The Sins of David's Sons
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
2 ሳሙኤል የዳዊትን ህይወት የሚቀጥል ተከታታይ ድራማ እንደ ሚመስል ይሰማል - ድራማን፣ ጅብዱን እና የኃጢዓትን ሙሉ ጥቅል ፤ በመሰረቱ ያ በ 2ሳሙኤል ለሆነ ነገር ብሎ ከሴት ጋር የሚተኛ አይነት ነው ፡፡ በ 1ሳሙኤል ዳዊትን የተቀባን እንደ ሚወክል እና በ 2ሳሙኤል በዘላለማዊ ዙፋን ጥሪዉን እናያለን ፤ ነገር ግን በዚህ ሁሉ መካከል ላይ ዳዊት ፍፁም እንዳልነበር አሳይቷል ፡፡ የዚህ ሁሉ አስገራሚዉ አካል ዘላለማዊ ዙፋን በዳዊት ፍፁምነት ላይ የተደገፈ አለመሆኑ ነው ፤ ያ ስለ እኛም ተመሳሳይ ነው - ከእግዚአብሄር ጋር በስራችን ላይ የተመሰረተ ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ፡፡
የዳዊት ዘር ለዘላለም ይገዛል በሚለዉ የእግዚአብሄር ተስፋ የሆነዉን ዳዊታዊ ኪዳንን አጥንተናል እንዲሁም የዮናታንን ዘር ከኋላዉ እንደሚመለከት ከዮናታን ጋር የነበረዉን የዳዊትን ኪዳን አይተናል ፡፡ በዳዊት ፀጋ የዮናታንን ልጅ የሜሚቦስቴን ልጅ ሆኖ መኖርን አይተናል ፤ ትናትና ከቤርሳቤህ ጋር የዳዊትን ማመንዘር እና የግድያ ኃጢዓት ላይ ተመልክተናል ፡፡
2 ጢሞ (2፡ 22) የሚለው “ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞትግን ሽሽ በንጽሑም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል “ ፤ ይህ ጥቅስ የ 2ሳሙኤል 13 ጥናታችን መዋቅር ነው ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (13፡ 1-9)፡ ዳዊት ቤርሳቤህን በመመልከቱ አመንዝራ አይን ነበረው እንዲሁም ልጁ አምኖንም በአንድ በኩል የወንድሞ የአቤሴሎም እህት በሆነችዉ በትዕማር አመንዝራ አይኖች ነበሩት (ቁጥር 1) ፡፡ የአቤሴሎም እናት (እና የትዕማር እናት) የጌሹር ንጉስ ሴት ልጅ ሚካ ነበረች የአምኖን እናት አኪናሆም ነበረች ፤ “ የአይን ፍቅር “ የሚለዉ ቃል አምኖን በትዕማር ቁጥጥር ስር እና ያመነዘረ ነበር ፡፡ አምኖን የዳዊት በኩር ነበር አቤሴሎም ደግሞ ሰዎስተኛ ወንድ ልጁ ነበር ፡፡
አምኖን በእህቱ በትዕማር በአካሉ ተማሞ ነበር ምክንያቱም ድንግል ነበረች (ቁጥር 2) (ዘሌ 18፡ 11) ፤ የአምኖን ጓደኛ እና የአጎት ልጅ ኢዮናዳብ ብልጥ እና ልምድ ያለዉ ነበርና አምኖን ለምን ግራ እንደ ተጋባ ጠየቀው ፤ አሞኖን ከወንድሙ እህት በፍቅር እንደ ወደቀ ገለፀ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ኢዮናዳብ እቅድ አቀረበለት - አምኖን የታመመ ሆኖ በማስመሰል ዳዊትን ለእርሱ ምግብ እንድታዘጋጅለት እህቱን ትዕማርን እንዲልክለት እንዲጠይቀዉ ነበር (ቁጥር 5)፡፡ አምኖን ኢዮናዳብ እንደመከረዉ አደረገ ዳዊትም አምኖን እንደ ጠየቀው አደረገ (ቁጥር 6-7) ፤ በዚህ ሁኔታ ዳዊት ሴት ልጁን ለአምኖን አሳልፎ መስጠቱ ጥፋተኛ እንደ ነበር ይሰማል ፡፡ ትዕማር በአምኖን ፊት ምግብ አዘጋጀች ፤ በተዘጋጀም ጊዜ አምኖን ሁሉንም በማስወጣት ለመመገብ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ (ቁጥር 8-9) ፡፡ ከወጣትነት ምኞት መሸሽ ለንማር ይገባናል (ሮሜ 6፡ 12፣ 1ቆሮ 6፡ 18-19፣ ቆላ 3፡ 5፣ 1ጴጥ 2፡ 11) ፡፡
2-ሳሙኤል (13፡ 10-20)፡ ትዕማር ለአምኖን ምግብ አመጣችለት ይዟትም ከእርሱ ጋር ለመጠኛት እንድትመጣ ነገራት (ቁጥር 10-11) ፤ “ እንዲህ አይነት ነገር በእስራኤል አይሰማምና “ አታዋርደኝ ብላ ለመነችዉ (ቁጥር 12) ፤ ትዕማር አምኖን እንዲያገባት ለዳዊት እንዲነግረዉ ነገረችዉ (ቁጥር 13) ፡፡ አምኖን ፈልጎ የነበረዉ ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ ስለ ነበር የወንድሙን እህት በመድፈር የፈለገዉን አገኘ (ቁጥር 14) ፤ አምኖን በመድፈር አዋረዳት ፡፡ ትዕማር ስለ ምትፈልገዉ እና ስለ ተሰማት አልተጨነቀም ነበር ፡፡
ከዚያ በኋላ መፅሀፍት አምኖን ትዕማርን እንደ ጠላት እና አዉጥቶ እንደ ጣላት ይናገራል (ቁጥር 15) ፡፡ ትዕማር አዉጥቶ እንዳይጥላት ነገረችዉ ነገር ግን እርሷን አስወጥቶ ከኋላዋ በር ዘግቶባት ነበር (ቁጥር 16-18) ፡፡ ትዕማር የንጉስ ድንግል ልጅ ቀሚስ - እረጅም ህብር ልብስ ለብሳ ነበር ፤ ልብሱን በመቅደድ በራሷ ላይ አመድ በማድረግ እንደ ኃዘን ምልክት እጇን በራሷ ላይ በማድረግ ሄደች (ቁጥር 18-19)(ኢዮ 1፡ 20፣ 2፡ 12፣ ኤር 2፡ 37) ፡፡ አቢሰሎም ምን እንደ ተፈጠረ ሰማ የአደባባይ እፍረትን ለማስወገድ ወደ ቤቱ ወሰዳት (ቁጥር 20) ፡፡
2-ሳሙኤል (13፡ 20-29)፡ ንጉሱም አምኖን ትዕማር ላይ ያደረገዉን ሰማ በኃይልም ተበሳጨ ነገር ግን ስለዚያ ምንም ነገር የሚያደርግ አልመሰለም (ቁጥር 21) ፤ አቤሴሎምም ዝም አለ (ቁጥር 22) ፡፡ ዳዊት እና አቤሴሎም ሁለቱም እንደ ተደፈረች አወቁ ፈጣን ምላሽም አላደረጉም ፤ ከሁለት አመት ቆይታ በኋላ አቤሴሎም ዳዊትን፣ ልጆቹን እና አገልጋዮቹን የቀጠራቸዉን አዲስ ሸላቾቹን ለማየት እንዲመጡ ጋበዛቸው ፤ ሁሉንም ለመስጠት ዳዊት ባልፈቀደ ጊዜ አቤሴሎም እንዲሄድ እንዲፈቀድለት ጠየቀ (ቁጥር 25-26) ፡፡ ዳዊት አምኖን ለምን እንደሚሄድ ጠየቀ አቤሴሎምም ለመነዉ ዳዊትም ፈቀደ (ቁጥር 26-27) ፡፡ ዳዊት በቤተሰቡ ዉስጥ የነበረዉን ቸግር ለመፍታት ያለመከረ ደካማ አባትን ይመስላል ፤ ዳዊት አምኖንንና ሁሉንም ልጆቹን ላከ ፡፡ አቤሴሎም የአባቱን ተግባር በወንድሙ ላይ በቀልን ለመዉሰድ በማድረግ ለእርሱ ሰዎች በሚነግራቸዉ ጊዜ አምኖንን ለመግደል የተዘጋጁ እንዲሆኑ ነገራቸዉ (ቁጥር 28) ፡፡ ወጣቶቹም አቤሴሎም እንዳዘዛቸዉ አደረጉ የቀሩትም የዳዊት ልጆች ሁኔታዉን ሸሹ (ቁጥር 9) ፡፡
2-ሳሙኤል (13፡ 30-39)፡ ለንጉስ ዳዊት ሁሉም ልጆቹ እንደ ሞቱ ቃል በደረሰዉ ጊዜ በሀዘን ተመታ(ተሸነፈ) (ቁጥር 30-31) ፤ ነገር ግን ኢዮናዳብ ዳዊትን በትክክል የተፈጠረዉን ነገረው አቤሴሎምም ትዕማር ከተደፈረች ጊዜ ጀምሮ ይህን አቅዶ እንደ ነበር ገለፀለት (ቁጥር 32-33) ፡፡ ኢዮናዳብ የቀድሞዉ የአምኖን ጓደኛ ዘዴዉን በመስራት ጥሩ ተግባር እያደረገ ነበር ፤ ኢዮናዳብ ብሎት እንደ ነበረው የተረፉት ወንድሞቹ ወደ ዳዊት በተመለሱ ጊዜ አቤሴሎም ሸሸ (ቁጥር 34-35) ፡፡ ዳዊት፣ ልጆቹ እና አገልጋዮቹ አምኖንን በማጣታቸዉ አለቀሱ (ቁጥር 36) ፡፡ ዳዊት ሁል ጊዜ ስለ አምኖን ማዘኑን ሲቀጥል አቤሴሎም ወደ ጌሹር ንጉስ ሸሸ (ቁጥር 37) ፤ ዳዊት ስለ አቤሴሎም መናፈቅ እስከሚጀምር ጊዜ አቤሴሎም በጌሹር ሰዎስት አመት ተቀመጠ (ቁጥር 38-39) ፡፡
መደምደሚያ
አምኖን ከወጣትነት ምኞት ባለመሸሹ ምክንያት ቤተሰቡን ትርምስ አገኘው ፤ ሰዎች ኋጢዓት ዉስጥ በሚወድቁ ጊዜ ችግሩ በቤተሰባቸዉ ላይ እንደሚሆን ይረሳሉ ፡፡ ነገሮች ሲቆሽሹ ! ከእነዚህ የወጣትነት ምኞቶች መሸሽ አለብን ፡፡ ይልቁንስ ፅድቅን፣ ፍቅርን፣ እምነትን እና ሰላምን ለመከተል መሮጥ አለብን ፤ ምክንያቱም ይህ ካልሆነ ትርምስ ይከተለናል ፤ በጌታ በተጠራንባቸዉ ነገሮች ላይ በንፁህ ልብ ለመሮጥ መምረጣችንን እርግጠኞች መሆን አለብን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 407.
Nelson’s Commentary, p. 407.
ጥያቄዎች
-
አምኖን በግዴለሽነት ወደ ትዕማር በግልፅ ያደረገዉ ምን ኃጢዓት ነበር (ዘሌ 18፡ 9-11፣ 20፡ 17፣ ዘዳ 27፡ 22) ? በቤርሳቤህ የአባቱ ምሳሌ ተፅዕኖ አድርጎበታል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
ወዲያዉኑ ስለ ትዕማር እየተሰማዉ በጀመረ ጊዜ አምኖን እንዴት አፀፋዊ መልስ ሰጠ ? (ዘፍ 39፡ 9-10፣ ማቴ 5፡ 27-30፣ 2ጢሞ 2፡ 22)
-
ትዕማር እያደረገ የነበረዉ ክፉ እና ሞኝነት እንደ ነበር አምኖንን ልታሳምነዉ ለመሞከር ምን አለች ? ምክሯን ለምን እንዳልተቀበለ ምን ታስባላችሁ ?
-
በአምኖን ላይ ለአገልጋዮቹ የአቤሴሎም እቅድ ምን ነበር ? አቤሴሎም እቅዱን ለመተግበር ትዕማር ከተደፈረች በኋላ ምን ያክል ጊዜ ጠበቀ ?
-
በ 2ሳሙኤል 14 ለዳዊት እና ለልጁ አቤሴሎም እርቅ ሆኗል ? ከአንድ ሰዉ ጋር እርቅ ያደረጋችሁበት ጊዜ በህይወታችሁ ነበራችሁ ? ለማድረግ ለእናንተ አስቸጋሪ ነበር ?
-
2 ሳሙ (14፡ 14) የሚለው “ እግዚአብሄርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም ነገር ግን የተጣለ ሰዉ ፈፅሞ ፈፅሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል “ ፤ ይህ የእግዚአብሄርን ባህሪይ እንዴት ትገልፁታላችሁ ? (2 ጴጥ 3፡ 9)
-
በ 2ሳሙኤል (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 13:11
“When she brought them to him to eat, he grabbed her and said, ‘Come sleep with me, my sister!’”
የዳዊት ልጅ አምኖን ለእንጀራ እህቱ ትዕማር የወሲብ ፍላጎት በነረው ፡፡ አምኖን ከእግዚአብሔር ጋር አካሄዱን ያደረገን ሰው ምክር ከመጠየቅ ይልቅ አምኖን ብልህ ለነበረ ጓደኛው ኢዮናዳብ ስሜቱን አጋራ ፡፡ ኢዮናዳብም አምኖን ትዕማርን ብቻውን ማግኘት የሚችልበትን መንገድ መከረው ፡፡ ምክሩም ሰራ ይህም አምኖንን እህቱን በመድፈር የወሲባዊ ስሜቱን እንድፈጽም አደረገው ፡፡ ነገሮችም ቀጥለው አምኖን በወንድሙ በአቤሴሎም በበቀል ተገደለ ፡፡ የዳዊት ቤተሰበም ተጨነቁ ፡፡ የኃጢአትን ፈተና ከመሸሽ ይልቅ አምኖን በኃጢአት ወደቀ የዚህም መዘዝ ወደ ለብዙ ቤተሰቦች ተረፈ ፡፡
አማኞች ጽኑ ወደ ኃጢትም እንዳትገቡ ፡፡ ከስጋዊ ምኞቶቻችሁ እንድትርቁ ታዛችኋል ፡፡ መሸሽ ፍጥነትንና ጥረትን ይጠይቃል ፡፡ ሁኔታው አስቸጋሪ ሲሆን ትሸሻለህ በፍጥነት መራቅም ይኖርብሃል ፡፡ ከዝሙት መሸሽ ማለት የወሲብ ስሜት እንድሰማን ከሚያደርግ ሰው ከቤት በመውጣት በቶሎ መሸሽ ሊሆን ይችላል ፡፡ የወሲብ ምስሎችን በማየት የምትፈተን ከሆነም ኮምፒውተርህን ቲቪህን ወይም ስልክህን መተው ማለት ነው ፡፡ ፈተናውን ከተቋቋምክ ከዚያ ብርቱ እንድትሆንና ክርስቶስን እንድትሻ ከሚፈልጉ ሰዎች ጎራ ራስህን ታሰልፋለህ ፡፡ እግዚአብሔር ፀንተህ ትቆም ዘንድ ኃይልንና ብርታትን ሰጥቶሀል ፡፡ መንፈሱም በውስጥህ ያግዝህና ይመራህ ዘንድ ታላቅ ነው ፡፡ የጌታን ስም ጥራ ስትሸሽም ብርታትን ታገኛለህ ፡፡
“ መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና እኅቴ ሆይ ነዩ ከእኔም ጋር ተኚ አላት ፡፡ “
- 2ኛ ሳሙኤል 13፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 6፡18 –“ ከዝሙት ሁሉ ሽሹ ፡፡ ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከስጋ ውጭ ነው ዝሙትን የሚሰራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሰራል ፡፡ “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡22 –“ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል ፡፡ “
1ኛ ጴጥሮስ 2፡11 –“ ወዳጆች ሆይ ነፍስን ከሚወጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።