Historical Books 1 Kings

Solomon's Temple

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 258 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ነገስት መፅሀፍት ዉስጥ እየሄድን ነው ፤ በቀደምት ታሪክ ስንኝ ለማጣት ቀላል ሊሆን ይችላል ፤ በእነዚህ ታሪኮች እና ስሞች ላይ ለመዝለል ፈታኝ ሊሆን ይችላል ፤ ይሁን እንጂ እነዚህን ታሪኮች በማጥናት የክርስቲያኖች ህይወት የሚጠቀምበት ወቅቶች አሉ ፡፡ እንዳትዘሉዓቸዉ አበረታታችኋለሁ ፤ ከመፅኀፍ ልናገኝባቸዉ የምንችለበት ብዙ መንገዶች አሉ ፡፡ በዚህ ፅሁፍ የሰለሞን ቤተ መቅደስ መገንባትን እናያለን ፡፡

ትምህርት

1-ነገስት (5፡ 1)፡ ሰለሞን የተቀባ ንጉስ እንደ ነበር ነገሩን በሰማ ጊዜ የጢሮስ ንጉስ ኪራም አገልጋዮቹን ወደ ሰለሞን ለከ ፡፡ ኪራም የዳዊት ምርጥ ጓደኛ ነበር ፡፡ ሰለሞን የመንግስት አስተዳደር ትርጉሙን እና ከአባቱ ዳዊት ጋር ያለዉ ህብረትን አስፈላጊነት እንደ ተማረ አምናለሁ ፡፡

1-ነገስት (5፡ 2-5)፡ ሰለሞን ለኪራም አባቱ በዙሪያዉ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ቤተ መቅደሱን መገንባት እንዳልቻለ በመግለፅ መለሰለት ፤ ሰለሞን በተጨማሪም ሰላምን እየኖረበት በመሆኑ ምክንያት የአባቱን መቅደስ ለመስራት እንዳቀደ አጋራው ፡፡

በ 2ሳሙ (7፡ 2) የእግዚአብሄርን ቤት ለመስራት አቅዶ የነበረዉ ዳዊት ነበር ፤ ዳዊት የሚኖርበትን የእግዚአብሄር መገኘት ከነበረበት ጋር በማነፃፀር መቅደሱን ለመስራት በመወሰን ተፈጥሮአዊ ምክንያቶችን እየተጠቀመ እንደ ነበር አምናለሁ ፡፡ እግዚአብሄር ናታንን ወደ ዳዊት በመሄድ መቅደሱን ለመስራት ጊዜዉ እንዳልሆነ እንዲነግረዉ ነገረው ፤ የቤተ መቅደሱ መሰራት በዳዊት ሳይሆን በእግዚአብሄር ጊዜ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሄራዊ ነዉ ብለን የምናምንበትን ግላዊ ምርጫችንን ለማስገባ ቀላል ነው ፡፡ ጥያቄው እግዚአብሄር እንዴት እንድናመልከዉ ይፈልጋል እና እኛ እንዴት ልናመልከዉ እንፈልጋለን የሚል ነው ?

1-ነገስት (5፡ 6-9)፡ ሰለሞን ኪራምን ዝግባ ምርጥ እንጨት እንደ ነበርና የኪራም ሰዎች እንጨቶቹን ለመቁረጥ የተመረጡ ነበሩ ነገረዉ ፤ ከዚያም ሰለሞን ኪራምን ዛፎችን እና ሰራተኞችን በማቅረብ የግንባታ ስራዉን እንዲደግፈዉ ጠየቀዉ ፡፡ ሰለሞን ለዛፎቹ፣ ለሰራተኞቹ እንደ ሚከፍል እና ፕሮጀክቱን ለመርዳት አገልጋዮቹንም እንደሚሰጥ ቃል ገባለት ፡፡ ኪራም የሰለሞንን እቅድ በሰማ ጊዜ ተደሰተ ፡፡

1-ነገስት (5፡ 10-12)፡ ሰለሞን ለኪራም ስራዉ እንደ ቀጠለ 125,000 መስፈሪያ ስንዴ እና 1,160 ጋሎን ዘይት በየአመቱ ላከ ፡፡ እግዚአብሄር ለሰለሞን በሰጠዉ ጥበብ ምክንያት በሰለሞን እና ኪራም መካከል ሰላም እና ህብረት ነበር ፤ እግዚአብሄር ሰለሞንን እንደ ሰላም ጠባቂ አሰልጥኖታል ፡፡

1-ነገስት (6፡ 1-6)፡ ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደሱ እስራኤላዊያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ እስከ 480 አመት አልተሰራም ነበር ፤ ቤተ መቅደሱ 125 ጫማ እርዝመት፣ 42 ጫማ ስፋት እና 62 ጫማ ከፍታ ነበር ፡፡ ለትልቅ ቤተ ክርስቲያን ስንጠቀም ስለ ሰለሞን ቤተ መቅደስ መጠን እና በጌጥ የመዋቡን ዝርዝር ለመረዳት አስቸጋሪ ነው ፡፡

1-ነገስት (6፡ 7)፡ የመቅደሱን ዉጨኛዉን ቅጥር ለመስራት የተጠቀመበት ድንጋይ ቀድመዉ የተቆረጡ ስለ ነበር በእግዚአብሄር ቤት ድምፅ አይኖራቸዉም ፡፡ አንድ ሰዎች ቤተ መቅደሱን በተመለከቱት ጊዜ በዉጪ ድንጋይ እንዲሁም ደግሞ በዉስጥ ወርቅ ያያሉ ፡፡

1-ነገስት (6፡ 14-38)፡ ዉስጡ በፅዶች እና በአንድ ላይ የሚገጣጠሙ የመስሪያ እቃዎች የተሰራ ነበር ፣ በንፁህ ወርቅ የተሸፈነ ስለ ነበር ሸካራ እንጨት እና ሌሎች እቃዎች በየግላቸዉ አይታዩም ነበር (ቁጥር 21-22) ፡፡

ቁጥር 23 የመቅደሱን ዉስጥ ጌጣጌጥ(መዋብ) በዝርዝር ይገልፃል ፡፡ 10 ክንድ ቁመት እና ስፋት(21 ጫማ ቁመት እና 21 ጫማ ስፋት) በነበረዉ ቅድስተ ቅዱሳኑ ላይ የተሰሩ ሁለት ኪሩቤሎች ነበሩ ፤ በመፅሀፍት ኪሩቤል የት ላይ ነበር ? መጀመሪያም በግምት 5ጫማ ከፍታ በነበረዉ ታቦት ላይ የተቀመጠ ሁለት ኪሩቤል ነበር ፡፡ የአዲሱ ኪሩቤል ክንፍ ቅድስተ ቅዱሳኑን በመሸፈን ዉጨኛዉ ክንፎቹ የዉጨኛዉን ቅጥር ሲነካ ዉስጠኛዉ ክንፎቹ ደግሞ የሌላኛዉን ኪሩቤል ክንፍ ይነካል ፡፡ ሀሳቡ የስርየት መቀመጫዉ እግዚአብሄር ሊያርፍበት የመጣበት ነበር ነገር ግን ሰለሞን ለእግዚአብሄር ክብር ማደሪያ ቤተ መቅደስን ለመስራት እየሞከረ ነበር (2 ሳሙኤል 7) ፡፡

1-ነገስት (6፡ 11)፡ ወደ ቁጥር 11 ዘለን እስኪ እንመለስ ፤ በመቅደሱ ይህን ሁሉ ዉበት በመግለፅ መካከል ላይ እግዚአብሄር ለሰለሞን “ ትዕዛዜን የምትከተል ከሆነ በዚህ ስፍራ አድራለሁ “ አለው ፤ አሪፍ ስለ ሆነ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ አድራለሁ አላለም ፡፡ በሰለሞን መታዘዝ እግዚአብሄር እመጣለሁ አለ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በራሳችን መንገድ እና ሀሳብ መስራት እንፈልጋለን ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር አንድ ነገራችንን ይባርካል - መታዘዛችንን ፡፡ እግዚአብሄርን ወደ ራሴ ምርጫ ለማጣጣም በመሞከሬ እገረማለሁን ? የሰለሞን ቤተ መቅደስ ለእግዚአብሄር የመጀመሪያዉ ቋሚ ማደሪያ ስፍራ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ስንዘጋው አዲስ ኪዳን ላይ ማን እንደ ሆንን እንመልከት ( 1 ቆሮ 3፡ 16-17) ፤ ጳዉሎስ የእግዚአብሄርን መንፈስ ስለተቀበልነዉ ስለ ሁላችንም ይናገር ነበር ፤ አሁን እግዚአብሄር የሚያድርብን ቤተ መቅደሶች ነን ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እግዚአብሄር ሊያንቀሳቅሰን እና ሊመራን ይችላል (ሐዋ 7፡ 44-50) ፡፡ ሀሳባችንን እና ምርጫችንን ከእግዚአብሄር ፍላጎት በላይ ለማስቀመጥ በፈለግን ጊዜ እግዚአብሄርን መልሰን በመቅደስ ዉስጥ ወይም በሚያምር ሳጥን ዉስጥ ለማስቀምጥ በምንሞክር ጊዜ ያስደንቀኛልን ? ፀሎቴ ማምለክ እና መርካት እንዲሆን እንጂ የሚይዝ እና የሚያስጨንቅ ነገር እንዳላደርግ እግዚአብሄር እንዲረዳኝ ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ኪራም ሁልጊዜ ዳዊትን እንደሚወደዉ እንዴት አሳዬ (2ሳሙ 5፡ 11፣ 2ዜና 2፡ 3) ? በዳዊት እና በኪራም መካከል የነበረዉ ግንኙነት ለሰለሞን እንዴት ጠቀመው ?
  2. ዳዊት እንደ ንጉስ በአገዛዙ ጊዜ መቅደሱን መገንባት ለምን አልቻለም (1ዜና 22፡ 8) ? ሰለሞን በስልጣን ዘመኑ ጊዜ መቅደሱን መገንባት ለም ቻለ ? (1 ነገ 4፡ 24)
  3. በዳዊት የህዝብ ቆጠራ መሰረት መቅደሱን መገነንባት ለመርዳት ምን ያክል ሰዉ ነበር ያለው (2ሳሙ 24፡ 9) ? ምን ያክል እስራኤላዊያን ሰዎችን ሰለሞን ተጠቀመ ?
  4. አይሁዶች እና አሕዛቦች ሁለቱም በመቅደሱ ግንባታ ላይ መሳተፋቸዉ(መረዳዳታቸው) ለምን አስፈላጊ ሆነ ? (ኢሳ 49፡ 6፣ 56፡ 6-7፣ ማቴ 21፡ 13፣ ኤፌ 2፡ 11-22)
  5. በቤተ መቅደሱ ግንባታ ጊዜ እግዚአብሄር ለሰለሞን ለምን እንደተናገረዉ ምን ታስባላችሁ (1ነገ 6፡ 11-13) ? በሚገለገል ጊዜ ለእግዚአብሄር በጣም ጥቅሙ ምንድን ነው ? (ኤፌ 6፡ 6)
  6. በ 1ነገስት (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 6:11–13

“The word of the LORD came to Solomon: ‘As for this temple you are building—if you walk in My statutes, observe My ordinances, and keep all My commands by walking in them, I will fulfill My promise to you, which I made to your father David. I will live among the Israelites and not abandon My people Israel.’”

ለንጉስ ሰለሞንና ለእስራኤል የእረፍት ዘመን በመጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መገኘት መኖርያ ቦታን ያገኝ ዘንድ ቤተ መቅደስ መስራት ጀመረ ፡፡ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ይሰራ ዘንድ ጥበበኞችንና የተካኑ ሙያተኞችን ተጠቅሟል ፡፡ በግንባታውም መሀል ሀሳቡን ያሳውቀው ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሰለሞን መጣ “ በሥርአቴ ብትሄድ ፍርዴንም ብታደርግ ትመላለስበትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ ለአንተ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ “ ፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን የሚጠብቀው የመቅደሱ ግርግዳ በጌጥ ያገጤ ከሆነና የወርቅ ምንጣፍ ያለው ከሆነ ብቻ ነው አላለም ፡፡ እግዚአብሔር ለሰለሞን ደግሞ ያሳወቀው የእርሱ ፍለጎት በመንገዱ ይሄድ ዘንድ ብቻ መሆኑን ነው ፡፡

እግዚአብሔር የአንተ ሰውነት የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጥህ ይኖራል ፡፡ እግዚአብሔር ውጫዊውን ሰውነት ቆንጆ አድርገህ እንድታስደስተው አልጠየቀህም ፡፡ መንገዱን እንድትከተል ነው የጠየቀህ ፡፡ እውነተኛ ውበት ከውስጥ ነው ሚፈልቀው ፡፡ አሁን ራስህን ጠይቅ “ ውጫዊውን ቤተ መቅደሴን በመገንባት ላይ ነው ያተኮርኩት ወይስ በውስጤ ያለውን መንፈስ ቅዱስ በመከተል ላይ ? በመንገዱ ስትሄድ በውስጥ ያለ ውበት ወደ ውጪ ይንጸባርቃል ፡፡

“ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ሰለሞን መጣ እንድህ ሲል ስለዚህ ስለምትሰራው ቤት በስርአቴ በትሄድ ፍርዴንም ብታደርግ ትመላለስበትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ ፡፡ በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ ህዝቤንም እስራኤልን አልጥልም ፡፡ “

  • 1ኛ ነገሥት 6፡11-13

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳያስ 66፡2 –“እነዚህን ሁሉ እጄ ሰርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሁት መንፈሱም ወደ ተሰበረ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ፡፡ “

1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16 –“ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? “

1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20 –“ ወይስ ስጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን ? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም ስለዚህ በስጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ ፡፡ “