Historical Books 1 Kings

Solomon's Anointed Reign

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Something Greater 1 Kings 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 255 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አሁንም 12ቱን የታሪክ መፅሀፍት ማጥናት ላይ ነን ፤ እስካሁን አምስቱን ሸፍነናል ፡፡ ልክ እንደ 1 እና 2 ሳሙኤል ሜንዲይ እነዚህ ሁለት መፅሀፍት ወደ አንድ ሙሉ ስዕል( አንድ ገፅ ተብሎ ወደ ሚጠራ) ሁለቱን ስዕሎች አጣምራቸዋለች ፡፡ ለ 1ነገስት ቃላችን የሚበልጥ ነገር ነው ፤ ክርስቶስ እንዴት ከሰለሞን እንደ ሚበልጥ ለማሳየት የሰለሞንን ህይወት ከኢየሱስ ህይወት ጋር እናወዳድራለን ፡፡ 2 ሳሙኤል መጨረሻ ላይ ዳዊት ዙፋኑን እንዲወርስ ሰለሞንን እያዘጋጀዉ ነበር ፤ 1 ነገስት ዋና የመሪነት ሽግግር ጊዜን ያሳያል ፡፡ የዳዊት ኪዳን ከ 2 ሳሙኤል 7 አሁን ወደ ሰለሞን የተላለፈ ነበር ፡፡

ከመጀመሪያው 1 እና 2 ነገስ አንድ መፅሀፍት ነበሩ ፤ ከዚያ በፊት እነዚህ መፅሀፍት የሳሙኤል ሰዎስተኛዉ እና አራተኛዉ ክፍል ነበሩ ፡፡ መፅሀፉ ከ561-538 መካከል ከክርስቶስ ልደት በፊት የተፃፈ ነበር ፤ በመፅፍ ዉስጥ ታሪካዊ ማስረጃው ከሰለሞን ድርጊት መፅሀፍት፣ ከእስራኤል ነገስታት ከዜና መፅሀፍት (1ነገ 14፡ 19) እና ከይሁዳ ነገስታት ከዜና መፅሀፍት ነበር (1ነገ 14፡ 29) ፡፡ በተጨማሪም ለ 1ነገስት በኢሳያስ እና በኤርሚያስ ማጣቀሻች አሉ ፡፡ ማክአርቱር “ አንድ የተነሳሳ ፀሀፊ በባቢሎን ግዞት ጊዜ እነዚህን ቀድመዉ የተቀመጡ ማቴሪያሎችን እንደ ተጠቀመ ያስቀምጣል “ ፡፡

1 ነገስት 1-11 የሰለሞንን ዘመነ መንግስት እና የይሁዳን እና የእስራኤልን አንድ መሆንን ይሸፍናል ፤ በ 1ነገስት 12 ይህ አንድ የሆነ መንግስት መታገል በመጀመር በሰሜን እና በደቡብ መንግስት መከፋፈል ነበር ፡፡ በ 2ነገስት የደቡቡ መንግስት የይሁዳ ታሪክ የተዘረዘረ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ የነገስት መፅሀፍ ትክክለኛ ታሪክ ትክክለኛ ያልሆነ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የተተረጎመ ታሪክም እንደ ነበር ፤ ፀሀፊዉ….የእስራኤልን ትምህርት ለስደተኞች ለማዉራት ፈለገ … ለምን የእግዚአብሄር የስደት ፍርድ መጥቶ እንደ ነበር ይገልፃል “ ፡፡ ዋናዉ ነገር፡ ጸሀፊዉ ስደተኞቹ የሙሴ ህግ እስራኤላዊያን ታዛዦች እንዲሆኑ እንደ ሚጠይቅ አለመታዘዝ ወደ ቅጣት እና ስደተኛ እንደሚያደርግ መረዳታቸዉን እርግጠኛ ለመሆን ፈለገ ፡፡ በ 1ነገስት ዉስጥ የሚያልፈዉ የተለመደው ጭብጥ “ በእግዚአብሄር ፊት ከፉ ነገር ስላደረጉት “ የእስራኤል እና የይሁዳ ነገስታቶች ነው ፡፡ እግዚአብሄርም ነገስታቶቹን ህዘባቸዉን ወደ እግዚአብሄር እንዲመልሱ እንዲያስተካክሏቸው ነቢያቱን ላከ ፤ የእግዚአብሄርን ነቢያትና ማስጠንቀቂያቸውን ባልተቀበሉ ጊዜ ነቢያቱ ሁለቱም ነገስታት እንደሚሰደዱ ይናገራሉ ፡፡

በመልከዓ ምድር አቀማመጥ እስራኤል ሁሉንም ምድር በሰሜን ከዳን በደቡብ እስከ ቤርሳቤህ ያካተተ ነው ፡፡ በመፅሀፉ መጀመሪያ ላይ ንድፉ ከሌለኛዉ በኋላ አዲሱ ንጉስ ስለ እያንዳንዱ ማስረጃዎች በሌላ መንግስት ከዘመናዊ አስተዳደር ስልጣን የመረከቢያን ጊዜ፣ ዙፉኑን በመሰደ ጊዜ የንጉሱ እድሜንየንግስናዉን ቦታ እና እርዝመት የሚያሳዉቅ ነው ፡፡ በይሁዳ የነገስታት መስመር የእናቲቱ ስም ተሰጥቷል ፡፡ ሌሎች መረጃዎች የእያንዳንዱን የንጉስ ስልጣን ዘመን ግምት የሰጡ ነበር (መልካም አድርጎ ነበር ወይስ ክፉ አድርጎ ነበር የሚለውን) ፡፡ በመጨረሻም በንጉሱ ዘመን ማብቂያ ላይ የታሪካዊ ማስረጃ ዋቢ የተሰጠዉን ማስረጃ ያረጋግጣል እንዲሁም መሞቱን መቀበሩን እና የስኬታማዉን መለያ ያሳዉቃል ፡፡

ማክአርቱር ለ 1ነገስት ሰዎስት ስነ መለኮታዊ ጭብጦችን ያቀርባል፡ 1) “ እግዚአብሄር ለህጉ ባለመታዘዛቸዉ ምክንያት እስራኤልን እና ይሁዳን ፈረደባቸው “ ፤ 2) “ የእዉነተኛ ነቢያት ቃል ወደ ማለፍ መጣ “ እና 3) እግዚአብሄር ለዳዊት የገባዉን ቃል ኪዳን ማስታወሱን “ ፤ በዚህ መነሻነት ወደ 1 ነገስት እንቆፍር(እናጥና) ፡፡

ትምህርት

1-ነገስት (1፡ 1-10)፡ ዳዊት 70 አመት አካባቢ እንደ ነበር በታመመ ጊዜ አይሞቀዉም ነበር (ቁጥር 1) ፤ አገልጋዮቹ እንደ ተንከባካቢ ለዳዊት መቆም የምትችል አንድ ድንግል ሴት እንደ ምትገኝ ነገሩት (ቁጥር 2) ፡፡ የቀደምት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፀሀፊ ጆሴፍስ በሁለተኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን “ የጤነኛ ሰዉ አካልን ለታመመ ሰዉ ለመንከባከብ ሙቀት የሚሰጥ “ የህክምና ማስታገሻ በመሆን መጠቀሱን ፅፏል ፡፡ አገልጋዮቹ ዳዊትን ለመንከባከብ አንዲት ሱናማዊት ቆንጆ ሴት አቢሳን አገኙ ፤ ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም (ቁጥር 4) ፤ የዳዊት አራተኛ ወንድ ልጁ የተረፈዉ ትልቁ ልጁ አዶኒያስ ንጉስ እሆናለሁ በማለት ተነሳ ፤ በፊቱ የሚሮጡ ፈረሰኞች፣ ሰረገሎች፣ ጦረኞች ነበሩት (ቁጥር 5) ፡፡ አዶኒያስ ራሱን አስበለጠ (ሉቃ 14፡ 11) ፤ ዳዊት ዝምተኛነቱን በማሳየት በፍፁም ለድርጊቱ አልወቀሰዉም (ቁጥር 6) ፡፡ አዶኒያስ በዳዊት በዳዊት የጦር አዛዥ በእህት ልጆቹ ኢዮአብ እና አቢያታር አሴረ ፤ ለዙፉን ጥያቄዉን ለመደገፍ ተስማሙ (ቁጥር 7) ፤ ይሁን እንጂ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን እና የዳዊት ኃይለኛ ተዋጊዎች አዶኒያስን አልደገፉም (ቁጥር 8) ፡፡ አስታዉሉ፡ በቁጥር 8 ሳሚም በዳዊት ላይ እርግማን በማድረግ እና ድንጋይ በመወርወር የተጠቀሰዉ አልነበረም (1ነገ 2፡ 8-9፣ 2ነገ 4፡ 7፣ 18) ፡፡ አዶኒያስ እንስሳትን በመሰዋት ንጉሳዊ ወንድሞቹን፣ የይሁዳን ሰዎች እና የሰለሞንን አገልጋዮችን ጋበዘ ፤ ከእርሱ በኩል ያልወገኑትን አልጋበዘም (ቁጥር 9-10) ፤ ዙፋንን ከሰለሞን ለመዉሰድ እየሰራ ነበር ፡፡

1-ነገስት (1፡ 11-31)፡ ናታን ቤርሳቤህን እየሆነ ስለነበረዉ ነገራት እርሷም ንጉስ ለመሆን ስለ ሰለሞን ዉርስ ንጉስ ዳዊትን በመጠየቅ አዶኒያስ ዉርሱን ከሰለሞን ለመዉሰድ እየሞከረ እንደ ነበር ገለፀች ፡፡ ዳዊት ለእስራኤል ከእርሱ በኋላ ዙፋኑ ላይ ማን እንደ ሚቀመጥ እንዲነግራቸዉ ጠየቀችዉ (ቁጥር 11-20) ፤ ናታንም ወደ ዳዊት በመምጣት ቤርሳቤህ ነግራዉ የነበረዉን በማረጋገጥ ነቢያቱን እና እርሱን ሳያካትት አዶኒያስ ከዳዊት ጀርባ እያደረገ የነበረዉን ገለፀለት (ቁጥር 21-27) ፡፡ ዳዊት በፊቱ ቤርሳቤህን በመጥራት ሰለሞን የእርሱ ትክክለኛ ወራሹ እንደ ነበር እንደ ገና ማለላት (ቁጥር 28-31) ፡፡

1-ነገስት (1፡ 32-40)፡ ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንነቢዩን ናታንን እና በናያስን ጠራ ፤ በፊቱ በመጡ ጊዜ ሰለሞንን በዳዊት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ በእስራኤል ላይ እንደ ንጉስ ለመቀባት ወደ ግዮን እንዲወስዱት አዘዛቸው (ቁጥር 32-37) ፡፡ ሰለሞን በዳዊት በቅሎ ላይ መጋለቡ እስራኤልን ዳዊት ዙፋኑን ለሰለሞን እያስተላለፈ እንደ ነበር ያሳያል (ዘካ 9፡ 9) ፡፡ ሰዎቹ ሰለሞንን በዳዊት በቅሎ ላይ በማድረግ ወደ ጊዮን በመዉሰድ ከመገናኛዉ ድንኳን ዘይት በመቀባት ዳዊት እንዳዘዛቸዉ አደረጉ ፡፡ የቀንደ መለከት ነፉ ህዝቡም ሰለሞንን እንደ ንጉሳቸዉ ገለፁ (ዮሐ 12፡ 13) ፤ ከዚያም “ ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለዉ ወጡ ሕዝቡም ዘፈን ይዘፍኑ ነበር በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው ፤ ከጩኸታቸዉም የተነሳ ምድር ተናወጠች “ (ቁጥር 38-40) ፡፡

1-ነገስት (1፡ 41-53)፡ አዶኒያስ ምን ተፈጥሮ እንደ ነበር ቃል ደረሰው ( ቁጥር 41-48) ፤ አዶኒያስ እና እንግዶች ሁሉ ከዜናዉ የተነሳ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ (ቁጥር 49) ፡፡ አዶኒያስ ሰለሞንን በጣም በመፍራት የመሰዊያዉን ቀንድ ያዘ (ቁጥር 50) ፤ የእርሱ ድሪጊት ለምህረት እየጠየቀ እንደ ነበር እና ሳያስበዉ አድርጎት ለነበረዉ ጥፋት እንዲድን ማለት ነው (ዘሌዋዉያን 4፣ ዘጸ 21፡ 12-14) ፡፡ ሰለሞን አዶኒያስ ሰለሞን እንደ ማይገድለዉ እንዲሚልለት ለመጠየቅ የመሰዊያዉን ቀንድ ይዞ እንዳለ ቃል ደረሰዉ (ቁጥር 51) ፤ ሰለሞን በአዶኒያስ ክፋት ካላገኘበት እንደ ማይገድለዉ ተስማማ (ቁጥር 52) ፡፡ ሰለሞን በፊቱ አዶኒያስ መጣለት ፤ አዶኒያስ ለንጉስ ሰለሞን እጅ በመንሳት ከፈለ አዶኒያስንም ቤቱ ላከዉ ማለትም በይቅርታ ላከው (ቁጥር 53) ፡፡

መደምደሚያ

በ 1ነገስት እያየን ያለነው በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሰባት ምዕራፎች ምንም እንኳን ሰለሞን የሚያስደንቅ የእግዚአብሄር ሰዉ ቢሆንም ኢየሱስ የሚበልጥ ነው (ማቴ 12፡ 42) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 387.

  2. MacArthur, p. 388.

  3. MacArthur, p. 388.

  4. MacArthur, p. 389.

  5. MacArthur, p. 389.

  6. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Samuel (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 428.

ጥያቄዎች

  1. አዶኒያስ ይህን ለማድረግ ለምን ፈለገ ? (2ሳሙ 15፡ 1-12፣ 1ነገ 1፡ 6) ይህ የአባቱ ኃጢዓት ወደ እርሱ እንዳለፈ ያሳያል ? (ዘጸ 20፡ 5፣ ዘዳ 5፡ 9)
  2. ለዙፋኑ ወራሽ እንዲሆን ከሌሎቹ ልጆቹ ይልቅ ዳዊት ሰለሞንን ለምን እንደ መረጠ ምን ታስባላችሁ ?
  3. በቁጥር13 ናታን ቤርሳቤህንስለ አዶኒያስ እቅድ ለራሱ ከመናገር ይልቅ ወደ ዳዊት ፊት እንድትሄድ መናገሩ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?
  4. በቁጥር 50 አዶኒያስ “ የመሰዊያዉን ቀንድ ያዘ “ ፤ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ይህ የተጠቀሰበት ሌላ ጊዜ ነበር (ዘጸ 21፡ 14፣ 1ነገ 2፡ 28-29)
  5. በ 1ነገስት ዉስጥ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Kings 1:29-30

“The king swore an oath and said, ‘As the Lord lives, who has redeemed my life from every difficulty, just as I swore to you by the Lord God of Israel: Your son Solomon is to become king after me, and he is the one who is to sit on my throne in my place, that is exactly what I will do this very day.’”

ንጉስ ዳዊት ሸምግሎ በክፍሉ ተቀምጦ ነበር ፡፡ በዚያም ነበረ ነቢዩ ናታንና ቤርሳቤህ ስለ ዳዊት ልጅ አዶንያስ ራሱን የንጉሱ ተተኪ አድርጎ መሾሙን በተጨማሪም ሰዎች ንጉስ እንድሆን ይደግፉት ዘንድ መሰብሰቡንና ማሳደሙን ያወሩለት ዘነድ የሄዱት ፡፡ ዳዊትም ያለማመንታት ከእርሱ በኋላ የሚነግሰው ሰለሞን እንደሆነ ማለ ፡፡ ናታንና ካህኑ ሶዶቅም ይቀቡት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ህዝቡም አድሱን ንጉሳቸውን ሰለሞንን በዳዊት በቅሎ ወደ ከተማ በወጣ ጊዜ አከበሩት ፡፡ ሁሉም ተደሰተ አዶንያስ ግን ለነፍሱ ፈራ ፡፡ ሰለሞን ግን አዶንያስ በእርሱ ላይ ላደረገው ትምክህት የተሞላበት ተግባር ምህረትንና ይቅርታን አደረገ ፡፡ የእግዚአብሔርም እጅ በሰለሞን ላይነበረ ፡፡

በብዙ መንገድ ሰለሞን ከኢየሱስ ጋር ሊነፃፀር ይችላል ፡፡ ሰለሞን በበቅሎ ላይ ተቀምጦ ነበር የነገሰው ፣ ንጉስ ሁኖ ተቀብቶ ነበር ፣ ትልቅ ጥበብ ነበረው ፣ ምህረትንና ይቅርታንም ያደርግ ነበር ፡፡ ምንም እንኳ ኢየሱስ ከሰለሞን ቢበልጥም ኢየሱስ የመጣው ባህያ ላይ ተቀምጦ ህዝቡም “ ሆሳእና “ ብለው እየጮኹ ነበር ፡፡ የተቀባው ኢየሱስ ኃጢአትህን ሁሉ ይቅር ብሏል ፤ ጸጋን ምህረትንና የዘላለም ህይወትን ሰጥቶሃል ፡፡ ኢየሱስ የነገስታት ንጉስ የጌቶችም ጌታ ነው ፡፡ ዛሬ ጌታን አምልክ በፊቱም ስገድ ፤ ከዚህ ዓለም ነገርም ረቅ ከሞትም ላዳነህ ለእርሱ ልብህን አፍስስ ፡፡ ምስጋናህ ይገባዋል እርሱ ሁሉን ቻይ ነውና ፡፡

“ ንግሡም ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን በእውነት ልጅሽ ሰለሞን ከእኔ በኋላ ይነግሳል በእኔም ፈንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ እንድሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ ብሎ ማለ ፡፡ “

  • 1ኛ ነገሥት 1፡29-30

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 12፡42 –“ ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትፈርድበታለች የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና እነሆም ከሰለሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ ፡፡ “

ዮሐንስ 14፡12 –“ እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል ፡፡ “

1ኛ ጢሞቲዎስ 6፡15 -16 –“ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል ፡፡ እርሱ ብቻ የማይሞት ነው ፣ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል ፣ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን አሜን ፡፡ “