Historical Books 2 Samuel

Absalom's Rebellion Against the King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 250 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 2ሳሙኤል 13 የዳዊት ልጅ አምኖን የወንድሙን እህት ትዕማርን ደፈረ ፤ ወንድሟም አቤሴሎም የእርሱ ሰዎች አምኖንን በበቀል ከመግደላቸዉ በፊት ሁለት አመት ጠበቀ ፡፡ ንጉስ ዳዊት በኃዘን በመጨነቅ በአምኖን ሞት በየቀኑ አዘነ ፤ አቤሴሎም ከእስራኤል በመሸሽ አቤሴሎምና ዳዊት በምዕራፍ 14 ከመታረቃቸዉ በፊት ሰዎስት አመት በዚያ አልነበረም ፡፡ በምዕራፍ 15 አቤሴሎም በዳዊት ዙፋን ላይ ማሴር በመጀመር ራሱን ንጉስ ብሎ አወጀ (2 ሳሙ 15፡ 10) ፤ አቤሴሎም እና ጦሩ ኢየሩሳሌም እንደ ቀረቡ ዳዊት ከአገልጋዮቹ ጋር ሸሸ የኢየሩሳሌምም ህዝብ ተከተሉት (2ሳሙ 15፡ 14) ፡፡ በመጨረሻም አቤሴሎም እና የዳዊት ሰራዊት እርስ በእርስ ፊት ለፊት በተገናኙ ጊዜ 20,000 ተገደሉ (2 ሳሙ 18፡ 6-8) ፤ ያም በምዕራፍ 16 ላይ መነሻና ግጭቱ እየተደረገበት የነበረውን ስሜት ሁለቱንም ይሰጣል ፡፡

ትምህርት

2-ሳሙኤል (16፡ 1-4)፡ ዳዊት ከቀረበዉ አቢሴሎም ሰራዊት ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ በኋላ በሜሚቦስቴ አገልጋይ ለዳዊት እና ለአገልጋዮቹ ምግብ ከነበረዉ ከሲባ ጋር ተገናኘ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ዳዊት ሜሚቦስቴ የት እንደ ነበር ጠየቀ ፤ ሲባ የሳዖል መንግስት ለእርሱ ይመለስልኛል ብሎ በመጠበቅ በኢየሩሳሌም እንደ ተቀመጠ መለሰለት (ቁጥር 3) ፡፡ ከዚያም ዳዊት የሜምፊቦስቴ የነበረዉን ሁሉ ለሲባ ሰጠው (ቁጥር 4) ፤ ዳዊት ሲባ ያለዉን ቢቀበልም ዉሸት ነበረበት ፡፡ ሲባም ራሳቸዉን ለመሸፈን ለማመቻቸት እየሰራ ነበር ፡፡

2-ሳሙኤል (16፡ 5-8)፡ ዳዊት ወደ ብረቂም ሄደ ፤ የሳዖል ዘመድ የጌራ ልጅ ሳሚ ከቤት በመዉት በዳዊት ላይ መራገም ጀመር በዳዊት ላይ እና በሰዎቹ - በአገልጋዮቹ፣ ከኢየሩሳሌም በሆኑት ሰዎች ላይ እና በዳዊት ወታደሮች ላይ ድንጋይ ወረወረ (ቁጥር 5-6) ፤ በተጨማሪም ሳሚ ዳዊትን በግድያ በመክሰስ (2 ሳሙ 3፡ 27-29፣ 4፡ 1-12፣ 7፡ 25-27) እግዚአብሄር መንግስቱን ለአቤሴሎም እንደ ሰጠዉ ዳዊትን ነገረው (ቁጥር 7-8) ፡፡ የሳሚ ቃል ከእግዚአብሄር አልነበረም ነገር ግን ጥቂት እዉነት ነበረው ፡፡

2-ሳሙኤል (16፡ 9-14)፡ የዳዊት ወንድም ልጅ አቢሳ ሳሚን “ እንደ ሞተ ዉሻ “ በመግለፅ እራሱን በመቁረጥ ዝም እንዲያስብለዉ ዳዊት እንዲፈቅድለት አማከረው (ሰቁጥር 9) ፡፡ “ የሞተ ዉሻ “ የሚለዉን ሀረግ ሜምፊቦስቴ በዳዊት ፊት ሲገኝ ሁኔታዉን ዋጋ ቢስ እና የተናቀ መሆኑን እንደ ገለፀበት አይተናል ፡፡ ዳዊት ልጁ አቤሴሎም ሊገድለዉ እየመጣ ሳሚ የእግዚአብሄር ቃል በእርሱ ላይ እያመጣ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 11) ፤ የአቢሳን ምክር ከመቀበል ይልቅ ዳዊት ትዕግስትን እና ገደብን አሳዬ (ቁጥር 12) ፡፡ ሳሚ ዳዊትን እና ሰዎቹን መከተሉን በመቀጠል ዳዊትን በመርገም ድንጋይ እና ቆሻሻ በእርሱ ላይ ወረወረ (ቁጥር 13) ፡፡ ሳሚ ያላቆመ ብስጭት “ በስጋ የዳዊት እሾክ “ ሆኖ ነበር (2 ቆሮ 12፡ 7-10) ፤ ይህን አይነት ጥቃት ለማሸነፍ ብቸኛዉ መንገድ በእግዚአብሄር ሰላም ማግኘት ነው፡፡ ዳዊት እና አገልጋዮቹ ከዚህ ከማያቋርጥ ጥቃት ደክመዉ ስለ ነበር በጊዜዉ ለማረፍ ቆሙ (ቁጥር 14) ፡፡

2-ሳሙኤል (16፡ 15-19)፡ ወዲያዉኑም አቤሴሎም እናየሚከተሉት እስራኤላዊያን በኢየሩሳሌም ደረሱ ፤ “ በእግዚአብሄር ጠቢብ “ እንደ ሆነ ይታሰብ የነበረዉ ከዳዊት አማካሪዎች አንዱ አኪጦፌል ከእርሱ ጋር ነበር (ቁጥር 15) ፡፡ ምናልባት አኪጦፌል የቤርሳቤህ ወንድ አያት መሆኑ ጠቃሚ ነው ፤ በቁጥር 16 የዳዊት ጓደኛ ኩስ በአቤሴሎም ፊት በመከሰት “ ሽህ አመት ያንግስህ ! “ አለ አቤሴሎም የኩሲ ታማኝነት የት ነበር በማለት ጠየቀ (ቁጥር 17) ፡፡ ኩሲ እግዚአብሄር መርጦት የነበረዉን የአቤሴሎም አባትን ንጉስ ዳዊትን እንዳገለገለዉ በተመሳሳይ ልጁን እንደ ሚያገለግለዉ መለሰለት (ቁጥር 18-19) ፡፡

2-ሳሙኤል (16፡ 20-23)፡ አቤሴሎም አኪጦፌልን ቀጣይ ምን እንደ ሚያደርግ ምክርን ጠየቀ (ቁጥር 20) ፤ አኪጦፌል አቤሴሎምን ዳዊት በኢየሩሳሌም ትቷቸዉ ከሄደዉ ቁባቶቹ ጋር እንዲተኛ በዚህም ለዳዊት አሰቀያሚ ይሆናል (ቁጥር 21) ፡፡ ከዳዊት ቁባቶች ወይም ህጋዊ ካልሆኑት ሚስቶቹ ጋር በመተኛት አቤሴሎም ለዳዊት ዙፋን መብቱን የሚያረጋግጥ ይሆናል ፤ አቤሴሎም በሰገነቱ ጣሪያ ላይ ድንኳን ነበረው የዳዊትን እያንዳንዳቸዉን ቁባቶቹ ሁሉም እስራኤላዊያን ምን እየተፈጠረ እንደ ነበር እንዲያዩ በመፍቀድ ወሰዳቸው (ቁጥር 22) ፡፡ በ 2ሳሙ ( 12፡ 11-12) በዳዊት ኃጢዓት ማስተዋወቅ ላይ ይህ በናታን የተተነበዬ ነበር ፤ ከኩሲ አንዳንድ እርግማኖች የናታንን ትንቢት የያዘ ንግግር ወደ እዉነት መምጣጡት አደንቃለሁ ፤ አቤሴሎም ይህን ድርጊት ለማድረግ የተቀበለዉ ምክር ከሌላ ቤተሰብ አባል የመጣ ነው ፡፡ ምዕራፉ የኢጦፌል ምክር የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ሚናገር አንድ ሰዉ ተቀበለዉ በሚል ንግግር ያጠቃልላል (ቁጥር 23) ፡፡

መደምደሚያ

ተላት በእኛ ላይ በዉሸት እና በክስ በመጣብን ጊዜ በእምነት እና በጥንካሬ እንመልሳለን ? ሰዎስት ምክሮች አሉ፡

  1. የጠላትን ዉሸት መቋቋም ፡፡ ጠላት ዉሸጻም እና የዉሸት አባት ነው (ዮሐ 8፡ 44) ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ የሚመጣ (ዮሐ 10፡ 10) ፤ “ እንግዲህ ለእግዚአብሄር ተገዙ ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙከእናንተም ይሸሻል “ (ያዕ 4፡ 7) ፡፡

የአባታችሁን ድምፅ ካወቃችሁት ከጠላት መለየት ትችላላችሁ ፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ድምፁን ያዉቁታል (ዮሐ 10፡ 27) በቃሉም ይጓዛሉ (ዮሐ 8፡ 31-32) ፤ ስለዚህ ከእርሱ ፍቅር ምንም ሊለየን አይችልም (ሮሜ 8፡ 12፣ 39) ፡፡

በክርስቶስ ባላችሁ ስፍራ በልበ ሙሉነት መጓዝ ! በክርስቶስ ከፍ ብለን ከሁሉም ገዚዎች እና ስልጣናቶች በላይ በሆነው(ኤፌ 1፡ 20-21) በእርሱ አጠገብ ተቀምጠናል (ኤፌ 2፡ 6) ፡፡ ከክፉ አድኖናል (ቆላ 1፡ 13-14፣ 2፡ 14-15) ፤ ኢየሱስ የጠላትን በጣም ዋጋ ያለዉን መጠቀሚያውን መሳሪያ ክስን በማስወገድ ወደ መልኩ ቀየረን (ሮሜ 12፡ 2)

በህይወታችሁ አንድ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ መቀበል ከጀመራችሁ በ 1ዮሐ (2፡ 20) ላይ ባለዉ ቅባት በልበ ሙሉነት መጓዝ ትጀምራላችሁ ፤ ይህ በመንገዱ ምንም ይምጣ በቅባቱ ለመጓዝ ዳዊት አግኝቶት የነበረው ነው ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2003, p. 373.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Samuel (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 414.

  3. Nelson’s Commentary, p. 389.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Bible Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 262.

ጥያቄዎች

  1. ህዝቡ በእርሱ ፍቅር እንዲወድቁ አቤሴሎም ያደረገዉ ምን ነበር ? ይህ ስልት ሰርቶ ነበር ? የመጨረሻ ግቡ ምን ነበር ?
  2. በቀረቡአቸዉ ሰዎች ተላልፈዉ በተሰጡት ሁለቱም ዳዊት በአቤሴሎም በተደረገው እና ኢየሱስ በይሁዳ በተደረገዉ መካከል ጥቂት ተመሳሳይነቶች ምን ናቸው ? (2ሳሙ 15፡ 9-23፣ ማቴ 26፡ 36፣ ዮሐ 13፡ 27)
  3. በ 2ሳሙ (15፡ 24-29)የዳዊትን እምነት እግዚአብሄር እንዴት እዉቅና ሰጠ ?
  4. በ ሳሙ (15፡ 31) ያደረገው የዳዊት ፀሎት ዉጤት ምን ነበር ? በህይወቱ እዚህ ስፍራ ላይ የዳዊት ልብ ከብዶ ነበር ፤ በዚያ ሁኔታ እንዴት እንፀልያለን ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  5. በ 2ሳሙኤል 16 ሳሚ ዳዊትን ስለምን ሰደበው ? ዳዊት ክሱን እንዴት አስተናገደ (2 ሳሙ 15፡ 26) ? እነዚህን ነገሮች በማለት ሳሚ እንዴት ህጉን ጣሰ ? (ዘጸ 22፡ 28)
  6. በ 2ሳሙኤል 15-16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 16:13–14

“So David and his men proceeded along the road as Shimei was going along the ridge of the hill opposite him. As Shimei went, he cursed David, and threw stones and dirt at him. Finally, the king and all the people with him arrived exhausted, so they rested there.”

ዳዊትና ሰዎቹ ከቤታቸው በሸሹ ጊዜ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ዳዊትን መራገም ጀመረ ፡፡ እንድሁም ድንጋይ ይወረውር ትቢያም ይበትን ነበር ፡፡ እነርሱም ስለ ጉዞአቸውና ሳሚ ስላስከተለባቸው ጭንቀት ደክመው ነበርና ያርፉ ዘንድ በዚያ ቆሙ ፡፡

አስበኸዋል በጉዞ ላይ ሳለህ ድንጋይ ሲወረወርብህ ባላይህም ላይ ትቢያ ሲበተንብህ ወይም ርግማን ባላይህ ሲጠራብህ ? እስኪ ለደቂቃ ቆም በልና አስበው ትረዳው ይሆናል ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገውን የራስህን ጉዞ አስብ ፤ በመንገድህ ከጠላት ስለሚመጣብህ ስድብና ነቀፋም እንድሁ ፡፡ እነዚህ ነቀፋዎች እስከ መጥፋት ያደርሱህ ይሆን ለመቆም አቅም እስክታጣ ድረስ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በድካመህ ጊዜ በፀጋው ብርቱ እንደሚያደርግህ ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ በማንኛውም የጥቃት ከበባ ውስጥ ሳለህ በእግዚአብሔርና በእርሱ እውነት ብርታትን ታገኛለህ ፡፡ ከእግዚአብሔር የሆነውን ቅባት አስብ ፤ ቅባትህን ስትይዝ በመንገድህ ምንም ይምጣ ብርቱ ትሆናለህ፡፡ እግዚአብሔር በጠላት ላይ አሸናፊ ያደርግሃል ድልንም ትቀዳጃለህ ፡፡

“ ዳዊትና ሰዎቹም በመንገድ ይሄዱ ነበር ሳሚም በተራራው አጠገብ በእርሱ ትይዩ እየሄደ ይራገም ድንጋይም ይወረውር ትቢያም ይበትን ነበር ፡፡ ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደክመው ነበር በዚያም ዐረፉ ፡፡ “

- 2ኛ ሳሙኤል 16፡13-14

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-10 –“ ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የስጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ ይኸውም እንዳልታበይ ነው ፡፡ ስለዚህ ነገር ከእኔ እንድለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ ፡፡ እርሱም ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ ፡፡ እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ ፡፡ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና ፡፡ “
  • ቄላስያስ 2፡15 –“ አለቅነትንና ስልጣናትን ገፎ ድል በመንሳት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው ፡፡ “
  • 1ኛ ዮሐንስ 2፡20 –“ እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀባላችኋል ሁሉንም ታውቃላችሁ ፡፡ ”