Historical Books 2 Samuel

David's Anointed Mighty Men

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 254 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ 2 ሳሙኤልን እንጨርሳለን ፤ በ አንደኛ እና ሁለተኛ ሳሙኤል ጥናታችን ብዙ ተምረናል ፡፡ በእነዚህ መፅሀፍት ወደ አሁኑ ጊዜ በቀላሉ የሚሸጋገሩ መርሆች አሉ ፡፡ 2 ሳሙኤል 23 የዳዊትን የመጨረሻ ቃሎች ይመዘግባል (ቁጥር 1-7) ፤ ዳዊት ስላረጀ በህይወቱ ላይ ኋላዉን ተመለከተ ፡፡ የምዕራፉ ቀሪዉ ስለ ዳዊት ኃያላን ሰዎች ነው (ቁጥር 8-39) ፡፡

ትምህርት

2-ሳሙኤል (23፡ 8-10)፡ የዳዊት ኃያላን ሰዎች በ 1ዜና ምዕራፍ አስራ አንድም ተጠቅሰዋል ምናልባት የተለያዩ ስሞች ተጠቅመዉ ይሆናል ነገር ግን ዝርዝሮቹ የፀኑ ናቸው ፡፡ መጀመሪያ የተጠቀሰው በአንድ ጊዜ በጦሩ 800 መቶ ሰዎችን የገደለው ከነዓናዊዉ ኢያቡስቴ ነበር (ቁጥር 8) ፡፡

ቀጣዩም እጁ “ ከሰይፉ ጋር እስኪጣበቅ “ ድረስ ፍልስጤማዊያንን በበቀል ያጠቃዉ ከዳዉት ጋር ከነበሩት ከሰዎስቱ ጋር የነበረው ኤልያና ነበር ፤ በዚያ ቀን እግዚአብሄር ለእስራኤል ታላቅ ድል ሰጠ (ቁጥር 10) ፡፡

ሰዎስተኛው የአሮዳዊዉ የአጌ ልጅ ሳማ ነበር ፤ ሳማ የምስር ማሳ ከፍልስጤማዊያን ተከላከለ “ እግዚአብሄርም ታላቅ ድል አደረገ “ (ቁጥር 11-12) ፡፡

2-ሳሙኤል (23፡ 13-17)፡ በታላቅ ጀግንነታቸዉ እና ፍራት ስለሌለባቸው ዳዊት እነዚህን ሰዎስቱን እዉቅና ሰጣቸዉ፡፡ በደም ተደግፎ የተደረገን ነገር በፈለገ ጊዜ ያደረጉትን ለማግኘት በእነርሱ ላይ መደገፍ እንደሚችል አወቀ ፤ እነዚህ ሰዎስቱ በዓዶላ ዋሻ ወደ ነበረዉ ወደ ዳዊት መጡ (ቁጥር 13) ፤ ዳዊት በኃይል በመጠማቱ የፍልስጤማዊያን ጭፍራ በሩብ ሰፍሮበት ከነበረው ከቤቴ ልሄም ጉድጓድ ዉሃን ፈልጎ ነበር (ቁጥር 14-15) ፤ በምላሹ እነዚህ ሰዎስት ኃያላን ሰዎች በፍልስጤማዉያን መስመር በኩል በመስበር ከጉድጓዱ ዉሃን በመቅዳት ለዳዊት አመጡለት ፤ ነገር ግን ዳዊት ለመጠጣት እምቢ በማለት እንደ ሚፈስስ ቁርባን ለእግዚአብሄር በምድር ላይ አፈሰሰው (ቁጥር 16) ፡፡ ዳዊት ዉሃው ለእርሱ ዉሃ ለማግኘት“ ህይወታቸዉን አደጋ ዉስጥ ጥለዉ የነበሩት ሰዎች ደም “ ነበር አለ (ቁጥር 17) ፡፡

2-ሳሙኤል (23፡ 18-23)፡ በቁጥር 18 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ ከሰዎስቱ እንደ መሪ የተጠቀሰ ነው (ቁጥር 18) ፤ ሌለኛዉ የኢዮአብ ወንድም አሳሄል ከኃያላኑ ሰዎች መካከል የተጠቀሰ ነው (ቁጥር 24) ፡፡ ኢዮአብ የዳዊት ሰራዊት አዛዥ ነበር ፡፡ ሰዎስቱም የዳዊት እህት የጽሩያ ልጆች ነበሩ ( 1ዜና 2፡ 13-16) ፤ እንደ እህት ልጅ እነዚህ ሰዎች በወጣትነት እድሜዉ በዙሪያዉ ነበሩ ፡፡ የዳዊት እህት ዳዊት የወደፊቱ ንጉስ እንደ ሚሆን ስለ ሳሙኤል ቅባት አዉቃለች ፡፡

እግዚአብሄር በሳሙኤል መፅሀፍት በኩል በምናየዉን በዘሩ መስመር ስለ ተቀባው ዋና እቅድ አለዉ በአዲስ ኪዳን በኢየሱስ በኩልም ማስረጃ ነው ፤ ይህን ማስረጃ ለማግኘት የክፉ ጥፋት የቅናት ጉዳይ እና ኩራት ቢኖርም በእነዚህ ሌሎች ሰዎች እና ክስተቶች እግዚአብሄር ያደረገዉን እናያለን ፡፡

2-ሳሙኤል (23፡ 24-39)፡ በምዕራፍ 23 የሁሉም ኃያላን ሰዎች ስም ዝርዝር ነው - ብዙዎቹ ስሞች በመፅሀፍት በሌላ ቦታ የትም ላይ ያልተጠቀሱ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለዳዊት ዉጊያ ታላቅ ድል ያመጡ ነበሩ ፤ ለእኛ ቅባት የእግዚአብሄር እቅድ እንደ ሆነ እዉቅና እንድንሰጥ አስፈላጊ ነው ፡፡ አሳሄል ከሚዳቆ በይበልጥ በፍጥነት መሮጥ የሚችል እንደ ነበር ተገልፃል (2 ሳሙ 2፡ 18) ፤ ኢዮአብ ኮማንደር ለመሆን የመሪነት ችሎታ ነበረው ፤ እያንዳንዳቸዉ ኃያላን ሰዎች የተለዬ ነገር አምጥተዋል ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ በእነዚህ በእያንዳንዳቸዉ በጥሪያቸዉ ዉስጥ መስራት ነበር ፤ ቅባቱ አላማ የሌሽ አይደለም ነገር ግን እያንዳንዳቸዉን ሰዎች እግዚአብሄር በእቅዱ ዉስጥ የሚጠቀመው በእያንዳንዳቸዉ ሰዎች ላይ የተቀመጠ መፈፀሚያ ነው ፡፡

እነዚህ 37 ኃያላን ሰዎች የእግዚአብሄር መሳሪያ ነበሩ ፤ እያንዳንዳቸዉ አስፈላጊ ነበሩ ፡፡ በቁጥር 39 የመጨረሻዉ ስም ኬጢያዊዉ ዖርዮን አስታዉሉ ፤ የቤርሳቤህ ባል ዖርዮን በጦርነት እንደ ነበሩ ወደ ሚስቱ ቤቱ በመሄድ ለዳዊት ጦር ከተጠራበት ተግባር ዉጪ ስላልሄደ ዳዊት ኃጢዓቱን ለመሸፈን አስገደለው ፡፡ እቅዱን እንዲተገብሩለት እግዚአብሄር እነዚህን ሰዎች በስፍራቸዉ አስቀመጣቸው ፤ እነዚህ 37 ሰዎች ተጠርተዋል ምክንያቱም በዳዊት ህይወት እያንዳንዳቸው የእግዚአብሄር እቅድ ድርሻ ስለ ነበራቸው ፡፡ ዳዊት በራሱ መንግስቱን አላዳነም ፤ እንደ ተቀባ በዳዊት ህይወት የሆነው ስለዳዊት አልነበረም የእግዚአብሄር እቅድ ወደ መፈም እንዲመጣ እንጂ ፡፡ ስለ እኛ ማንነት፣ ስለ ስኬታችና እና ስለ ስጦታችን አይደለም - ሁሉም በእግዚአብሄር እቅድ ስለ መቀባት ነዉ ፤ ስለእኛ አይደለም ፡፡ እነዚህ 37 የዳዊትን መቀባት እዉቅና በመስጠት ስለ ዳዊት ማንኛዉንም ነገር ያደርጋሉ - ለእርሱ ዉሃ ለማምጣት የፍልስጤማዊያን መስመር እንኳን አልፈዋል ፡፡ ቅባታችንን እንደ እግዚአብሄር እቅድ አካል በስነስርዓት መዉሰድን አስቡ ፡፡

የእግዚአብሄር እቅድ በዳዊት በኩል የእስራኤልን መንግስት መመስረት ነበር (ማቴዎስ 1፡ 1) ፤ የኢየሱስ የዘር ሀረግ ብዙ ትዉልድን ይሸፍናል በዚህ ሁሉ በኩል የሚሄደዉ አንዱ ነገር የእግዚአብሄር እቅድ ነው ፡፡ የእግዚአብሄር ወንጌል የእግዚአብሄር እቅድ ነው (ሮሜ 1፡ 1-4) ፡፡ የዳዊት ቅባት በመንግስቱ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚፈፀመዉን የእግዚአብሄርን መንግስት ይወክላል ፤ በመንግስቱ በእግዚአብሄር ዉጤት የእግዚአብሄር እቅድ እናያለን ፡፡ ቅባት በፍፁም ስለ እኛ አይደለም ፡፡ በህይወታችን እንዴት እንደ ምንኖር ከህይወታችን ጋር ለማገናኘት ለመወሰን መመልከት አለብን ፤ የእርሱ ኃያል ሰዉ ለመሆን የእግዚአብሄር ቅባት መመልከት አለብን ፡፡ ለራሳችን ትኩረትን የሚስቡ ስብዕናዎችን በማጥፋት ለእግዚአብሄር አድርጉት ፤ በምናመልከዉ ጊዜ የምናደርጋቸዉን ክርክሮች ወደ ጎን በማስቀመጥ እርሱን ብቻ እናምልከው ፡፡

2-ሳሙኤል (24፡ 1-17)፡ 1 ዜና 21፡ 1 ይህን ተመሳሳይ ክስተት ያቀርባል ነገር ግን በተሸለ ያብራራል “ ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሳ እስራኤልም ይቆጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው “ ፤ ከምቾት ልንሳብበት የምንችልበት አንድ ነገር በግልፅ ለመስማት በምንወድቅ ጊዜ ባሉ አንዳንድ ጊዜዎች ነው ፡፡ ዳዊት የሂወቱ መጨረሻ እየቀረበ ነበር ፤ የእስራኤልን ህዝብ መቁጠር ለምን ፈለገ ? ምናልባትም ዳዊት ህይወቱ እንዴት ተቆጥሮ እንደ ነበር ለመለካት እየተመለከተ ነበር - ቅርሱ ፡፡ ኢዮአብ ለምን ዳዊት የህዝብ ቁጥር መዉሰድ እንደ ፈለገ ጠየቀው (ቁጥር 3) ፤ እንደ ዳዊት ሰራዊት አዛዥ ኢዮአብ በእስራኤል ከማንም በላይ ብዙ ተቃዉሞችን እና ደም መፋሰሰን ያየ ነበር ፡፡ ቆጠራዉ ከዘጠኝ ወር በላይ ወሰደ (ቁጥር 8) ለኢዮአብም የቆሸሸ ነበር (1ዜና 21፡ 6) ፡፡ ወታደሮቹን በመቁጠር ከእስራኤል 800,000 ሰዉ እና ከይሁዳ 500,000 ሰዉ መዘገቡ (ቁጥር 9) ፡፡ ዳዊት ለእርሱ ምን ያክለክ ጀግና ወታደሮች እንደ ነበሩት ማወቅ ፈለገ ፤ ኢዮአብ በብዙ የወታደሮች ቁጥር በፍፁም ተደግፈዉ እንደማያዉቁ ያውቃል ምክንያቱም እግዚአብሄር ድልን ስለ ሰጣቸው ፡፡

እንደ ገና ይህ ለዳዊት የአስተሳሰብ ማስተካከያ ሆነ ፤ ዳዊት ኃጢዓቱን አወቀ እግዚአብሄርም ጥፋቱን እንዲያርቅለት ጠየቀ (ቁጥር 10) ፤ ነገር ግን 70,000 የዳዊት ወታደሮች እግዚአብሄር ለእስራኤል በላከዉ መቅሰፍት ሞቱ (ቁጥር 15) ፡፡ እንደ ገና የዳዊት ኃጢዓት ዉጤት ታላቅ ነበር ፡፡

በእግዚአብሄር ቅባት ወይስ ደግሞ ነገሮችን ለራሳችን ጥንቃቄ አድርጎ በማሰብ እንጓዛለን ፤ ከእግዚአብሄር ቅባት ዉጪበሆንን ጊዜ አጥፊ ዉጤት ሊኖረው የሚችለዉን መንገድ ለመጓዝ እንመርጣለን ፡፡ ይህን በየቀኑ አጥብቀን መያዝ ያስፈልገናል …. አስደናቂዉ ጌታን ለማወቅ ብቸኛዉ ነገር በህይወታችን ትርጉም ያለው በእግዚአብሄር ቅባት ሁል ጊዜ መጓዝ ነው ፡፡

መደምደሚያ

በብሉይ ኪዳንም እንኳን ሮሜ (8፡ 28) አሁንም እዉነት ነው “ እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንዳ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናዉቃለን “ (ኪንግ ጀምስ ዕትም) ፤ በእግዚአብሄር ቅባት ወይስ ደግሞ ነገሮችን ለራሳችን ጥንቃቄ አድርገን በማሰብ እንጓዛለን ፤ ከእግዚአብሄር ቁባት ዉጪ በሆንን ጊዜ አጥፊ ዉጤት ሊኖረዉ የሚችለዉን መንገድ ለመጓዝ እንመርጣለን ፡፡ ይህን በየቀኑ አጥብቀን መያዝ ያስፈልገናል ….አስደናቂዉን ጌታ ለማወቅ ብቸኛው ነገር በህይወታችን ትርጉም ያለው በእግዚአብሄር ቅባት ሁል ጊዜ መጓዝ ነው ፡፡ በዙሪያችን በእግዚአብሄር መሳሪያነት በኑሮአችን ዉስጥ ከሚፈሰዉ ከእግዚአብሄር ቅባት ዉጪ ምንም አይደለንም ምንምም ስለሌለን እግዚአብሄር አላማ ላይ እናትኩር ፡፡

2-ሳሙ (24፡ 24) ዳዊት የሚቃጠል መስዋዕት ወደ ሚሰዋበት ቦታ ዞረ ምክንያቱም ዋጋ የሚያስወጣ ለእግዚአብሄር ምንም ነገር ሰዉቶ ስለማያውቅ ፡፡ ለአምላኮች ዊጪ አለ ፡፡ በቅባት እና በትህትና እንዴት መሄድ እንዳለብን እንዲያስተምረን እግዚአብሄርን እንጠይቀዉ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ዉሃ እንደ ጠማዉ ከተናገረ በኋላ (2ሳሙ 23፡ 15) የእርሱ ኃያላን ሰዎች ያመጡለትን ዉሃ ለምን አልጠጣውም (ቁጥር 16-17) ? በህይወታችሁ ከሌላ ሰዉ ወይም ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር ጠይቃችሁ ከዚያ ያልተቀበላችሁበት ጊዜ አላችሁ ? ለምን ?
  2. የዳዊትን 37 ኃያላን ሰዎጭ መጥቀስ ለምን አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ? (ማቴ 26፡ 6-13)
  3. 2ሳሙ (24፡ 1) የእግዚአብሄር ቁጣ በእስራኤል ላይ እንደ ነደደ መዝግቧል ፤ የዚህ ንዴት ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ዳዊት ይህን በትክክል አስተናግዶታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ምሳ 16፡ 18፣ ሉቃ 12፡ 16-12)
  4. 2ሳሙ (24፡ 15) በዳዊት ኃጢዓት ምክንያት 70,000 ሰዎች እንደ ሞቱ ይናገራል ፤ ብዙ ጊዜ በእናንተ ኃጢዓት ምክንያት የተጎዳን ሰዉ እንዴት ትመለከቱታላችሁ ?
  5. ብዙ ጊዜ ምንም የማያስወጣችሁን ነገር ለእግዚአብሄር እንዴት ታቀርባላችሁ ? ( 2ሳሙ 24፡ 24) ?
  6. በ 2ሳሙኤል 23-24 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 24:10

“David’s conscience troubled him after he had taken a census of the troops. He said to the LORD, ‘I have sinned greatly in what I’ve done. Now, Lord, because I’ve been very foolish, please take away Your servant’s guilt.’”

ዳዊት ሰላም ነበር በሰላሳ ሰባቱም ብርቱ ሰዎቹ ተከቦ ነበር ፡፡ አርጅቶም ነበር ፤ በውጊያም ድልን አገኘ ፡፡ ግን ዳዊት በሆነ ምክንያት በሞኝነት የእስራኤልንና የይሁዳን ህዝብ ቆጠራ የማድረግ ፈተና ውስጥ ወደቀ ፡፡ ይህም እግዚአብሔርን አስቆጣ ዳዊትም አወቀው ፡፡ ዳዊትም ተጸጸተ በጣምም ተጨነቀ ፡፡ በምላሹም ዳዊት ፈጥኖ ንስሀ ገባ ፤ ነገሮችንም እንዴት እንደገና እንደሚያስተካክል ጠየቀ ፡፡ ስለዚህም ሀገር አቀፍ ቸነፈር ሆነ በቸነፈሩም ከህዝቡ ሰባ ሽህ ሰው ሞተ ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር የዳዊትን ልመና ሰማ መቅሰፍቱም ተከለከለ ፡፡

የሆነ ነገር ልክ እንዳልሆነ ተሰምቶህ ያውቃል ? ከጭንቀት ተላቀሃል ወይስ ማታ ለመተኛት ትቸገራለህ ? በጭንቅላትህ ደግመህ ደጋግመህ አንድን ነገር ታሰታውሳለሀ ? ቁምና እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ ስተህና እርሱን በድለህ ከሆነ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡ ይህ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ከሀጢአትህ ያነጻሀል ፡፡ ኝስሀ እስካልገባህ ድረስ የጥፋተኝነት ስሜቱ ካንተ አይርቅም ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉን የሚያውቅና የሚወድ ነው ፡፡ ነገሮችን ለማስተካከልና ይቅርታን ለመጠየቅ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፡፡ለአእምሮህ ከሚሰማህ ከባድ ስሜት ያሳርፍሀል ፡፡ አሁን ስለ ይቅርታውና ምህረቱ አመስግን ፡፡ ደግሞም አስታውስ ምንም ነገር ከእርሱ ፍቅር እንደማይለይህ ፡፡

“ ህዝቡንም ከቄጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው ዳዊትም እግዚአብሔርን ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ አሁን ግን አቤቱ ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባርያህን ኃጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው ፡፡ “

  • 2ኛ ሳሙኤል 24 ፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሞ 9፡1 –“ በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ አልወሽምም ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱሰ ይመሰክርልኛል ፡፡ “

ኤፌሶን 2፡4-5 –“ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን ፡፡ “

1ኛ ጴጥሮስ 3፡16 – “ በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንድያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ ፡፡ “