The Dedication of the House of God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በብሉይ ኪዳን የታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ ቀጥለናል ፡፡ ኮንስታብል 1 ነገስት 8 “ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ በጣም የመለየት አገልግሎት መዝገብ የተዘረዘረበት እንደሆነ ፤ እንዲሁም በተጨማሪም በ 1እና በ 2 ነገስት በስነ-መለኮታዊ በጣም አስፈላጊ የሆነ ፅሁፍ እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡ የእስራኤልን የእግዚአብሄር ቤት ምርጡን ስዕል ይሰጠናል ፡፡ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ሲገነባ የሚበልጥ ነገር እየገነባ ነበር ፤ ኢየሱስ ከዚያ የሚበልጥ ነው ፡፡ ይህ ምዕራፍ ከረጅሞች አንዱ ነው - ስልሳ ስድስት ቁጥር ይረዝማል ፤ ዋይርስቤ ምዕራፉን በዚህ መንገድ ይከፋፍለዋል፡ የእግዚአብሄር ቤት (ቁጥር 1-11)፣ የምስክርነት ቤት (ቁጥር 12-21)፣ የፀሎት ቤት (ቁጥር 22-53)፣ የምስጋና ቤት (ቁጥር 54-61) እና የህብረት(የደህንነት) ቤት (ቁጥር 62-66) ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት (8፡ 1-11)፡የእግዚአብሄር ቤት ፡፡ ሰለሞን የእስራኤልን ሽማግሌዎች በአንድ ላይ አመጣ - “ የነገድ አለቆችን እና የቤቶች መሳፍንቶች “ “ በእያንዳንዱ የቤተሰብ ዘር ዉስጥ ትልቅ ወንዶች “ ነበሩ ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በድንኳኑ ማደሪያ ነበር ነገር ግን በኢየሩሳሌም በጣም ወደ ተሻለ ስፍራ እየተጓዘ ነበር ፤ የእግዚአብሄር መገኘት ከሚንቀሳቀስ ቦታ ወደ ቋሚ ቤት የተንቀሳቀሰ ሆነ (ቁጥር 1) ፡፡ ቤተ መቅደሱ ከተጠናቀቀ ከ 11 ወር በኋላ በጣም ቅዱስ ወር የድንኳኑ በዓል ወይም የዳስ በዓል በሆነበት በሰባተኛዉ ወር ተሰበሰቡ (ቁጥር 2) ፤ ሁሉም የእስራኤል ወንድ መገኘት ይጠበቅባቸዉ ነበር ፡፡ ካህናቱ እና ሌዋዊያኑ ወደ ኢየሩሳሌም ታቦቱን፣ የድንኳኑን ማደሪያ እና የተቀደሰዉን እቃ ሁሉ አመጡ (ቁጥር 3-4) ፤ በዚያን ጊዜም ሰለሞን እና የእስራኤል ሰዎች ሊቆጠሩ የማይቻሉ ብዙ በጎች እና ከብቶች ሰዉ (ቁጥር 5) ፡፡ ካህናቱ ታቦቱን በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ከኪሩቤል ስር አስቀመጡት (ቁጥር 6-8) ፤ በታቦቱ ዉስጥ ያለዉ ብቸኛዉ ነገር የሙሴ አስዕርቱ ትዕዛዞች የነበሩበት ድንጋይ ነበሩ እነዚህም ነገሮች በቤተ መቅደሱ ዉስጥ አዲስ ያልነበሩ ብቸኛ ነገሮች ነበሩ (ቁጥር 9) ፡፡ ካህናቱ በመጡ ጊዜ የእግዚአብሄር ክብር በመዉረድ ቤተ መቅደሱን ሞላው (ቁጥር 10-11) ፡፡
1-ነገስት (8፡ 12-21)፡የምስክርነት ቤት (ሰለሞን የእግዚአብሄር መገኘት በቤተ መቅደሱ መምጣቱን ምስክርነት ሰጠ) (ቁጥር 12-13) ፤ ይህ አስተሳሰብ የእስራኤል ነፃነት ሊሆን የሚችለዉ ወደ እግዚአብሄር መገኘት በመምጣት እንደ ሆነ ያሳያል ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር በፍፁም በህንፃ ዉስጥ በመሆን፣ ወይም በድንኳን ዉስጥ በመሆን ወይም በሌላ ስፍራ አይወሰነም ፡፡ ሁሉም እንደ ቆሙ ሰለሞን በተሰበሰቡት ፊት ቀጠለ (ቁጥር 14) ፤ ሰለሞን የእግዚአብሄርን መልካምነት እና ለዳዊት መታመኑን አሁን ደግሞ በእርሱ በኩል መታመኑን አሳሰባቸው (ቁጥር 15-21) ፡፡
በ 2ሳሙኤል 7 ከዳዊት ጋር እንደ ሚሰራ ቃል በመግባት እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር ኪዳን አድርጓል ( ቁጥር 12-16) ፤ ሰለሞን አባቱ መስራት ፈልጎ የነበረዉን ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስን ሰራ ፡፡ በመጨረሻም የእግዚአብሄር ኪዳን ከአብርሃም እና ከዳዊት ጋር ያደረገው በኢየሱስ ይፈፀማል (ኤር 31፡ 31-34) ፡፡
1-ነገስት (8፡ 22-53)፡የፀሎት ቤት ፡፡ የሰለሞን ምስክርነት የፀሎት ጊዜ ሆነ ፤ በተለመደ በግለሰብ ፀሎት አቋቋም (ዘጸ 9፡ 29) እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት ፀለየ (ቁጥር 22) ፡፡ እግዚአብሄር ተስፋዉን በመፈፀሙ ሰለሞን በመረዳት የፀለዬ ይመስላል (ቁጥር 23-24) ፤ ስለዚህ አስቡ የእግዚአብሄር ተስፋ ለዳዊት ሰለሞን ባያደርገዉም አልተፈፀመም ፡፡ ከዚያም ሰለሞን እግዚአብሄርን መገኘቱንና ጥበቃዉ ጠየቀው ( ቁጥር 25-30) ፡፡
በመፅሀፍት ስላልተለመዱ አይነት ፀሎቶች ብዙ አሉ፡ የሙሴ ፀሎት ስለ እስራኤል (ዘጸ 32፡ 8-14)፣ የዳዊት ፀሎት ለይቅርታ እና ለንስሀ ፀለዬ (መዝ 51)፣ የሕዝቅያስ ልመና ለነፃ መዉጣት እና ለፈዉስ (2 ነገ 19፡ 14-19፣ 20፡ 1-7)፣ የዳዊት የመሰጠት ፀሎት (መዝ 139)፣ የያቤፅ ፀሎት (1ዜና 4፡ 10)፣ የጌታ ፀሎት (ማቴ 6፡ 9-13)፣ ለመዳን የዮናስ ፀሎት (ዮና 2፡ 29)፣ የዳዊት ፀሎት ለነፃ መዉጣት (መዝሙር 3)፣ የሀና ፀሎት ( 1 ሳሙ 2፡ 1-10)፣ የነህምያ ፀሎት ለስኬት (ነህ 1፡ 1-2፡ 9) እንዲሁም የኢየሱስ ፀሎት ስለ መታዘዝ (ሉቃ 22፡ 37-46) ፤ በመፅሀፍት በጣም ብዙ ሰዎች በፀሎት ኃይል ወደ እግዚአብሄር ፊት የመጡ አሉ ፡፡ በቁጥር 30 ሰለሞን የእስራኤል ሰዎች ከየትም ሆነዉ ወደ ኢየሩሳሌም ሲፀልዩ ከዛሬ ጀምሮ እንደ ሚሰማ አረጋገጠላቸዉ ፡፡
ዋይርስቤ ሰለሞን እግዚአብሄርን የጠየቀዉን ሰባት ልመናዎች ለይቷል፡
- በምድሩ ስለ ፍትህ (ቁጥር 31-32፣ 2ዜና 6፡ 22-23) ፡፡ ሰለሞን “ በበደለኛዉ እና በፃድቁ መካከል እንዲፈርድ ጠየቀ “ ፡፡
- በጦርነት ሲሸነፉ (ቁጥር 33-34፣ 2ዜና 6፡ 24-25) ፡፡ ሰለሞን “ እግዚአብሄርን በጦርነት ለመሸነፋቸዉ ምክንያት የሆነዉን ኃጢዓት ይቅር እንዲላቸው ጠየቀ “ ፡፡
- በምድሪቱ ስለ ርሀብ (ቁጥር 35-36፣ 2ዜና 6፡ 26-27) ፡፡ ሰለሞን እግዚአብሄርን በምድራቸዉ ላይ ረሀብ እንዲመጣ ያደረገዉን ኃጢዓታቸዉን ይቅር እንዲላቸዉ ጠየቀ ፡፡
- ስለ ሌሎች ተፈጥሮአዊ መቅሰፍቶች (ቁጥር 37-40፣ 2ዜና 6፡ 28-31) ፡፡ ሰለሞን ወደ ኢየሩሳሌም ሲፀልዩ በምላሹ በእነርሱ ላይ መቅሰፍት አምጥቶ ስለ ነበረዉ ኃጢዓት የእግዚአብሄርን ምህረት ጠየቀ ፡፡
- ለመፀለይ ስለሚመጡ እንግዶች (ቁጥር 41-43፣ 2ዜና 6፡ 32-33) ፡፡ ሰለሞን እግዚአብሄርን እግዚአብሄርን በመፍራት ወደ ኢየሩሳሌም ስለሚፀልዩት እንግዶች ጠየቀ ፡፡
- በዉጊያ ስላለ ሰራዊት (ቁጥር 44-45፣ 2ዜና 6፡ 34-35) ፡፡ ሰለሞን እግዚአብሄርን እስራኤላዊያን ወደ ኢየሩሳሌም በሚፀልዩ ጊዜ ለሰራዊቱ ድል ማድረግን እንዲያደርግላቸው ጠየቀ ፡፡
- ስለ ሽንፈት እና ስለ ምርኮ (ቁጥር 46-53፣ 2ዜና 6፡ 36-39) ፡፡ ሰለሞን እግዚአብሄርን ወደ ኢየሩሳሌም በፀለዩ ጊዜ “ ከምርኮ መመለስን እንዲያመጣላቸው ጠየቀ “ ፡፡
1-ነገስት (8፡ 54-61)፡የምስጋና ቤት ፡፡ የሰለሞን እጆች በጠቅላላዉ ፀሎቱ ወደ ሰማይ እንደ ተዘረጉ ቆዩ ፤ ቁጥር 56 “ በባሪያው በሙሴ ከሰጠው ከመልካም ተስፋ ሁሉ አንድ ቃል አልወደቀም “ ተብሎ ተመዝግቧል ፡፡
1-ነገስት (8፡ 62-66)፡የደህንነት ቤት ፡፡ ሰለሞን እና ሕዝቡ ለእግዚአብሄር የደህንነት መስዋዕት 22,000 ከብቶች እና 120,000 በጎች አቀረቡ ፤ 15ኛዉ ቀን ላይ ሰለሞን የእስራኤል ሰዎች ቤታቸዉ ላካቸው ፡፡ “ እግዚአብሄርም ለባሪያዉ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ተደስተው ሀሴትም አድርገው ወደ ስፍራቸው ሄዱ “ (ቁጥር 66) ፡፡
መደምደሚያ
እነዚህ ሁሉ ሆኑ ምክንያቱም ከምዕራፍ 8 መጀመሪያ የእስራኤል ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሄር ለመቀደስ በአንድ ላይ መጥተዉ ነበር ፡፡ ኮንስታብል “ እግዚአብሄር እስራኤልን በሲና ተራራ ላይ ህጉን ከሰጣቸዉ ጀምሮ በስነ መለኮታዊ አስፈላጊነት ይህ በእስራኤል ትልቅ ክስተት ነበር ፤ በመጨረሻም እስራኤል በታላቅ ክብር ቦታ ከነገሰዉ አምሏኳ ጋር በተስፋይቱ ምድር ሆነች ፤ አሁን እስራኤል በታሪኳ ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቀውን በአለም ላይ ጥሪዋን ለመፈፀም በስፍራዉ ነበር “ (ዘጸ 19፡ 5-6) ፡፡ 1 ነገስት 8 በ 2ሳሙኤል 7 የተሰጡት ትንቢታዊ ቃሎች ጀመሩ ፡፡
Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Kings, p. 52; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1kings.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 1 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), pp. 424-431.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 404.
Wiersbe, pp. 427-429.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
MacArthur, p. 405.
Constable, p. 57.
ጥያቄዎች
-
ታቦቱን ለመቀደስ የሰለሞን የመጀመሪያዉ ድርጊት ምን ነበር ? ሰለሞን በአባቱ በዳዊት እርምጃ እንዴት ተከተለ ? (2ሳሙ 6፡ 17)
-
ሰለሞን በፀሎቱ አጉልቶ ያሳያቸዉ ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ? በተለይም በራሳችሁ የፀሎት ህይወት ትፀልዩታላችሁ ?
-
የእስራኤል ህዝብ መለያ ምልክት ምን ነበር ? (ዘጸ 33፡ 13-23፣ 1ነገ 8፡ 10-11፣ ሮሜ 9፡ 4)
-
ሰለሞን በመቆም ለመፀለይ እጆቹን ወደ ሰማይ መዘርጋቱ ምን ማለት ነው ? (ዘጸ 9፡ 29፣ 33፣ 1ነገ 8፡ 22፣ 54፣ 2ዜና 6፡ 13፣ መዝ 63፡ 4፣ ዕዝ 9፡ 5፣ 1ጢሞ 2፡ 8)
-
በቁጥር (15-21) የእግዚአብሄርን መልካምነት እና መታመንን እንዴት ታዩታላችሁ ( 2ሳሙ 7፡ 2፣ 12-13፣ 25) ? እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች በማድረግ ተስፋዉንለምን ፈፀመ ?
-
በ 1ነገስት 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 8:54–56
“When Solomon finished praying this entire prayer and petition to the LORD, he got up from kneeling before the altar of the LORD, with his hands spread out toward heaven, and he stood and blessed the whole congregation of Israel with a loud voice: ‘May the LORD be praised! He has given rest to His people Israel according to all He has said. Not one of all the good promises He made through His servant Moses has failed.’”
ሰለሞን ለእግዚአብሔር የተሰራውን አድሱን ቤተ መቅደስ ቀደሰ ፡፡ ተንበርክኮም ስለ ታማኝነቱ እግዚአብሔርን አመሰገነ ደግሞም ህዝቡን ያስብ ዘንድ ጸለየ ፡፡ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ሰለሞን በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ነበር ፤ ቤተ መቅደሱን ባረከ በእግዚአብሔር መገኘትም ውስጥ ህብረትን አደረገ ፡፡
በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት ስትቀርብ ስለ አቋምህ አስብ ፡፡ ተንበርክከህም ሆነ ቆመህ ለእግዚአብሔር ያለህን ፍቅር ብትገልጽ ችግር የለውም ፡፡ አሁን ደቂቃ ውሰድ ለመንበርከክ ወይም ለአክብሮት ራስህን ወደ መሬት ዝቅ ለማድረግ ፡፡ ምናልባትም ወደ ውጭ ወጥተህ እጆችህን ወደ ሰማይ በማንሳት የእርሱን ድንቅ ስራ ማየትም ያሻህ ይሆናል ፡፡ በህይወትህ ታማኝ ስለሆኑ ኪዳኖቹ አመስግነው ፡፡ አንዳንዴ ከህጻናት ጋር ለማውራት ስትፈልግ መሬት ላይ መቀመጥ እንዳለብህ ሁሉ በልብህ ውስጥ የሆነ ነገር ሲፈጠርም ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ በማድረግ ከእርሱ ጋር አውራ ፡፡ ሌሎች ሊያስቡ ስለሚችሉት ነገር አትጨነቅ ፡፡ ይህን ህብረት ከሰማዩ አባትህ ጋር አድርግ ፡፡
“ ሰሎሞንም ይህችን ጸሎትና ልመና ሁሉ ለእግዚአብሔር ጸልዮ በፈጸመ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ እጁንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ነበርና ከእግዚአብሔር መሰዊያ ፊት ተነሳ ፡፡ ቆሞም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ በታላቅ ድምጽ ሲመርቅ እንድህ አለ እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለህዝቡ ለእስራኤል እረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን በባሪያው በሙሴ ከሰጠው ከመልካም ተስፋ ሁሉ አንድ ቃል አልወደቀም ፡፡ “
- 1ኛ ነገሥት 8፡54-56
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 133(134) ፡ 1-2 –“ እነሆ እግዚአብሔርን ባርኩ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ ፡፡ “
ዳንኤል 6፡10 –“ ዳንኤልም ጽህፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ እየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ በየእለቱ ሶስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም ፡፡ “
ራዕይ 7፡11 –“ መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሸማግሌዎቹ በአራቱም እንሰሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፉ ለእግዚብሔርም እየሰገዱ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።