The Deception of the Man of God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ወደ 1 ነገስት 13-14 ጥናት ስንጓዝ ወደ መዘበራረቅ እንጓዛለን ፤ ይህ ጥናት በክፉ እና በመግደል ከሆነዉ ከመሳፍንት ትምህርት ጋር በትንሹ ይመሳሰላል ፡፡ በ 1ነገስት 11-12 የሰለሞንን መሞት እና የመንግስቱ ወደ ሁለት አዲስ መንግስት መከፋፈልን አይተናል፡ ኢዮሮብዓብ በሰሙኑ በመንግስት በእስራኤል አስሩ ነገድ ላይ እንደ ንጉስ እና የሰለሞን ልጅ ዮሮብዓም በደቡቡ መንግስት በይሁዳ ነገድ ላይ እንደ ንጉስ በመሆን ፡፡ ኢዮሮብዓም የሰለሞን አገልጋይ ነበር ነገር ግን ነቢይ ሰለሞን በሞተ ጊዜ በአስሩ ነገዶች ላይ ንጉስ እንደ ሚሆን ነገረው ፡፡ 1 ነገስት 11 በጠቅላላ ስለ ሰለሞን ችግር እና ኃጢዓት ሲሆን 1 ነገስት 13 ስለ ኢዮሮብዓም ችግር እና ኃጢዓት ነው ፡፡
ትምህርት
ዋይርስቤ ምዕራፍ 13 ወደ እነዚህ ክፍሎች ይከፍላል፡
1-ነገስት (13፡ 1-2)፡መልዕክቱ ፡፡ አንድ የእግዚአብሄር ሰው በመገለጥ ከእግዚአብሄር በመስማት ኢዮሮብዓም መሰዊያዉ ላይ ለማቃል እየተዘጋጀ በነበረበት ጊዜ በኢዮሮብዓም መልዕክት ወደ ቤቴል ይሄዳል (ቁጥር 1) ፤ ኢዮሮብዓም በንግስና ስፍራ እና የክህነትን ተግባርወስዷል - ሁለቱም መጥፎ ናቸው ፡፡ መሲሁ እስኪመጣ ድረስ ንጉስ በፍፁም በክህነት ተግባር ላይ የሚሳተፍ አልነበረም (2ዜና 26፡ 16-23) ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዉ ከዳዊት ቤት የሆነዉ ኢዮስያስ ንጉስ እንደሚሆን እና በመንግስቱም በክፉዉ እንደሚቀጥል ተናገረ (ቁጥር 2) ፡፡ ኮረብታዎችን በቃጠለ ጊዜ፣ ተክክል ያልሆኑትን ካህናቶች ባረደ ጊዜ፣ አሼር አምድን በማቃጠል መሰዊያን ባጠፋ ጊዜ እና መሰዊያዉን ያረከሱትን የሙታንን አጥንት ባቃጠለ ጊዜ ከ300 አመታት በኃላ የኢዮስያስ አገዝ ዘመን ይመጣል ፡፡ ቤቴል ብዙዎች ነቢይ ለመሆን ለመማር ይመጡበት የነበረ ማህበረሰብ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዉ ለኢዮሮብዓም መሰዊያዉ የጠፋ እንደ ሚሆን እና አመዱ እንደ ሚፈስስ በመግለፅ የእግዚአብሄርን መልዕክት ጨረሰ (ቁጥር 3) ፡፡
1-ነገስት (13፡ 4-6)፡ተዓምራቱ ፡፡ ንጉስ ኢዮሮብዓም እጆቹን በመዘርጋት ወደ እግዚአብሄር ሰዉ በማመልከት ሰዉዬዉን እንዲያስሩት ለጠባቂዎቹ ነገራቸው ፤ እንደ ተናገረ እጁ ደርቃ ቀረች ወደ ደህናም አልተመለሰችም (ቁጥር 4) ፤ የእግዚአብሄርም ሰዉ ንግግር ወደ እዉነት መጣ - መሰዊያዉ ተሰነጠቀ አመዱም ከመሰዊያዉ ላይ ፈሰሰ (ቁጥር 5) ፡፡ ንጉሱም ሰዉዬዉን እጁ እንድትመለስ ስለ እግዚአብሄርን ቸርነት እንዲፀልይለት ጠየቀው ፤ ሰዉየየው አደረገ የንጉሱም እጅ ሙሉ በሙሉ ዳነች (ተመለሰች) (ቁጥር 6) ፡፡
1-ነገስት (13፡ 7-10)፡ስልታዊዉ እርምጃው ፡፡ ንጉሱ የእግዚአብሄርን ሰዉ ወደ ቤቱ እንዲመጣ ጋበዘው ስለዚህም የሚታደስ እና የሚሸለም ሊሆን ይችላል (ቁጥር 7) ፤ ዋይርስቤ ኢዮሮብዓም “ ጎበዝ ሰዉ እንደ ነበር እና ለመመገብ እቤቱ በመጋበዝ ነቢዩን በመጋበዝ ሊያጠምደዉ እንደ ሞከረ “ ይናገራል ፡፡ ነቢዩም የኢዮሮብዓም ቤት ግማሹን ቢቀበልም እንኳን እንደ ማይበላና እንደ ማይጠጣ መለሰለት ምክንያቱም እግዚአብሄር ይህን እንዳያደርግ ነግሮት ስለ ነበር (ቁጥር 8-9) ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዉ ስለ ኢዮሮብዓም ኃጢዓት የእግዚአብሄርን መልዕክት ከተናሀረ በኋላ ከኢዮሮብዓም ጋር በልቶ ቢሆን ድርጊቱ “ የምስክርነቱ እና የአገልግሎቱ ዉጤታማነት ይጠፋል “ ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዉ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ በሙሉ ተከተለ መጥቶበት ከነበረዉ መንገድ በተለየ መንገድ ተመለሰ (ቁጥር 10) ፡፡
1-ነገስት (13፡ 11-34)፡ስህተቱ ፡፡ በቤቴል ኢዮሮብዓም ህዝቡን ጣዖቶችን ወደ ማምለክ እየመራ ነበር ፤ የእግዚአብሄር ነገር ሆኖበት በማያውቀዉ ምድር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ይኖር ነበር (ቁጥር 11) ፡፡ የሽማግሌዉ ነቢይ ልጆች በቤቴል የእግዚአብሄር ሰዉ የእግዚአብሄርን መልዕክት በተናገረ ጊዜ ተፈጥሮ የነበረውን ነገሩት (ቁጥር 11) ፤ ነቢዩም በየትኛዉ መንገድ እንደ ሄደ ጠየቃቸው ልጆቹም ነገሩት (ቁጥር 12) ፤ ልጆቹንም አህያዉን ለእርሱ እንዲያዘጋጁለት ነገራቸው ከእግዚአብሄርም ሰዉ ኃላ ተከተለ(ሄደ) (ቁጥር 13) ፡፡ ነቢዩም የእግዚአብሄርን ሰዉ ከአንድ አድባር ዛፍ ስር አገኘው ፤ ነቢዩም የእግዚአብሄር ሰዉ እንደ ነበር በመጠየቅ ለመመገብ ወደ ቤቱ ከእርሱ ጋር እንዲሄድ ጋበዘው (ቁጥር 14-15) ፤ የእግዚአብሄር ሰዉም እግዚአብሄር በዚያ ምግብ እንዳይበላ እና እንዳይጠጣ እንዲሁም በተመሳሳይ መንገድ እንዳይመለስ እንደ ነገረው ገለፀለት ቁጥር 16-17) ፤ ነቢዩም የእግዚአብሄርን ሰዉ በመልዓክት ወደ ቤት እንዲመለስ እንደ ተነገረው ነገረው (ቁጥር 18) ፡፡ ሽማግሌዉ ነቢይ የእግዚአብሄርን ሰዉ ዋሸዉ የእግዚአብሄርም ሰዉ የሽማግሌዉን ማጭበርበር ለመለየት ወደቀ (ቁጥር 19) ፡፡ ሽማግሌዉ ነቢይ ለምን ዋሸ ? ማክአርቱር “ ምናልባትም በቤቴል የራሱ ልጆች አምላኪዎች ወይም ካህናቶች ስለነበሩ ይህ ሰዉዬ በንጉሱ ሞገስ ለማግኘት የእግዚአብሄር ሰዉ ለራሱ ፍላጎት ከእግዚአብሄር ሰምቶ እንደ ነበር በማስመሰል በማሳየትእንደ ፈለገ ይናገራል “ (ኤር 23፡ 16፣ ሕዝ 13፡ 2፣ 7) ፡፡
እየተመጉቡ ሳለ የእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄርን ሰዉ ዋሽቶት ለነበረዉ ነቢይ መጣ ፤ ነቢዩ ለእግዚአብሄር ሰው ለእርሱ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ባለመታዘዙ አጥንቶቹ አያቶቹ መቃብር ጋር እንደማይደርስ ነገረው (ቁጥር 20-21) ፡፡ እስራኤላዊያን ሙታናቸዉን ከአያቶቻቸዉ መቃብር ጋር በተለመደ በተመሳሳይ የቀብር ስፍራ ይቀብራሉ (መሳ 8፡ 32፣ 2 ሳሙ 2፡ 32) ፤ ይህ ክብር ማጣትን ያመለክታል ፡፡ ሽማግሌዉ ነቢይ አህያዉን ለእግዚአብሄር ሰዉ አዘጋጀ (ቁጥር 23) ፤ በቤቱ መንገድላይ የእግዚአብሄር ሰዉ በአንድ አንበሳ በመጠቃት መንገዱ ላይ ተገደለ ፤ አህያዋ እና አንበሳዉ ከሬሳዉ አጠገብ ቆመዉ ነበር (ቁጥር 24) ፤ ለሰዉዬዉ ሬሳ ይህ የአንበሳዉ እና የአህያይቱ ተፈጥሮአዊ ምላሽ አልነበረም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አንበሳዉ ከእግዚአብሄር ሰዉ እና ከአህያይቱ አጠገብ የቆመበት መንገድ የሚያሳየዉ አንበሳዉ የእግዚአብሄር አስፈሳሚ እንጂ ለምግብ ብሎ እንዳልገደለው ይገልፃል “ ፤ በሬሳዉ አጠገብ የሚያልፉ ሰዎች ወደ ቤቴል ተመልሰዉ በመሄድ አይተዉ የነበረዉን ተናገሩ (ቁጥር 25) ፡፡ ሽማግሌዉ ነቢይ በእግዚአብሄር ሰዉ ላይ የእግዚአብሄር ቅጣት እንደ ደረሰበት ባወቀ ጊዜ በመሄድ የሰዉዬዉን ሬሳ በመመለስ በሞቱ አዘነ በራሱ ቤተሰቦችም መቃብር ቀበረው (ቁጥር 26-30) ፤ ሽማግሌዉም ነቢይ ልጆቹን የእግዚአብሄርን መልዕክት ተሸክሞ በነበረው ከእግዚአብሄር ሰዉ አጥንት አጠገብ አካሉን እንዲቀብሩት አዘዛቸው (ቁጥር 31-32) ፡፡ ከዚህ በኋላም ኢዮሮብዓም ንስሀ አልገባም ወይም የእግዚአብሄር ቃል አልሰማም ፤ ከኃጢዓቱ ስላልተመለሰ ቤቱ ይጠፋል (ቁጥር 33-34) ፡፡
መደምደሚያ
በኑሮአችን የእግዚአብሄር ድምፅ መታመ እንጂ “ ስለ እርሱ ሌሎች የሚነግሩንን አይደለም “ ፤ እግዚአብሄር የመጀመሪያ ምንጫችን መሆን አለበት ፤ ሁሉም ነገር በዚያ ዉስጥ መጣራት አለበት (1ዮሐ 2፡ 26-27) ፡፡ የእግዚአብሄር ድምፅ መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን ?
ገርጅ ሲማስ የእግዚአብሄርን ድምፅ ለማረጋገጥ www.gregsimas.org ላይ 10 መንገድ ያቀርባል፡
- ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል ? (መዝ 119፡ 105፣ 2ጢሞ 3፡ 16)
- በደንብ ክርስቶስን እንድመስል ያደርጋል ? (ሮሜ 8፡ 29)
- ባለቤቴ እና ቤተሰቦቹ ያፀድቁታል ? (ምሳ 11፡ 14፣ አሞ 3፡ 3፣ ኤፌ 5፡ 21)
- በመንፈሳዊ ነገር የበሰሉ ሰዎች ያረጋግጡታል ? (ምሳ 11፡ 14፣ 15፡ 22፣ ኤፌ 3፡ 10)
- በእግዚአብሄር እንዳደረገኝ ፅኑ ያደርጋል ? (ሮሜ 12፡ 6፣ 1ጴጥ 4፡ 10)
- በእኔ ላይ ከተነገረዉ ትንቢታዊ ቃል ጋር ይገኛኛል ? (1ጢሞ 4፡ 14)
- ያንቀሳቅሰኛል ? (ሮሜ 12፡ 11)
- ይዘረጋኛልን ? (2ቆሮ 12፡ 9፣ ፊል 3፡ 13-14)
- እምነት ይፈልጋል ? (ሮሜ 10፡ 17፣ 2ቆሮ 5፡ 7፣ ዕብ 11፡ 6)
- በነገሩ ሰላም አለኝ ? (ፊል 4፡ 7)
በእነዚህ ዝርዝሮች በኩል ከተጓዛችሁ በህይወታችሁ የእግዚአብሄር ድምፅ መሆኑን በማረጋገጥ ዉሳኔ ለማድረግ አምስት ወር አትዉሰዱ ፡፡ ይህ ሂደታችሁን ለማዘግየት አይደለምየሰማችሁት ከእግዚአብሄር መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ ፤ የእግዚአብሄር ሰዉ በግልፅ ከእግዚአብሄር ሰምቷል ምን እንደ ሚያደርግም ቢያዉቅም ላታለለዉ ሽማግሌ ነቢይ በመሰጠቱ ትዕዛዝ ጣሰ ፡፡ የሰማችሁትን ነገር ተከተሉ(ያዙ) እንጂ ሌላ አትጨምሩ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), pp. 456–457.
Wiersbe, p. 457.
Wiersbe, p. 457.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 414.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 1 Kings (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 447.
ጥያቄዎች
-
በ 1ነገ (13፡ 18) ሽማግሌዉ ነቢይ የእግዚአብሄርን ሰዉ ለምን እንደ ዋሸዉ ምን ታስባላችሁ ? በእናንተ አስተያየት የእግዚአብሄር ሰዉ ምን ማድረግ አለበት ? ( 1ዮሐ 4፡ 1)
-
አንበሳዉ የእግዚአብሄርን ሰዉ ገድሎ ሳይበላ ለምን እንደ ተወዉ ምን ታስባላችሁ ? ይህ እንስሳቶች የእግዚአብሄር ቃል እንደ ሚታዘዙ ምሳሌ ነው ? (መዝ 148፡ 7)
-
በ 1ነገ (13፡ 33) ኢዮሮብዓም ከሁሉም ሰዎች ቡድን ካህናትን አደረገ ፤ ይህ ለምን ነበር ኃጢዓት የሆነው (ዘኁ 8፡ 16-18) ? ለእነዚህ ኃጢዓቶች የሚከፍለዉ ክፍያ ምን ነበር ? ( 1 ነገስት 14)
-
በ 1ነገስት (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 13:16–17
“But he answered, ‘I cannot go back with you, eat bread, or drink water with you in this place, for a message came to me by the word of the LORD: You must not eat bread or drink water there or go back by the way you came.’”
ኢዮርብዓም ንጉስ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው መገለጥን ከእግዚአብሔር ይዞ ወደ ኢዮርብዓም መጣ ፡፡ ቃሉም በሆነ ጊዜ ንጉስ ኢዮርብዓም ወደ ቤቱ ጋበዘው እረፍትንና በረከትንም አቀረበለት ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እንጀራም እንዳይበላ ውኃም እንዳይጠጣ ነገሮት ነበርና እምቢ አለ ፡፡ በዚህ ረገድ የእግዚአብሔር ሰው ለእግዚአብሔር ልዩ ምሪት ታዛዥ ነበረ በአካሄዱም ጽኑ ነበረ ፡፡ ነገር ግን በኋላ ሸማግሌው ነብይ በተከተለውና ከእርሱም ጋር ተመልሶ ምግብ እንድበላ ውኃም እንድጠጣ በጠየቀው ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው ተመለሰ ፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምጽ ሳይታዘዝ ቀረ ስለዚህም ከባድ ቅጣትን ተቀበለ ፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ስትራመድ በህይወትህ ላይ ድምጹን ልታምን ይገባል ልትጣበቅበትም እንድሁ ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ “ በጎቼ ይሰሙኛል ድምጼንም ያውቁታል “ ፡፡ ሌሎች ይናገሩህ ይሆናል ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሰማኸውን ካወክ ሌሎች በቀላሉ ሊያሳምኑህ አይችሉም ፡፡ የሆነ ሰው የሆነ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ወይም ላንተ መልእክት ቢኖረው አድምጠው ፡፡ ነገር ግን ከማድረግህ ወይም ከመመለስህም በፊት ጊዜ ውሰድ እግዚአብሔርን በቃሉ ፣ በሌሎች ፣ እንድሁም ሰላምን በመስጠት ያረጋግጥልህ ዘንድ ጠይቅ ፡፡ እግዚአብሔር ከነገረህ ጋር ተቃራኒ ከሆነ እንዳታመቻምች ወይም እንድያሳምንህ እንዳትፈቅድ ፡፡ አግዚአብሔር በህይወትህ ለድምጹ ያለህን ታዛዥነት ያከብራል ፡፡
“ እርሱም ከአንተ ጋር እመለስና እገባ ዘነድ አይቻለኝም በዚህም ሰፍራ ከአንተ ጋር እንጀራ አልበላም ውኃም አለጠጣም በዚያ እንጀራ አትብላ ውኃም አትጠጣ በመጣህበትም መንገድ አትመለስ በሚል በእግዚአብሔር ቃል ተብሎልኛልና አለ ፡፡ “
- 1ኛ ነገሥት 13፡16-17
ተጨማሪ ጥቀስ
- ኢሳይያስ 30፡21 –“ ወደ ቀኝም ወደ ገራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ መነገዱ የህች ናት በእርሰዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ ፡፡ “
- ዮሐንስ 10፡27 –“ በጎቼ ድመጼን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል ፡፡ “
- ገላትያ 5፡7-8 – “ በመልካም ትሮጡ ነበር ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ ? ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።