Historical Books 1 Kings

Hearing God's Whisper

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 266 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ 1 ነገስት መጨረሻ እየቀረብን ነው በኤልያስ ላይ ይህን ፅሁፍ እወደዋለሁ ፡፡ ሁላችን ከእግዚአብሄር መገኘት በኋላ የነበረንን አስገራሚ ጊዜ የሚያስረሳ ስሜት ቀምሰናል ፤ ለምሳሌ በቴክሳስ መነቃቃት 50 የወንጌል ስርጭት ቀንትን ከጨረስን በኋላ ሀሳባዊ እና ስሜታዊ ፍትጊያ ነበር ፤ ኤልያስ የነበረበት ይህ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከሰማይ እሳት ሲያዘንብ ከዚያም ደግሞ ለእስራኤል ዝናብ ሲሰጥ አይቷል ፤ ነገር ግን አክዓብ ኤልዛቤልን ኤልያስ ስላደረገዉ የነገራት ቢሀንም የነገራት ሁሉም ነገር እዉነት ስለ መሆኑ አናዉቅም ፡፡ ያዕ (5፡ 17) “ ኤልያስ እንደኛ አይነት ተፍጥሮ “ እንደ ነበረዉ ይገልፃል ፡፡ ዋይርስቤ “ የኪንታሮትን እና የጎስቋላነትን ታላቅነት በመግለፅ “ እንኳን መፅኀፍ ቅዱስን ያመለክታል በዚህም በ 1ነገ (18-19) “ ኤልያስን በከፍታዉ ላይ እና በዝቅታዉ ላይ እናየዋለን “ ፡፡ ይህ ፅሁፍ በአገልግሎት ራሱን ካፈሰሰ በኋላ የኤልያስን ሰብዓዊነት(ሰዉ መሆንን) ያሳያል (መዝ 39፡ 5) ፡፡

ትምህርት

ዋይርስቤ ምዕራፍ 19 በዚህ ጥናት ወደ ምንከተለው ወደ አራት ክፍል ይከፋፍለዋል፡ “ የጠላት የአደገኛ መልዕክት “፣ “ የመለዓኩ የፀጋ መልዕክት “ ፣ “ የፈጣሪዉ የኃይል መልዕክት” እና “ የእግዚአብሄር የተስፋ መልዕክት “ ፡፡

1-ነገስት (19፡ 1-4)፡የጠላት የአደጋ መልዕክት ፡፡ አክዓብ ኤልዛቤልን ሁሉንም ነገር ነገራት ለኤልያስም ነፍሱን እንደ ምትወስዳት ቃል በመግባት ለኤልያስ መልዕክት ላከችለት (ቁጥር 1-2) ፡፡ መልዕክቱ ከንጉሱ ከአክዓብ የመጣ ሳይሆን ከንግስቲቱ መሆኑ የሚያስደንቅ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ኤልዛቤል ነቢዩን ወደ ሰማዕትነት በመቀየር ከህይወቱ ይልቅ በሞቱ ህዝቡ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያመጣ “ ያስቀምጣል ፡፡ ኤልዛቤል “ ለኤልዛቤሎች “ እቅድ ያላት ትመስል ነበር ፤ ምንኛዉንም ሁኔታ ለራሳቸዉ ለመስራት ተመለከቱ - በህይወታችሁ ወይም በአገልግሎታችሁ የምትፈልጉት ሰዉ የለም ፡፡

ኤልያስ የኤልዛቤልን መልዕክት ተቀበለ ፈራም ፤ ከደቡብ ወደ ቤርሳቤህ ሮጠ ወደ በርሃም ለመሄድ አገልጋዮን በዚያ ተወዉ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ቻርለስ ሱፐርገን “ ኤልያስ በተሸነፈ ጠላት ፊት አፈገፈገ ብሏል “ ፤ ኤልያስ ቀድሞዉኑ አሸንፏቸዉ ከነበረዉ ጠላቱ ሮጠ ፡፡ “ እግዚአብሄር የኤልያስን ፀሎት በመመለስ(1 ነገ 18፡ 36-37) የእግዚአብሄር እጅ ወንዙ ላይ እርሱ ላይ ነበረች (1 ነገ 18፡ 46) ነገር ግን አሁን በእምነት ሳይሆን በማየት እየተጓዘ ነበር ፡፡ ኤልያስ “ ህይወቱን ለማዳን በእግዚአብሄር ፊት እየሮጠ ነበር “ ፤ ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ ወደ ምድረበዳ በመጓዝ በአንድ ክትክታ ዛፍ ስር በመቀመጥ እግዚአብሄር ህይወቱን እንዲወስድ ፀለየ (ቁጥር 4) ፡፡

1-ነገስት (19፡ 5-8)፡የመለዓኩ የፀጋ መልዕክት ፡፡ የፅሁፉ አጠቃላይ ነገሩ ቁጥር 5 ላይ ይቀየራል ፡፡ ኤልያስ በዛፉ ስር ተኝቶ ሳለ አንድ መለዓክ ነካውተነስቶም እንዲበላ ነገረው (ቁጥር 5) ፤ ቫንሴ ሀቭነር “ ተለይተን የማንመጣ እና የማናርፍ ከሆነ ተለይተን እንመጣለን “ ይላል ፡፡ ይህ መልዓክቶች በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን ለሆነ ሰዉ የተገለጡበት ብቸኛዉ ጊዜ አልነበረም (ሐዋ 12፡ 7) ፤ በተመለከተ ጊዜ ኤልያስ በጋሉ ድንጋዮች ላይ የተጋገረ ዳቦ እና አንድ ማሰሮ ዉሃ አገኘ (ቁጥር 6) ፡፡ መለዓክት ሊያገለግሉን እንደ ሚመጡ አስታዉሱ (ዕብ 1፡ 14፣ መዝ 91፡ 11) ፡፡ በቁጥር 7 መልዓኩ “ የእግዚአብሄር መልዓክ ተብሎ የተጠቀሰ ነው “ ይህ ቅድመ ክርስቶስን እንደ ሚያመለክት አምናለሁ ( ዘፍ 16፡ 10፣ ዘጸ 3፡ 1-6፣ መሳ 2፡ 1-4) ፤ ከነቢያቶች ታላቅ ለሆነዉ አንዱ ክርስቶስ ታይቷል ፤ ለሁለተኛ ጊዜም ተኛመገበዉም ኤልያስም ጉዞዉን መቀጠል ቻለ ፡፡ ኤልያስ በላ ጠጣም ከዚያም በምግቡ ጥንካሬ ወደ እግዚአብሄር ተራራ ኮሬብ ተራራ (ወይም ሲና ተራራ) ላይ 200 ማይል ርቀት ያክል 40 ቀን እና ሌሊት ተጓዘ (ቁጥር 8) ፡፡

1-ነገስት (19፡ 9-14)፡የፈጣሪዉ የኃይል መልዕክት ፡፡ ኤልያስ አንድ ዋሻ ዉስጥ ገባ ምሽቱንም በዚያ ቆየ (ቁጥር 9) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዋሻዉ “ በዕብራዊያን የተፃፈበት መንገድ “ ይህ ዋሻዉ ሙሴ የእግዚአብሄርን መገኘት በእግዚአብሄር ተራራ ላይ ባገኘው ጊዜ ራሱን ደብቆበት የነበረውእንደ ነበር (ዘጸ 45) “ እንደ ሚያመለክት ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር ኤልያስን ለምን ወደ ዋሻዉ እንደ መጣ ጠየቀው (ቁጥር 9) ፤ ኤልያስ ያደረገበትን ሁሉንም፣ ህዝቡ እግዚአብሄርን እንደ ተወ እናነቢያቶቹ እንደ ተወገዱ ገለፀ (ቁጥር 10) ፡፡ እግዚአብሄር ኤልያስን ተነስቶ ከዋሻዉ ዉጪ በእግዚአብሄር ፊት እንዲቆም ነገረው ፡፡

እግዚአብሄር በተራራዉ ላይ በሚጮኽ ኃይለኛ እና ተራሮችን በሚሰነጥቅ ንፋስ እና በምድር መናወጥ አለፈ ነገር ግን እግዚአብሄር በአንዱም ላይ በንፋሱም ወይም በመሬት መናወጡም አልነበረም (ቁጥር 11) ፤ በ ሐዋ (2፡ 2-3) እግዚአብሄር በንፋስ ሲገለጥ እና በዘካ (14፡ 4-5) በመሬት መናወጥ ሲገለጥ ብናይም በኤልያስ ያ አልነበረም ፡፡ ቀጥሎም እሳት መጣ (ዘጸ 40፡ 38) ነገር ግን እግዚአብሄር በእሳቱ ዉስጥ አልነበረም ፤ በመጨረሻም ቀስ ያለ ሽኩሹክታ ነበር የእግዚአብሄርም ድምፅ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኤልያስ ለመብረቅ ተጣራ ለእሳቱ እና ለሀገራዊ መነቃቃት ተጠርቶ ነበር ፤ ኤልያስ ያላየዉ ነገር እግዚአብሄር በብዙ ሰዎች ህይወት እየሰራ እንደ ነበር ነበር “ ፡፡ በዝምታ እና በፀጥታ በህዝብ በእያንዳንዱ ቀን ኑሮ ዉስጥ እየሰራ ነበር ፤ ነገር ግን ኤልያስ ለመነቃቃት ስለ እሳቱ እና ስለ ብርሃኑ እየተመለከተ ነበር ፡፡

ኤልያስ ድምፁን አወቀዉ ፊቱንምበመጎናፀፊያዉ በመሸፈን በዋሻዉ መግቢያ ላይ ቆመ (ቁጥር 13) ፤ ድምፁ እንደ ገና ኤልያስ በዚያ ምን እያደረገ እንደ ነበር ጠየቀው (ቁጥር 13) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የእግዚአብሄር ጥያቄ “ በተለየበት በራሱ ተልዕኮ መሰረት በተለመደዉ በህይወቱ መንገድ ላይ የትም ቦታ እግዚአብሄርን የሚያገለግልበት ጊዜ እንደ ሆነ “ የሚያመለክት እንደ ሆነ ያትታል ፡፡ በእግዚአብሄር ጥያቄ በቁጥር 10 መጀመሪያ ያለዉን ኤልያስ ደገመ “ …..እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ፤ ነፍሴንም ሊወስዷት ይሻሉ አለ “ (ጥር 14) ፡፡

1-ነገስት (19፡ 15-21)፡የእግዚአብሄር የተስፋ መልዕክት ፡፡ እግዚአብሄር ኤልያስን በሶሪያ ላይ እንደ ንጉስ አዛሄልን እንዲቀባው በመጣበት መንገድ መልሶ ላከው (ቁጥር 15) ፤ አስታዉሉ እግዚአብሄር በኤልያስ ተስፋ አልቆረጠም እንድናደርገዉ ከሚፈልገዉ በምናጉረመርም ወይም በምንሮጥ ጊዜም እንኳን በእኛም ተስፋ አይቆርጥም ፡፡ እግዚአብሄርም ኤልያስን በጥሪዉ እንዲጓዝ በአዲስ መንገድ ላከው (መዝ 103፡ 11-14) ፤ ኤልያስም ኢዩን በእስራኤል ላይ እንደ ንጉስ ሊቀባ እና አልሳን እንደ ነብይ የእርሱን ቦታ እንዲወስድ ሊቀባ ይሄዳል (ቁጥር 16) ፡፡ ኢዩ፣ አዛሄል እና ኤልሳዕ እንደ እግዚአብሄር መሳሪያ የሚጠቅሙ ይሆናሉ (ቁጥር 17) ፡፡ እግዚአብሄር ለአምላካቸዉ ለያህዌ ታማኝ የሆኑ 7,000 ሰዎች እንደ ነበሩ አመለከተ (ቁጥር 18) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኑሮአቸዉ አስደናቂ ያልሆነ ነገር ግን ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነዉ የሚኖሩ በሁሉም ህዝብ መካከል የነበሩ እንደ ነበሩ እንደ አንድ ማህበረሰብ ይገልፃቸዋል “ ፡፡ ኤልያስ በመታዘዝ ምላሽ ሰጠ በእርሻዉ ላይ ሲሰራም ኤልሳዕን አገኘዉ መጎናፀፊያዉንም ወረወረበት (ቁጥር 19) ፤ ኤልያስ ያስበዉ እና ይሰማዉ የነበረዉን ሁሉንም ነገር ተቋቋመ ምክንያቱም አሁንም እግዚአብሄር በእሱ ህይወት አላማ ስለ ነበረው ፡፡ ኤልሳዕ ቤተሰቡን ለመሰናበት ጊዜ ጠየቀ ከዚያም በመታዘዝ እና በመታመን ኤልያስን ተከተለው (ቁጥር 20-21) ፡፡

መደምደሚያ

ኤልያስ እግዚአብሄርን በእግዚአብሄር ኃይል ሳይሆንበእግዚአብሄር ዝግ ባለ ድምፅ አገኘው ፤ ብልጭልጭ ወይም የማይረባ አልነበረም ነገር ግን ኤልያስ በሁሉም ቀን ህይወቱ የሰማዉ የእግዚአብሄር ሹክሹክታ ነበር ፤ በዚህም ምክንያት ኤልያስ ወደ ኤልሳዕ በመጎናጸፊያዉ ማለፍ ቻለ ፡፡ በአሁኑ ስዓትበምንም ሁኔታ ዉስጥ ብትሆኑም ለእናንተ ተስፋ አላችሁ - በህይወታሁ ዉስጥ እግዚአብሄር መስራት መቀጠል ይችላል !

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 475.

  2. Wiersbe, pp. 475–480.

  3. Wiersbe, p. 476.

  4. Wiersbe, p. 476.

  5. Wiersbe, p. 476.

  6. Wiersbe, p. 476.

  7. Wiersbe, p. 476.

  8. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 1 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 455.

  9. Nelson’s Commentary, p. 455.

  10. Nelson’s Commentary, p. 455.

  11. Nelson’s Commentary, p. 455.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ነገ (19፡ 2) ኤልዛቤል በቀጣዩ ቀን የኤልያስን ህይወት እንደ ምትወስደው ማለች ፤ የእግዚአብሄርን ኃይል ከታየየ በኋላ ስለ ህይወቱ ኤልያስ ለምን በመፍራት ሮጠ ? ይህ በማቴ (14፡ 20-31) ጴጥሮስን ያስታዉሳችኋል ?
  2. አንድ መለዓክ ኤልያስን በጋለ ድንጋይ የተጋገረ ዳቦ አበላዉ ዉሃም አጠጣው ፤ የእነዚህ እያንዳንዳቸዉ ነገሮች ( ዳቦ፣ ድንጋይ እና ዉሃ) እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? (ዮሐ 4፡ 14፣ 6፡ 35፣ 1ቆሮ 10፡ 4)
  3. እግዚአብሄር ኤልያስን በተራራው ላይ በፊቱ እንዲቆም ጠራው ፤ በአጠገቡ እግዚአብሄር እያለፈ በነበረበት ጊዜ ምን ክስተት ተካሄደ (1ነገ 19፡ 11-13) ? እግዚአብሄር በመፅሀፍት ዉስጥ በሚናገር ጊዜ እንዴት ነዉ የተገለፀው ? ( 1ሳሙ 3፡ 6፣ መዝ 29፡ 3-8፣ 68፡ 33፣ ኤር 10፡ 13፣ ሕዝ 43፡ 2፣ ራዕ 1፡ 10፣ 15)
  4. በ 1ነገ (19፡ 10, 14) በእስራኤል ልጆች ላይ ኤልያስ ያቀረባቸዉ ሰዎስት ክሶች ምን ነበሩ ?
  5. በ 1ነገስት 20 ብዙ ጊዜ ሰዎች ወደ አካብ ከሶሪያ ጋር ለመዋጋት በሚል ከእግዚአብሄር በሆነ መልዕክት መጡ ፤ እግዚአብሄርን እንዳላገለገለ እና አክብሮት እንዳልነበረው ብናዉቅም አክዓብ ለምን እንደ ተጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ( 1ነገ 18፡ 18) ? እግዚአብሄር እስራኤልን ከሶሪያ ለምን አዳነ ? (1ነገ 20፡ 13፣ 28)
  6. በ 1ነገስት (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 19:4–5

“But he went on a day’s journey into the wilderness. He sat down under a broom tree and prayed that he might die. He said, ‘I have had enough! LORD, take my life, for I’m no better than my fathers.’ Then he lay down and slept under the broom tree. Suddenly, an angel touched him. The angel told him, ‘Get up and eat.’”

ኤልያስ እግዚአብሔርን ከሶስት የድርቅ አመታት በኋላ ዝናብ ባዘነበ ጊዜ ታምራዊና ኃይለኛ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ ቢያየውም ፤ ጠላት ግን እርሱን ሊያስፈራራው ችሎ ነበር ፡፡ ፈርቶም ነፍሱን ለማዳን ሸሸ ፡፡ ኤልያስም ወደ ምድረ በዳ ብቻውን ሄደ ከክትክታም ዛፍ በታች ተቀመጠና ይሞት ዘንድ ጸለየ ፡፡ ለእግዚአብሔር “ ይበቃኛል “ አለ ፡፡ ነገር ግን ከዚያ መልአክ ተገለጠለትና “ የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነስተህ ብላ “አለው ፡፡ ይበላና ይጠጣም ዘንድ መልአኩ ምግብና ውኃ ሰጠው ፡፡ ኤልያስም በረታ ወደ እግዚአብሔርም ጥሪም አድስ ጉዞን ጀመረ ፡፡

በአገልግሎትህ ፣ በስራህ ፣ በቤተሰብህ ወይም በትዳርህ ውስጥ “ ይበቃኛል “ በሚል አጋጣሚ እራስህን አግኝተኸው ታውቃለህ ፡፡እንድህ ሲገጥምህ ይህንን አስተውስ ፡- ሊያልቅልህ እንደሆነ በሚሰማህ ጊዜ እንኳ ጠላትም ምንም መውጫ መንገድ እንደሌለ ሲነግርህ ተስፋ እንዳትቅርጥ ፡፡ ሁልጊዜም ተሰፋ አለ ፡፡ በኤልያስ ድካም ውስጥ እግዚአብሔር እውነትን ፣ ምግብን ፤ ውኃን በተጨማሪም “ ተነስ “ ይለው ዘንድ መልአክን ላከ ፡፡ ዛሬ እነዚህን ቃላት መስማት ያስፈልግህ ይሆናል ፡- ተነስ ! ወይም ምናልባት እነዚህን ቃላት ተስፋ ለቀረጠ ጓደኛህ መንገር ያስፈልግህ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሔር ገና ነገርህ እያለቀ መሆኑን ስታሰብ ይሰጥሃል ፡፡ ተስፋ አትቁረጥ ፡፡ እግዚአብሔር ያነሳሃል እንደገናም ጠንካራ ትሆን ዘንድ ያበረታሃል ፡፡ ይህን ኃይልን በሚሰጥህ በክርሰቶስ ትችላለህ ፡፡

“ እርሱም አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ሄደ መጥቶም ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና ፡- ይበቃኛል አሁንም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ ብሎ እንድሞት ለመነ ፡፡ በክትክታውም ዛፍ በታች ተጋደመ እንቅልፍም አንቀላፋ እነሆም መልአክ ዳሰሰውና ተነስተህ ብላ አለው ፡፡ “

- 1ኛ ነገሥት 19፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 27(28)፡7 –“ እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ ስጋዬም ደስ ይለዋል ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ ፡፡ “
  • መዝሙር 72(73)፡26 –“ የልቤ አምላክ ሆይ ልቤና ስጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው ፡፡ “
  • ኢሳይያስ 40፡31 –“ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም ፡፡ “