Historical Books 1 Kings

Solomon Sinned Against God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 262 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ሰለሞን እንዴት በሀብት እና በጥበብ ባለፀጋ እንደ ሆነ ተመልክተናል ፤ ንግስት ሳባ በአካል ጥበቡን ባየች ጊዜ ትንፋሽ ያጠራት ቢያደርጋትም በ 1ነገስት 11 ብስጭት ወደ ደማቅ አገዛዙ መቅረቡን በመግለፁ ሁሉም ተቀይሯል ፡፡ የሰለሞን ህይወት ብዙ ሚስቶች በመኖሩ በኃጢዓት ተወሰደ ፤ ተቃርኖ ገጠመው በፊት በህይወቱ ችግር ያለነበረዉ ጉዳይ ቆይቶ ግን ችግር ሆነ ፡፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 11 በእነዚህ ክፍል ዘርዝሮታል፡ “ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ቃል ጣሰ (ቁጥር 1-8)፣ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ ገፋ(አልተቀበለም) (ቁጥር 9-13)፣ ሰለሞን የእግዚአብሄር ቅጣትን ተቋቋመ (ቁጥር 14-25)፣ ሰለሞን የእግዚአብሄርን አገልጋዮች ተቃወመ (ቁጥር 26-43) “ ፡፡ ዛሬ ከሰለሞን የሚበልጠዉ ላይ መመልከታችንን እንቀጥላለን ፡፡

ትምህርት

1-ነገስት (11፡ 1-8)፡ሰለሞን የእግዚአብሄርን ቃል ጣሰ ፡፡ ሰለሞን ብዙ የሌላ አገር ሴቶችን ወደደ በእግዚአብሄርም ትዕዛዝ ላይ በተቃራኒዉ እየሄደ እንደ ነበር ያውቃል ( ዘዳ 7፡ 1-3) ፤ እነዚህን ሴቶች መዉደዱ ልቡን ከእግዚአብሄር አዞረው በዘዳ (17፡ 17) እግዚአብሄር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል (ምሳ 19፡ 3) ፡፡ ከብዙ ሚስቶቹ በተጨማሪም ሰለሞን ሌሎች አማልክቶችን የሚያመልኩ አገባ ፤ የማያምኑትን ስለ አለማግባት መፅሀፍት ግልፅ ያደርጋል - በማያምኑ ራሳችሁን አታስጠምዱ ፡፡ ሰለሞን እስራኤላዊ ያልሆኑ ሴቶችን በማግባት ተመልሶ ወደ አለም ባርነት ሄደ ፡፡ ዋይርስቤ “ መጀመሪያ ከአለም ጋር ጓደኛ ነበር (ያዕ 4፡ 4) ከዚያ በአለም ተያዘ (ያዕ 1፡ 27) ከዚያ በመቀጠል አለምን ወደ መዉደድ መጣ (1ዮሐ 2፡ 15-17) ከዚያም ከአለም ጋር ተስማማ (ሮሜ 12፡ 2) “ በማለት ይናገራል ፤ አይኖችችንን በእግዚአብሄር ላይ የማናደርግ ከሆነ ይህ ብዙዎቻችንን ወደ ታች ሊያንሸራትተን የሚችል አሸራታች ቁልቁለት ነው (ቁጥር 1-3) ፡፡ ሰለሞን ባረጀ ጊዜ ብዙ ሚስቶቹን ወደ ሌሎች አማልክቶችን እንዲያመልክ እንዲወስዱት ፈቀደላቸው - አምልኮአቸዉ ወሲባዊ ድርጊትን እና የማይነገሩ ተቃዉሞን ያካተቱ አማልክቶችን (ቁጥር 4-8) ፡፡

1-ነገስት (11፡ 9-13)፡ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ ገፋ ፡፡ ከአለም ጋር በምንስማማ ጊዜ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ሌላ እድልን ይሰጠናል ፡፡ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ እና ቁጣ በመተዉ በኃጢዓቱ ቀጠለ ፤ እግዚአብሄርም የዳዊትን ኪዳን ለማስቀጠል የይሁዳን ነገድ እና የኢየሩሳሌም ከተማ በመተዉ ብቻ ከሰለሞን ልጅ ላይ መንግስቱን እቀደዋለሁ አለ ፤ የቀረዉ እስራኤል ለአገልጋዩ ለኢዮሮብዓም ይሰጣል ፡፡

1-ነገስት (11፡ 14-15)፡ሰለሞን የእግዚአብሄርን ቅጣት ተቋቋመ ፡፡ እግዚአብሄር በሰለሞን ላይ ጠላቶችን አስነሳበት ፤ መጀመሪያ እግዚአብሄር ኤዶማዊዉን ሃዳድን አስነሳበት ፡፡ በ 2 ሳሙ (8፡ 13-14) ዳዊት በኤዶም ሁሉንም ወንዶች የገደለ አዛዥ ኢዮአብ ነበረው ፤ ነገር ግን ሃዳድ ህፃል ልጅ እያለ ወደ ግብፅ ሸሽቶ ነበር ፤ ቆይቶ ፈርዖን የሚስቶን እህት ለሃዳድ ሙሽራ እንድትሆነው ሰጥቶታል ፡፡ ሃዳድ ኢየአብና ዳዊት ሁለቱም እንደ ሞቱ በሰማ ጊዜ ወደ ራሱ ሀገር ለመመለስ ዝግጁ ነበር (ቁጥር 14-22) ፡፡ ቀጥሎም እግዚአብሄር ሌላ ጠላት ደማስቆያዊን ሬዞንን አስነሳ ፤ ሬዞንንም ከጌታዉ ከሱባ ንጉስ የኮበለለ ነበር እናም ጦሩን ሰበሰበ ፡፡ ሬዞን እስራኤልን በመጥላቱ የሰለሞን ጠላት ነበር (ቁጥር 23-25) ፡፡

1-ነገስት (11፡ 26-43)፡ሰለሞን የእግዚአብሄር አገልጋዮች ተቃወመ ፡፡ ሰለሞን ኢዮሮብዓም ኃያል እንደ ነበር ስላየው በዮሴፍ ቤት ሰራተኞች ላይ ሾመው ፤ ዋይርስቤ ኢዮሮብዓምን የእስራኤል ሰዎች በሰለሞን የኃይል ሰራተኞች በተለይም ለእርሱ የሚሰሩት አይሁዶች በደከሙ ጊዜ ከኤፍሬም እና ከምናሴ ነገድ ላይ በነበሩ የጉልበት ሰራተኞች ላይ ተሾሞ የነበረ ኤፍሬማዊ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ በዚያን ጊዜ ነቢዩ አኪያ ወደ ኢዮሮብዓም በመንገድ ላይ መጣ ፤ አኪያ አዲስ ለብሶት የነበረዉን አዲስ ካፓ ለ12 ቁርጥራጭ ቆረጠው ፤ አኪያ ኢዮሮበዓምን አስሩን ቁራጭ እንዲወስድ በመንገር እግዚአብሄር መንግስቱን ከሰለሞን እጅ እንደ ሚቆርጠው እና እንዲያስተዳድር አስሩን ነገድ ለኢየሮብዓም እንደሚሰጠው ገለፀ (ቁጥር 26-33) ፡፡ ነቢዩ ለኢየሮብዓም ሰለሞን ከአለም ጋር ጓደኛ(ወዳጅነት በመፍጠሩ) በመሆኑ ምክንያት ሰለሞን መንግስቱን እንደሚያጣው ነገሩን እየነገረው ነበር፡፡ እግዚአብሄር ለምህረቱ እና ለዳዊት ለገባዉ ኪዳን ምልክት የሰለሞንን ልጅ መንግስት ድርሻ እንደሚጠብቅለት ገለፀ (ቁጥር 34-37) ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር ከኢዮሮብዓም ጋር ተመሳሳይ ቃል ኪዳን አደረገ ፤ በእግዚአብሄር መንገድ የሚጓዝ ከሆነ እግዚአብሄር ከእርሱ እና ከቤቱ ጋር ስለሚሆን ታላቅ ስሮዉ መንግስት ይሆናል (ቁጥር 38-39) ፡፡

ሰለሞን ኢዮሮበዓምን ስላልወደደዉ ሊገድለዉ ሞከረ ፤ ኢዮሮብዓም ወደ ግብፅ በመሸሽ ሰለሞን እስኪሞት ድረስ በዚያ ቆየ ፡፡ የመጨረሶቹ ቁጥሮች (ቁጥር 41-43) የሰለሞንን መንግስት አገዛዝ የመዝጊያ ቀንን ይሰጣል ፡፡ የሰለሞን ልጅ ዮሮብዓም ከአባቱ መሞት በኋላ ንጉስ ሆነ ፤ በሰለሞን መሞት ላይ መንግስቱ ወደ ሁለት መንግስት ተከፍሎ ነበር፡

ይሁዳ የደቡቡ መንግስት (የይሁዳ ነገድ እና የኢየሩሳሌም ከተማ) በንጉስ ዮሮብዓም ስር

እስራኤል ሰሜናዊዉ መንግስት (በሰሜን የሚገኙት አስሩ ነገዶች) በንጉስ ኢዮሮብዓም

ይህ ሁሉ በሰለሞን አለመታዘዝ ምክንያት መጡ፡

መደምደሚያ

የሰለሞን መንግስት ለምን ነበር የተከፈለው ? ሙሴ ለአይሁድ ንጉሶች ግልፅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡

  1. ንጉስ ብዙ ፈረሶችን ማግኘት(መፈለግ) የለበትም (ዘዳ 17፡ 16) ፤ ሰለሞን 1,400 ሰረገሎች እና 12,000 ፈረሰኞች (1 ነገ 10፡ 26) ነበሩት ፡፡
  2. ንጉስ ብዙ ሚስቶች መፈለግ የለበት (ዘዳ 17፡ 17) ፤ ሰለሞን 700 ሚስቶች እና 300 ቁባቶች ነበሩት ( 1ነገ 11፡ 3) ፡፡
  3. ንጉስ ብዙ ብር እና ወርቅ መፈለግ የለበትም (ዘዳ 17፡ 17) ፤ ሰለሞን በጣም ብዙ ወርቅ ነበረው የወርቅ መጠጫ እቃ እና የቤት እቃዎች ነበሩት ነገር ግን በንፅፅር ዋጋ በማጣቱ ብር አልነበረውም (1 ነገ 10፡ 21) ፡፡

እግዚአብሄር በሰለሞን ተበሳጭቶ ነበር (1ነገ 11፡ 9-11) ሰለሞንም አንዱ አልነበረም ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ አንዱ ነው፡

ኢየሱስ በጣም ብዙ ወርቅና ብር የለዉም ፤ ሁሉንም ሰጥቷል ስለሆነም ኃብታሞች እንሆናለን (2 ቆሮ 8፡ 9) ፡፡

ኢየሱስ ብዙ ፈረሶች የሉትም ነገር ግን የተወሱ አንድ ዉርጫ ተጠቀመ (ዮሐ 12፡ 14) ፡፡

ኢየሱስ ብዙ ሚስቶች የሉትም ነገር ግን አንድ ሙሽር ብቻ ነበረችዉ -ቤተ ክርስቲያን (ኤፌ 5፡ 25-27) ፡፡

ዘካ (9፡ 9) ይህን ሁሉ በአንድ ላይ ስለ ሚበልጠዉ ያስቀምጠዋል፡ “ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዩ ፤ እነሆ ንጉስሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱ ግልገል በዉርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል “ ፡፡ ይህ ሁሉ ስለ ንጉሱ መምጣት የሚገልፅ ነው - ስለ ኢየሱስ ! ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), pp. 439–443.

  2. Wiersbe, p. 441.

  3. Wiersbe, p. 443.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ነገ (11፡ 14) እግዚአብሄር ሰለሞን ላይ ጠላትን ማስነሳት ጀመረ ፤ በራሳችን ኑሮ ሌሎች አማልክቶችን በፈለግን ጊዜ እግዚአብሄር ጠላትን ያስነሳብናል ብላችሁ ታምናላችሁ ? አዎ ከሆነ ይህ የሆነባችሁን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  2. በ 1ነገ (11፡ 31-32) ስለ ዳዊት ሲል እግዚአብሄር አንዱን ነገድ ለምን አዳነ ? (2ሳሙ 7፡ 12-13፣ ማቴ 1፡ 1-17)
  3. ንጉስ ዮሮብዓብ ለምክር ሽማግሌዎችን ለምን ጠየቀ ከዚያስ ለምን እንዳልተከተለዉ ምን ታስባላችሁ ? ምክር ጠይቃችሁ ያልተከተላችሁበት ጊዜ ነበራችሁ ? አዎ ከሆነ ለምን ?
  4. ኢዮሮብዓም የእስራኤል ሰዎች ለማምለክ በኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሄር ቤት ስለ ሄዱ ይገሉኛል ብሎ እንዲያስብ ምን አደረገው ? (1 ነገ 12፡ 26-27)
  5. 1 ነገ (12፡ 33) የኢዮሮብዓም ንግግር ወደ ጣዖት አምልኮ መለሰ ፤ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜም ይህን እናደርጋለን ? በህይወታችሁ ጣዖቶች ማን ወይስ ምንድን ናቸው ?
  6. በ 1ነገ (12፡ 33) ኢዮሮብዓም ለእስራኤል ልጆች “ በልቡ ባሰበዉ “ቀን ላዘጋጀው ግብዣ ቀን አስፈላጊ ነገር ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ኤር 17፡ 9፣ ማቴ 12፡ 34)
  7. በ 1ነገስት (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 11:3–4

“He had 700 wives who were princesses and 300 concubines, and they turned his heart away from the LORD. When Solomon was old, his wives seduced him to follow other gods. He was not completely devoted to Yahweh his God, as his father David had been.”

ሰሎሞንም በንግሰናው መጨረሻ ደረሰ ፡፡ በአለም ላይ ካለ ከማንም ይልቅ ብዙ ጥበብና ሀብት ነበረው ፡፡ ነገር ግን ከዚያ ልቡ ተጠለፈ እግዚአብሔርንም አልተከተልም ፡፡ ልቡን ከእግዚአብሔር ወደ ሌሎች አማልክት የሚያዘነብሉ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሶስት መቶ ቁባቶችም ነበሩት ፡፡ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉን አደረገ እግዚአብሔርም በእርሱ ላይ ተቆጣ ፡፡ የሰሎሞንም መንግስት መውደቅ ጀመረ ፡፡ እግዚአብሔር ሰሎሞንን አይኑን በእርሱ ላይ ብቻ እንድያደርግ ቢነግረውም ሰሎሞን ግን ጊዜው በሄደ ቁጥር ሳተ ከእግዚአብሔር ያልሆነውንም ነገር በብዙ ፈለገ ፡፡

የአለም ነገር ብዙ እንድትፈልግ ያማልልሃል ፡፡ ይህ ግን የሚሆነው በምሽት ብቻ አይደለም በየቀኑ የምትወስናቸው ትናንስ ከእግዚአብሔር መንገድ የሚቃረኑ ውሳኔዎች ልብህን ይጠልፉታል ፡፡ ሳታውቀው የራስህን መንግስት ገንብተሃል የራስህን መንገድና ሰዎችም እንድሁ ፡፡ ተጠንቀቅ ! የሰሎሞን ህይወት ትምህርት ይሁንህ ፡፡ ወደ ህይወት የምትወስደው ደጅ ጠባብ ናት አስቸጋሪም ናት ፡፡ በጠባብዋ ደጅ ለመግባት እንድትችል በክርስቶስ ልብህን አድስ በቃሉም ላይ አትኩር ፡፡ ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረት አድርግ ፡፡ አስታውስ የተቀባኸው በእውነት ትመላለስ ዘንድ እንጂ በዚህ አለም ውሸት አይደለም ፡፡ ለነፍስ እርካታህ ኢየሱስ በቂ ነው ፡፡

“ ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሶስት መቶም ቁባቶች ነበሩት ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት ፡፡ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፈጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንድሁ አልነበረም ፡፡ “

- 1ኛ ነገሥት 11፡3-4

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ 7፡13-14 –“ በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ወደ ህይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ፡፡ “
  • ሮሜ 12፡2 –“ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን አለም አትምሰሉ ፡፡ “
  • 1ኛ ዮሐንስ 2፡27 –“ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም ነገር ግን የእርስ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ፡፡ “