God Answered David's Prayers
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ሳምንት 2 ሳሙኤልን በመጨረስ ወደ 1 ነገስት እንገባለን ፡፡ 2 ሳሙኤል ከአንዱ በኋላ ሌላ ትልቅ ክስተት ነበረው ፤ በምዕራፍ 7 በዳዊት ኪዳን እና ዘላለማዊዉ ዙፋን ላይ ተመልክተናል ፡፡ ከመቀባቱ በኋላ የዳዊት የኃጢዓት ህይወት በምናደርገዉ ነገር ጥሪያችንን ልናጣዉ እንደ ማንችል ያረጋግጥልናል ፤ ሰዉ ወደ መግደል በመራው ከቤርሳቤህ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት በማድረግ በዝሙት እንደ ቆሸሸ (2 ሳሙኤል 11) መዘበራረቅ በቤተሰቡ በኩል ከሆነበት አመታት በኋላ ዳዊታዊ ኪዳኑ በስፍራዉ አለ ፡፡ በዛሬዉ ጥናታችን በዳዊት መንግስት እስካሁን በ 2ሳሙኤል ካየነዉ ነገሮች በጣም የተበላሸ ሲሆን እናያለን ፤ በ 2ሳሙኤል 9 ዳዊት ለምርጥ ጓደኛዉ ለዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ርህራሄን አሳዬ ፡፡ በዚህ ራህራሄ ማሳየት እና ከሳሚ ጋር (2ሳሙኤል 16) በመገናኘት መካከል ሰዎስት አመት ቆይታ ነበር ፤ ይህ የጊዜ ቆይታ በ 2ሳሙኤል 21 ዝርዝር ሲሆን የዘመን ቅደም ተከተሉን የተበቀ አይደለም ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (21፡ 1-4)፡ ይህ የሰዎስት አመት ጊዜ እስራኤል ድርቅን የቀመሰበት አመት ነው ፤ ዳዊት ለምን ብሎ በጠየቀ ጊዜ ሳዖል እና ቤተሰቡ የገባዖናዊያንን ደም አፍስሰዉ ስለ ነበር እንደ ነበር ተነገረው (ቁጥር 1) ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር እንዳዘዛቸው እስራኤላዊያን ያልሆኑትን ከተስፋይቱ ምድር ለማጥራት በመሞከር “ ሳዖል ከ 400 አመት በፊት በኢያሱና እስራኤል ንብረታቸዉን ወስዶባቸዉ በነበሩት በገባዖናዊያን መካከል ተደርጎ የነበረዉን ኪዳን እንደ ሰበረው “ ይገልፃል (ኢያ 9፡ 3-27፣ 2 ሳሙ 21፡ 2) ፡፡
ሮሜ (8፡ 28) የሚለው “ እግዚአብሄርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናዉቃለን “ ፤ ፒፐር ዮሐንስ የጭንቅን አምስት አላማዎች አጋርቷል፡
- ንስሀ ፡፡ ችግሮቻችን ከእግዚአብሄር ጋር ካለን ግንኙነት ሊያርቁን ካገኙን ነገሮች እንድንመለስ ለእኛ መጥሪያችን ነው ስለሆነም ወደ እርሱ መመለስ እንችላለን (ሉቃ 13፡ 4-5) ፡፡
- መተማመን ፡፡ ችግሮቻችን ለኑሮአችን በእግዚአብሄር ወደ መታመን እንድንመለስ ይጠሩናል ( 2ቆሮ 1፡ 8-9) ፤ ፓሰተር ጎርድይ አንድ ቀን በዙሪያችን እየነዳን እንደ ነበር በክስተቱ እግዚአብሄር እንዲሰራ ቦታ እንደምንሰጠው ነግሮናል ፡፡
- ቅድስና ፡፡ ችግራችን የእግዚአብሄር ደቀ መዝሙር እንድንሆን ያስተምረናል በዚህም በቅድስናዉ እና በቅዱስነቱ ለመኖር መማር እንችላለን (ዕብ 12፡ 6፣ 10-11) ፤ ችግራችን እርሱን በደንብ እንድንመስለዉ ያደርጉናል ፡፡
- ሽልማት ፡፡ ችግራችን በሰማይ ለሽልማታችን እንድንዘጋጅ ይረዳናል ( 2ቆሮ 4፡ 17) ፡፡
- አስታዋሽ ፡፡ ችግራችን ኢየሱስ ለኛ እንዴት መከራ እንደ ደረሰበት እንድናስታዉስ ይረዳናል በዚህም በእግዚአብሄር ፍርድ አንጨነቅም (ፊል 3፡ 10) ፡፡
ርሀባ ሲደርስበት ዳዊት ያደረገዉ ወደ መጣው መሲህ አመልክቷል ፡፡
2-ሳሙኤል (21፡ 3-9)፡ ከእግዚአብሄር ከሰማ በኋላ ዳዊት ለእነርሱ የሳዖልን ድርጊት እንዴት ሊያስተሰረይላቸዉ እንደ ሚችል ሊሰማቸዉ ገባዖናዊያንን ሰበሰባቸው (ቁጥር 3) ፤ ገባዖናዊያን ገንዘብ አልፈለጉም ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት የሚሰቅሉዓቸዉ ሰባት የሳዖል ወንድ ዘር የሆኑ እንዲሰጧቸዉ ጠየቁ ፤ ዳዊትም ተስማማ (ቁጥር 4-6) ፡፡ ከዮናታን ጋር በነበረዉ መሀላ ምክንያት ዳዊት የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነው ነገር ግን ሌሎች ሰባት ዘሮችን አሳልፎ ሰጣቸው (ሌላ ሜሞፊቦስቴ ተብሎ የሚጠራዉን ያካተተዉን የቤተሰብ አባል በማካተት ) (ቁጥር 7-8) ፡፡ ሰባቱ ገብስ በሚሰበሰብበት በመጀመሪያዉ ቀን ላይ በአንድ ተራራ ላይ ተሰቀሉ (ቁጥር 9) ፡፡
2-ሳሙኤል (21፡ 10-14)፡ የሪጽፋ ሁለት ልጆች ከተሰቀሉት ከሰባቱ መካከል ስለ ነበሩ ወደ ተራራዉ በመሄድ ለራሷ ማቅ ልብስ አነጠፈች በዚህም ሰዉነታቸዉን ከአዕዋፍታ እና ከዱር እንስሳት መከላከል ቻለች ፡፡ በዚያም እንደ ነበረች ዝናብ በሰዎነታቸዉ ላይ ወረደ ፤ ዳዊት እግዚአብሄር አዝዞት እንደ ነበረዉ ስላደረገ ርሀቡ አበቃ (ቁጥር 10) ፡፡ ዳዊት ሪጽፋ አድርጋ የነበረዉን በሰማ ጊዜ የሳዖልን እና የዮናታንን አጥንት ከኢያቢስ ገለዓድ በመዉሰድ ሪጽፉ ወደ ነበረችበት አመጣቸው ፤ ተሰቅለዉ የነበሩትንም የሰባቱን አጥንት በመሰብሰብ ሁሉንም በሳዖል አባት በቄስ መቃብር ዉስጥ ቀበሩአቸው (ቁጥር 11-14) ፤ እግዚአብሄርም ለምድሪቱ ፀሎትን መለሰ ፡፡
መደምደሚያ
በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ከሽፋን ስር ያሉ ነገሮችን በመጥረግ እንዳይገጥሙን ወይም ለመመርመር ለመሞከር እናዘነብላለን ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ተሰብሮ የነበረዉ ኪዳን መመርመር እና ትክክል በማድረግ እንዲተገበር ፈለገ፡፡ የሚያስገርመዉ ነገር የሆነን ነገር ትክክል ለማድረግ ሰባት ሰዎችን አንሰቅልም ምክንያቱም ቀድሞ ኢየሱስ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ስለ ተሰቀለ ፤ ይሁን እንጂ ሁላችንም በእግዚአብሄር ላይ ካልተደገፍን በድርቅ ወቅት ላይ ነን ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን ወደ መስቀሉ በምንመጣ ጊዜ ህይወትን እንቀበላለን !
ዳዊት እግዚአብሄርን ስለ ተመለከተ የዳዊትን ፀሎቶች መለሰለት ፤ እግዚአብሄር ለእኛም እንደዛዉ ማድረግ ይፈልጋል ፤ ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ባለን ግኝኙነት ብቻ ሊሆን ይችላል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2003, p. 380.
John Piper, “Five Purposes for Suffering,” www.desiringGod.com.
ጥያቄዎች
-
በ 2ሳሙ (21፡ 1-14) እግዚአብሄር ዳዊትን ለድርቅ የሰጠበት ምክንያት ምን ነበር ? ስለዚህ ነገር ዳዊት ምን አደረገ ?
-
በ 2ሳሙኤል ቁጥር 17 የዳዊት ጦር ሰዎች ወደ ዉጊያ ከእነርሱ ጋር መሄድ እንደ ማይችል ለምን ነገሩት (2ሳሙ 18፡ 3) ? በድርሻቸዉ ላይ ይህ ጥሩ ዉሳኔ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ?
-
2 ሳሙ (22፡ 29) እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ? (መዝ 27፡ 1፣ 119፡ 105፣ ኢሳ 9፡ 2፣ 60፡ 1፣ ዮሐ 8፡ 12፣ 12፡ 36-37)
-
በ 2ሳሙኤል (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 21:1
“During David’s reign there was a famine for three successive years, so David inquired of the Lord. The Lord answered, ‘It is because of the blood shed by Saul and his family when he killed the Gibeonites.’”
በዳዊት ዘመን ለሶስት አመት በእስራኤል ራብ ሆነ ፡፡ ዳዊትም እነዚህ የስቃይ ጊዜያት ለምን በእነርሱ ላይ እንደሆነ እግዚአብሔር ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም ይህ ሳኦልና ቤተሰቡ የገባዖን ሰዎችን ስለ ገደሉ እንደሆነ ተናገረ ፡፡ ዳዊትም ይህን ነገር ለማስተካከል የሚያደርገውን ያውቅ ዘንድ በትህትና ወደ ገባዖናውያን ሄደ ፡፡ ገባዖናውያንም የጠየቁትን ነገር ለማድረግ ተስማማ ፡፡ ከዳዊት የስርያት ተግባር በኋላ እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ዳዊት የለመነውን ሰማ ራቡም አበቃ ፡፡
ስለምን የችግር ጊዜያትን እያሳለፍክ እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠይቀኸው ታውቃለህ ? ወይም ለምን የተወደደ ሰው ህመምን እንደሚሸከም ? ወይም ስለምን ያንተ ልጅ በአስቸጋሪው መንገድ መሄድ አለበት ብለህስ ፡፡ በችግር ጊዜ ማስታወስ ያለብን ቁልፉ ነገር ቶሎ ከእግዚአብሔር ምሪት እና እርዳታ መጠየቅ ነው ፡፡ በእርሱ ለሚታመኑት ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንደሚደረግላቸው ኢየሱስ ተናግሯል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ስትመለስ ይረዳሀል የምትችልበትንም አቅም እንድሁ ፡፡ ወደ ንስሀም ይመራሀል ወይም በራስህ ሳይሆን በእርሱ በደንብ እንድትታመን ያደርግህ ይሆናል ነገር ግን ሁሌም እርሱ ይረዳህ ዘንድ ከጎንህ ነው ፡፡ ዛሬ በችግር ውስጥ ከሆንክ እግዚአብሔር ካንተ ጋር በመሆኑ ተስፋ አድርግ ፡፡ በችግርህ ብቻህን አይደለህም ፡፡
“ በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል ቀጥሎ ቀጥሎ ራብ ሆነ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም የገባዖን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት አለ ፡፡ “
- 2ኛ ሳሙኤል 21፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ቆሮንቶስ 1፡8-9 –“ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ወንድሞች ሆይ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና ስለ ሕይወታችን እንኳ ተሰፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር አዎን ሙታንን በሚያነሳ በእግዚአብሔር እንጅ በራሳችን እንዳንታመን እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር ፡፡ “
ፊልጵስዮስ 3፡10 –“ እርሱንና የተንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ በመከራውም እንድካፈል ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ ፡፡ “
ዕብራውያን 12፡7-11 –“ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና……….. ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሰዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።