David's Last Words
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ሳሙኤል 23 ከሞላ ጎደል የዳዊትን የመጨረሻዉን ቃል አይተነዋል ፤ እነዚህ ጥቅሶች እንደ ንጉስ ከተቀመጠ በኋላ ዳዊት ለልጁ ለሰለሞን የነበረዉ የመጨረሻ ቃሎች ነበሩ ፡፡ በመፅሀፍት ዉስጥ የምናየዉ በተለይም በእነዚህ ጥቅሶች ድርጊት ዉጤት እናዳለው፣ ምህረት እንደሚያስፈልገዉ እና መታመን እንደ ሚገኝ ነው ፡፡ በዚህ ምዕራፍ በታየዉ ፀጋ መጠን የምንገረም እንሆናለን ፤ ዛሬ የዚህን ምዕራፍ እያንዳንዱ ሀሳብ ከዳዊት እስከ ሰለሞን በአንድ ላይ እንዴት እንደሚጣጣም እናያለን ፡፡
ትምህርት
1-ነገስት (2፡ 1-3)፡ የመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ከዳዊት ለሰለሞንየእግዚአብሄር ቃል እንዲያከብር በማነቃቃት መንፈሳዊ ኃላፊነቶች ነበሩ ፤ እነዚህ ቁጥሮች ለሰለሞን ቁልፍ ቁጥሮች ነበሩ ፤ የዳዊት ማበረታታት ለሰለሞን እግዚአብሄር የሚፈልገዉን እንዲያደርግ ነበር ፡፡ ይህ ለምን ነበር ያስፈለገው ? ምክንያቱም መታዘዝ ወደ በረከት ስለሚመራ ፡፡ በህይወት አኗኗር ዉስጥ ለእግዚአብሄር ቃል መታዘዝንየሚተካዉ ነገር የለም ፤ ለእኛም እዉነቱ ተመሳሳይ ነው ፤ ኢየሱስ “ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለቱ ላይ የሰራን ልባም ሰዉን ይመስላል አለ “ (ማቴ 7፡ 24) ፡፡
1-ነገስት (2፡ 4)፡ ሰለሞን የዳዊት ልጅ ነበር እግዚአብሄርም ዳዊትን የማያቆም መንግስቱን ቃል ገብቶለት ነበር (2 ሳሙ 7፡ 14-16) ፤ ነገር ግን ይህ የማያቋርጥ መንግስ የሚቀጥለዉ በእግዚአብሄር ቃል ላይ ባለ መታዘዝ መሰረት ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ተስፋ ለዳዊት ሁኔታዊ ወይም ከሁኔታ የዘለለ ነበር ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ሊፈታዉ የሚችለዉ የተነሳ ዉጥረት አለ ፤ ሰለሞን እንደ አባቱ እና እንደ ሌሎች ነገስታቶች ወደ ዉድቀት ይመጣል ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል ፡፡
1-ነገስት (2፡ 5-9)፡ እነዚህ ጥቅሶች ለሰለሞን እንደ ፖለቲካዊ ኃላፊነት አገልግለዋል ፤ ለመንግስቱ ከባድ የሆኑ ስጋቶች ነበሩ ፡፡ ዳዊት ያላለቁ ጉዳዮች ነበሩት ፡፡ እዚህ የተጠቀሱትን እነዚህን ግለሰቦች እንመልከት፡
ኢዮአብ በሙሉ ግራ መጋባት ዉስጥ ነበር - ድሎች እና ሀዘኖች እና ራስን የመቆጣጠር እጥረት ነበሩ ፡፡
- ኢዮአብ የዳዊት የእህት ልጅ ነበር (1 ዜና 2፡ 13-17 ፡፡
- የኢዮአብን ወንድም በመግደሉ በበቀል አቤነርን ገደለዉ ….ነገር ግን አቤኔር ለዳዊት ቃል ከገባ በኋላ ምህረትን ተቀበለ (2ሳሙኤል 2) ፡፡
- ለዳዊት ትዕዛዝ ባለመታዘዝ አቤሴሎምን ገደለው (2 ሳሙኤል 18) ፡፡
- የራሱን የአጎት ልጅ አሜሳይን በማታለል ገደለው (2 ሳሙኤል 20) ፡፡
- በዳዊት ኃጢዓት ላይ ጥሩ ምክር ሰጠ (2 ሳሙኤል 24) ፡፡
- ከአዶኒያስ ጋር የአድመኛዉ አባል ነበር (1 ነገስት 1) ፡፡
- ዳዊት ለኢዮአብ ሰላም እንደ ማይሆን አዘዘ (ቁጥር 6) ፡፡
ቤርዜሊ ታማኝ ነበር ፤ ንጉሳዊ ጡረታ የተሰጠዉ ይሆናል ማለትም ከንጉሱ ገበታ ላይ ይበላ ነበር ማለት ነው (ቁጥር 7) ፡፡ የቤርዜሊን ዘር በዕዝራ እና በነህምያ መፅሀፍት ተጠቅሰዋል ፡፡
ሳሚ ሰለሞን በአይኖ እንዲጠብቀዉ ዳዊት የፈለገዉ ሰዉ ነበር ምክንያቱም ሳሚ ዳዊትን ረግሞት ነበር ቆይቶ ግን ምህትን ጠይቋል ፡፡ ጥያቄዉ ዳዊት በእዉነት ምህረትን ሰጥቶታልን ? ሳሚ ምናምንቴ ነበር አልተቀጣምም ነገር ግን ዳዊት ሰለሞን እንዲቀጣው ፈለገ ፡፡ ሳሚ ከቢኒያም ነገድ ነበር ፡፡
1-ነገስት (2፡ 10)፡ ዳዊት ሞተ ፡፡ የዳዊት መቃብር በታሪካዊ ሳይሆን በዘመናዊ በኢየሩሳሌም በፂዎን ተራራ የተቀመጠ ነው ፡፡ ብዙ ታሪክ ፀሀፊዎች እና የጥንተ ህይወት አጥኒዎች ይህ መቃብር የዳዊት ትክክለኛ ማረፊያ ቦታ እንደሀን አያስቡም ፡፡ የት ተቀብሮ እንደ ነበር አናዉቅም ነገር ግን ከአባቶቹ ጋር እንደ ሆነ እናውቃለን ፡፡
1-ነገስት (2፡ 11-12)፡ 1 ነገስት 1-4 የእስራኤልን ወርቃማዉን እድሜ ይገልፃል ፤ ዳዊት ለ40 አመታት አስተዳድሮ ነበር ሰሎንም ለ40 አመታት አስተዳደረ ፡፡ አሁን እኛ ወርቃማዊ እድሜ መሀከል ላይ ነን ፡፡ በቁጥር (13-46) ሰለሞን የዳዊትን ትዕዛዞች ፈፀመ(ተገበረ) ፡፡
1-ነገስት (2፡ 13)፡ ሰለሞን አዶኒያስ በአጠራጣሪ እቅድ ቤርሳቤን በጎበኘ ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታ እንደ ንጉስ የራሱን የስልጣን ጊዜዉን ጀምሮ ነበር ፡፡ አዶኒያስ በ 1ነገስት 1 ራሱን ንጉስ ለማድረግ አንሙከራ አድርጎ እንደ ነበር እና ቤርሳቤህ የሰለሞን እናት እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡
1-ነገስት (2፡ 14-18)፡ አዶኒያስ ወደ ቤርሳቤህ በመሄድ ልጇን አቢሳን እንድትድርለት ጠየቃት ፡፡ በኃይለኝዉ ቆንጆ ነበረች ፡፡ አዶኒያስ አዲሲቱን ሚስት አቢሳን ለማግባት በመፈለግ ጥሩ ሀሳብ እንደ ሆነ ሰለሞንን እንድታሳምነው ቤርሳቤህን ጠየቃት ፤ ቤርሳቤህ ልታግዘዉ ተስማማች ፡፡
1-ነገስት (2፡ 19-22)፡ ቤርሳቤህ በአዶኒያስ ጥያቄ ሰለሞንን ጋር በቀረበች ጊዜ ሰለሞን እምቢ አለ ፡፡ አንድ ንጉስ በሞተ ጊዜ ሁሉም ንብረቱ (ሚስቶቹን እና ቁባቶቹን ጨምሮ) ለዘፉኑ ወራሽ ይሆናሉ ፡፡ በ 2ሳሙ (16፡ 20-22) አዶኒያስ ዙፋኑን ለመጠየቅ ለሁሉም ኃጢዓቱን እና ሙከራዎቹን ለማየት በሙሉ እይታ ከአባቱ ሚስቶች እና ቁባቶች ጋር ተኛ ፡፡ አዶኒያስ በዙፋኑ ላይ ጥያቄ ለማንሳት እንዲሆነው አቢሳን እንደ ሚስት ይወስዳታል ፡፡
1-ነገስት (2፡ 23-24)፡ ሰለሞን አዶኒያስ እንዲሞት ወሰነ ፤ 1 ነገ (1፡ 52) የሚናገረው “ ሰለሞንም እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም ፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል አለ “ ፡፡ ከመዝሙር “ (የዳዊት ኃጢዓት ከእርሷ….) ” ዉጪ ይህ የቤርሳቤህ የመጨረሻዋ መጠቀስ ነው በተጨማሪም ይህ የአቢሳ የመጨረሻ መጠቀስ ነበር ፡፡ አንዳንዶች ሱናማዊት ስለ ነበረች አቢሳ የሰለሞን ሱናማዊ ዜማ እንደ ነበረች(መኃ 6፡ ) ያመለክታሉ ነገር ግን ይህ የማይመሳሰል ነው ፡፡ ምን አይነት ግራ የሆነ ሰዎስት ጎን ፍቅር ነው !!!
2 Merida, Kinde Line 434.
1-ነገስት (2፡ 25)፡ አዶኒያስ ከሰለሞን አገልጋዮች በአንዱ ተገደለ ፡፡
1-ነገስት (2፡ 26-27)፡ ካህኑ አቢያተር ተገልፆ የነበር ሌላ አስደናቂ ባህሪይ ነበረው ፤ ጉዳዩ ሴራ ነበር ፤ ባዖል ላይ ለዳዊት እና ለዳዊት በአቤሴሎም ላይ ታማኝ ነበር ፤ ነገር ግን በሴራዉ ከአዶኒያስ ወገነ ፡፡ በሳዶቅ በዳዊት ስር እንደ መገናኛ ታላቅ ካህን አገልግሏል ፤ ሰለሞንም ከክህነቱ አስወገደው ፡፡
1-ነገስት (2፡ 28-46)፡ የሰለሞንን ድርጊት ኢዮአብ እንደ ሰማ የዳነ እንዲሆን በመፈለግ ወደ መሰዊያዉ ቀንድ ሸሸ ፤ ኢዮአብ ንፁህ ስላልነበር ድነት አይመጣለትም ይገደልም ነበር ፡፡ ድርጊት ዉጤት አለው ፡፡ በእስራኤል እንዲቆይ ቸርነት የተደረገለት ሳሚ ብቻ ነበር ፤ በዚያም ተቀመጠ ተመልሶም በመምጣቱ ስላለመታዘዙ ተገደለ ፡፡
መደምደሚያ
ስለዚህ ፅሁፍ ክርክሩ ይቀጥላል ፡፡ የሰለሞን ድርጊት ተገቢ ወይስ የማይገባ ነበር ? አናዉቅም ፤ የነገስት ፀሀፊ እነዚህ ክስተቶች አስፈላጊናቸዉ ወይስ ችላ ከማለት ዉጪ በቀላሉ ክስተቶቹን ይናገራል ፡፡ ፀሀፊዉ ንጉስ ስለ ነበር ተፋላሚዎቹን አጥፍቷቸዋል ይላል ፤ ቶኒይ ሚሪዳ “ ምናልባትም ይህ በብዙ የኛን ኑሮ የሚመስል የተቀላቀለ ፍላጎት ነው ፤ ይህ ፍትሀዊ አለመሆኑን የማይገለፅ ነገር ግን በመሪነት የሰዉ ልጅን ድካም በማሳየት ለፍፁም ንጉስ እና ለተሸለ መንግስት የሚያስፈልግ ነው ፤ እግዚአብሄር ይመስገን በፀጋው በተስፋዉ መልካም በማድረግ በክርስቶስ የሚያስፈልገንን መሪ እንደ ሰጠን “ ፅፏል ፡፡
3 Merida, Kinde Line 514.
Tony Merida, Christ-Centered Exposition Commentary: Exalting Jesus in 1 & 2 Kings (Nashville: B&H Publishing Group, 2015), Kindle Line 434.
ጥያቄዎች
-
በ 1ነገ (2፡ 2-4) ዳዊት ሞቱ እንደ ተቃረበ ተናገረ ፤ ሰለሞን እንዲያደርግ ምን አዘዘው ? ዳዊት የዘረዘራቸዉን የሚያጠቃልሉት ሁለቱ ትዕዛዞች ምን ናቸው ? (ማቴ 22፡ 37-40)
-
ዳዊት ሰለሞንን ሲያዘው የሰለሞንን ጥበብ ሁለት ጊዜ ተናግሯል (1 ነገ 2፡ 6፣ 9) ፤ ይህን ባህሪይ በልጁ ወይም በሁለቱም ተመልክቶ ወደ መሆን እየጠራዉ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ሮሜ 4፡ 17 ፣ 2ቆሮ 5፡ 7፣ ዕብ 11፡ 1፣ 3)
-
ዳዊት ሰለሞንን ባልተጠቀሱ ብዙ ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያመጣ እንዲሆን አበረታታው ፤ ዳዊት ለምን አላወራባቸዉም (አልተናገረባቸውም) ? በእነዚህ ሁኔታዎች በተቀባዉ በአዲሱ ንጉስ የተገለጠ ምህረት ታያላችሁ ( 1 ነገ 2፡ 26፣ 36-38) ? የዚህ የፍትህ እና የምህረት ጥምረቶች ስለ ክርስቶስ እንዴት ያሳስቧችኋል ? ( ማቴ 12፡ 17-21፣ ዮሐ 3፡ 16-18፣ ሮሜ 5፡ 8-9)
-
በአዶኒያስ ስልጣን መዉጣት ላይ በነበረዉ ድርሻ አቢያታር አልተገደለም ነገር ግን እንደ ካህን እንዳያገለግል ወደ ቤት ተላከ ፤ በሴሊሆ የኤሊን ቤት በተመለከተ ይህ የምን ትንቢት መፈፀም ነበር ? (1 ሳሙ 2፡ 30)
-
በ 1-ነገስት 2 የሰለሞን መንግስት በፅኑ የተመሰረተ ስለመሆኑ ብዙ ማጣቀሻዎች ተደርገዋል ( 1-ነገ 2፡ 12፣ 24፣ 45-46) ፤ እንዲመሰረት ምን እረዳው ? (ምሳ 25፡ 5)
-
በ 1ነገስት 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Kings 2:2-3
“As for me, I am going the way of all of the earth. Be strong and be courageous like a man, and keep your obligation to the Lord your God to walk in His ways and to keep His statutes, commands, ordinances, and decrees. This is written in the Law of Moses, so that you will have success in everything you do and wherever you turn.”
በዳዊት የመጨረሻ ቀናት ከሙሴ ህግ ለሰለሞን ትዕዛዝ ሰጠው ፡፡ “ በርታ ሰውም ሁን ፤ የአምላክህን ትእዛዝ ጠብቅ ፤ በመንገዱም ሂድ ፤ ሥርዓቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩን ጠብቅ ፡፡ የሙሴን ህግ ብትጠብቅ በምታከናውነውና በምትሄድበት ሁሉ ይሳካልሃል ፡፡ ከዚያም ዳዊት የጥቂት ሰዎችን ታሪክ በእርሱም ላይ ያደረጉትን ነገር ነገረው አይኑንም በእነርሱ ላይ ያደርግ ዘንድ አዘዘው ፡፡ ዳዊትም ከሞተ በኋላ ሰለሞን ያባቱን ቃል ተከተለ ፤ ልቡንም በእግዚአብሔር ላይ በማድረግ በስልጣንና በጥበብ ተራመደ ፡፡
እንደ ሰለሞንና እስራኤላውያን ሁሉ አንተም የእግዚአብሔርን ቃል ታውቃለህ ፡፡ የእርሱን እውነት በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዛቱን ታውቃለህ ፡፡ እናም አሁን በኢየሱስ በማመን የዘላለም ህይወት አለህ ፡፡ ጸጋውን ተቀብለሃል በውስጥህም ባለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በየቀኑ መራመድ ችለሃል ፡፡ እውነቱን ባንዱ ጆሮህ ሰምተህ በሌላው ማፍሰስ ቀላል በሆነበት ጊዜ ላይ በእርሱ እውነት እየተራመድክ ነው ? ግን ይህን ከማወቅህ በፊት በአለም መንገድ ተመላለስክ ፡፡ ቀስ በቀስም ሌሎች አማልክት ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ከመሲሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ባላይ አስፈላጊ ይሆኑብሃል ፡፡ የሰማዩ አባትህ ልክ ዳዊት ሰለሞንን እንዳዘዘው “ በመንገዱ እንድትሄድ “ ያዝሃል ፡፡
“ እኔ የምድሩን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ በርታ ሰውም ሁን የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ በሙሴ ህግ እንደ ተጻፈ ሥርዓቱንና ትዕዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ጠብቅ ፡፡ “
- 1ኛ ነገሥት 2፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 118(119)፡1 –“ በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው ፡፡ “
ምሳሌ 23፡26 –“ ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ ፡፡ “
ሮሞ 12፡2 –“ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።