The Coming of Revival
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
1 ነገስት 18 ጎርደን ኮርንዋል ስነ መለኮታዊ ሴሚናሪ ላይ በግል አስተያዬቴ በሪቫይቫል በጣም የተሰጠ እና አርቆ አስተዋይ፣ በደንብ የሚያዉቅ እና ስርዓት ያለዉ በሆነዉ በዶክተር ሮበርት ኮልማን ስር ጥናት ጊዜዬ መልሶ ይወስደኛል ፡፡ በዶክተር ሮበርት ኮልማን ስር ከሰዎስት አመታት በኋላ በዚህ ፅሁፍ ለዶክትሬት የሚሆን ፅሁፍ እፅፋለሁ ፡፡ ዋልት ካሲየር ለመነቃቃት ጊዜን የሚያስተካክል አንድ መፅሀፍ እንደ ገና አነቃቃን የሚል መፅሀፍን ፅፏል ፤ ካሲየር በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን በሁለቱም “ እግዚአብሄር እግዚአብሄር የሚሆንበት ጊዜ ነው “ በሎ በጠራዉ በዛሬዉ ፅሁፍ ላይ መሰረት ያደረገ ስለ መነቃቃት የሚያስደንቁ ብዙ ቁጥሮችን ፅፏል ፡፡ 1 ነገስት 18 የመነቃቂያ ጊዜ ምዕራፍ ይባላል ምክንያቱም በዉስጡ ያለዉ ልብለሀገራዊ መነቃቃት እና ለእግዚአብሄር መገለጥ አስፈላጊ ስለሆነ ፡፡ በደንብ እግዚአብሄር እግዚአብሄር እንዲሆን ስፍራ ልንሰጠዉ ይገባል - ህዝባችንን እና አኗኗራችንን ለማነቃቃት አንደሚፈልገዉ በማድረግ ፡፡
በ 1ነገስት 17-18 እስራኤል ተከፍሎ ሁለት አዲስ መንግስት እስራኤል በደቡብ እና እስራኤል በሰሜን ተፈጥሮ ነበር ፤ ሁለቱም መንግስታት ብዙ ነገስታትን አሳልፈዋል ነገር ግን ሁሉም እንደ አንድ በእግዚአብሄር እይታ ክፉ ነበር ፡፡ እዚህ ላይ መንግስታቱ ከተከፋፈሉበት (931 ከክርስቶስ ዉልደት በፊት) 58 አመታት አልፎ ነበር ፡፡ በሰሜን መንግስታት ክፉ ነገር አድርገው በ 1ነገስት የተመዘገቡት፡ ኢዮሮብዓም ለህዝቡ እንዲያመልኩ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን ሰራ (1 ነገ 15፡ 26)፣ ልጁ ናዳብ አባቱ ማምለክ በጀመረባቸዉ ጣዖቶች ቀጠሉ (1 ነገ 15፡ 26)፣ ባአሳ ዙፋኑን ለመዉሰድ ንጉስ ናዳብን ገደለው (1 ነገ 15፡ 27)፣ የባአሳ ልጅ ኤላ ሰካራም እና ገዳይ ነበር (1 ነገ 16፡ 8-9)፣ ዘምሪ በኤላ ላይ ክህደት በመፈፀም ዙፋኑን ወሰደ (1 ነገ 16፡ 20)፣ ዘንበሪ ህዝቡን ወደ ጣዖት አምልኮ መራ (1 ነገ 16፡ 25-26) እና የዘንበሪ ልጅ አክዓብ ኤልዛቤልን አገባ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገስታት ይበልጥ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ (1 ነገ 16፡ 30-31) ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት 17፡ በሰሜኑ መንግስት ፍፁም የሆነ ክፋት ነበር ፤ በዚህም መነሻነት እግዚአብሄር ምድሪቱ ላይ ስለሚያወርደዉ ርሀብ ለማሳወቅ እግዚአብሄር ቴሴቢያዊዉን ኤልያስን ላከ (ቁጥር 1) ፡፡ ከአዋጁ በኋላ ኤልያስ በኮራት ፋፋ ዉስጥ(ቁጥር 2-7) ከዚያም በአንዲት መበለት ሰራፕታ ጋር ተደበቀ (ቁጥር 8-24) ፤ በ 1ነገስት 18 ዉስጥ ስንጓዝ እግዚአብሄር እግዚአብሄር እንዲሆን እንፈቀድ የሚለዉን ከካሲየር ስንመለከት ሰዎስት አነጋገሮችን(መግለጫዎችን) እጠቀማለሁ ፡፡
1-ነገስት (18፡ 1-6)፡ደፋሮች ያደርገናል፡ ከአክዓብ ሰዎስት አመት ከተደበቀ በኋላ እግዚአብሄር ኤልያስን ዝናብ ይዘንባል ከመለዉ መልዕክት ጋር በአክዓብ ፊት እንዲገለጥ ላከው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ደፋሮች በመሆን የእግዚአብሄርን ቃል ለማድረስ መራመድ ያስፈልገናል (ዘዳ 31፡ 6፣ ኢያ 1፡ 9፣ 1ዜና 28፡ 20) ፡፡ አክዓብ በአክዓብ ቤት አዛዥ እና እግዚአብሄርን ይፈራ የነበረዉን (ነቢይ ያልነበረዉን ነገር ግን የስሙ ትርጉም “ የእግዚአብሄር አገልጋይ “ የሚል የነበረውን አብድዩን ጠራው ፡፡ ኤልዛቤል ሌሎቹን ሁሉንም አሳርዳቸዉ በነበር ጊዜ አብድዩ የእግዚአብሄርን 100 ነቢያቶች በሁለት ዋሻ ዉስጥ በመደበቅ ምግብ እና ዉሃ ይሰጣቸዋል ነበር (ቁጥር 3-4) ፡፡ ንጉስ አክዓብ በሌለኛዉ አቅጣጫ በሚሄድበት ጊዜ አብድዩ በምድሪቱ በአንድኛዉ መንገድ ፈረሶቹን፣ በቅሎዎቹን ከብቶቹን በርሀብ እንዳይሞቱ ለማዳን እንዲመግባቸዉ ተላከ (ቁጥር 5-6) ፡፡
1-ነገስት (18፡ 7-20)፡ አብድዩ እየተጓዘ ሳለ ኤልያስ “ በድንገት አገኘው “ ፤ አብድዩም ወዲያዉኑ አወቀው (ቁጥር 7) ኤልያስም አብድዩን ለአክዓብ እንደ ተመለሰ እንዲነግረዉ ላከው (ቁጥር 8) ፤ አብድዩ ኤልያስን የእግዚአብሄርን ነቢያት ደብቆ በመንከባከብ ራሱን አደጋ ዉስጥ አስገብቶ ሳላ መልዕክቱን በማድረስ በአክዓብ እንዲገደል ለምን መልሶ እንደሚልከዉ ጠየቀው (ቁጥር 9-14) ፡፡ አብድዩ ታዘዘ አክዓብም ኤልያስን አገኘው አስቸጋሪዉ ብሎ ጠራው (ቁጥር 15-17) ፤ ኤልያስም አክዓብ እና አባቱ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመተዉ ጣዖት በማምለክ እስራኤልን እንዳጠፉ ተናገረ (ቁጥር 18) ፡፡ ኤልያስ አክዓብን ከሁሉም ከባዖል እና ከማምለኪያ አፀድ ነቢያትን ጋር በቀርሜሎስ ተራራ ላይ እንደሚያገኘዉ ነገረው (ቁጥር 19-20) ፡፡
ስለ አብድዩ ስነ መለኮታዊ ዉይይቶች አስደናቂዎች ናቸው ፤ ብዙዎች አብድዩ እንደ አክዓብ አገልጋይ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነቱን እንዳመቻመቸ ያስባሉ ፤ ካሲየር ይህን እንደ ማመቻመች አይቀበለዉም በአብድዩ ባህሪይ አለመፅናትን ይፅፋል፡
- እግዚአብሄር ተከታዩን ሰዉ በማየቱ የተደሰተበትን ምንም ማስረጃ አልሰጠም ፡፡
- ኤልያስ እንደ ተመለሰ ሄዶ ለአክዓብ ለመናገር ቅር ተሰኝቷል ፡፡
- ራሱን ያማከለ እና ስለ ራሱ ደህንነት ብቻ እያሰበ ነበር እንጂ ስለ እግዚአብሄር ደህንነት አልነበረም ፡፡
- የአምላክን ቃል ተጠራጠረ እግዚአብሄርንም አልፈራም ፡፡
- ስለ ራሱ ድርጊት ከወጣትነቱ በኃይል የተከላከለ ነበር ፡፡
1-ነገስት (18፡ 21-29)፡ኃይሉን ያሳየናል ፡፡ ኤልያስ ህዝቡን በእግዚአብሄር እና በአማልክቶች መካከል ፊት እና ኃላ እያላችሁ እስከመቼ ትቆያላችሁ በማለት ጠየቃቸው ፤ ህዝቡም ሊመልስሉት እንኳን አልቻሉም ( ራዕ 3፡ 15-16) ፡፡ ኤልያስ በጊዜዉ ሌሎች ነቢያቶች ቢኖሩም የእግዚአብሄር ነቢይ ብቸኛዉ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 22) ፤ ምናልባትም “ ከ 450 ከባዖል ነቢያት ጋር ብቻዉን በመቆም ለመጋፈጥ ያተኮረ ነበር “ ፤ በቁጥር 23-25 ኤልያስ የባዖልን ነቢያቶች በሚሰዋዉ በሬ ላይ ወርዶ በእሳት ሲመልስ የሚታየው የሁሉ በላይ ይሆናል በማለት ፈተናቸው (መዝ 71፡ 18፣ 147፡ 4-5፣ ኤር 10፡ 12-13) ፡፡ የባዖል ነቢያቶች ኤልያስ የነገራቸውን መስዋዕቱን በማዘጋጀት የባዖል አምላካቸዉ ወደ ታች እንዲወርድ ለስዓታት በመጥራት አደረጉ (ቁጥር 26) ፤ ቀትርም ሲሆን ኤልያስ በድርጊታቸዉ በማሾፍ በደንብ እንዲያደርጉት አደረጋቸው (ቁጥር 27-29) ፤ ማንም አማላክት አልመለሰም ፡፡
1-ነገስት (18፡ 30-39)፡ ኤልያስ ህዝቡን በፊቱ በመሳብ ጠፍቶ የነበረዉን የእግዚአብሄርን መሰዊያ እንደ ገና በመስራት አስራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ አራት ማድጋ ዉሃ የሚይዝም ጉድጓድ በዙሪያዉ አደገ (ቁጥር 30-32) ፤ ቀጥሎም ኤልያስ መስዋዕቱን በማዘጋጀት ከዚያም በሚነደዉ እንጨት ላይ እና በመስዋዕቱ ላይ አራቱን ማድጋ ዉሃ እንዲያፈሱት ጠራቸው (ቁጥር 33) ፤ ኤልያስ ይህን ሁለት ጊዜ ደጋግመዉ እንዲያደርጉት አዘዛቸው (ቁጥር 34) ጉድጓዱንም በዉሃ ሞሉት (ቁጥር 35) ፡፡ ኤልያስ የማታዉን መስዋዕት ማቅረብ በመጀመር ለእስራኤል እግዚአብሄር የሰጠዉን ተስፋ በመጥቀስ የአብርሃምን፣ የይስሐቅን እና የያዕቆብን አምላክ ጠራ (ቁጥር 36) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የኤልያስን ፀሎት ወደ ሁለት ክፍል ከፈለው (ቁጥር 37)፡ “ መጀመሪያ ብቻዉን የሚኖር አምላክ እንደ ሆነ በግልፅ ለህዝቡ እንዲገለጥ ፈለገ ፤ ሁለተኛ ለእግዚአብሄር ህዝብ ሙሉ መነቃቃት እንዲሆን ፀለዬ “ ፤ የእግዚአብሄር እሳት በመዉረድ እንጨቱን፣ ድንጋዩን፣ አፈሩን እና በጉድጓድ የነበረዉን ዉሃ በላች (ቁጥር 38) ፡፡ የሚመለከተው ህዝብ ኃይሉ ከአምላካቸዉ ከእግዚአብሄር እንደ መጣ አወቁ (ቁጥር 39) ፡፡
1-ነገስት (18፡ 40-46)፡ፀሎታችንን ይመልሳል ፡፡ ኤልያስ የእስራኤልን ህዝብ የባዖልን ነቢያት እንዲያርዱ ነገራቸው (ቁጥር 40) ከዚያም አክዓብን ዝናቡ ስለሚዘንብ ሄዶ እንዲበላ እና እንዲጠጣ ነገረው (ቁጥር 41) ፡፡ አክዓብ እየበላ ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ አናት ላይ በመሄድ በፀሎት ተደፋ (ቁጥር 42) ፤ ከዚያም ኤልያስ አገልጋዮቹን ዝናቡ መንገድ ላይ እንደ ነበር ወደ ባህሩ እንዲመለከቱ ሰባት ጊዜ ነገራቸው (ቁጥር 43-44) ፡፡ ሰባተኛዉ ጊዜ ላይ አገልጋዩ በሰማዩ ላይ ትንሽዬ ዳመና አየ ኤልያስም አገልጋዩን አካዓብን ሰረገላዉን በመጫን ዝናቡ ሳይመጣበት ተራራዉን እንዲወርድ እንዲነግረዉ ነገረው ፤ አክዓብ በዝናቡ ተራራዉን መዉረድ እንደ ጀመረ ወደ ኢይዝራኤል እንዲቀድመዉ የእግዚአብሄር ኃይል ኤልያስ ላይ ነበር ፤ ከአክዓብ ፊትም 13 ማይል ወደ ኢይዝራኤል ሮጠ (ቁጥር 45-46) ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር እያንዳንዳችን ደፋሮች እንድንሆን ይፈልጋል ፤ “ዝናብ እንዲዘንብ “ እንድንፀልይ ይፈልጋል ፡፡ የዚህ አይነት ፀሎት ለመፀለይ በቂ እምነት እና ጀግንነት አላችሁ (ያዕ 5፡ 16-18) ? እንደ ኤልያስ መፀለይ እንችላለን እግዚአብሄር ለመመለስ ይፈልጋል ፡፡ ያን ታምናላችሁ ? ይህን በምታምኑ ጊዜ በእዉነቱ መነቃቃት መምጣት ይችላል ፡፡
Walter C. Kaiser, Jr., Revive Us Again, rev. ed. (Geanies House Fearn, Tain Ross–shire IV20 1TW, Scotland, UK: Christian Focus Publications, 2013), pp. 77–87.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 1 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 454
Nelson’s Commentary, p. 454.
ጥያቄዎች
-
ከእርሱ ቃል ዉጪ ጠብታ ወይም ዝናብ እንደ ማይኖር በተናገረ ጊዜ በ 1ነገ (17፡ 1) ኤልያስ ወደ ታሪኩ ገባ ፤ ወደ ፊት ይህን አይነት ተመሳሳይ ኃይል የሚኖረዉ ማነው (ራዕ 11፡ 6) ? ያዕ (5፡ 17) ኤልያስን ምን አይነት ሰዉ ነበር የሚለው ? ይህ ጥቅስ እኛን እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያዬን እንዴት በራስ መተማመናችንን ይደግፋል ? (ያዕ 5፡ 16)
-
እግዚአብሄር ኤልያስን በዚያ ባለች አንዲት መበለት እንድትመግበው ወደ ሰራፕታ እንዲሄድ አዘዘዉ ፤ በሉቃ (4፡ 24-26) ኤሊያስ በዚያ የተላከ እንዲሆን ኢየሱስ ምን ምክንያት ሰጠ ?
-
ኤሊያስ መበለቲቱን ባገኛት ጊዜ እርሷ እና ልጇ በቅርብ እንደ ሚሞቱ ለምን ጠበቀች (1ነገ 17፡ 12) ? ከእግዚአብሄር ተዓምራዊ ስጦታን አየች ፤ በ 1ነገ (17፡ 24) “ የእግዚአብሄር ሰዉ እንደ ሆንህ የእግዚአብሄርም ቃል በአፍህ እዉነት እንደ ሆነ አሁን አወቅሁ “ ለምን አለች ?
-
በ 1ነገ (18፡ 12) አብድዩ የተናገረዉ(ያወጣው) ፍራት የእግዚአብሄር መንፈስ “ ጥሩ(አደገኛ) “ ያልሆነን ነገር እንደ ሚያደርግ የተመሰረተ ይመስላል ፤ መንፈስ ቅዱስ ስራ እንድትሰሩ ሲያደርግ “ ጥሩ (አደገኛ) “ የሆነ ስሜት ተሰምቷችኋል ያውቃል ?
-
የባዖል ነቢያቶች እና ኤልያስ እንዲመልሱላቸዉ ለአምላኮቻቸዉ መፀለይ ጀመሩ ( 1ነገ 18፡ 26፣ 37) ፤ የባዖል ነቢያቶች ለመልስ ምን ያክል ጊዜ ጠበቁ ? እግዚአብሄር በእሳት በመለሰ ጊዜ የህዝቡ ፈጣን ምላሽ ምን ነበር ?
-
በ 1ነገስት (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 18:38–39
“Then Yahweh’s fire fell and consumed the burnt offering, the wood, the stones, and the dust, and it licked up the water that was in the trench. When all the people saw it, they fell facedown and said, ‘Yahweh, He is God! Yahweh, He is God!’”
በራቡ ጊዜ ሶስት አመትን ከተደበቀ በኋላ ለአካብ ይገለጥ ዘንድ እንድሁም እግዚአብሔር ዝናብን እንደሚልክ እንድናገር እግዚአብሔር ኤለያስን ላከው ፡፡ በንጉስ አካብና በእሰራኤል ሀዝብ ሁሉ ፊት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ዝናብን እንድልክ ወደ አብርሃም ወደ ይስሀቅ ወደ ያዕቆብ አምላክ በድፍረት ጸለየ ፡፡ መጀመሪያ ህዝቡ ዝናብን ይሰጥ ዘንድ ወደ በኣል ጸለዩ ነገር ግን በኣል አልመለሰም ፡፡ እግዚአብሔር ግን በኃይል መለሰ ፡፡ አምላክ መስዋዕቱን ትበላ ዘንድ እሳትን ላከ ፡፡ ህዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ “ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው አሉ ! እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው ! “ አሉ ፡፡ ከዚያም በኋላ ኤልያስ በእግዚአብሔር ፊት በጉልበቱ ሰገደ እግዚብሔርም በምድሪቱ ሁሉ ዝናብን በማድረግ መለሰ ! ከሶስት አመት በኋለም ዝናብ ሆነ ህዝቡም የአምላክን ኃያለ ስራ አዩ !
እግዚአብሔር ለእርሱ በጀግንነትና በድፍረት እንድትኖር ይነግርሃል ፡፡ እርሱ በራስህ ብርታት ሳይሆን በእርሱ ኃይል እንድትኖር ይፈልጋል ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ በመታመን ፡፡ ይህ በጸሎት ነው ሚጀመረው እግዚአብሔር በህይወትህ ኃይሉን እንድያሳይ በመጸለይ ነው ፡፡ ዛሬ በድፍረት የምትጸልየው ስለ ምንድን ነው ፡፡ እግዚአብሔርን መጠየቅ ትችላለህ ምክንያቱም እንደሚሰማህ ስለምታውቅ ፡፡ ደፋር ሁን ደግሞም እግዚአብሔር ጸሎትህን እንደሚሰማ እመን ፡፡ እግዚአብሔር ጸሎትህን በመለሰልህ ጊዜም እግዚአብሔር በህይወትህ የሰራውን ስራ ለሌሎች መስክር ! እንዳንተ አምላክ ያለ ሌላ አምላክ የለም ፡፡
“ የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች የሚቃጠለውን መስዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹነም አፈሩንም በላች በጉድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ ላሰች ፡፡ ህዝቡም ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው ፡- እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው ፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው ፡፡ “
- 1ኛ ነገሥት 18፡38-39
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 45፡5-6 –“ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለም በፀሀይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ፡፡ “
ሚክያስ 7፡7 –“ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ አምላኬም ይሰማኛል ፡፡ ”
1ኛ ዮሐንስ 5፡14-15 –“ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው እንደ ፈቃዱ እንዳች ብንለምን ይሰማናል ፡፡ የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።