Jesus is Greater Than Solomon
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና በቤተ መቅደሱ መለየት ላይ ሰለ ሰለሞን ፀሎት ተመልክተናል ፡፡ ከፀሎት በኋላ ሰለሞን 22,000 ከብቶች እና 120,000 በጎች ለእግዚአብሄር በማቅረብ ሰዋ ፡፡ እስራአኤል በጥሩ የሰላም ዘመን ላይ ነበረች ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት (9፡ 1-9)፡ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን፣ የነገስታት መኖሪያዉን እያንዳንዱ ነገር ለመስራት የዘረዘራቸዉን ጨርሶ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ለሰለሞን ሁለተኛ ጊዜ በመለገለጥ ዳዊት እንደሄደዉ እንዲጓዝ አዘዘዉ (ቁጥር 2-4) ፤ እግዚአብሄር የሰለሞንን ንጉሳዊ ዙፋን ሰለሞን ትዕዛዙን እስከጠበቀ ድረስ በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንደሚሆን ቃል ገባለት ነገር ግን ሰለሞን ወይም ልጆቹ ከእሩሱ ከተመለሱ መስመሩን ያቆመዋል (ቁጥር 5-9) ፡፡
1-ነገስት (9፡ 10-14)፡ ሰለሞን ለንጉስ ኪራም ለኪራም ወርቅ ምላሽ በእስራኤል 20 ከተሞችን ሰጠው ነገር ግን ኪራም በከተሞቹ ደስ ስላልተሰኘ የከቡል አገር ብሎ ጠራቸው (ቁጥር 10-14) ፡፡
1-ነገስት (9፡ 15-23)፡ የማከማቻ ከተማዎች በተገደዱ ሰራተኞች እንደ ገና መገንባት የተዘረዘረ ነው ፡፡
1-ነገስት (9፡ 24-28)፡ ይህ የሰለሞን ሎሎች ተግባሮች ሪፖርት ነው - ሚስቱ ወደ ቤቱ መጣች፣ በእግዚአብሄር መሰዊያ ላይ በአመት ሰዎስት ጊዜ መስዋዕት ያቀርባል እንዲሁም የጦር መርከቦችን ሰርቷል ፡፡ ዋይርስቤ ሰለሞንን “ እንደ አንድ ትልቅ ስራ ፈጣሪ ፤ ከብዙ ህዝቦች ጋር የንግድ ስምምነቶችን ያደረገ፣ ብዙ መርከቦችን የሰራ እና ይህን ለእርሱ እንዲቆጣጠሩለት የኪራምን የባህር ነገር አዋቂ ሰዎችን የቀጠረ እንደ ነበር “ ገልፆታል ፡፡ ሰለሞን ሸቀጦችን አስመጪ፣ አለም አቀፋዊ ምሳሌ እና ለአህዛብ ስለ አምላኩ ምስክር ነበር ፡፡ ከፍተኛ በጀት አስተዳድሯል ምናልባትም የእንስሳትም ባር ነበረው (መክ 2፡ 4-9) ፡፡
1-ነገስት (10፡ 1-22)፡ በመላዉ አለም ዉስጥ ያሉት ሰዎች ሰለሞንን አወቁት ፤ የሰለሞን ታላቅነት ቢኖርም ኢየሱስ “ ከሰለሞን የሚበልጥ በዚያ “ እንደ ነበር ተናገረ (ማቴ 12፡ 42) ፡፡ ኢየሱስ እንዴት እንደ ሚበልጥ ለማረጋገጥ ከሰለሞንን እና ከሳብን ቃለ ምልልስ መካከል መዉሰድ እፈልጋለሁ ፡፡ ሳባ አረቢያን በረሀ አካባቢ የምትገኝ ነበረች (አሁን የመንተብሎ በሚታሰበው) ፡፡ ንግስቲቱ በጉዞዋ ከሆነ ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም ከ 1,200 እስከ 1,500 ማይል ተጉዛለች ፡፡
ኢየሱስ ከሰለሞን የሚበልጠዉ እንዴት ነው፡
- ሰለሞንን ፤ ንግስቲቱ ስለ ሰለሞን በመስማት ራሷ ልታይ መጣች (ቁጥር 1) ፡፡
ኢየሱስን ፤ ህዝቡ ምን እንደ ሆነ እና ምን እያደረገ እንደ ነበር ለማወቅ ወደ ኢየሱስ መጡ ( ዮሐ 12፡9፣ 12)፡፡
ሰለሞንን ፤ ሰለሞንን በአስቸጋሪ ጥያቄዎች ልትፈትነዉ መጣች (ቁጥር 1) ፡፡
ኢየሱስን ፤ የኃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን ሊፈትኑት መጡ (ማቴ 22፡ 12፣ 23፣ 34-35፣ 46) ፡፡
ሰለሞን ፤ ለእርሷ ለመግለፅ ለሰለሞን ምንም ነገር አስቸጋሪ አልነበረም (ቁጥር 3) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ያዉቃል ! (ዮሐ 16፡ 30፣ 21፡ 17) ፡፡
ሰለሞን ፤ የሰለሞን ጥበብ መልስ አሳጣት (ለመናገር ትንፋሽ አሳጣት ) (ቁጥር 5) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ሁሉም ሰዉ በመደነቅ እና በመገረም ደነገጡ (ማቴ 9፡ 8፣ ሉቃ 5፡ 25-26) ፡፡
ሰለሞንን ፤ መጥታ እስክታይ ድረስ የሰማችዉን አላመነችም (ቁጥር 6-7) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ማንም ያላየው….እግዚአብሄር ለሚወዱት ያዘጋጀው ( 1ቆሮ 2፡ 9) ፡፡
ሰለሞን ፤ የሰለሞን ጥበብ እና ብልፅግና ሰምታ ከነበረው በጣም ይበልጥ ነበር ( ቁጥር 7) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ጥበብ ሁሉ በኢየሱስ የተሰወረ ነው (ኢሳ 11፡ 2፣ ቆላ 2፡ 3) ፡፡
ሰለሞን ፤ የሰለሞን አገልጋዮች ደስተኞች ነበሩ (ቁጥር 8) ፡፡
ኢየሱስ ፤ኃዘን እና እምባ/ለቅሶ አይኖርም (ራዕ 21፡ 4) ፡፡
ሰለሞን ፤ ሰለሞንን ስጦታ ሰጠችዉ (ቁጥር 10) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ሰበዓ ሰገሎች ኢየሱስን ስጦታ አመጡለት ፤ እንደ ገና ህዝቦች ለእስራኤል ሀብት ያመጣሉ (ኢሳያስ 60፣ ማቴ 2፡ 11) ፡፡
ሰለሞን ፤ የንግስቲቷን ሁሉንም ፍላጎት ሰጣት (ቁጥር 13) ፡፡
ኢየሱስ ፤ የልባችንን ፍላጎት ይሰጠናል (መዝ 37፡ 3፣ ማቴ 21፡ 22) ፡፡
ሰለሞን ፤ ሰለሞን ታላቅ ኃብት አከማቸ (ቁጥር 14-22) ፡፡
ኢየሱስ ፤ ሁሉም የእርሱ ሆኖ ሳለ ስለ እኛ ሲል ድሀ ሆነ (መዝ 50፡ 10-11፣ 2ቆሮ 8፡ 9) ፡፡
1-ነገስት (10፡ 23-29)፡ ሰለሞን ታላቅ ጥበብ ነበረው በአለም ላይ ያለዉ ሁሉ ስለ ጥበቡ መስማት ፈለጉ (ቁጥር 24) ፡፡ ቀዌ (ቁጥር 28) ምናልባትም የቀዌ ከተማ ነበረች ፤ በ 9 መቶ ክፍለ ዘመን በኤሲያ ጥቃቅን ፅሁፍ በተገኘዉ ከተማዋን ጠቅሷታል ፡፡ ሰለሞን ፈረሶች ከሚያገኝባቸዉ ቦታዎች ይህ እንዱ ነበር ፤ የፈረሶቹ ስብስብ ሰለሞንን ወደ ተከለከለዉ ትልቅ ቁጥር ፈረሶችን መፈለገ በመምጣት በእዉነቱ ወደ መጣስ ይጠጋል (ዘዳ 17፡ 16) ፡፡ ሰለሞን ፈረስ ሻጭ ሆኖም ነበር (ቁጥር 29) ፤ ሰለሞን በብዙ ሀብታም ነበር የኢየሱስ ሀብት ግን የሚበልጥ ነው (መዝ 50፡ 10-11፣ 2ቆሮ 8፡ 9) ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ ከሰለሞን የሚበልጥ ነው ፤ ኢየሱስ የመጨረሱ ንጉስ ነው !
ፊል (2፡ 9-11)፡ “ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሄር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለዉን ስም ሰጠው ፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድር በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ፤ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሄር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው “ ፡፡
ራዕ (5፡ 12 -13)፡ “ በታላቅ ድምፅ ፡፡ የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ ፡፡ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባህርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ዉስጥ ያለ ሁሉ ፡፡ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፉኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ “ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በ 1ነገ (9፡ 2) እግዚአብሄር ለሰለሞን ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠለት ፤ መጀመሪያዉ ጊዜ መቼ ነበር ለምንስ ? (1ነገ 3፡ 5)
-
በ 1ነገ (9፡ 12) ኪራም ሰለሞን ሰጥቶት በነበረው ከተሞች ለምን ደስተኛ እንዳልሆነ ምን ታስባላችሁ ? ከቡል ማለት ምን ማለት ነው ? (1 ነገ 9፡ 13)
-
ሰለሞን ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ጥበበኛ ከነበር የሌሎች ሀገር ሴቶችን ለምን እያገባ እንደ ነበር እና ብዙ ፈረሶች ለምን እንደ ኖሩት ምን ትላላችሁ ? (ዘዳ 7፡ 3-4፣ 17፡ 16-17፣ 1 ነገ 9፡ 16፣ 0፡ 26)
-
በ 1ነገ (10፡ 9) (በአዲሱ ኪንግ ጀምስ ዕትም) “ አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሄር የተባረከ ይሁን ! እግዚአብሄር እስራኤልን ለዘላለም ወድዶታልና ስለዚህ ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ንጉስ አድርጎ አስነሳህ “ ፤ በንጉስ ሰለሞን መንግስት ዉበት በኩል አምላኩ እዉነተኛ አምላክ እንደ ነበር ለማስተዋል ለንግስት ሳባ ቀላል ነው ? (ማቴ 12፡ 38-42)
-
የሰለሞን ምድራዊ መንግስት ከሰማያዊ መንግስት ጋር እንዴት ይወዳደራል(ይነፃፀራል) ? (1 ነገ 10፡ 18-20፣ ራዕ 21፡ 10-21)
-
በ 1ነገስት (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 10:6–8a
“She said to the king, ‘The report I heard in my own country about your words and about your wisdom is true. But I didn’t believe the reports until I came and saw with my own eyes. Indeed, I was not even told half. Your wisdom and prosperity far exceed the report I heard. How happy are your men.’”
ቤተ መቅደሱና የሰሎሞን ቤት ተሰርቶ ተፈጸመ ፡፡ ከዚያም ሰሎሞን መንግስቱን እግዚአብሔር በሰጠው ጥበብ አሰፋ ፡፡ በምድር ላይ ያሉ ነገሥታትን ሁሉ በሀብቱና በጥበቡ ይበልጥ ነበር ፡፡ ለዚህም ነበር ስለ ሰሎሞን የሰማችው ሁሉ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ንግሥት ሳባ የመጣችው ፡፡ የሰማችውም ነገር እውነት በመሆኑ የሰለሞን መንግስት አስደነቃት ፡፡ በርግጥም የሰሎሞን መንግስት ታላቅ ነበረ አገልጋዮቹ ጭምር ደስተኞች ነበሩ ፡፡
አንድ ሰው ስላንተ የሰማው እወነት መሆኑን ያይ ዘንድ አንተን ለመጎብኘት ቢመጣ ? ጉብኝታቸው ያስደነግጥሀል ወይስ “ ኑ ግቡ ! “ ለማለት ነጻ ትሆናለህ ? የእግዚአብሔር ፍላጎት ላንተ ህይወትህን በቅንነትና በንጹህ ህሊና እንድትኖር ነው ስለዚህም ድንገተኛ ጉብኝት ሲደረግ ህይወትህ የአፍህን ቃል ይመሰክራል ፡፡ ነገር ግን “ ድንገተኛ እንግዳው “ አንተ ማንም እንዳያውቅ የምትፈልገውን ነገር ማወቅ ቢፈልግ ምን ታደርጋለህ ? በረጅሙ ተንፍስ ምንም ችግር የለው ምክንያቱም ከሰሎሞን የሚበልጥ ኢየሱስ የተባለ ስለመጣ ፡፡ ኢየሱስ ስላንተ ሁሉንም ያውቃል ፡፡ የት እንደምትታገል ያውቃል በዚያም ካንተ ጋር ለመራመድ አለ ፡፡ በዚያም ውስጥ ይወድሃል ፡፡ ህይወትህን ለክርስቶስ አሳልፈህ ስትሰጥ እንድትጸናና መሄድ እንድትቀጥል የሚያስችልህን ጸጋ ይሰጥሃል ፡፡ ዛሬ በእርሱ ኃይል ታመን ፡፡ በዚህ አለም ፍጹም ለመሆን በራስህ ኃይል የምትታገልበት ምንም ምክንያት የለም ምክንያቱም ጸጋው በአንተ ውስጥ ታላቅ ነውና ፡፡
“ ንጉሡንም አለችው ስለ ነገርህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው ፡፡ እኔም መጥቼ በአይኔ እሰካይ ድረሰ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር እነሆም እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር ጥበብህና ሥራህ ከሰማሁት ዝና ይበልጣል ፡፡ በፊትህ ሁልጊዜ የሚቆሙ ጥበብህንም የሚሰሙ ሰዎችህና እነዚህ ባሪያዎችህ ምስጉኖች ናቸው ፡፡ “
- 1ኛ ነገሥት 10፡6-8
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማቴዎስ 12፡42 –“ ንግሰተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትወልድ ጋር ተነሰታ ትፈርድበታለች የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡9 –“ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶሰን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና ሀብታም ሲሆን እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ተሆኑ ዘነድ ሰለ እናንተ ድሀ ሆነ ፡፡ “
- 1ኛ ዮሐንስ 4፡4 – “ ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል በአለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።