡፡ መሰባበር እና የመንግስት መበታተን እያለ እንኳን እግዚአብሄር እቅድ ነበረው ፤ የሚበልጠዉ ነገር እየመጣ እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡ ዉጊያዉ፣ ስብራቱ፣ ክፍፍሉ መሀከል ላይ እግዚአብሄር ወደ ክርስቶስ የሚያመለክት አንድ ለተረፈ(ለዳነ) ዘር ፈቀደ ፡፡ የ 2 ነገስትን መፅሀፍ ስናጠና የክርስቶስን ስዕል እናየዋለን - ክርስቶስን እና አማኞችን (2፡ 1-22)፣ ክርስቶስን እና አለምን (4፡ 38-41) እና ክርስቶስ እና ኃጢዓተኞች (5፡ 1-41) ፡፡ በ 2ነገስት 1 ሞዓብ በእስራኤል ላይ አመፀ (ቁጥር 1)፣ ኤልያስ አካዝያስ ገሰፀው (ቁጥር 2-16)፣ የእስራኤል ንጉስ አካዝያስ ሞተ ኢዮራምም እንደ ንጉስ አካዝያስን ተካ (ቁጥር 17) ፡፡ ለመሲሁ በ 2ነገስት ሀረጉን በኤልያስ ህይወት ዉስጥ ዕናየዋለን፡ የዳነ(የተረፈ) ዘር ፡፡
ትምህርት
2-ነገስት (2፡ 1)፡ ኤልያስ በቀርመሎዎስ ተራራ ላይ እሳት እንዲወርድ የጠየቀ እንደ ነበር እና በአክዓብ ፊት የሮጠ ነቢይ እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡ እግዚአብሄር ኤልያስን በኃይለኛ ንፋስ ወደ ሰማይ ይወስደዋል ፤ ኃይለኛ ንፋስ በመብረቅ እና በአዉሎ ንፋስ የተወሳሰበ የተለዬ ማዕበል ነበር ( ኢዮ 38፡ 1፣ 40፡ 6፣ ኤር 23፡ 19፣ ዘካ 9፡ 14) ፤ ይህ ማዕበል ከእግዚአብሄር ነበር መገኘቱም በማዕበሉ ዉስጥ ነበር ፡፡
2-ነገስት (2፡ 2)፡ ኤልያስ እና አልሳዕ ሁለቱም ነቢያት ነበሩ ፡፡ ኤልያስ ለኤልሳዕ “ እግዚአብሄር ወደ ቤቴል ልኮኛልና በዚህ ቆይ አለው “ ፤ ኤልሳዕም “ አልለይህም አለ “ ፡፡ ቤቴል ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን ከስድስት እስከ ስምንት ማይል ርቀት ላይ ነበረች የሀሰት አምልኮ በዚያ ስፍራ የሚደረግ በመሆኑ ምክንያት መጥፎ ዝና ነበራት ፡፡
2-ነገስት (2፡ 3)፡ በቤቴል ደረሱ የነቢያትም ልጆች ሊገናኙአቸዉ መጡ ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር የነቢያት ልጆች “ ለጥናት፣ ለማበረታታት እና ለአገልግሎት የሚገናኙ እና ምናልባትም በአንድ ላይ የሚኖሩ የነቢያት ማህበር እንደ ነበሩ “ ይገልፃል ፡፡ ለኤልሳዕም “ እግዚአብሄር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አዉቀሀልን ? “ አሉት ለእነርሱም “ አዎ አዉቃለሁ ፤ ዝም በሉ “ አላቸው ፡፡
2-ነገስት (2፡ 4)፡ እንደ ገና ኤልያስ ኤልሳዕን እንዲቆይ ለማድረግ ሞከረ ምክንያቱም እግዚአብሄር ወደ ኢያሪኮ እየላከዉ ስለ ነበር ፤ አንደ ገና ኤልሳዕም “ አልለይህም “ አለው ፡፡ ኢያሪኮ ከቤቴል ደቡብ ምስራቅ 14 ማይል ነበረች፡፡
2-ነገስት (2፡ 5)፡ ሁለቱ ሰዎች በኢያሪኮ በደረሱ ጊዜ የኒቢያቶች ልጆች እንደ ገና በመምጣት ኤልሳዕን “ እግዚአብሄር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው አዉቀሃልን ? “ ላሉትም “ አዎ አዉቃለሁ ፤ ዝም በሉ “ አላቸው፡፡ በተቆጣጣሪዉ(በኃላፊዉ) በጣም ትክክለኛ ጊዜዉን ማድረግ ፈለገ ፡፡
2-ነገስት (2፡ 6-8)፡ ለሰዎስተኛ ጊዜ ኤልያስ እልሳዕን በዚያ እንዲቀር ነገረው ፤ ለሰዎስተኛ ጊዜ ኤልሳዕም “ አልለይህም “ አለው ፤ ከእነርሱም ሁለቱ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ ፡፡ ሁለቱ ሰዎች ዮርዳኖስ ወንዝ ላይ በሌላኛዉ በኩል ከነቢያት ልጆች 50ዎቹ አጋጠሟቸው ፤ ኤልያስ መጎናፀፊያዉን ወስዶ በመጠቅለል ወንዙን መታዉ ፤ ወዲያዉኑ ወንዙ ተከፈለ ፤ ሁለቱ ሰዎችም በደረቅ መሬት ላይ ተሻገሩ ፡፡ ይህ የሀሳብ የሚያሞቅ ነው ! ኤልያስ ተዓምር ሰሪ ነበር!
2-ነገስት (2፡ 9-10)፡ ኤልያስ ኤልሳዕን ከመወሰዱ በፊት ምን እንዲያደርግለት ጠየቀው ፤ ኤልሳዕም “ መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ “ አለው ፡፡ በዚያ ኃይል መስራት እና መጓዝ ፈለገ ፤ ዕጥፍ በረከት ፈለገ ወይም ማክአርቱር እንደ ፃፈው “ የእግዚአብሄርን እጥፍ መንፈስ “ ፈለገ ፡፡
ኤልሳዕ ቁሳዊ በረከትን አልፈለገም ፤ የተባረከ መሆን ፈለገ የእግዚአብሄርንም አላማ በቅድሚያ መስራት ቻለ ፡፡ ኤልያስ ኤልሳዕ አስቸጋሪ የሆነ ነገር እንደ ጠየቀ አመለከተው ፤ የኤልሳዕ ጥያቄ የሚሆን እንዲሆን ወደ እግዚአብሄር ያተኮረ መሆኑ አስፈላጊ ይሆናል ፡፡
በራሳችን ህይወት የእግዚአብሄርን መንፈስ እጥፍ መቀበል ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ? መመልከት ያስፈልገናል ፡፡
2-ነገስት (2፡ 11)፡ ሁለቱ ሰዎች እያወሩና እየተጓዙ ሳለ አንድ የእሳት ሰረገላ በፈረሶች ሰረገላ የሚገፋ ከሰማይ በመምጣት ሁለቱን ለያያቸው ፤ ኤልያስም ወደ ሰማይ ተወሰደ ፡፡ ኤልያስ አልሞተም ወደ ሰማይ ተወሰደ እንጂ (ዘፍ 5፡ 24) ፤ እግዚአብሄር ሰዎችን ወደ ሰማይ የወሰደበት ብዙ አጋጣሚዎች የሉም ፡፡
2-ነገስት (2፡ 12-15)፡ ኤልሳዕ ጮኸ ልብሱንም ቀደደ ፤ የኤልያስንም መጎናፀፊያ በማንሳት ዉሃዉን መታው ፤ ይህንን ባደረገም ጊዜ ዉሃዉ ተከፈለ ፡፡ ከየት ተማረው ? ከእናንተ ፊት ከሚሄዱ ሰዎች መማር ትችላልችሁ ፡፡ የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ ወደ ታች ተደፉ ፤ የኤልሳዕን ቅባት አይተዉ ነበር ፡፡
2-ነገስት (2፡ 16-17)፡ ሌሎቹ አምሳዎቹ ነቢያቶች የኤልያስ አካል ከመንፈሱ በመለየት የሆነ ስፍራ ተቀምጦ ይሆናል በማለት የኤልያስን አካል ሄዶ ለመፈለግ ፈለጉ ፡፡ ኤልሳዕ ምንም ነገር እንደ ማያገኙ ያውቃል ነገር ግን ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ሰዎቹ እንዲሄዱ ፈቀደላቸው ፤ ለሰዎስት ቀናት ፈለጉት ኤልያስን ግን ሊያገኙት አልቻሉም ፡፡ በኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ በተመለሱ ጊዜ “ አትሂዱ አላልኋችሁምን ? “ አላቸው ፡፡
2-ነገስት (2፡ 19-21)፡ የከተማዋ ሰዎች ለኤልሳዕ ምድሪቱ እና ዉሃዉ የተረገመ እንደ ሆነ ነገሩት ፡፡ ኢያሱ ኢያሪኮ ላይ እርግማን እንዳስቀመጠ አስታዉሱ (ኢያ 6፡ 26) ፤ በ 1ነገ (16፡ 34) ደግሞ ኢያሪኮ በንጉሱ ልጆች ዋጋ ላይ እንደ ገና ተመስርታ ነበር ፡፡ ኤልሳዕም የሀገሪቱን ሰዎች አንድ ማሰሮ ከጨዉ ጋር እንዲሰጡት ጠየቃቸው ፤ ወደ ወንዙም ሄደ ጨዉን ወደ ዉሃዉ ወረወረው ዉሃዉም ተፈወሰ ፡፡ እስከ አሁኑ ጊዜ ድረስ ጤነኛ ነው ፡፡ ይህን ታሪክ እወደዋለሁ ፤ ይህ ታሪክ የእግዚአብሄር መገኘት ከኤልሳዕ ጋር እንደ ነበር ያሳያል ፡፡
2-ነገስት (2፡ 22-25)፡ ጥቂት ወጣት ወንዶች ኤልሳዕን አሾፉበት ምክንያቱም መላጣ ስለ ነበር ፤ በመዞርም ረገማቸው ፤ ሁለት ሴት ድቦች በመዉጣት ከልጆቹ 42ቱን ገደሏቸው ፡፡ በኤልሳዕ ግራ አትጋቡ !
መደምደሚያ
ሁልጊዜ አላማን ለማሳካት ተግተን እንስራ ፤ በደንብ ስትከተሉ እግዚአብሄር የሰጣችሁን መጎናፀፊያ ታነሳላችሁ ፤ ሁላችንም ከእግዚአብሄር ቅባት ተቀብላችኋል (1ዮሐ 2፡ 20-27) ፡፡
2 van Gorder.
Paul van Gorder. The Old Testament Presents . . . Reflections of Christ (Grand Rapids, MI: RBC Ministries, 1982) https://www.thebookwurm.com/ref-2kin.htm.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 424.
MacArthur, p. 432.
ጥያቄዎች
-
ብዔልዜቡልን ሳይሆን እግዚአብሄርን ፈልገዉ ቢሆን የኤልያስ መልስ ለመልዕክተኞቹ የተለዬ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ (1ነገ 1፡ 3-4) ? አዎ ከሆነ ለምን ?
-
ንጉስ አካዝያስ አምሳዎቹን ቡድኖች ወደ ኤልያስ በላከ ጊዜ አሳቡ ምንድን ነው ? (2ነገ 1፡ 9፣ 11፣ 13)
-
በ 2ነገስት ኤልያስ ኤልሳዕን ለምን እንዲቆይ ነገረው ኤልሳዕስ ለምን አልሰማዉም ?
-
በ 2ነገ (2፡ 9) ኤልያስ ለኤልሳዕ “ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻዉን ለምን “ ለምን አለው ?
-
በግል አስተያየታችሁ ኤልሳዕ በኢያሪኮ ለነበሩት የነቢያት ልጆች (2ነገ 2፡ 16) በኤልያስ ላይ ምን እንደ ተፈጠረ ያለነገራቸዉ ለምን ነበር ?
-
በ 2ነገ (2፡ 19-22) ዉሃ መጥፎ ምድሪቱም የማታፈራ ነበር ፤ ኤልሳዕ አዲስ ማሰሮዉን ምንን(ስለምን) ለማመልከት ጠየቀ (2 ቆሮ 4፡ 7፣ 5፡ 17) ? ዉሃዉን ስላነፃው እና ምድሪቱን ስለፈወሰዉ ጨዉ ምን እንደ ሚወክል ምን ታስባላችሁ ? (ማቴ 5፡ 13)
-
በ 2ነገስት (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 2:9
“After they had crossed over, Elijah said to Elisha, ‘Tell me what I can do for you before I am taken from you.’ So Elisha answered, ‘Please, let me inherit two shares of your spirit.’”
ኤልሳ ፈፅሞ ከኤልያስ ጎን አልተለየም ነበር ፤ ኤልያስ ደግሞና ደጋግሞ “ በዚህ ቆይ “ ባላው ጊዜ ሳይቀር ኤልሳ አልተለየውም ከእርሱ ጋር አብሮ ተጓዘ ፡፡ በመጨረሻም ኤልያስ እልሳን አየውና “ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን “ አለው ? ኤልሳም ከኤልያስ የፈለገውን መጠየቅ ነበረበት ፡፡ እርሱም በኤልያስ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ኃይል እጥፍ ለመነ ፡፡ እግዚአብሔርም ኤልያስን በአውሎ ነፋስ ከወሰደው በኋላ ፤ ኤልሳ የኤልያስን መጎናፀፊያ አንስቶ የእግዚአብሔርን ተአምረኛ ኃይል ማስቀጠል ጀመረ ፡፡ የኤልሳንም ልመና እግዚአብሔር እንደ ሰማ ታየ ፡፡
ሁሉም በኢየሱስ የሚያምን የራሱን መጎናፀፊያ ተቀባሏል ማለትም የመንፈስ ቅዱስን ሙሉ ቅባት ፡፡ በየቀኑ ከኢየሱስ ጋር ስትራመድ ፣ ለእግዚአብሔር መንግስት መቀባትህን አስታውስ ኃይሉም አብሮህ እንዳለ እንድሁ ፡፡ ለፅድቅ በተራብክና በተጠማህ ጊዜ እግዚአብሔር ያጠግብሃል ፡፡ በእርሱ ስትሞላ ህይወትህ ኃይሉን ያንፀባርቃል ፡፡ በኩራትና በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ኃይሉን ግለጠው ፡፡
“ ከተሸገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው ኤልሳዕም መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 2፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 62(63)፡1 – “ አምላኬ አምላኬ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ወኃ በሌለበት በምድረ በዳ ፡፡ “
ማቴዎስ 5፡6 – “ ፅድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ይጠግባሉና ፡፡ “
1ኛ ዮሐንስ 2፡20 –“ እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል ሁሉንም ታውቃላችሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።