Historical Books 1 Kings

Good or Evil in God's Sight

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 264 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሪቫይቫል ት/ቤት አላማዬ ወደ ቃሉ በጥልቅ እንድትገቡ ነው ፤ በምናጠናቸዉ በእነዚህ ታሪካዊ መፅሀፍቶች ዉስጥ በጣም ብዙ ትርጉም አለ ፡፡ ለእናንተ ቃሉን እንደ አዲስ ብራንድ በማንበብ ምን እንድትሰሙ እንደሚፈልግ እግዚአብሄር ጠይቁት ፤ ቃሉን በዉስጥም በዉጪም እንድናዉቀዉ እፈላጋለሁ ይህ ከሆነ የእግዚአብሄር ቃል ለሌሎች ለመናገር ትዘጋጃላችሁ ፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናቶች በሰለሞን ያለመታዘዝ ኃጢዓት ምክንያት የእስራኤል ህዝብ ወደ ሁለት መንግስት መከፈሉን አይተናል ፤ ይሁን እንጂ ስለ ዳዊት ኪዳን እነዚህ መንግስቶች ተመልሰዉ አንድ በመሆን በእስራኤል ዙፋን ላይ የዳዊት ቤት እንደ ሚነግስት እናውቃለን ፡፡ የእስራኤል መንግስት (የሰሜኑ ክፍል) ለ 250 አመታት የቆዩ 9 ስሮዉ መንግስትን አስተናግዷል ፤ የይሁዳ መንግስት (የደቡቡ ክፍል) የይሁዳን ነገድ የያዘው የዳዊት ቤት ለ350 አመት ቆዬ፡፡ 1ነገስት 15 ከ913 እስከ 885 ከክርስቶስ ልደት በፊት የይሁዳን እና የእስራኤልን የሁለቱንም ነገስታት ይሸፍናል ፤ የደቡቡ መንግስት የዳዊት ቤት ወደ አንድ ነገር ያመለክታል - ስለሚበልጠው ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡

በሀአይምሯችሁ የንጉሳዊ ዘርን ለመጠበቅ ከሰለሞን ሞት በኋላ በ 1ነገስት 15 ዉስጥ የእያንዳንዳቸዉ ነገስታት እነዚህ ነበሩ፡

ይሁዳ (ደቡባዊዉ መንግስት) እስራኤል (ሰሜናዊ መንግስት)

ሮብዓም (ክፉ ንጉስ) ኢዮሮበዓም (ክፉ ንጉስ)

አብያም(ክፉ ንጉስ) ናዳብ (ክፉ ንጉስ)

አሳ (መልካም ንጉስ) ባዖስ (ክፉ ንጉስ)

የደቡቡ መንግስት የዳዊትን የዘር መስመር እና የዳዊትን ኪዳን ጠበቀ ፡፡

ትምህርት

1-ነገስት (15፡ 1-8)፡ በንጉስ ኢዮሮብዓም 18 አመት በእስራኤል (በሰሜኑ መንግስት) አገዛዝ አብያም ሮብዓምን በመከተል የይሁዳ (የደቡብ መንግስት) ንጉስ በመሆን ሰዎስት አመት ገዛ (ቁጥር 1-2) ፡፡ የአብያ ስም የእብራዊ ቃል “ ለአባት “ የሚለው እና ብዙ ጊዜ ለከነዓናዊያን አምላክ የሚጠቅም “ ባህር “ ከሚለው ዕብራዊ ቃል ጋር የተዋሀደ ነበር ፤ ምናልባትም “ ይህ ስም ቀድሞ በይሁዳ አገዛዝ በንጉሳዊ ቤተሰብ በመምጣት ከነዓናዊያንን ተፅዕኖ ያንፀባርቃል “ ፡፡ አብያ አባቱ ዮሮብዓም አድርጎት የነበረውን ሁሉንም ኃጢዓት በማድረግ ቀጠለ እንጂ ዳዊት እንደ ነበረው ለእግዚአብሄር የተሰጠ አልነበረም (ቁጥር 3) ፤ ዮሮብዓም ቢያንስ 18 ሚስቶች ነበሩት ከዳዊት ጋር በነበረዉ የእግዚአብሄር ኪዳን ምክንያት ኢየሩሳሌምን ለመመስረት የዳዊትን ልጅ ተጠቀመ (ቁጥር 4) ፡፡ በኬጢያዊዉ ዖሪዮ ካደረገው በስተቀር ዳዊት ለእግዚአብሄር ታዛዥ ነበር (ቁጥር 5) ፤ ዮሮብዓም እና ኢዮሮብዓም በዮሮብዓም ህይወት ዉስጥ በጦርነት ላይ ነበሩ (ቁጥር 6) ፡፡ አብያም እና ኢዮሮብዓም ጦርነት ላይ ነበሩ ነገር ግን አብያ እግዚአብሄርን በመታመን አሸናፊ ነበር (2 ዜና 13፡ 2-20) ፤ ለአብያ የዜና እረፍት በቁጥር 7-8 ስርዓቱን ተመስግቦ የተሰጠ ነው ፡፡

1-ነገስት (15፡ 9-15)፡ አሳ አብያን በመከተል 41 አመታት ገዛ (ቁጥር 9-10) ፤ አሳ ጥሩ አገዛዝ ነበረው በእግዚአብሄር ፊት መልካም የሆነዉንም አደረገ (ቁጥር 11) ፡፡ አሳ ግብረ ሰዶማዊያንንም አስወገደ፣ አባቱ አድርጓቸው የነበረዉን ጣኦቶች አንቀሳቀሰ (አስወጣ)፣ የአሼርም ፀያፍ ስዕል አግኝቶባት ስለ ነበረም እናቱን መዓክን እቴጌ እንዳትሆን ሻራት ፡፡ ንጉስ አሳ የእናቱን የብልግና ስዕል በመወርወር አቃጠለው (ቁጥር 12-13) ፤ ማክአርቱር እንደ እቴጌ እናቱን የብልግና ስዕል ሰርታ እንደ ነበረች፣ “ አስከፊ፣ አስቀያሚ ነገር “ የነበረ ጣዖት ምናልባትም “ የወሲባዊ ትርጉም “ የነበረዉ ነገር ፈጥራ እንደ ነበረች “ ብልሹ “ ይገልፃታል ፡፡ አሳ የማምለኪያ ኮረብታዎችን አላጠፋም (ቁጥር 14) ምክንያቱም ለእግዚአብሄር መስገጃነት ሊጠቀምባቸዉ ስለሚችል ልቡ በጠቅላላ ህይወቱ ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ የተሰጠ ነበር ( 1ነገ 8፡ 61፣ 2ዜና 14፡ 4፣ ማቴ 22፡ 37-38) ፤ በተጨማሪም አሳ ነገሮችን ወደ እግዚአብሄር እሱና አባቱ ለእግዚአብሄር ወደ ለዩት ቤተ መቅደስ አመጣ (ቁጥር 16) ፡፡

1-ነገስት (15፡ 16-22)፡ እንደ መልካም ንጉስ አሳ ያለማቋረጥ ከእስራኤል ንጉስ ከባአስ ጋር ሰልፍ ነበር (ቁጥር 16) ፤ በሚያናድድ ሁኔታ ከ19 የይሁዳና የእስራኤል ነገስታቶች ዉስጥ ስምንቶቹ ብቻ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ነገር አደረጉ ፡፡ አሳ በአሁኑም ጊዜ ለእኛ አስፈላጊ ነው ፤ ባአስ ከአሳ ጋር መገኛኘቱን ለመቁረጥ ራማን ሰራ (ቁጥር 17) ፤ አሳ ከባአስ ረዳቶቹ ከአንዱ ጋር ስምምነት በማድረግ የእስራኤልን ከተሞች አጠቃ ፤ በመጨረሻም ባአስ ራማን መገነባት ትቶ ቤቱ ተመለሰ ፡፡ ንጉስ አሳ በይሁዳ ያለዉን ሁሉንም ሰዉ የራማን ድንጋዮች እና ጣዉላዎች እንዲያስወግዱ አዘዛቸው በዚህም ደግሞ መገንባት አይችልም ፡፡

መደምደሚያ

አሳ በራሱ ቤተሰብ ህይወት ዉስጥ የነበረዉን ኃጢዓት በማወቅ እናቱን ከቤተ መንግስቱ አስወጣት ፤ ጣዖቶችን እና ቅዱስ ላይሆኑ ነገሮችን ከምድሪቱ አስወገደ ፡፡ ለእኛ የምንመለከታቸዉ ጥያቄዎች፡

  1. ከኑሮአችን ልናስወግዳቸዉ የሚያስፈልጉ ነገሮች ምንድናቸው ?
  2. ያለዉ ቅዱስ ያልሆነዉ ነገር ምንድን ነው ?
  3. ምን ጣዖቶችን ፈጥረናል ወይስ መጀመሪያ በሚያስፈልግ ስፍራ ይዘነዋል ?

ሌላ ሰዉ እንዲባረክ ከህይወታችሁ ማስወገድ የሚያስፈልጋችሁ ነገር ምንድን ነው ? አሳ ምናልባትም የእናቱን ክፉ

ነገር በማስወገድ ቤተሰቡ ተሰናክሏል ነገር ግን ነገሩ እንዲቀመጥ ስላልፈቀደ ከእግዚአብሄር በረከት ሊሆንለት ቻለ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 415.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 1 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 449

  3. MacArthur, p. 415.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ነገ (15፡ 3-4) ክፉ ነገስታት እንዲገዙ እግዚአብሄር ለምን እንደ ፈቀደ ምን ታስባላችሁ ? (2 ሳሙ 7፡ 8-9)
  2. በ 1ነገ (15፡ 28-30) ባኦስ ነገሰ የኢዮሮብዓም ዘር ሁሉንም ንጉስ አረደ ፤ እግዚአብሄር ስለ ነገረው አደረገው ወይስ እግዚአብሄር ቃል ኪዳኑን ለመፈፀም እግዚአብሄር አንድ ክፉ ንጉስ ተጠቀመ ? ለምን እንደዛ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  3. አክዓብ ንጉስ ሆነ ከእርሱ በፊት ማንም ንጉስ ካደረገዉ በላይ በእግዚአብሄርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ ፤ አክዓብ በምን መንገድ የከፋ ነበር ?
  4. በ 1ነገስት (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 15:11

“Asa did what was right in the LORD’s eyes, as his ancestor David had done.”

በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን ካደረጉ ከብዙ ነገሥታት መንገስ በኋላ ነጉሥ አሳ ነገሠ ፡፡ ንጉሥ አሳም አርባ አንድ አመት ነገሠ በእግዚአብሔር ፊትም ቅን የሆናውን አደረገ ፡፡ ሶዶማውያንንም አስወገደ ፣ ጣዖታትን ሁሉ አራቀ እንድሁም የዘር ኃጢአትን ጭምር እናቱን እቴጌ እንዳትሆን በመሻር በተጨማሪም ጣዖቱዋን ሰብሮ በማቃጠል ተቃውሟል ፡፡ ባጠቃላይ አሳ እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኘውን ነገር ሁሉ ከኮረብታ መስገጃዎች በቀር አስወገደ ፡፡ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ነበረ ፡፡

ንጉሥ አሳ ወደ እናቱ ቤት ሄዶ የጣዖት ምስልን አገኘ ፡፡ የነገሥታት ንጉሥ የሆነው ወደ ቤትህ መጥቶ መወገድ ያለበትን ነገር ያገኝ ይሆን ? በህይወትህ ጣዖት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ወይም ተግባሮችን አስብ ፡- የቴሌቪዥን ፕሮግራም ፣ ለረጅም ሰዓት ጌም መጫወት ፣ በስልክ ላይ ያሉ መተግበሪያዎች ወይም በልብስ ሳጥን ውስጥ ያሉ ልብሶች ፡፡ ምናልባት አንተም የምትሳተፍበት ተግባር ይኖር ይሆናል ምክንያቱም ደግሞ የቤተሰብህ የዘር ሀረግ ሁሉ ስለተሳተፉበት ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ እንደሆነ ታውቃለህ ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን ጠይቅ “ልቤ ለአንተ ፍጹም ይሆን ዘንድ በቤተ ላስወግደው የሚገባ ነገር አለ ይሆን ? “ ከዚያም በመታዘዝ ምንም ይሁን እግዚአብሔር የሚገልጥልህን ነገር አስወግድ ፡፡

“ አሳ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ ፡፡ “

  • 1ኛ ነገሥት 15፡11

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 6፡21 –“ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና ፡፡ “

ሮሜ 6፡1-2 –“ እንግዲህ ምን እንላለን ? ጸጋ እንድበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን ? አይደለም ፡፡ ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን ? “

1ኛ ቆሮንቶስ 8፡5-6 –“ መቼም ብዙ አመልክትና ብዙ ጌቶች አሉ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ ለአኛስ ነገረ ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንደ አምላክ አብ አለን ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በአርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን ፡፡ “