Historical Books 1 Kings

The Death of Ahab

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 267 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለ 1ነገስት መፅሀፍ ሀረጋችን የሚበልጥ ነው በመጀመሪያዎቹ 11 ምዕራፎች ዉስጥስለ ሰለሞን በግልፅ አይተናል ፤ የመፅሀፉ ቀሪዎች ነገስታት ከነገስታቶች ጋር ሲዋጉ ህዝቦች እርስ በእርሳቸው ሲዋጋ በብዙ የመሳፍንትን ጥናት እንደ መሰለ ይሰማል ፡፡ የሰለሞን አገዛዝ አንድነት አምጥቷል ፤ ይሁን እንጂ ከሰለሞን ሞት በኋላ እስራኤል የተከፋፈለ መንግስት በመሆን ወደ ትርምስ ተወረወረ ፡፡

በ 1ነገስት 20 ኤልዛቤል ኢይዝራኤላዊዉን ናቤቴን በመግደል (ቁጥር 1-14) አክዓብ የናቡቴን የወይን እርሻ ወሰደ (ቁጥር 15-16) ኤልያስም መጣና በአክዓብ ላይ የእግዚአብሄርን ፍርድ አወጀበት (ቁጥር 17-19) ፤ ለ 1ነገስት ለመጨረሻዉ ምዕራፍ መነሻዉ ያ ነው ፡፡ ምዕራፍ 22 የኤልዛቤልና እና የአክዓብን ታሪክ ይቀጥላል እንዲሁም በይሁዳ ስለ ነበረዉ ሌለኛ መልካም ንጉስ ኢዮሳፍጥ ታሪክ ያወራል ፡፡ ይሁዳ በኢዮሳፍጥ ስር የሰለማ ጊዜን ቀምሷል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ በሶርያዊያን በገጠመዉ ከፍ ያለ ማስፈራራት አክዓብ ከሰዎስት አመት በፊት ጥቅሙን ለማስጠበቅ አቅቶት ነበር ፤ በዘገለዓድ ስልታዊ ከፍተኛ ስፍራን ሬማት መልሶ እንዳልተቆጣጠረ አመልክቷል “ ፡፡ እነዚህን ፅሁፎች ስታነቡ የሚበልጥ እንደ ሆነ የሚያብራሩትን በኢታሊክ የሆኑትን አትኩሩ ፡፡

ትምህርት

1-ነገስት (22፡ 1-5)፡ዋይርስቤ “ ከሰዎስት አመት በኋላ ቤን ሀዳድ አባቱ የወሰዳቸዉን የእስራኤልን ከተሞች ለመመለስ ስምምነቱን አልጠበቀም ነበር በዚህም አክዓብ ከሶሪያ ጋር በመዋጋት መልሶ ዪቀበልበት ጊዜ መሆኑን እንደ ወሰነ “ ይገልፃል ፡፡ ጦርነት ከሌለበት ሰዎስት አመት በኋላ የይሁዳ ንጉስ ኢዮሳፍጥ በህግ የልጁ አባት የነበረዉን የእስራኤልን ንጉስ አክዓብን ጎበኘ (ቁጥር 1-2) ፡፡ አክዓብ ኢዮሳፍጥን ለሬማ ዘገለዓድ ለመዋጋት እንዲረዳዉ ጠየቀው (ቁጥር 3) ፤ ኢዮሳፍጥ ከዚህ በፊት ከአክዓብ ጋር የተዋጋ ቢሆንም የአክዓብን ጥያቄ ተቀበለ ( ቁጥር 4) ፡፡ ኢዮሳፍጥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግ አቆመ (ቁጥር 5) ፤ የዚህ ችግሩ የቅደም ተከተል ነው - ኢዮሳፍጥ መጀመሪያ ዉሳኔ አደረገ ከዚያ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሄር ጠየቀ ፡፡

እራሳችንን ከማን ጋር እንደምናስተባብር መጠንቀቅ አለብን ! ኢዮሳፍጥ ልጁ የአክዓብን ሴት ልጅ እንዲያገባ በመፍቀድ የተደረገዉን የሚያዉቀውን አመቻመቸ ፡፡ ከማይመጣጠነን ጋር የተጠመድን መሆን አንችልም (ምሳ 4፡ 14-17) ፤ አክዓብ እና ኤልዛቤል ክፉዎች ነበሩ ኢዮሳፍጥም ልጁ ከዚያ ቤተሰብ እንዲያገባ በመፍቀድራሱን እና ህዝቡን ከእስራኤል ጋር በመተባበር መሰለፍን መረጠ ፡፡ ክፉ ልብ ከነበራቸዉ ጋር አንድነት በመፍጠር ከማይመጥኑት ጋር የተጠመደ በሆነ ጊዜ ነገሮች ተወሳሰቡበት ፡፡

1-ነገስት (22፡ 6-12)፡ አክዓብ 400 ነቢያቱን ሰብስቦ ወደ ጦር ልዉጣ ብሎ ጠየቃቸው ፤ ሁሉም አክዓብ መስማት የሚፈልገዉን በመንገር እንዲሄድ ነገሩት (ቁጥር 6) ፡፡ ኢዮሳፍጥ አንዳቸዉም የእግዚአብሄር ነቢይ እንዳልነበሩ በማወቅ የእግዚአብሄር ነቢያት የት እንደሚገኙ ጠየቀ (ቁጥር 7) ፤ አክዓብ ለእርሱ መልካም ነገር ስለ ማይናገር የሚጠላዉ አንድ ቀርቶ እንደ ነበር መለሰለት (ቁጥር 8) ፤ ኢዮሳፍጥም ያን ነቢይ የይምላ ልጅን ሚክያስን ለማየት ጠየቀ ፡፡ ለሚክያስ እንደ ተላከ የአክዓብ ሌሎቹ ነቢያቶች ታላቅ ድል እንደሚሆንለት ተስፋ ገቡለት (ቁጥር 11-12) ፡፡ ትክክለኛ ምክር በማዳመጥ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግ አለብን !

1-ነገስት (22፡ 13-28)፡ መልዕክተኛዉ ነቢዩን ሚክያስን የአካዓብ ጦርነት ድል እንደሚሆንለት በመናገር ከሌሎቹ ነቢያት ጋር እንዲቀላቀል ነገረው (ቁጥር 13) ፤ ሚክያስም እግዚአብሄር ከሚናገረዉ ዉጪ ምንም ነገር ለመናገር እምቢ አለ (ቁጥር 14) ፤ መስማማት የለብንም ነገር ግን ለእግዚአብሄር ደስታ እንጂ ለሰዉ አይደለም ! በተጠየቀ እና በንጉሱ በእዉነት እንዲናገር በተጣደፈ ጊዜ (2ዜና 18፡ 14-15) ሚክያስ ንጉስ አክዓብን ወደ ጦሩ እንዲሄድ እና እግዚአብሄርም “ ለንጉሱ “ ድል እንደሚሰጠው ነገረው (ቁጥር 15) ፡፡ ንጉሱም ስላላመነው ሚክያስን እንደ ገና ጠየቀው ሚክያስም ሁለት ራዕዮችን ነገረው ፤ በመጀመሪያዉ ራዕይ ሚክያስ እስራኤል ከመሪ ዉጪ የተበተነ እንደ ሚሆን ተናገረ (ቁጥር 16-17) ፤ ራዕዮች መሲሁ እስከሚመለስ ድረስይከሰታሉ ስለዚህም በብዙ ራዕዮችን ማየት እንችላለን (ኢዩኤል 2፣ ሐዋ 2) ፤ ይህ ሰዎች ሁሉም ቦታ ነበሩ ማንም ግን እየተጠነቀቀላቸዉ እንዳልነበር ወደ ሚል የተለመደ ስዕል ያመለክታል (ማቴ 9፡ 36) ፡፡ አክዓብ ራዕዩን በመረዳት ሚክያስ የመሸነፍ ራዕይ ብቻ ስለ ሰጠው ቅር ተሰኘ (ቁጥር 18) ፤ ሚክያስም በሁለተኛው ራዕዩ መለሰለት፡ እግዚአብሄር በዙፋኑ ላይ በሰማይ ሰራዊት ተከብቦ ተቀምጦ ነበር አክዓብን ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲዘምት ማን ያስተዋል አለ መንፈስም ለመሄድ ተስማማ “ እርሱም ወጥቼ በነቢያቶች ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሁናለሁ አለ “ (ቁጥር 19-22) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እነዚህ ነቢያቶች በክፉ ተፅዕኖ ስር ሆነ ዉ እንደተነበዩ ነገር ግን ሀሰተኛ ትነብያቸው አካዓብ ሊሰማ የሚፈልገዉ እንደ ነበር “ ያጋራል ፡፡ ኢዮሳፍጥ እግዚአብሄር በአክዓብ ነቢያቶች አፍ አሳሳች መንፈስ አስቀምጦ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 23) ፡፡ እግዚአብሄር ለክፉ የተጠቀመባቸዉ ሌሎች ምሳሌዎች (ኢዮ 1-2፣ ዮሐ 13፡ 21-30) ፡፡

ከአካዓብ ነቢያቶች አንዱ ሴዴቅያስ ሚክያስን ፊቱን በመምታት የእግዚአብሄር መንፈስ እርሱን ትቶ ወደ ሚክያስ ይሄዳልን በማለት ጠየቀው (ቁጥር 24) ፤ ተቃርኖ መጠበቅ አለብን ፡፡ ሚክያስ ሴዴቅያስን ሚክያስ ልክ እንደ ነበር የሚያዉቅበት ቀን እንደ ሚመጣ ነገረው (ቁጥር 25) ፤ አክዓብ ሚክያስን መልሶ ዳቦ እና ዉሃ ብቻ እየተመገበ በሰላም እስኪመለስ ድረስ በሚል ትዕዛዝ ወደ ወህኒ ቤት ላከው (ቁጥር 26-27) ፡፡ ሚክያስም አክዓብ በሰላም ከተመለሰ እግዚአብሄር ለእርሱ እንዳልተናገረው መለሰለት (ቁጥር 28) ፡፡ አንዴ የእግዚአብሄር ቃል ከተናገርንእርግጠኞች እና ፀንተን የቆምን መሆን አለብን !

1-ነገስት (22፡ 29-40)፡ ንጉሶቹ ጦራቸዉን በሬማት ዘገለዓድ (ቁጥር 29) ፤ አክዓብ ራሱን ደበቀ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ የነገስታትን ልብስ ለብሶ ነበር (ቁጥር 30) ፡፡ አክዓብ የሚክያስ ትንቢት ወደ እዉነት እንዳይመጣ ለማስወገድ እየሞከረ ነበር ፡፡ የሶሪያ ንጉስ 32 የሰረገላ አዛዦቹን ከእስራኤል ንጉስ ጋር ብቻ እንዲዋጉ አዘዛቸው (ቁጥር 31) ፤ ኢዮሳፍጥን በንጉሳዊ ልብሱ ባገኙት ጊዜ ወደ እርሱ ተመለሱ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ በፍርሀታ ጮኸ (ቁጥር 32) ፤ ሰረገሎቹም ከኢዮሳፍጥ ተመለሰ (ቁጥር 33) ፡፡ አንድ ሰው ቀስቱን በድንገት ወደ አየር ተኮሰው የእስራኤልም ንጉስ አክዓብን በደረት መከላከያው እና በታችኛዉ ጥሩሩ መካከል ወጋዉ (ቁጥር 34) ፡፡ አክዓብ ሰረገለኛዉን ከዉጊያዉ እንዲያስወጣው ነገረው (ቁጥር 35) ፤ አክዓብ በሰረገላዉ ላይ ተደግፎ ነበር ደሙም ለሞት እየፈሰሰ የቀረውን የጦሩን ኃይል ተመለከተ (ቁጥር 36) ፡፡ ፀሀይ እንደ ጠለቀች የሚክያስ ትንቢት ወደ እዉነት መጣ እያንዳንዱም ሰዉ ወደ እራሱ ቤት ወይም ምድር ተላኩ (ቁጥር 37) ፡፡ አክዓብ በሰማሪያ ተቀበረ (ቁጥር 37) ፡፡ ሰረገላዉንም በሰማሪያ ኩሬ በዚያ የቀረዉን ዉሾች በሚልሱበት፣ አመንዝሮች በሚታጠቡበት እግዚአብሄር ቃል እንደ ገባው ታጠበ (ቁጥር 38) ፡፡ አክዓብ ከአባቶቹ ጋር አረፈ ልጁም አካዝያስ የእስራኤል ቀጣዩ ንጉስ ሆነ (ቁጥር 40) ፡፡

1-ነገስት (22፡ 41-50)፡ ኢዮሳፍጥ ከእግዚአብሄር ፍቃድ ዉጪ ያደረጋቸዉ ሰዎስት ማመቻመቾች፡

  • ሙሽራዋን አመቻመቸ፡ የልጁን ሙሽራ የአክዓብን እና የኤልዛቤልን ሴት ልጅ እንዲያገባ በመረጠ ጊዜ አመቻመቸ ፡፡
  • ዉጊያዉን አመቻመቸ፡ እስራኤል ሶሪያን በአጠቃ ጊዜ በህግ የልጁ አባት ከሆነዉ በእስራኤል ንጉስ በአክዓብ ጉዳይ ዉስጥ በመወሳሰብ የራሱን ህይወት አጥቶ ነበር ፡፡
  • ጀልባን አመቻመቸ፡ በእግዚአብሄር ቅሬታ ጠፍተዉ የነበሩ ከአክዓብ እና በህግ ከኢዮሳፍጥ ወንድም ወንድ ልጅ ከአካዝያስ ጋር የንግድ ትስስር ተስማማ ፡፡

መደምደሚያ

ከዚህ ምን ልንማር እንችላለን ? በእግዚአብሄር ፈቃድ ጣፋጭ ቦታ ላይ መጓዝ ቀጥሉ ፡፡ ራሳችሁን ከማን ጋር እንደምታጣምሩ ተጠንቀቁ ፤ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ፈልጉ ፡፡ በሂደቱ ትክክለኛዉን አማካሪ አዳምጡ ፤ ስታዳምጡ ከሀሰተኛ እዉነት ጋር አትስማሙ ወደ ክፉም አትግቡ ፡፡ ተቃርኖ መጠበቅ ትችላላችሁ ነገር ግን ይህን ስታደርጉ ለራሴ የምማረዉ አንድ ነገር ፀንቶ መቆምን እና ከእግዚአብሄር በሰማነዉ እርግጠዮች ሆኖ በቀመጥን ነው ፡፡ በይሁዳ ወደ እኛ መምጣት ስለሚጀምሩ እነዚህን ሁሉ እዉነት ስለሚመስሉ ነገሮች ያወራል ነገር ግን ሀሰት ናቸው ፡፡ ፍፁም እዉነት ስላለን ስራችን ለዚህ እዉነት የፀናን በመሆን እንድንሄድ እግዚአብሄርን መጠየቅ ነው ፡፡ እዉነቱ ላይ መፅናት እንችላለን ምክንያቱም ኢየሱስ ካወራናቸዉ ከእነዚህ ነገስታቶች የሚበልጥ ስለ ሆነ !

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 1 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 458.

  2. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 488.

  3. Nelson’s Commentary, p. 458.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ነገ (21፡ 3) የአባቶቻቸዉ ዉርስ ምን ነበር በጣም ያስፈለገዉስ ለምን ነበር (ዘኁ 36፡ 9-12) ? በመንግስቱ ዉርሳችን ምንድን ነው (ኤፌ 1፡ 14፣ 18፣ ዕብ 9፡ 15፣ 1ጴጥ 1፡ 4) ? “ ሳንሸጥ እና ሳንነግድ “ እንዴት ይዘነዉ ልንፀና እንችላለን ?
  2. ኤልዛቤል ለሁለት ሰዎች በኃሰት ከሰዉ ናቡቴን እንዲገድሉት አመቻቸች ፤ ይህ እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? (ማቴ 26፡ 59፣ ማር 14፡ 55)
  3. ኤልዛቤል የናቡቴን ሞት ለማስጀመር የንጉሱን ስልጣን ተጠቀመች ንጉስ አክዓብም እንዲሆን ፈቀደ ፤ እግዚአብሄር ተጠያቂ አድርጎታል ( 1ነገ 21፡ 18-19) ? ይህ በዘፍ (3፡ 6፣ 3፡ 17) ስለ አዳም ያስታዉሳችኋል?
  4. አክዓብ በእርሱ እና በቤተሰቡ ላይ የእግዚአብሄርን ፍርድ ከሰማ በኋላ ራሱን አዋረደ ፤ እግዚአብሄር እንዴት መለሰለት (1ነገ 21፡ 28-29) ? ይህ ስለ እግዚአብሄር ባህሪይ ምን ይነግረናል ? (ዘጸ 34፡ 6-7፣ ሕዝ 18፡ 23)
  5. በ 1ነገስት 22 ምን ያክል ትንቢቶች ተፈፅሞ ታያላችሁ (1ነገ 22፡ 34፣ 38) ? ለእናንተ ተነግሯችሁ የነበረዉ ትንቢቶች መፈፀማቸዉን ቀምሳችሁ ታውቃላችሁ ?
  6. በ 1ነገስት (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 22:8

“The king of Israel said to Jehoshaphat, ‘There is still one man who can ask Yahweh, but I hate him because he never prophesies good about me, but only disaster. He is Micaiah son of Imlah.’ ‘The king shouldn’t say that!’ Jehoshaphat replied.

የይሁዳ ንጉስ ኢዮሳፍጥ ባአባቱ በንጉስ አሳ መንገድ ሄደ በእግዚአብሔርም ፊት ቅን የሆነውን አደረገ ፡፡ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ በራሱ ውሳኔ የሚወስንባቸው እና ከዚያ በእቅዱ ላይ እግዚአብሔርን የሚያስገባባቸው ጊዜያት ነበሩ ፡፡ ጦርነት በገጠመው ጊዜ ንጉስ ኢዮሳፍጥ መጀመሪያ የእግዚአብሔር ሰው ካልሆነው ከአክኣብ ጋር ተጣመረ እና ከዚያ በኋላ ደግሞ ለምሪት እግዚአብሔርን ፈለገ ፡፡ ኢዮሳፍጥ እራሱን ከማን ጋር እንደሚያጣምር ሲወስን ጠንቃቃ አልነበረም ከዚያም አልፎ እርሱ የሚያምነውን ነገር የመቻምች ነበር ፡፡

ከክርስቶስ ጋር ስትራመድ ጠላት ሊያምታታህና ከጌታ እንድትርቅ ሊያባብልህ ይፈልጋል ፡፡ ራስህን ከማን ጋር እንደምታጣምር ተጠንቀቅ ፡፡ እግዚአብሔርን ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ራስህን ስታጣምር ያስቱሃል ከክርስቶስም ያርቁሃል ፡፡ ነገር ግን እንዳንተ ካሉ አማኞች ጋር ጊዜ ስትወስድና ስትጣመር እርስ በእርሳችሁ ትተናነጻላችሁ ፡፡ አሁን ደቂቃ ውሰድና አስብ በህይወትህ ምክር ስትሻ የምትፈልጋቸው እነማን ናቸው ፡፡ ከጌታ ጋር ነው ሚራመዱት ወይስ በራሳቸው መንገድ ? ከከርስቶስ ጋር እየተራመድክ ከሆነ በእርሱ እውነትና መንገድ ላይ መሆንህን አረጋግጥ ፡፡

“ የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሳፍጥን እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ አለው ፡፡ ኢዮሳፍጥም ንጉስ እንዲህ አይበል አለ ፡፡ “

  • 1ኛ ነገሥት 22፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 27፡17 –“ብረት ብረተን ይስለዋል ሰውም ባልንጀራውን ይስላል ፡፡ “

2ኛ ቆሮንቶስ 6፡14 –“ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ጽድቅ ከአመጽ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና ? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው ፡፡ “

1ኛ ዮሕንስ 4፡1 –“ ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ብዙዎች ሀሰተኞች ነቢያት ወደ አለም መጥተዋልና ፡፡ “