Solomon's Wisdom
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ መሄዳችንን ስንቀጥል ያጠናነዉ እያንዳንዱነገር አብሮ መሄድ የሚችል ይመስላል ፡፡ እያንዳንዱ መፅኀፍት ስለ ምን እንደ ነበር ሊያስታዉሰን በሚችለዉ ስዕል ላይ እንደ መመልከት ነዉ የሚሰማኝ ፡፡ በሁሉም ጥናታችን ላይ መሲሁን ለመመልከት እንድንቀጥል አፈልጋለሁ ፤ በ 1ነገስት መፅኀፍ ዉስጥም አለ ፤ በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ ስንሄድ ስለ መጣዉ መሲህ እንዴት እንደሚያመለክቱ እንድንመለከት እፈልጋለሁ ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት (3፡ 1)፡ ይህ ጥቅስ የሰለሞን ህይወታ ታላቅ ማጠቃለያ ነው ፡፡ ሰለሞን የግብፁን ንጉስ የፈርዖንን ልጅ በማግባት አንድነት አደረገ ፤ ሰለሞን ቤተ መንግስቱን እየሰራበት በነበረው፣ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ በነበረበት እና በኢየሩሳሌም ዙሪያ ቅጥር በነበረበት ወደ ዳዊት ከተማ መጣች ፡፡
1-ነገስት (3፡ 2)፡ በዚህ ጊዜ ሰዎች መስዋዕት በከፍታ ቦታ መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ምክንያቱም ቤተ መቅደስ ስላልነበር (1 ነገ 1፡ 7-13) ፡፡ አዲሱ ቤተ መቅደስ ከተጨረሰ በኋላ በከፍታ ቦታ መሰዋት ተወገዘ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 3-4)፡ ሰለሞን ወደ አንዱ ኮረብታ ስፍራ በመሄድ መስዋዕት በማድረግ እጣን አነደደ ፤ ከዚያም ወደ ገባዖን ተጓዘ ምክንያቱም በእስራኤል ታዋቂ ኮረብታ ስለ ነበር ፡፡ በዚያ 1,000 የሚቃጠል መስዋዕት አቀረበ ፤ ገባዖን ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን ሰባት ማይል ነበረች እንዲሁም የሙሴ የድንኳኑ ማደሪያ እና የንሀሱ ታቦት ከመጀመሪያዉ ተገንብቶበት ከነበረዉ ተመሳሳይ ቦታ ነበር ፡፡
1-ነገስት (3፡ 5)፡ ገባዖን ላይ በምሽት በህልም እግዚአብሄር ለሰለሞን ተገለጠለት ፤ እግዚአብሄር ሰለሞንን “ ምን እንድሰጥህ ለምን ? “ እግዚአብሄር ሊናገረን ህልም እና ራዕይ ይጠቀማል ፡፡ ህልሞቻችሁን ዋጋ ቢስ እንዳታደርጉ ፤ ህልም ካላችሁ ከእግዚአብሄር ሊሆን ይችላል ብላችሁ በማሰብ ፃፉት፣ ህልሙ ስለ ምን እንደ ሆነ ፀልዩምን እንደሚያስቡ ለማየት ለሌላ ሰዉ አጋሩት ፡፡ ኢዩ (2፡ 28) እና ሐዋ (2፡ 17) ሁለቱም ህልም እና ራዕይ በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደሚሆኑ ይናገራሉ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 6-7)፡ ሰለሞን ምንም ነገር ከመጠየቁ በፊት ለእግዚአብሄር ምስጋና አቀረበ ፡፡ ብዙዎች ሰለሞን በዚያን ጊዜ በግምት 20 አመት አካባቢ እንደ ነበር ያምናሉ ፡፡ የእግዚአብሄርን ተስፋ እና ትልቅ ስዕል ተረድቷል እንዲሁም በጣም ልጅ እንደ ነበር አዉቋል (1 ጢሞ 4፡ 12) ፤ የእግዚአብሄር እርዳታ እንደሚያስፈልገዉ አዉቋል ፡፡
1-ነገስት (3፡ 8)፡ ሰለሞን እንደ ንጉስ ከ 4,000,000 ሰወች በላይ እንዳገለገለ ይታመናል ፤ የ 2ሳሙኤል (24፡ (0 ፀሀፊ በእስራኤል 800,000 ተዋጊ ሰዎች እና በይሁዳ ደግሞ 500,000 ተዋጊ ሰዎች እንደ ነበሩ ፅፏል ፤ ሴቶችን፣ ልጆችን፣ ሽማግሌዎችን እና መዋጋት የማይችሉትን ሰዎች ስትጨምሩበት ብዙ ህዝብ ነው ፡፡ ሰለሞን ለእግዚአብሄር እና ለአባቱ የገባዉን ቃል ኪዳን ለማክበር ፈለገ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 9)፡ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመዳኘት በክፉ እና በበጎዉ መካከል ለመለየት ታዛዥን ልብ ጠየቀ ፤ ሰለሞን ምሳሌ (4፡ 5-7) ፅፏል ፡፡ የጥበብን ዋጋ ስላዬ በጥሪዉ መሄድ የሚችል እንዲሆን ፈለገ ( 1ቆሮ 1፡ 24፣ ያዕ 1፡ 5) ፡፡
1-ነገስት (3፡ 11-13)፡ ሰለሞን ታዛዥ ልብ ጠየቁ እግዚአብሄርን አስደሰተው እግዚአብሄርም የሰለሞንን ጥያቄ ሰጠው ፤ እግዚአብሄር ሰለሞንን ጥበበኛ እና የሚያስተዉል ልብን ሰጠው ፡፡ ሰለሞን በመለኮታዊ የተለየ ነበር ፤ የሰለሞን ራስን መሰረት ባላደረገ ጥያቄዉ መሰረት እግዚአብሄር በሀብት እንዲሁም በክብር ባረከው ፡፡ የሰለሞንን መንግስት የሚያክል አልነበረም ፡፡
1-ነገስት (3፡ 14)፡ እግዚአብሄር ሰለሞንን መንገዱን የሚጠብቅ እና አባቱ ንጉስ ዳዊት ያዘዘዉን መንገድ ካደረገ ረጅም እድሜ እንደሚኖር ነገረው (መዝ 90፡ 10) ፡፡ ዳዊት ከ 70 አመት በፊት ሞተ እንዲሁም ደግሞ ሰለሞን 70 አመት አካባቢ ሞተ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 15)፡ ሰለሞን ነቃ ህልም እያየም እንደ ነበር አወቀ ፤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመሄድም በእግዚአብሄር የኪዳን ታቦት ፊት መስዋዕት አመጣ ፤ ግብዣም አደረ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 16-22)፡ በግብዣዉ መካከል ላይ ሁለት ጋለሞታ ሴቶች የሰለሞን ፍርድ የሚያስፈልገዉን ሁኔታ አቀረቡ ፡፡ እነዚህ ሁለት ሴቶች ተመሳሳይ ቤት ዉስጥ ይሆራሉ ሁለቱም በቅር የወለዷቸዉ ልጆች ነበሯቸው ፤ አንዷ ሴት በመሸ ጊዜ የሌለኛዋ ልጅ እንደ ሞተ ተናገረች ፤ ያቺ ሴት በመነሳት የሌለኛይቱን ልጅ በመዉሰድ የኔ ነዉ በማለት ተናገረች ፡፡ ይህ ማስረጃ ለሰለሞን እንደ ቀረበለት ሌለኛዋ ሴት በመናገር “ የሞተዉ ነዉ የአንቺ ልጅ አለች “ ፤ ሴቶቹ በንጉሱ ፊት መከራከር ጀመሩ ፡፡
1-ነገስት (3፡ 23-25)፡ ሰለሞን ሰይፉን እንዲሰጡት በመጠየቅ ፤ ሴቶቹን ህይወት ያለዉን ልጅ እንደሚከፍለዉ እና እያንዳንዳቸዉ ግማሽ እንደ ሚቀበሉ ነገራቸው ፡፡
1-ነገስት (3፡ 26-27)፡ እዉነተኛ እናቱ በጭንቀት እና በርህራሄ ተሞላች ፤ ሲገደል ከማየት ልጇ ሰጠች ፤ ሌለኛይቱ ሴት ንጉሱን በመቀጠል ልጁን በግማሽ እንዲቆርጠዉ ነገረችዉ ፡፡ ከዚያም ሰለሞን ለልጁ ትክክለኛዉ እናት ለመጀመሪያይቱ ሴት ልጁን ሰጠው ፡፡
1-ነገስት (3፡ 28)፡ መላዉ እስራኤል ስለ ሰለሞን ጥበብ ሰሙ ፈሩም ፡፡ የእግዚአብሄር ጥበብ ከእርሱ ጋር እንደ ነበረች አወቁ ፡፡
መደምደሚያ
ሰለሞን ማንኛዉንም መጠየቅ በቻለ ጊዜ ጥበብን ጠየቀ ፡፡ በዚያም ጥበብ የሰለሞን የስልጣን ዘመን ሰላም ነበር ፡፡ መፅሀፍ ቅዱሳዊዉ ምሁር ጳዉል ቫን ጎርደር የሰለሞን አገዛዝ ታዋቂ ሆኖ የነበረበትን አምስት ምክንያቶች ይሰጣል፡
- ጥበብ (1 ነገ 3፡ 9-12፣ 4፡ 29-34)፡ በማቴ (12፡ 14) ንግስት ሳባ የሰለሞንን ታላቅ ጥበብ ለመስማት መጣች ፤ አግኝታ የነበረው በእስራኤል ከሰለሞን የሚበልጥ ነገር የእግዚአብሄር መገኘት እንደ ነበር ነው ፡፡ በ 1 ነገ (3፡ 9-12) ያለዉ ጥበብ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ኢሳ (11፡ 2-4) ስለ ኢየሱስ ተንብዮ ነበር ፤ ሰለሞን እና ኢየሱስ ሁለቱም ጥበብ አላቸው ነገር ግን የኢየሱስ ጥበብ ይበልጣል ፡፡
ሰላም እና ብልፅግና (1 ነገ 4፡ 25)፡ ይህ በተለየ አገር ሰላም እና ብልፅግና ያልተለመደ ነበር (1 ነገ 4፡ 25፣ ሚክ 4፡ 3-4) ፤ ከሰለሞን የሚበልጠዉ ኢየሱስ ነበር ፡፡
የመቅደሱ መገንባት (1 ነገስት 5-7)፡ ይህ የሰለሞን አገዛዝ ከፍ ያለ ቦታ ነበር (ሕዝቄል 40-49፣ 2ተሰ 2፡ 3-4፣ ራዕ 11፡ 1-2) ፡፡ መሲሁ በሚመለስ ጊዜ ሰዎስተኛ ቤተ መቅደስ ይኖረናል ፡፡
እግዚአብሄር መቅደሱ ይገባል (1 ነገስት 8)፡ የቤተ መቅደሱ ስራዎች በመጠናቀቅ ተቀደሱ (ሚክ 4፡ 2) ፡፡
ከንግስት ሳባ ጉብኝት (1 ነገስት 10)፡ ህዝቦች በመምጣት ይሰግዱለታል (ዘካ 14፡ 8-9፣ 16) ፤ ስለ ሰለሞን ሁሉም ነገር ወደ ሚበልጠዉ ያመለክታል ፤ በማቴ (12፡ 42) ኢየሱስ “ ከሰለሞን የሚበልጥ በዚህ አለ “ ፡፡
Paul R. Van Gorder, The Old Testament Presents . . . Reflections of Christ: 1 Kings, available online at http://www.thebookwurm.com/ref-1kin.htm.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር ለሰለሞን በህልም በመገለጥ እግዚአብሄር ምን እንዲሰጠዉ እንደ ሚፈልግ በጠየቀው ጊዜ ሰለሞን ምን ጠየቀ ? ሰለሞን እንዴት ትህትና አሳዬ ? (1 ነገ 3፡ 6-9)
-
ሰለሞን ከጠየቀዉ በተጨማሪ እግዚአብሄር ምንድን ነገሮችን ሊጨምርለት ቃል ገባ ( 3፡ 13-14) ? ይህ ወደ 1 ነገስት ጭብጥ የሚበልጠዉ ነገር ወደ ሚለው እንዴት ያመለክታል ? ( 1ነገ 1፡ 47፣ ዕብ 1፡ 8-9)
-
በሁለቱ ገለሞታ ሴቶች መካከል ከሰለሞን ፍርድ በኋላ መላዉ እስራኤል ሰማ ፈሩም ምክንያቱም ፍትህን እንዲያሰፍን የእግዚአብሄር ጥበብ በእርሱ ላይ እንደ ነበር ስላዩ ፤ ይህ ለምን ለፍራት ምክንያት ይሆናል ? (ኢዮ 12፡ 22፣ መዝ 72፡ 4-5፣ ምሳ 15፡ 12፣ 21፡ 15፣ 2ቆሮ 5፡ 10)
-
1ነገ (4፡ 20) እስራኤል እና ይሁዳ እንደ ባህር ዳር አሸዋ ብዙ እንደ ነበሩ ይናገራል ፤ ይህ የየትኛዉ ትንቢት መፈፀም ነው (ዘፍ 22፡ 17) ? ይህ እግዚአብሄር ተስፋዉን መፈፀም እንደ ሚቀጥል መተማመን ያመጣል? (2ቆሮ 1፡ 20)
-
የሰለሞን ጥበብ የምስራቅ ልጆችን ጥበብ እና የግብፃዊያንን ሁሉ ጥበብ በለጠ ፤ የክርስቶስ አይነት የሆነዉ እንዴት ነው ? (ማቴ 12፡ 42፣ 1ቆሮ 1፡ 30፣ ቆላ 2፡ 2-3)
-
በ 1ነገስት (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 3:9
“So give Your servant an obedient heart to judge Your people and to discern between good and evil. For who is able to judge this great people of Yours?”
እግዚአብሔር በህልም ለሰለሞን ተገለጠለት እንድህም አለው “ ምን እንድሰጥህ ለምን ? “ ሰለሞንም ጥበብን ጠየቀ ፤ በህዝቡ ላይ መፍረድ ይችል ዘንድ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ አስተዋይ ልቦናን ፈለገ ፡፡ እግዚአብሔርም በሰለሞን ጥያቄ ደስ ተሰኘ ፡፡ ሰለሞንም እንደ ንጉስ ጥሪውን ሲያራምድ የለመነውን ጥበብ እግዚአብሔር እንደሰጠው ለሁሉም ተገለጠ ፡፡ በትህትና ጥበብን ስለለመነ እግዚአብሔር ጨምሮ ባለጠግነትንና ክብርን ሰጠው ያለ ልክም ባረከው ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔርን የሆነ ነገር መጠየቅ ብትችል ምንድን ነው ምትጠይቀው ? አድስ ቤት ? የተስተካከለ ግንኙነት ? ከበሽታ መፈወስ ? እንድህ እንድህ እያለ ይቀጥላል ፡፡ ግን ጥበብን ለምነህ ታውቃለህ ? ዛሬ ጀምር ፡፡ በቀን ውሎ አጋጣሚዎችህ ትልቅም ይሁን ትንሽ ውሳኔ ለመወሰን ጥበብን ከእግዚአብሔር ለምን ፡፡ ምን እንደምትበላ ፣ የት እንደምትሰራ ፣ ልጆችህን እንዴት እንደምታሳድግ ፣ በአስቸጋሪ ትዳር ውስጥ ያለ ጓደኛህን ምን እንደምትመክር ወይም ወንጌልን እንኳ ለማን እንደምትናገር እርሱን ጠይቅ ፡፡ እግዚአብሔር በልግስና ጥበብን ይሰጥህ ዘንድ ይፈልጋል ፡፡
“ ስለዚህም በሕዝብህ ላይ መፍረድ ይችል ዘንድ መልካሙንና ክፉውንም ይለይ ዘንድ ለባሪያህ አስተዋይ ልቡና ስጠው አለዚያማ በዚህ በታለቅ ሕዝብህ ላይ ይፈርድ ዘንድ ማን ይችላል ? “
- 1ኛ ነገሥት 3፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 4፡6-7 –“ አትተዋት ትደግፍህማለች ውደዳት ትጠብቀህማለች ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ ፡፡ “
ያዕቆብ 1፡5 –“ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን እርሱም የሰጠዋል ፡፡ “
ያዕቆብ 3፡ 17 –“ ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት በኋላም ታራቂ ገር እሺ ባይ ምህረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።