Historical Books 2 Samuel

Reasserting His Kingship

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 252 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሁለተኛ ሳሙኤል ጥሩ አሳሳል አለው ፤ መፅሀፉ ወደ ሚመጣዉ መሲህ ኢየሱስ የሚያመለክተዉን የዘላለም ዙፋን ለዳዊት በመሰጠቱ ይጀምራል ፤ ነገር ግን ከዚየ በኋላ ነገሮች መጥፎ ሆኑ ፡፡ ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ጉዳይ ስለ ነበረው የቤርሳቤህን ባል ለማስገደል አመቻቸ ፤ የዳዊት ልጅ አምኖን የወንድሙን እህት ትዕማርን ደፈራት ፤ እንዲሁም የትዕማር ወንድም አቤሴሎም የዳዊትን መንግስት ለመዉሰድ ሞከረ ፤ ከዚያም በኋላ ኢዮአብ እና ሰዎቹ አቤሴሎምን ገደሉት ፡፡ ከጦር ሜዳ የሆኑመልዕክተኛች ዳዊትን ስለ አቤሴሎም መሞት በነገሩት ጊዜ ዳዊት አለቀሰ ፡፡

ትምህርት

2-ሳሙኤል (19፡ 1-4)፡ አቤሴሎምን ለማሸነፍበተደረገዉ ዉጊያ ሀያ ሺ ወታደሮች ሞቱ ፡፡ አቤሴሎም በንጉሱ ላይ ጦሩን ቢመራም የንጉሱ ሰራዊት አሸነፈው ዳዊት እያዘነም ስለ ነበር ድሉ ወደ ኃዘን ተቀየረ ፡፡ ከደዚህ አይነት ትልቅ ድል በኋላ ወታደር አያዝንም ነገር ግን ዳዊት በአቤሴሎም ላይ ድልን ማግኘት ችሎ ስላልነበር ወታደሮቹ እንዳሸነፉ እንዲሰማቸዉ ቤት ሄዱ ፤ ዳዊትም እንዳዘነ ፊቱን በመደበቅ ተስፋ በመቁረጥ ዉስጥ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 5-7)፡ አቤሴሎምን የገደለዉ እና ችግሩን ጥንቃቄ የወሰደዉ ኢዮአብ ወደ ዳዊት በመምጣት በመልካም ዳዊት ሀዘኑን እንዲያበቃ ነገረው ፤ ኢዮአብ የዳዊት ሀዘን ወታደሮቹ ለእርሱ ያደረጉለትን ዋጋ አለመስጠት እንደሆነ በመግለፅ ዳዊት አቤሴሎም ከሚሞት ይልቅ ወታደሮቹ ቢሞቱ የሚሻለዉ እንደሆነ ነገረው ፡፡ በግልፅ ዳዊት የደስታ ወሬ ያስፈልገዉ ነበር ነገር ግን የኢዮአብ ድፍረት ችግር ፈጠረ ፡፡ ዳዊት በፍፁም እግዚአብሄርን አልተመለከተም ወይም ወደ እግዚአብሄር አልጮኸም ፤ ከዚህ በፊት ዳዊት ስለ ሳዖል እና ስለ ዮናታን ሞት ወደ እግዚአብሄር አለቀሰ ነገር ግን እዚህ ያን አላደረገዉም ፤ እግዚአብሄርን ሳይፈልግ በልጁ ሞት እያለቀሰ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 8-10)፡ ሰዎች በሩ ላይ በተቀመጡ ጊዜ ለስልጣን የተቀመጡ ነበሩ ፤ በበሩ ላይ የዳዊት መቀመጥ ለህዝቡ የመመለሱ እና የመሾሙ ምልክት ነበር ፤ ነገር ግን በስዓቱ ህዝቡ ስለ ንጉሱ ምን እንደሚያስቡ እርግጠኞች አልነበሩም ፡፡ በአንድ በኩል ዳዊት ህዝቡን ከፍልስጤማዊያን ታድጓቸዉ ነበር ፤ በሌላ በኩል ዳዊት አቤሴሎምን ሸሽቶት ስለ ነበር አቤሴሎም የተቀባ ንጉስ ሆኖ ነበር ፡፡ አሁን ህዝቡ ማን እንደ ሚከተል እርግጠኞች አልነበሩም ፤ ዳዊት በይሁዳ ነገድ ክፍል ላይ ብቻ ወይስ በሁሉም ነገድ ላይ ነበር ?

2-ሳሙኤል (19፡ 11-13)፡ ዳዊት እንደ ንጉስ ጥሪዉን እንደ ገና ማነሳሳት ጀመረ ፤ ለንጉስ ተግባር ራሱን ለማደስ ፈጣን እርምጃ ለመዉሰድ ጀመረ ፡፡ ዳዊት እንዴት ጨዋታዉን መጫወት እንዳለበት ያዉቃል ፤ ፖለቲካዊ መዋቅሩንም ያውቃል ፤ ይህ ማገገሚያ ዘመቻ ከመጀመር ጋር የሚመሳሰል ነበር ፡፡ ዳዊት ወደ ይሁዳ ሽማግሌዎች በመሄድ ዙፉኑን ማደስ ለመጀመር በዝምድና ትስስር ጥያቄ አደረገ ፤ አሜሳይም የዳዊት ወታደሮች እንደ አዛዥ የኢዮአብን ቦታ እንደሚወስድ ለአሜሳይም ቃል በመግባቱ ዉስጥ የፖለቲካዊ ስልቱ ነበር ፡፡ ዳዊት ምናልባትም ኢዮአብን በጉብን ጠላቱ አሜሳይም ለመተካት ፈለገ ምክንያቱም ኢዮአብ ከዳዊት ፍላጎት ዉጪ አቤሴሎምን ስለ ገደለው ከዚያም በኋላ በእርሱ ቀጠለ ፤ ነገር ግን ዳዊት አሜሳይን በማስተዋወቅ የአመፀዉን ሰራዊት አንድነት ለማዳን እየሞከረ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 14-15)፡ የዳዊት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ስልታዊ ስራን አስታረቀ ፡፡ ዳዊት በአቤሴሎም ኃዘን ስርዓት ተጎድቷል ፤ እንደ አባት ወይም እንደ ባል ባደረገዉ ስህተት አድርጓል ነገር ግን ኢዮአብ ስላነቃው የእግዚአብሄር የተቀባ ንጉስ በመሆን እንደ ገና በጥሪዉ ለመሄድ ጀመረ ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 16-20)፡ ሳሚ ዳዊት በተሰደደ እና ድንጋይ በመወርወር እርግማን በዳዊት እ በሰዎቹ ላይ በተደረገ ጊዜ ዳዊትን ተከትሎት የነበረ ሰዉ ነበር ፤ አሁን ሳሚ አድርጎት ስለ ነበረዉ ሁለተኛ አሳብ ነበረው ንጉሱን ለመቀበል በጥድፊያ ከእርሱ ጋር 1,000 ሰዎችን ከቢኒያም አመጣ ፤ ይህ በሳዖል ቤተሰብ ወደ መጨረሻ እየመጡ እንደ ነበር ያለፈዉ ጠላትነት ምልክት ነበር ፡፡ በሳዖል ቤት ሌላዉ አገልጋይ ሲባ ንጉሱን ሊገናኘዉ መጣ ፤ ሲባ ሜምፊቦስቴን ለመንከባከብ እምቢ ባለ ጊዜ ከዳዊት ፍላጎት ዉጪ ተግብሮ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ሳሚ ግን ላለፈዉ ተግባሩ ምክንያት አላደረገም ፤ ወደ ወቀሳ ዞር ለማለት አልሞከረም ነገር ግን ከሁሉም የዮሴፍ ቤተሰብ እንደ መጀመሪያ ዘር ወደ ፊት ለመጓዝ ዝግጁ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 21-23)፡ አቢሳ ከመጀመሪያዉ ሳሚን አይወደዉም ፤ በ 2ሳሙ (16፡ 9) ሳሙ ንጉሱን እየተሳደበ በነበር ጊዜ አቢሳ ዳዊትን “ ይህ የሞተ ዉሻ ጌታዬን ንጉሱን ስለምን ይረግማል ? ልሂድና ራሱን ልቁረጠዉ አለው ! “ በምዕራፍ 16 አቢሳ ሳሚን ሊገድለዉ ፈለገ አሁንም ሊገድለዉ ፈለገ ፡፡ በመሰረቱ የዳዊት ምላሽ “ ንጉሳችሁ አይደለሁምን ? በሁለቱም ወገን ለነበሩት ሰዎች በስልጣን ላይ የነበርኩ “ የሚል ነበር ፤ ዳዊት ሳሚን እንደ ማይገድለዉ ማለለት ነገር ግን ለሌላ እንደ ማያደርግበት ቃል አልገባለትም ፤ በ 1ነገ (2፡ 8-9) ዳዊት ሰለሞንን የሚለው “ በጌራ ልጅ በሳሚ ላይ አይንህን አድርግ…..እኔም ወደ መሃናይም በሄድሁ ጊዜ ብርቱ እርግማን የረገመኝ የብራቂም አገር ሰዉ የብናያማዊዉ የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ በአንተ ዘንድ ነው ፤ እርሱ ግን ዮርዳኖስን በተሸገርሁ ጊዜ ሊቀበለኝ ወረደ እኔም በሰይፍ አልገድልህም ብዬ በእግዚአብሄር ምዬለታለሁ ፡፡ አንተ ግን ጥበበኛ ሰዉ ነህና ያለ ቅጣት አትተወዉ ፤ የምታደርግበትንም አንተ ታዉቃለህ ሽበቱንም ከደም ጋር ወደ መቃብር አዉርደዉ “ ፡፡ ዳዊት ትልቅ ስዕል አመጣ ፤ የሀቀኝነት(የአንድነት) ሰዉ ነበር ነገር ግን ስርዓቱን እንዴት እንደሚሰራ ያውቃል ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 24-30)፡ ምናልባትም እንደ ሀዘን ምልክት ሜምፊቦስቴ ዳዊት ከኢየሩሳሌም ከወጣ ጀምሮ ታጥቦ ወይም ፀጉሩን አልተቆረጠም ነበር ፤ ሜምፊቦስቴ ዳዊትን ሲባ እዚያዉ ትቶት በመሄድ አህያዉን እንደ ወሰደበት ነገረው ፡፡ ዳዊት ማንኛዉ እዉነት እየነገረዉ እንደ ነበር እርግጠኛ ስላልነበር ዳዊት ሲባን እና ሜምፊቦስቴን ንብረታቸዉን እንዲካፈሉ አዘዛቸው ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 31-39)፡ ቤርዜሊን በዮርዳኖስ በሌላኝዉ በኩል በነበር ጊዜ ዳዊትን እንክብካቤ አድርጎለት ነበር ፤ አሁን ዳዊት ቤርዜሊን ከእርሱ ጋር እንዲመጣ ፈለገ ስለሆነም ሞገስን ይመልስለታል ፤ ቤርዜሊን እምቢ አለ ምክንያቱም አርጅቶ ስለ ነበር ዳዊት አቅርቦለት በነበረዉ ሁሉም መልካም ነገሮች መደሰት አይችልም ፤ በዚያ ፋንታ ቤርዜሊን ዳዊትን ምናልባትም የቤርዜሊን ልጅ የነበረዉን መዓምን እንዲወስደዉ ጠየቀዉ ዳዊትም ተስማማ ፡፡

2-ሳሙኤል (19፡ 40-43)፡ ዳዊት በጥሪዉ መጓዝ እንደ ጀመረ በእስራኤል ሰዋች (በአስሩ ነገድ) እና በይሁዳ ነገድ መካከል ክርክር ነበር ፤ የእስራኤል ሰዎች በዳዊት በድብቅ የይሁዳ ነገድ ለምን ዮርዳኖስን እንደ ተሸገረ ለማወቅ ይጠይቃሉ ፡፡ በሁለቱ ነገዶች መካከል ያለዉ ምሬት ሰለሞን በሞተ ጊዜ መከፋፈል ይሆናል ነገር ግን በንጉስ ዳዊት ምክንያት እዚህ ጋር ሁሉም አብረው መጥተዋል ፡፡

መደምደሚያ

በመጨረሻም ዳዊት ዉድቀቱን እና ፍራቱን ተቋቋመ ምክንያቱም እንደ ንጉስ ጥሪዉን ስለ ተከተለ ፤ ዳዊት ጥሪዉን በመከተሉ ምክንያት የእስራኤል ሰዎች በአንድ መጡ ፡፡ 1 ቆሮ (7፡ 17) “ ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሄር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሄር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመስላል “ ይላል ፤ ዳዊት በትሪዉ መጓዝ በጀመረ ጊዜ ሁሉም ተፅዕኖ ተደርጎበታል ፡፡ ኤፌ (4፡ 1) “ እንግዲህ በጌታ እስር የሆኑህ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ “ ይላል ፤ ዳዊት ከእግዚአብሄር ጥሪ ተቀብሎ ነበር እናም አሁን በጥሪዉ መጓዝ አስፈለገው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የዳዊት ሰዎች ስለ አቤሴሎም ለዳዊት ለቅሶ እና ሀዘን እንዴት ምላሽ ሰጡ (2ሳሙ 19፡ 3) ? በዚህ መንገድ ለምን መለሱለት ( 2ሳሙ 19፡ 5-6) ? በአስቸጋሪ ጊዜ ጥበብ የጎደለዉ ስሜታዊነት ፈቅዳችሁ ታውቃላችሁ?
  2. በ 2ሳሙኤል 19 ስለ ሜምፊቦስቴ እዉነቱ ወጣ (2ሳሙ 16፡ 1-4) ፤ ንጉሱ ለሁኔታዉ እንዴት መፍትሄ አመጣ ? ወይስ እንዴት አደረገ ? በዘዳ (19፡ 18-19) መሰረት እንደ አንድ ሀሰተኛ ምስክር የሲባ ቅጣት ምን መሆን አለበት ?
  3. በ 2ሳሙ (20፡ 1-2) እንዳደረገዉ ልክ እንደ ሳቤዔ ተፅዕኖአቸዉን በመጠቀም ሰዎችን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሰለ ሚያዞሩ ስለ ተረገሙ ሰዎች አንዳንዴ አንብበናል ፤ ሰዎች የአመፅን ድምፆች በመስማት ለምን እንደ ሚከተሉዓቸዉ ምን ታስባላችሁ (ዘዳ 13፡ 13፣ 1ሳሙ 30፡ 22፣ ማቴ 27፡ 20፣ ሐዋ 14፡ 2፣ 21፡ 27-30) ? በተሳሳተ የተመራ ካለመሆን ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን ? (መዝ 1፡ 1-2፣ 86፡ 11፣ 119፡ 11፣ 105፣ 143፡ 8፣ 1ቆሮ 16፡ 13-14)
  4. የሳቤዔ እስራኤል ከዳዊት ዘንድ ድርሻ የለዉም የሚለዉ ክርክር እዉነት ነበር (2ሳሙ 20፡ 1) ? ሳቤኤል ምን ሆነ ? በ 2ሳሙ (20፡ 22) የከተማዋን ምላሽተፅዕኖ ያደረገችዉ የሴቲቱ ገለፃ ምን ነበር ? በዙሪያቸዉ ያሉትን ሰዎች ተፅዕኖ ያደረጉት ሳቤዔንና በቤሪም ቤተ መዓካ የነበረችዉን ሴት የእነዚህን ሁለት ሰዎች መንገድ እንዴት ታነፃፅሩታላችሁ ? (ምሳ 1፡ 7፣ 6፡ 12-19)
  5. በ 2ሳሙኤል (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 19:18

“They forded the Jordan to bring the king’s household across and do whatever the king desired.”

ልክ ዳዊት ጥሪውን እንደ ንጉስ ማራመድ ሲጀምር መንግስቱን ብቻ አልነበረም መልሶ ያገኘው ግንኙነቶቹንም ጭምር እንጂ ፡፡ የዳዊት ሰራዊት አለቃ ኢዮአብ ለዳዊት እውነቱን ተናገረው ስለ ልጁ ሞትም ሀዘን ውስጥ ሳለ ገሰጸው ፡፡ ከዚያም የጌራ ልጅ ሳሚ ስላደረገው ርግማንና ስድብ ይቅርታ ጠየቀ ፡፡ በትህትና ዳዊት ለሁለቱም ሰዎች ይቅርታን አደረገ ፡፡ ዳዊት ከድቶኛል ብሎ የሚያስበው ሜምፊቦስቴም በፊቱ ቀርቦ በአገልጋዩ ሲባ የተነገረውን የውሸት አውነት እውነቱን በመናገር አጋልጧል ፡፡ ዳዊትም ለሜምፊቦስቴ ርኅራኄ አሳየው ፡፡ ዳዊት የሰማንያ አመት የሆነውን ቤርዜሊን ስለ እርዳታው መረቀው ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግንኙነቶች ዳዊት ምህረትንና እውነትን አደረገ እንደ ንጉሥም ወደ ፊት ሲራመድ ሁሉንም ግንኙነቶች እንደገና መለሰ ፡፡ እግዚአብሔርም ስለ መታዘዙ ባረከው ፡፡

እግዚአብሔር እንደገና የሚመልስ አምላክ ነው ፡፡ ኃጢአተኛ የሆንከውን አንተን ከልጁ ጋር ወዳለው እውነተኛ ግንኙነት መለሶሀል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ፤ እንደ መንግስቱም ወራሽ ፤ እንደዚህ ላለ ጊዜም እንደተቀባ ሰው ወደ ተጠራህበት ጥሪ ሰትገባ እግዚአብሔር በህይወትህ ተቋርጠው የነበሩትን ነገሮች ይመልሳል ፡፡ በቅንነትና በፍቅር ጥሪይህን አስቀጥል ፡፡ ዛሬ ቆም በልና ወደ ልብህ ፤ ከሌሎች ጋር ወዳለህ ግንኙነት ወይም ከኢየሱሰ ጋር ወዳለህ ግንኙነት ይመልስህ ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ እርሱም ይመልስሀል ፣ ይመሰርትህማል ደግሞም ያጠነክርሀል ፡፡ ህይወትህ እግዚአብሔርን ስለ ምርኮው ሁሉንም ነገር አድስ ስለሚያደርግ ሀይሉም የማመስገን ይሁን ፡፡

“ ታንኳውም የንጉሥን ቤተ ሰብ ያሻግር ዘንድ ንጉሡም ደስ ያሰኘውን ያደርግ ዘንድ ይሸጋገር ነበር ፡፡ “

  • 2ኛ ሳሙኤል 19፡18

ተጨማሪ ጥቅስ

ገላትያ 6፡1 –“ ወንድሞች ሆይ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ ፡፡ “

ኤፌሶን 4፡1 –“ እንግዲህ በጌታ አስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ ፡፡ “

1ኛ ጴጥሮስ 5፡10 –“ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የፀጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል ፡፡ “