Extravagant Disobedience
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዚህ ምዕራፍ ጅማሮ ትኩረት ቤተ መቅደሱን መስራት ነበር ፡፡ የሙሴ ትዕዛዝ ለእስራኤል ንጉስ “ ነገር ግን ለእነርሱ ፈረሶችን አያበዛም ፤ እግዚአብሄር በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶቹን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም ፡፡ ልቡም እንዳይስ ሚስቶችን ለእርሱ አያበዛም ፤ ወርቅና ለእርሱ እጅግ አያበዛም “ አለ (ዘዳ 17፡ 16-17) ፡፡ እነዚህ ትዕዛዞች ከቀጣዮቹ ብዙ ምዕራፎች ጋር ግንኙነት አላቸው ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት (6፡ 38- 7፡ 1)፡ የ1 ነገስት 7 ጥናት በ 1ነገ ( 6፡ 38) ይጀምራል ፡፡ መቅደሱ በሰለሞን አገዛዝ በ 11 አመት ጊዜ በሰባት አመታት ዉስጥ እያንዳንዱ ዝርዝር አበቃ ፤ የራሱን ቤት ለመስራት ከፈጀበት ሁለት እጥፍ ሰለሞንን 13 አመት ፈጀበት (1 ነገስት 7፡ 1) ፡፡
ቤቱ ከአንድ ቤት የበለጠ ነበር ፤ ለሰለሞን የግል መኖሪያዉን እና ለመንግስቱ አስተዳደራዊ ማዕከልን ያካተተ ነበር ፡፡ በ 1ነገ (6፡ 38) እና በ 1ነገ (7፡ 1) መካከል የሚያነቃቃ ሽግግር አለ ፤ የተከሰተዉ መቋረጥ የጊዜ ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ነው ፡፡ ስራ በአንዱ መጠናቀቅ ዉስጥ ሌለኛዉ ከሆነ ወይም ስራ በኃለኛዉ እና በፊተኛዉ መካከል የሚጓዝ ከሆነ እነዚህ ሁለቱ እንዴት እንደተገነቡ እርግጠኞች አይደለንም ፡፡ 1 ነገ (9፡ 1) እና 1 ነገ (9፡ 10) የቤተ መቅደሱን ስራ እና የራሱን ቤት ስራ ይጠቅሳል ፤ በ 1ነገ (3፡ 1) ቅደም ተከተሉ መጀመሪያ መኖሪያ ቤቱ ከዚያ ደግሞ ቤተ መቅደሱ ነው ፡፡ ፀሀፊዉ አንባቢ ንፅፅሩን በማየት እርግጠኛ እንዲሆኑ ፈለገ ፤ 13 አመታት ለቤቱ ሰባት አመት ደግሞ ለቤተ መቅደሱ ፡፡
1-ነገስት (7፡ 2-12)፡ የህንፃዉ ዝርዝር፣ የፅዱ ወጋግራዎች እና ምሰሶዎች የተለዬ ነበር ፤ ቤቱ በብዙ መስኮቶች እና በሮች፣ አንድ ረጅም ኮሪደር እና አንድ አኡማዳ በምሰሶዎች ድዛይን የተደረገ ነበር (ቁጥር 2-6) ፡፡ ሰለሞን ጉዳዮችን የሚዳኝበት በፅድ ጣዉላ ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነ የዙፋኑን አዳራሽ አበጀ (ቁጥር 7) ፤ ትልልቅ ዉሳኔዎች በሁለቱ እናቶች ጥያቄ ላይ የተፈረደው ፍርድ እናዲሁም ንግስት ሳባ በደረሰች ጊዜ እንደ እንግዳ መቀበያነት እነዚህ ሁሉ በዚህ አዳራሽ ዉስጥ የተካሄዱ ነበሩ ፡፡ አስታዉሉ ንግስት ሳባ የመቅደሱን ዉስጥ አላየችዉም ፤ ስለ ሰለሞን ባወራች ጊዜ ሁሉም ክብር ከመኖሪያ ቦታዉ እየጠቀሰች ነበር ፡፡ ፅድ መልካም መዓዛ የሚሸት ለምስጥ መጎዳት በጥሩ የሚቋቋም ነው ነገር ግን በ ነገስት መጨረሻ ላይ ስንመለከተው ተቀጣጣይ ነው ፡፡ ሰለሞን የፈርዖን ልጅ ለነበረችዉ ለሚስቱ የሰራው ተመሳሳይ ቤት ነበረው ፤ ሌሎች ቤቶች እና መኖሪያዎች እንዲሁ በዉድ እቃዎች እና ድንጋዮች ተሰሩ (ቁጥር 8-12) ፡፡
አስራ ሁለት ጥቅሶች ለመስራት 13 አመታት የወሰደዉን የመኖሪያ ቤቱን ይገልፃል ፤ የ 1ነገስት ፀሀፊ እነዚህ ህንፃዎች እንደ ቤተ መቅደሱ አስፈላጊ መስለዉ አልታዩት ፡፡ የቤተ መቅደሱ ግንባታ በምዕራፍ 5 ክፍል የተገለፀ ነበር፣ የምዕራፍ 6 ሁሉም፣ የምዕራፍ 7 ክፍል እና የቤተ መቅደሱ መሰጠት አልመጣም ነበር ፡፡ ለሰለሞን ቤተ መንግስቱ አስፈላጊነቱ እንዴት ነበር ? ቤተ መንግስቱ ዋና ነገር በመሆን አደጋ ፈጥሮ ነበር ? ሰለሞን ከእግዚአብሄር ይልቅ ለራሱ የሚበልጥ ነገር ፈልጓል ?
በ ክፍል 62 ያለዉ የንፅፅር ዝርዝር፡ 1 ነገስት 9-10 ንጉሱ ኢየሱስ ከንጉስ ሰለሞን ጋር ሲወዳደር በመካከላቸዉ ያሉትን ታላቅ ልዩነቶች ይሰጣል ፤ እነዚህን ሁለት የግንባታ ስራዎች በምናወዳድር ጊዜ ቅድሚያ ላልተገባዉ(ያለስርዓት) እንደ ተሰጠ የሚነግር ይመስላል ፤ ይህ ፅሁፍ ለቤተ መንግስቱ የነበረዉ ወጪ በመልካምነት ልክ እንደ እግዚአብሄር በረከት ወይም የሰለሞን የተከፈለ ልብ ወይም ራስን በማዝናናት መጥፎ እንደ ነበር ግልፅ አይደለም ፡፡ አዲስ ኪዳን መዝናናት (መሞላቀቅ) ኃጢዓት ሊሆን እንደ ሚችል ያብራራል (ሉቃ 12፡ 17-21) ነገር ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ተቀባይ ሊሆን ይችላል ልክ የኢየሱስን ራስ እንደ ቀባቸዉ ሴትዮ (ማር 14፡ 3-9) ፡፡ ዋናዉ ነገር ስለ ገነባችሁት ነገር ሳይሆን የእግዚአብሄር ልብ ማግኘት ነው ፡፡ በ 1ነገስት ወደፊት ስንጓዝ እነዚህን ነገሮች እንዳትረሱ፡ 1) በሁለቱም የግንባታ ስራዎች ሰለሞን በግድ የተመለመሉ ሰራተኞችን (1 ነገ 5፡ 13-18) ፤ 2) ሰለሞን በእስራኤል ተቀምጠዉ የነበሩት እስራኤላዊያን ያልሆኑትን ይገዟቸዉ የነበሩ ባሪያ ሰራተኞችን ተጠቀመ (1 ነገ 9፡ 20-22) ፤ በመጨረሻዉ መዋቅሩ በኃይል ሰራተኞችን በጠቀም በህዝብ ዉስጥ ታላቅ ብስጭት ያስነሳል (ቁጥር 12) ፤ ይህ ሁሉ ከ 480 አመት በፊት ከባርነት ወጥተዉ ከነበሩ የሰዎች ቡድን መጣ ፡፡
1-ነገስት (7፡ 13-51)፡ ይህ ክፍል የቤተ መቅደሱን ግንባታ የመጨረሻ ክፍል እና የዉስጥ እቃዎችን ይሸፍናል ፡፡ ፀሀፊዉ የመቅደሱን ዝርዝር በጥቂቱ ያንቆለባበሰዉ ይመስላል ምናልባትም የቴክንካል እና የጥበበኞቸን ችሎታ ለእግዚአብሄር ክብር ተጠቅመዉት እንደ ነበር ያብራራል ፡፡ ይህንን ክፍል ስታነቡ ነገሮችን ለመፍጠር እግዚአብሄር የሰጣችሁን ስጦታ ለፈጣሪያችሁ ክብር እየተጠቀማችሁበት እንደ ሆነ ተመልከቱ ፤ የተገለፁት ሁሉም ነገሮች ትርጉም፣ ተፅዕኖ፣ ምስክርነት ወይም እንደ እይታ አጋዥነት አገልግሎት ነበራቸው ፡፡ ከእነዚህ ጥበበኛ ሰዎች አንዱ የነሀስ ባለሙያ የነበረው ጢሮሴያዊው ኪራም ነበር (ቁጥር 13-14) ፤ እያንዳንዳቸው 27 ጫማ ከፍታ እና 18 ጫማ ዙሪያ የነበሩ ሁለት ቀዳዳ የነሐስ ምሰሶዎች ሰራ ፤ በተጨማሪም ኪራም ሰባት ከግማሽ ጫማ ከፍታ የነበሩ በምሰሶዎቹ ላይ የሚቀመጡ ዓምዶችን አበጀ ፡፡ ዓምዱ እና ምሰሶዎቹ ሁለቱም በርብራብ ሸንተረር ስራዎች በአበባ ጉንጉን ሰንሰለት ስራዎች የተሸፈኑ ነበር (ቁጥር 15-20) ፡፡
ምሰሶዎቹ በኮሪደሩ ላይ ተተክለው ስም ተሰጣቸው - ለቀኙ አኡማድ (ምሰሶ) ያቁም ሲሆን ለግራዉ አኡማድ (ምሰሶ) ደግሞ በለዝ ነበር (ቁጥር 21-22) ፡፡ የምሰሶዎቹ ስም አስፈላጊ ነበር ፤ ያቁም የሚለዉ ስም ትርጉሙ “ ያቆመናል “፣ እንዲሁም የዳዊትን ዙፋን ለመመስረት የእግዚአብሄርን ተስፋ ለማጠናከር ተጠቅመዉበት የነበር እና ለመፈፀም የእግዚአብሄር ጥንካሬ( 2ሳሙ 7፡ 12-16) የሚል ነው ፤ በለዝ የሚለው ስም ትርጉሙ “ በእርሱ ጥንካሬ ነው “ የሚል ነው ፡፡ መዝ (21፡ 1 እና 13) በለዝ በሚለዉ ቃል ይጀምራልም ይጨርሳልም እንዲሁም በተጨማሪ የዚህን ጥንካሬ ስዕል ያካትታል ፡፡ ይህን በአንድ ላይ ስታስቀምጡት የዳዊትን ዙፋን ለመመስረት የእግዚአብሄርን ተስፋ በማቋቋም በእርሱ በመጠንከር ለመፈፀም የእግዚአብሄር ኃይል ይበልጣል ማለት ነው ፡፡
ቁጥር 26 በወርቅ ጥጃዉ ላይ ስለሚቀመጠዉ የዉሃ ማጠራቀሚያ ይገልፃል (እንዲሰሩት ተነግረዉ ስላልነበሩት) ፡፡ 11,000 ጋሎን ዉሃ በመንፃት ላይ የእግዚአብሄር ትኩረት ያሳያል ፤ አስታዉሉ በቤተ መቅደሱ ያልተጠሩ ሰባት ሻማ ማስቀመጫዎች ነበሩ ፡፡ ሰለሞን በራሱ ወርቃማ አበባ ነበረው ፤ ይህን ምእራፍ ስታነቡ የእነዚህን የሁሉንም ዝርዝር የተለየ ማስታወሻን ዉሰዱ ፡፡
በቁጥር 51 ቤተ መቅደሱ በመጠናቀቁ ንጉስ ሰለሞን የአባቱን የተቀደሱ ነገሮች ወደ ቤተ መቅደሱ አመጣ ፤ ነገር ግን ሰለሞን ቤተ መቅደሱን በተቀደሱት የአመቱ ወራት ሮሽ ሻሀናይ (አዲስ አመት)፣ ዮም ኪፐር (የስርየት ቀን) እና ሱኮዝ (የዳስ በዓል) በሚከበሩትን ሁሉ ለመለየት 11 ወራት ጠበቀ ፡፡ ለሚበልጥ ነገር ጠበቀ ፡፡ አሁን ቤተ መቅደሱ ለታቦቱ መምጣት ዝግጁ ነው ፡፡
መደምደሚያ
የሰለሞን ቤተ መቅደስ ክብር ትንፋሽ የሌለን አድርጎ እንደ ሚለቀን የሚታሰብ ነበር ፤ ግራይ ኢንሪንግ “ የክርስቶስ ተከታዮች ይህን ክብር አጥብቀን ስናስብ እንደ ጉባኤ እና እንደ ግል እንደ እግዚአብሄር ቤተ መቅደስ መገለፃችንን ማስታወስ እንደ ሚያስፈልገን “ ፅፏል (1 ቆሮ 3፡ 1-17፣ 6፡ 19-20) ፡፡ እግዚአብሄር ከህዝቡ የሚፈልገዉ መታዘዝን እንጂ ህንፃን አይደለም ፡፡ ቆይተዉ የእስራኤል ህዝቦች የቤተ መቅደሱ መገኘት የእግዚአብሄርን ቸርነት እንዳረጋገጠላቸዉ አመኑ ፤ በእርግጥ አንዳንድ የነቢዩ ኤርምያስ ጥብቅ ትምህርቶች ሀሰት የሆነዉን እምነት በማስተካከል ነበሩ ፡፡
የ 1ነገስት አንባቢ ቤተ መቅደሱ ከእግዚአብሄር መለኮታዊ ፍርድ እንዳላዳናቸዉ ያውቃል ምክንያቱም በምርኮ በባቢሎን እያሉ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህን ቃሎች እያነበቡ እና እየሰሙ ስለ ነበር ፤ መቅደሱ መዉደም ላይ ነበር ፡፡ ነገስት ተፅፎ የነበረዉ አንዱ በዚያ ምክንያት ነው - በስደት በባቢሎን ለአይሁዶች ጥያቄን ለመመለስ፡ ይህን እንዴት አገኘነው ? ከዚህ የምንወስደው በማንኛዉም ጊዜ ለእግዚአብሄር ለመታዘዝ ተቀያሪ ስንጠቀም እግዚአብሄር ፍርድን ያመጣል ነው ፡፡
Gary Inrig, Holman Old Testament Commentary: 1 & 2 Kings (Nashville: Broadman & Holman, 2003), p. 43.
ጥያቄዎች
-
ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ለመስራት ምን ያክል ጊዜ ፈጀ ? የራሱንስ ቤት ለመስራት ምን ያክል ጊዜ ወሰደበት ? በራሱ ህይወት ምቾት እና መደላደልን ስለ መፈለጉ ይህ ምን ያሳያል ?
-
የሁለቱ የነሀስ ምሰሶዎች ስም ምን ነበር ? እነዚህ ሁለት ስሞች ምን ማለት ናቸው ? ከእግዚአብሄር ባህሪይ ጋር እንዴት ይገናኛል ?
-
በ 1ነገ (7፡ 48) የገጹ ኅብስት አስፈላጊነት ምን ነበር ? (ዘሌ 24፡ 5-8)
-
በዛሬዉ ደረጃም እንኳን ቤተ መቅደሱ የሚያስደንቅ ነበር ፤ ይህን የሚያምር ቤተ መቅደስ አንድ አይነት ለነበረው ለእግዚአብሄር ለመገንባት የረዳዉን ተመሳሳይ ሰዉ ለማወቅ በሀሳባችሁ ዉስጥ ምን ይመጣባችኋል በኃጢዓቱ ምክንያት ለእስራኤል ፍርድ አምጥቷል ? (1ነገ 11፡ 6)
-
በ 1ነገስት 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 7:1
“Solomon completed his entire palace complex after thirteen years of construction.”
ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ብቻ አልነበረም ሰባት ዓመት የፈጀው በተጨማሪም ለእርሱና ለቤተሰቡም በጣም የረቀቀ ቤተ መንግስት ለመገንባትም አስራ ሶስት አመታት ፈጅቶበታል ፡፡ የቤተ መቅደሱ ዝርዝር እየተብራራ ሳለ የእግዚአብሔር መገኘት ማረፊያ ቦታ እንድሁም የቤተ መቅደሱ ዝርዝር ረቀቅ ባለ መልኩ ተገልጧል ፡፡ በመጨረሻም የመጨረሻ የሆነውን የቤተ መቅደሱን ዝርዝር በማውጣት ግንባታው ተጠናቋል ፡፡ ሰለሞን የተቀባው የእግዚአብሔር መገኘት ይቀመጥበት ዘንድ ቤተ መቅደስ እንድገነባ ነበር ፡፡ ከዚያም በኋላ ቤተ መቅደሱን በመገንባት ላይ ሳለ በተጨማሪ ትልቅና ሰፊ የሆነ ቤተ መንግስትም ገነባ ፡፡
በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ሳለህ ተደናቅፈህ ታውቃለህ ? የምትጸልይበትና ቃሉን የምታነብበት ጊዜ ይኖርህ ይሆናል ፤ በድንገት ወደ ሶሻል ሚድያ ስትገባ ወይም ራስህን የት ሄደህ እንደምትገዛ ስታስብ ስታገኘው ወይም የመጨረሻውን የእግር ኳስ ጨዋታ ማን እንደሚያሸንፍ ስታሰላስል ? በእግዚአብሔር ላይ ትኩረትህን አድርገህ እንዳትቆይ አሳብህን ለመስረቅ አለም ብዙ ነገር አላት ፡፡ ጌታ ልብህን በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንጂ በምድር ባሉት ላይ እንዳታደርግ ይነግርሃል ፡፡ በቅድምያ መንግስቱንና ጽድቁን ፈልግ ከዚያ ሌላው ሁሉ ይጨመርልሃል ፡፡ በእርሱ መገኘት ላይ ስታርፍና ሰታተኩር ሙሉ ደስታን ታገኛለህ ፡፡ ምናልባት ለሰላም ወደሚጋብዙህ ነገሮችን ታይ ይሆናል እየቀረበ ሲሄድ ግን ልብህን በክርስቶስ ላይ ማድረግ ብቻ ነው ፍጹም በሆነ ሰላም ውስጥ አንድትኖር የሚያደርግህ ፡፡ ዛሬም በክርስቶስ ላይ አትኩር ፡፡
“ ሰሎሞንም የራሱን ቤት በአሥራ ሦስት አመት ሠራ የቤቱንም ስራ ሁሉ ጨረሰ ፡፡ ”
- 1ኛ ነገሥት 7፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 5፡1-2 –“ ልጄ ሆይ ወደ ጥበቤ አድምጥ ጆሮህን ወደ ትምህርቴ መልስ ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንድጠብቁ ፡፡ “
ኢሳይያስ 26፡3 –“ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠበቃታለህ ፡፡ “
ቄላስያስ 3፡1-2 –“ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።