Historical Books 2 Samuel

Absalom's Fall

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 251 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኩሲ እና አኪጦፌል ዳዊትን የተለያየ ምክር ሰጡት ፤ ዳዊት የአኪጦፌልን ምክር ባልተቀበለ ጊዜ አኪጦፌል ራሱን ሰቀለ ፡፡ የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ከዳዊት ኃላ በዮርዳኖስ ላይ ሊያሳድደዉ ወሰነ ፤ እየሮጠ ዳዊት ጥቂት ድጋፍ አገኘ ፡፡

ትምህርት

2-ሳሙኤል (18፡ 1-3)፡ በምዕራፍ 18 ኢዮአብ ታዋቂ ሰዉ ይሆናል ፡፡ ስለ ዳዊት የሆነ ነገር ሆኖ ነበር ፤ ከቤርሳቤህ ኃጢዓት በኋላ ዳዊት የፈዘዘ ሆኗል ፤ እየተጓዘበት በነበረው ትክክለኛዉ ጥንካሬ እንደ ነበር ይህ አይከሰትም ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄርን የራሱን ልብ የተከተለ ሰዉ ነበር ፡፡ ዳዊት ወታደሮቹን በመከለስ ወደ ሰዎስት ከፈላቸዉ ፤ አንድ ሰዎስተኛዉ በኢዮአብ አዛዥነት ስር አስቀመጠ፣ አንድ ሰዎስተኛዉን በኢዮአብ ወንድም አቢሳ አዛዥነት ስር አስቀመጠ እና የመጨረሻዉ አንድ ሰዎስተኛ ደግሞ ከኢታይ አዛዥነት ስር አስቀመጠ(አደረገ) ፡፡ ዳዊት ከጦሩ ጋር ለመዝመት እንዳሰበ ገለፀ ነገር ግን ህዝቡ ከተማዋን እንዲጠብቅ በዚያዉ እንዲቀር ለመኑት (ቁጥር 2-3) ፡፡

2-ሳሙኤል (18፡ 4-5)፡ ዳዊት ህዝቡ እንደ ጠየቀዉ በማድረግ ሲሄዱ ጦሩን አበረታታ ፤ ነገር ግን ዳዊት ኢዮአብን የሁሉም ችግር መነሻ አቤሴሎም ቢሆንም እንኳን በአቤሴሎም ላይ ቀላል ነገር እንዲያደርግ አዘዘው ፤ ጦሩም ሰሙት !

2-ሳሙኤል (18፡ 6-8)፡ የኤፍሬም ጫካ የት አካባቢ እንደ ነበር በትክክል አናዉቀዉም ነገር ግን በአቤሴሎም አዣዥነት ስር የነበረዉን የእስራኤልን ጦር ለመክበብ የዳዊት ጦር ዘምቶበት የነበረ ጥቅጥቅ ደን ነበር ፡፡ አቤሴሎም አባቱን ሊገድል ወጥቶ ነበር ነገር ግን የእርሱ ጦር በኃይለኛዉ በዳዊት ሰራዊት ተሸነፈ ፤ ጫካው በዚህ ዉጊያ ከነበረዉ ሰይፍ በይበልጥ በህይወት የዋጣ በጣም አስፈሪ ነበር ፤ ያ የእግዚአብሄር እጅ ይሆናል !

2-ሳሙኤል (18፡ 9)፡ አቤሴሎም ራሱ በዛፍ ተይዞ ሲወዛወዝ ተገኘ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የአቤሴሎምን ስድስት ባህሪያትን ዘርዝሯል፡

  1. መልኩ - “ በእስራኤል ሁሉ ዘንድ እንደ አቤሴሎም በዉበቱ የተመሰገነ ሰዉ አልነበረም ፤ ከእግሩ እስከ ራሱ ድረስ ነዉር አልነበረበትም ፡፡ ጠጉሩም ይከብደው ነበርና በዓመት አንድ ጊዜ ይቆርጠዉ ነበር ፤ ሲቆረጥም የራሱ ጠጉር በንጉስ ሚዛን ሁለት መቶ ሰቅል ያህል ይመዘን ነበር “ (2 ሳሙ 14፡ 25-26) ፡፡ አቤሴሎም እንደ ነበረው በመፅሀፍ ማንም እንከን እንደ ሌለበት የተጠቀሰ አልነበረም ! በተቃራኒው የአቤሴሎም ፀጉር በዛፍ ላይ ገደለዉ ምክንያቱም ተላጭቶት ስላልነበር ፡፡
  2. ሀብቱ - አቤሴሎም የንጉስ ልጅ ነበር ስለዚህም በነበረበት ከተማ የራሱ ቤተ መንግስት ይኖረዋል ፤ በተመሳሳይ ጊዜም አቤሴሎም በግ ሸላቾች ቀጥሯል ፡፡
  3. ጥቅሙ - አቤሴሎም የዳዊትን ዙፋን እንደ ወረሻ በመስመር ላይ ነበር የዳዊትም ልብ ነበረው(ዳዊት ይወደዉ ነበር) ፤ በእዉነት ዳዊት ይወደዋል ፤ አቤሴሎም አምኖንን ከገደለዉ በኋላም እንኳን አቤሴሎም ለሰዎስት አመት ባለመኖሩ ዳዊት አዝኖ ነበር ፡፡
  4. ብስጭት - አምኖን እህቱን ትዕማርን በደፈራት ጊዜ አቤሴሎም በአምኖን ላይ በቀልን ወሰደ ፡፡
  5. ምኞት - ከሁለት አመት ስደት በኋላ ዳዊት ሳያዉቅ አቤሴሎም የኃይል ሰፈር መገንባት ጀመረ ፤ ዳዊትን ለማጥፋት አመፀን ገነባ ፡፡
  6. ጭንቀት - ጦሩ በዳዊት ጦር ተሸነፈ በራሱም ፀጉር በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ተገኘ ፡፡

አቤሴሎም በዚህ መንገድ አልሄደም ፤ ለዙፉኑ በቀጣይ ተራ ላይ ነበር ! ነገር ግን የእግዚአብሄርን ጊዜ የማትጠብቁ ከሆነ ሁል ጊዜ ለእናንተ ነገሮች በመልካም አያበቁም ፡፡

2-ሳሙኤል (18፡ 10-15)፡ ከዳዊት ሰዎች አንዱ በዛፍ ላይ አቤሴሎም መጠልጠል ላይ በመከሰት ይህን ለኢዮአብ ነገረው ፤ ኢዮአብ ወታደሩ ለምን ወደ ታች አልመታኸዉም በማለት ተገረመ ነገር ግን ወታደሩ አቤሴሎምን እንዳትጎዱት ብሎት የነበረዉን የዳዊትን ማስጠንቀቂያ አስታወሰ ፤ እዚህ ላይ ኢዮአብ ከመስመር አለፈ ፡፡ ዳዊት አዛዦቹን ለአቤሴሎም ረጋ ያሉ እንዲሆኑ ፈለገ ነገር ግን ኢዮአብ አቤሴሎምን በመግደል የመጀመሪያዉን እድል ወሰደ (አደረገ) ፡፡ አንዴ አቤሴሎም ጥንቃቄ ቢደረግለት ጦርነቱ የሚያበቃ ይሆናል ኢዮአብም ነገሩን ማቆሸሽ አይፈልግም ነበር ፡፡ አቤሴሎም በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ እያለ ሞተ ይህ ማለት በእርግማን ሞተ ማለት ነው (ዘዳ 21፡ 22-23) ፤ አቤሴሎም ዛፍ ላይ አልሞተም ምክንያቱም ጠላቶቹ በዚያ ስለ ሰቀሉት ፡፡ እነዚህን ክስተቶች እግዚአብሄር ያመቻቻቸዉ ይመስላሉ ፡፡

2-ሳሙኤል (18፡ 16-17)፡ ኢዮአብ ማጥቃቱን ለማስቆም ቀንደ መለከት ነፋ ፤ ኢዮአብ አቤሴሎም ከሞተ ጦርነቱ እንዳበቃ ያውቅ ስለ ነበር ፡፡ የንጉሱ ልጅ ቢሆንም እንኳን የአቤሴሎም አካል ወደ አንድ ጉድጓድ ዉስጥ ተወረወረ ፤ በድንጋይ የመወገር ምልክት በሆነ በአካሉ ላይ ድንጋይ ከመሩበት ፤ በብሉይ ኪዳን አመፀኛ ልጆች በድንጋይ ተወግረዉ እንዲገደሉ ተደንግጎ ነበር ፤ አቤሴሎም ዋና አመፀኛ ልጅ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (18፡ 18-23)፡ ሁለት ሰዎች ስለ አቤሴሎም መሞት ዜና ለንጉሱ ለመናገር ለመሮጥ ፈለጉ፡ አኪማዓስ እና ምናልባትም ኢትዮጲያዉዉ የነበረው ኩሲ ፤ በሀሳባቸው አቤሴሎም ስለ ሞተ ንጉሱን የሚያስፈራ አይኖርም የሚለዉን ምላክም ዜና ለንጉሱ ለማድረስ እየሮጡ ነበር ፡፡ ኩሲ ንጉሱን ለማግኘት ከባድ አቀማመጥ ባለዉ ስፍራ በኩል ቀጥተኛ መንገድን መረጠ ፤ ምናልባት የለመደ መልዕክት አድራሽ እና የለመደ ሯጭ ነበር ፡፡ አኪማአስ በኢየሩሳሌም በዳዊት ፊት መልዕክቱን ይዞ ሄዶ ነበር መልክአ ምድሩን በተሸለ ያውቀዋል ምክንያቱም ቀጥተኛነቱ ባነሰ መንገድ ሄደ ነገር ግን መጀመሪያ ስለ ደረሰ ፡፡

2-ሳሙኤል (18፡ 24-33)፡ ዳዊት ብቻቸዉን እየሮጡት ከነበሩት ሯጮች እዉነታ ምክንያት መልካም ዜና ጠብቋል ፤ አኪማአስ መጀመሪያ በመድረስ የዳዊት ሰረዊት ድል ማድረግን ሪፖርት አደረገ ነገር ግን ስለ አቤሴሎም እጣ (ሁኔታ) አልነገረውም ፡፡ አኪማአስ መልካም ፍላጎት ነበረዉ ነገር ግን ሙሉዉን እዉነት አላደረሰም ፤ ተረጋጋም ስለ ዳዊት አመፀኛ ልጅ የመሞት መልካም ዜናን አላደረሰም ፡፡ ዳዊት ኩሲን ስለ አቤሴሎም ጠየቀው ኩሲም ስለ አቤሴሎም የመሞት ዜና አልደበቀም ፤ ኩሲ በሁሉም በዳዊት ጠላቶች ላይ ተመሳሳይ እጣ ተመኘ ፤ ነገር ግን ዳዊት በአቤሴሎም የመሞት ዜና እየተጨነቀ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት መጨረሻዉ ላይ አቤሴሎም እንደሚመለስ ተስፋ እንዳደረገ ይመስላል ፤ ዳዊት አባታችን እግዚአብሄር እኛን በእዉነት እንዴት እንደ ሚወደን በሚያስታዉስ መንገድ ልጁን ወደደው ፡፡ እግዚአብሄር አብ እኛን ወደ እርሱ ስቦ ለማምጣት ኢየሱስን እንደ ላከ ዳዊት ልጁን ወደ እርሱ ስቦ ለመመለስ ማንኛዉንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነበር ፡፡ በክርስቶስ ሞት ምክንያት ልጁ ወደ ህይወት ተመልሶ ስለ ሚመጣ ልጁ ሞተ የሚለዉን መልካም ዜና ማግኘት

ችለናል ፡፡

1ዮሐ (4፡ 10) የሚለው “ እግዚአብሄር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢዓታችንም ማስተሰሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሄርን እንደ ወደድነዉ አይደለም “ ፤ በአለም ላይ እግዚአብሄር ሁሉንም በዚህ መንገድ ይወዳል ፡፡ ዮሐ (3፡ 16) የሚለው “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረዉ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና “ ፤ የእግዚአብሄር እቅድ ሁልጊዜ ወደ ልጁ መልሶ ማምጣት ነው ፡፡ ሮሜ (8፡ 3) የሚለው “ ከስጋ የተነሳ ስለ ደከመ ለህግ ያልተቻለዉን እግዚአብሄር የገዛ ልጁን በኃጢዓተኛ ስጋ ምሳሌ በኃጢዓትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና “ ፡፡

ኢየሱስ ስለ እኛ ሞተ ፤ ሁልጊዜ የምተሰሙታ ታላቅ ዜና ነው ፡፡ የተለየው አካል ደግሞ ወደ ህይወት ተመልሶ መጥቷል ፤ ወደ ህይወት ተመልሶ በመምጣቱ ምክንያት እኛም ህይወት ይኖረናል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 417.

ጥያቄዎች

  1. ዳዊትን ስለ መከተለ ለአቤሴሎም የአኪጦፌል ምክር ምን ነበር ? ይህን በዳዊት ልጅ ላይ በዮሐ (11፡ 50) ከቀያፍ ሴራ ጋር ይነፃፀራል ፤ ይህ ምክር ስለ መሲሁ ሌላ ምን ክፍል ያስታዉሰናል ? (2 ሳሙ 17፡ 2፣ ማቴ 26፡ 31)
  2. ሁለት የተለያዩ ሰዎች አቤሴሎምን ጥሩ የሚመስል ምክር አቀረቡለት ፤ አቤሴሎም እና የእስራኤል ሽማግሌዎች ለመከተል የትኛዉን ምክር እንዴት አድርገዉ መረጡ (2 ሳሙ 15፡ 34፣ 2 ሳሙ 17፡ 14) ?
  3. ከሎዶባር የዓሚኤል ልጅ ማኪር ለዳዊት እና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ምግብ ያመጣላችሁ አንዱ ሰዉ ነበር ፤ በ 2ሳሙ (9፡ 4) ስለዚህ ሰዉዬ ሌላ ምን አንብበናል ?
  4. ዳዊት እና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ከአቤሴሎም እያመለጡ በነበሩ ጊዜ የታሰበ እቅድ ወይም ስልት ነበር (2ሳሙ 18፡ 1-3) ? ከጠላታችን ጥቃት ስር በሆንን ጊዜ በማስታወቅ ለስልታዊ ምላሽ የት እንዞራለን(ምላሽ እንሰጣለን) (ሮሜ 10፡ 3-5፣ ኤፌ 6፡ 11-18፣ ያዕ 4፡ 7-10፣ ይሁዳ 20-21 )
  5. ወታደሮቹ ወደ ዉጊያ በሄዱ ጊዜ የዳዊት ታላቅ ሀሳብ(ስጋት) ምን መሰለ (2ሳሙ 18፡ 5፣ 29፣ 32-33) ? ይህ ተገቢ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  6. በ 2ሳሙኤል (17-18) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 18:26

“The watchman saw another man running. He called out to the gatekeeper, ‘Look! Another man is running alone!’ ‘This one is also bringing good news,’ said the king.”

የንጉሥ ዳዊት ልጅ አቤሴሎም የዳዊት ባሪያዎች እስራኤልን በወጉ ጊዜ በዚያው ሞተ ፡፡ ስለዚህም ኢዮአብ ተዋጊዎቹን ለመሰብሰብና ውጊያው መጠናቀቁን ለማመልከት ቀንደ መለከት ነፋ ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ንጉሡ ዳዊት ማን ሄዶ መልካሙን ዜና ይናገር ዘንድ ተሰብስበው ተማከሩ ፡፡ ሁለት ሰዎችም ይሮጡና የምስራቹን ይናገሩ ዘንድ ወደዱ ፡፡ ሁለቱም በተለያየ መንገድ ሮጡ በተለያየ ጊዜም ደረሱ ተመሳሳይ የሆነ የምስራችንም ተናገሩ ነገር ግን በተለያየ መንገድ ነበር የተናገሩት ፡፡ ሁለቱም ግን ለንጉስ ዳዊት የምስራቹን በቀጥታ ወይም እውነት የሆነውን ብቻ አልተናገሩም ፡፡ ምንም እንኳ በውጊያ በተገኘው ድል የዳዊት መንግስት ቢመለስም ዳዊት ስለ መልካሙ ዜና ማለትም ልጁ ስለ ሞተ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነበረ ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ የያዝከው መልካም ዜና የልጁ መሞት ነው ፡፡ የኢየሱስ መሞት እግዚአብሔርን አባቱን ቢያሳዝነውም በእርሱ ለሚያምኑት በደላቸውን በመሸፈን ድልንና ተስፋን አስገኝቷል ፡፡ የምስራቹን በቀጥታና እውነቱን ብቻ ታደርሳለህ ? እውነቱ እግዚአብሔር ዓለምን መውደዱ ነው ስለዚህም አንድያና ብቸኛ ልጁን በእርሱ የሚያምኑ የዘላለምን ህይወት እንድያገኙ እንዳየጠፉ ወዶ ሰጠ ፡፡ ለእግዚአብሔር መንግሰት ክብርና ሞገስ ይሆን ዘንድ አንተ እንድትናገረው የተጠራኸው የምሰራች ይሄ ነው የልጁ መሞት ፡፡ ዛሬ የሩጫ ጫማህን አድርግ ከዝያም የወንጌሉን የምስራች አድርስ ፡፡

“ እርሱም ፈጥኖ ቀረበ ፡፡ ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኸ እነሆ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰወ አየሁ አለ ፡፡ ንጉሡም እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል አለ ፡፡ “

  • 2ኛ ሳሙኤል 18፡26

ተጨማሪ ጥቀስ

ዮሐንስ 3፡16 –“ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶኣልና ፡፡ “

ሮሞ 10፡15 –“ መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደተጻፉ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? “

1ኛ ዮሐንስ 4፡10 –“ ፍቅርም እንደዚህ ነው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተሰሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን አንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም ፡፡ “