David's Progressive Slide Into Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ በ 2 ሳሙኤል የትልቅ ታሪክ የአንድ ሳምንት ጥናት ነው ፡፡ መጀመሪያ በዳዊት ኪዳን ላይ ተመለከትን ከዚያም የዮናታን ልጅ ሜሚፊቦስቴን ወደ ራሱ ቤተሰብ በመቀላቀል(ልጁ በማድረግ) ዳዊት እንዴት ከዮናታን ጋር የነበረዉን ኪዳን እንደ ፈፀመ ተመለከትን ፡፡ የዛሬዉ ፅሁፍ ከቤርሳቤህ ጋር በዳዊት ኃጢዓት ዉስጥ የእስራኤል ስብራት ላይ እንመለከታለን ፤ “ ዳዊት ለዮናታን ከእርሱ ጋር አድርጎት የነበረዉን ኪዳን በመጠበቅ የታመነ ቢሆንም ለሁሉን ቻይ አምላክ ከእስራኤል ጋር ለነበረዉ ኪዳን ግን የታመነ አልሆነም “ ፡፡ ኮንስታብል በ 2ሳሙኤል 11 ማብራሪያዉን “ ምናልባት ይህ ከዉድቀት በኋላ በመፅሀፍ ቅዱስ ሁለተኛው በጣም በምጥፎነቱ የሚታወቅ ኃጢዓት ነው “ በሚል ንግግር ይገልፀዋል ፡፡ በዚህ አገባብ እንኳን የዳዊት ኪዳን የፀና ነው ዘላለማዊዉ ዙፋኑም ይሆናል ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (11፡ 1-2)፡የኔልሰን ማብራሪያ “ በምስራቅ አካባቢ ከአመታት መካከል በፀደይ ጊዜ ንጉስ ወደ ጦርነት ይሄዳል ምክንያቱም በወቅቱ ጥሩነት በመንገድ ላይ የተትረፈረፈ ምግብ ስላለ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ይሁን እንጂ ዳዊት ለጦርነቱ አዛዦቹን እና ሁሉንም ወታደሮቹን ላከ ነገር ግንእርሱ በኢየሩሳሌም ቀረ (ቁጥር 1) ፡፡ ዋይርስቤ በዳዊት ህይወት እና ሁኔታ ስለ ስራፈትነት ጉዳይ “ ስራ ፈትነት የስራ ማጣት ብቻ ሳይሆን…..ስራ ፈትነት ያላላማ የሆነ ተግባርም ነው “ በማለት ያመለክታል ፤ ሉቃ 9፡ 62) ፡፡ የተጠራበትን ለማድረግ ዳዊት ከጉድጓድ ወጥቷል ፤ ዳዊት ከአልጋዉ ላይ በመነሳት በሰገነቱ ላይ ሄደ ከሩቅም አንዲት ቆንጆ ሴት እየታጠበች አዬ (ቁጥር 2) ፡፡ ስራ ፈቶች በሆንን ጊዜ አሳባችን ሲመታን(ሲይዘን) አይኖቻችንን ከኢየሱስ ላይ ለማንሳት እናዘነብላለን ፡፡ ሲዊንዶል ያመለከተው፡ “ የሌላ ሰዉ ሚስት የወሰደዉ ይህን ንጉስ የተሰበሰቡ ሙሉ ሴቶች ነበሩት ፤ ቀላሉ እዉነት የወሲብ ፍላጎት በተሰበሰቡ ሙሉ ሴቶች የሚረካ አይደለም ፤ የሚጨምር ነው ፡፡ ብዙ ሴቶች መኖር የሰዉን ቅንዝርና አይቀንስም ስሜት ይቀሰቅሳል….ያነሳሳል….በተማረዉ ማህበረሰብ ዉስጥ ያለዉ አንድ ዉሸት ይህን ስሜት ከረካ ይረግባል ማለት ነው “ ፡፡ ዳዊት ይህ እንዲፈጠር አካባቢን(ሁኔታን አመቻቸ) ፈጠረ ፡፡ ሁኔታዉን መሸሽ ያስፈልገዉ ነበር (ማቴ 5፡ 27-28) ፤ተመልሶ ወደ ዉስጥ መሄድ ወይም ከሰዎቹ ጋር ወደ ጦር መሄድ ያስፈልገዉ ነበር ፡፡
ከአመቱ በፊት ሶሪያዊያን አሞናዊያን እየተጠጋ ከነበረዉ ከዳዊት ጦር ሸሽተዉ ነበር አሞናዊያንም ለመከላከል ወደ ረዓብ ከተማ ገቡ (2 ሳሙ 10፡ 14) ፡፡ ኢዮዓብ ከአንድ አመት በኋላ የረዓብን ከተማ በጦር ኃይል ለመክበብ ከጦር ጋር ተመለሰ ፤ ሲዊንዶል የፃፈው “ በጣም አስቸጋሪ ጊዜአችን ነገሮች ከባድ በሚሆኑ ጊዜ አይደለም ፤ አስቸጋሪ ጊዜዎች በጥገኛ ሰዎች ይፈጠራሉ ፤ እግዚአብሄር ላይ የተደገፋችሁ በሆናችሁ ጊዜ ኩራተኞች እንዳትሆኑ ፤ መትረፍ (መኖር) ትሁት ያደርጋል ፤ ኩራት ሁሉም ነገር በራሳችሁ አቅጣጫ ሲሆን የሚፈጠር ነው “ ፡፡
2-ሳሙኤል (11፡ 3-5)፡ ዳዊት የሴቲቱን ማንነት ቤርሳቤህ እንደ ሆነች ሰማ ወደ እርሱ እንዲያመጧት መልዕክተኞችም ላከ (ቁጥር 3-4) ፤ ዳዊት በእርሷ ላይ የማዘዝ ስልጣን ላይ ነበር ፡፡ ዳዊት እና ቤርሳቤህ ወሲባዊ ግንኙነት አደረጉ ከዚያም ቤት ተመለሰች ፤ ቤርሳቤህ ወደ ዳዊት በመጣች ጊዜ ከወር አበባ በኋላ ኃይማኖታዊ የመንፃት ስርዓቷን ፈፅማ ነበር ፡፡ ቤርሳቤህ አረገዘች ዳዊትም እንዲያዉቅ አደረገችዉ (ቁጥር 4-5) ፡፡ በህጉ አመንዝራነታቸዉ ክፉ ስለ ነበር ሁለቱም መገደል ነበረባቸው (ዘሌ 20፡ 10፣ ዘዳ 22፡ 22) ፤ ያ አልሆነም ዳዊትም ንስኃ አልገባም ስለሆነም ክፉነቱ እና ኃጢዓቱ አደገ ፡፡ 1 ዮሐ (1፡ 9) ምንም እናድርግ ኃጢዓታችንን እንድንናዘዝ ይገልፃል እግዚአብሄርም ይቅር ይለናል ፡፡
2-ሳሙኤል (11፡ 6-13)፡ የኃጢዓቱን ችግር ለመሸፈን ዳዊት ለኢዮአብ ጦሩ እንዴት እየተካሄደ እንደ ነበር ከሚል አዲስ ዜና ጋር እንዲነግረዉ ኬጢያዊዉን የቤርሳቤህን ባል ኦርዮን እንዲልከዉ መልዕክት ላከበት (ቁጥር 6) ፡፡ የኦሪዮን ሪፖርት ከሰማ በኋላ ዳዊት ወደ ቤቱ በመሄድ “ እግሩን እንዲታጠብ “ ነገረዉ ይህ ማለት(ትርጉሙ) ከሚስቱ ጋር እንዲተኛ ቁጥር 7-8) ፤ በተጨማሪም ዳዊት ወደ ቤቱ እንዲወስድ ምግብ ሰጠው ፤ ነገር ግን ኦርዮን ወደ ቤቱ አልሄደም ይልቁንስ ከወታደሮቹ ጋር መቆየትን መረጠ (ቁጥር 9) ፡፡ ዳዊት አርዮን ለምን ወደ ቤቱ እንዳልሄደ በጠየቀዉ ጊዜ ኦርዮንም ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ፣ ኢዮዓብና ወታደሮቹ ሁሉም በድንኳን ነበሩ ስለዚህ በአልጋዉ ላይ ከሚስቱ ጋር እንዴት ሊተኛ ይችላል (ቁጥር 10-11) ? አለ ፤ ኦርዮን ዳዊት እግዚአብሄር እንዲያድርበት ቤተ መቅደስ ሊሰራለት አሳይቶት ከነበረዉ ልብ ጋር ተመሳሳይ ልብ ነበረው ፡፡ ዳዊት ኦርዮን በኢየሩሳሌም እስከ ቀጣዩ ቀን እንዲቆይ እና በዚያ ምሽት ከእርሱ ጋር እንዲበላ እና እንዲጠጣ እንደ ጋበዘው ነገረው ( ቁጥር 12-13) ፡፡ ዳዊት ኦርዮን ከሰከረ ወደ ሚስቱ ይመለሳል ብሎ ተስፋ በማድረግ ጽዋዉን ወደ ኦርዮን አስተላለፈዉ ፤ ነገር ግን ሰክሮም እንኳን ኦርዮን ሀቀኝነቱን ያዘ ፡፡
2-ሳሙኤል (11፡ 14-21)፡ የኦርዮን ሁሉም ስልቶች ባልሰሩ ጊዜ ዳዊት እንዲያደርስ ለኦርዮን የሰጠዉን አንድ ደብዳቤ ለኢዮአብን ፃፈለት (ቁጥር 14) ፤ በቁጥር 15 ዳዊት ኦርዮን የሞቱን ፍርድ እንዲያደርስ ላከው ፡፡ ዳዊት ኢዮአብን ኦርዮን አስከፊ ዉጊያ ባለበት ግንባር እንዲያሰልፈዉ ከዚያም ወደ ኃላ እንዲሳቡ ይህ ሲሆን ኦርዮን ጠላቶችን ለመግጠም ብቻዉን ይቀራል ብሎ ነገረው (ምሳ 6፡ 23-33) ፤ ኢዮአብ የዳዊትን ትዕዛዝ ተከተለ ኦርዮንም በዉጊያዉ ሞተ (ቁጥር 16-17) ፡፡ ኢዮአብ የዳዊትን ትዕዛዝ በትክክል እንዳልተከተለ አስተዉሉ ምክንያቱም ወታደሮቹ ኦርዮን ብቻዉን አልተዉቱምም አላፈገፈጉምም ፤ ከዳዊት ሰዎች ጥቂት በዉጊያዉ ሞተዋል ፡፡ ኢዮአብ ለዳዊት ዳዊት በዉጊያዉ ለምን ወታደሮቹ እንደ ሞቱ ይጠይቃል ብሎ በማሰብ መልዕክት ላከለት ፤ ኢዮአብ መልዕክተኛዉን ኦርዮን ከወታደሮቹ ጋር እንደ ሞተ ለዳዊት እንዲነግረዉ ነገረው (ቁጥር 18-21) ፡፡
2-ሳሙኤል (11፡ 22-27)፡ መልዕክተኛው የኢዮዓብን መልዕክት ጦሩ መልሶ በመጠቃት በቀስተኞች በመመታታቸዉ ጥቂት ወታደሮች እና ኦርዮን እንደ ተገደሉ በመግለፅ አደረሰ ( ቁጥር 22-24) ፤ ዳዊት ዜናዉን የህይወት መጥፋቱን እንደ ትልቅ ጉዳይ በማድረግ አልወሰደዉም (ቁጥር 25) ፡፡ ቤርሳቤህ በባሏ መሞት አዘነች (ቁጥር 26) ፤ የኃዘን ጊዜዋ ባበቃ ጊዜ ቤርሳቤህ ወደ ዳዊት ተመለሰች ስምንተኛም ሚስቱ በመሆን አንድ ወንድ ልጅ ወለደችለት ፡፡ “ ነገር ግን ዳዊት ያደረገዉ ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ሆነ “ (ቁጥር 27) ፡፡
3 John MacArthur,
5 Charles R. Swindoll, David: A Man of Passion and Destiny. Great Lives from God’s Word series. (Dallas: Word Publishing, 1997), p. 182; quoted at Constable’s Expositional Bible Study Notes: 2 Samuel, p. 81; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2samuel.pdf.
ዳዊት ክፉ ነገር የፈፀመ ቢሆንም እግዚአብሄር ይዋጀዋል ፤ ማቴ (1፡ 6) የኢየሱስን የዘር መስመር መዝግቧል፡ “ እሴይም ንጉስ ዳዊትን ወለደ ፤ ንጉስ ዳዊትም ከኦርዮን ሚስት ሰለሞንን ወለደ “ ፡፡ ለኦርዮን በዳዊት የዘር መስመር ዉስጥ መጠቀሱ ክብር ነበረዉ ፡፡ በ ማቴዎስ 1 አራት ሴቶች ተጠቅሰዋል፡ ትዕማር፣ ርብቃ፣ ሩት እና ቤርሳቤህ (የኦርን ሚስት) ፤ ከእነዚህ ዉስጥ ሰዎስቱ በኃጢዓት የተለዩ(የታወቁ) ነበሩ ፤ በዚህ የወንድ የዘር ሀረግ ዝርዝር ዉስጥ መኖራቸው “ ዘላለማዊ አላማዉን ለመፈፀም እንግዳን(ምናልባትም ተግባረ ልክስክስ የሆኑትን) መጠቀም ብቻ እንደ ሚችላባቸዉ ሳይሆን በደንብ በመስራት ደስተኛ እንሚያደርጋቸው የእግዚአብሄር ልዓላዊ ፀጋ መርህን ማስረጃ ይሰጣል “ ፡፡
መደምደሚያ
የወሲብ ኃጢዓትን በማድረስ ይህ መሸፈን እፈልጋለሁ ፡፡ ዳዊት መሆን በሚገባዉ ቦታ አልነበረም ፤ ከቤርሳቤህ ጋር በተጋፈጠ ጊዜ አይኖቹን በእግዚአብሄር ላይ አላደረገም ፡፡ ይህ ታሪክ የተለዬ እንዲሆን ማድረግ የነበረበት ፤ ኮንስታብል ወሲባዊ ኃጢዓት ዉስጥ ከመዉደቅ እንዴት ራሳችንን እንደ ምንከላከል ብዙ ምክሮች ይሰጣል፡
- ማንኛችንም ለወሲብ ኃጢዓት አይደፈሬዎች አይደለንም (1 ቆሮ 10፡ 12) ፡፡
- በየቀኑ እግዚአብሄር ላይ ማትኮር ያስፈልገናል (ሉቃ 22፡ 46፣ ሮሜ 6፡ 12-13) ፡፡
- በትዳራችን ዉስጥ መቀራረብን ማሳደግ አለብን (ፊል 4፡ 11) ፡፡
- በባለቤቶቻችን ተጠያቂነትን ማሳደግ አለብን ፡፡
- የወሲፍ ምኞትን በመጠበቅ በሁሉም ወጪ ማምለጥ አለብን ፡፡
ምኞት ባያችሁ ጊዜ አምልጡ ፤ ዳዊት አላደረገው ፡፡
Thomas Constable, Constable’s Expositional Bible Study Notes: 2 Samuel, p. 77; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2samuel.pdf.
Constable, p. 78.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 2 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 332.
Swindoll, p. 183; quoted at Constable’s Expositional Bible Study Notes: 2 Samuel, p. 78.
Constable, p. 81.
A. Carr, The Gospel According to St. Matthew (Cambridge: University Press, 1913), p. 81; quoted in Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: Matthew, p. 24, available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/matthew.pdf.
Constable, pp. 84-85.
ጥያቄዎች
-
ጥሪዉን ከመፈፀም ዳዊት ከሰዎቹ ገር ወደ ጦርነት ከመሄድ ይልቅ በኢየሩሳሌም ተመልሶ ተቀመጠ ፤ መንፈስን ከመከተል (ጥሪዉን ከመከተል) ይልቅ በስጋ እየተጓዘ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ? ጥሪያችሁን ከመከተል ይልቅ ስጋችሁን ለመከተል የተፈተናችሁበ ጊዜ ነበር ?
-
በ 2ሳሙ (11፡ 4) ዳዊት መልዕክተኞቹን ቤርሳቤህን ወደ እርሱ እንዲያመጧት ላካቸዉ ፤ የኦሪዮ ሚስት እየነበረች እንዳወቀ ዳዊት ይህን ለምን አደረገ ? (ዘጸ 20፡ 14፣ 17)
-
በ 2ሳሙ (12፡ 13) እግዚአብሄር በፍጥነት የዳዊትን ኃጢዓት ይቅር አለው (መዝ 51፡ 4፣ 1ዮሐ 1፡9) ፤ ለምንስ ልጁ ሞተ ? በህይወታችሁ ዉስጥ ለኃጢዓታችሁ ምህረትን በተመለከታችሁ ጊዜ በእግዚአብሄር ይቅር እንደ ተባላችሁ ያወቃችሁበትን ነገር ግን የቆየዉን ዉጤቱን ደርሶባችሁ የነበረዉን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? ይህ በቀጣይ ጊዜ ኃጢዓትን ስትመኙ ለማስታወስ ይረዳችኋል ?
-
ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት ባደረገ ጊዜ (2 ሳሙ 12፡ 14) ለእግዚአብሄር ጠላቶች ለመሳደብ ታላቅ ደስታ የሰጣቸዉ ለምን ነበር (ሮሜ 2፡ 24) ? እኛ ኃጢዓት ስናደርግስ እንዴት ይሆናል ?
-
በ 2ሳሙ (12፡ 23) ዳዊት “ እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም አለ “ ፤ ዳዊት ልጁ የት ይሄዳል እያለ ነበር ? ይህ ምን አይነት ተስፋ ይሰጣችኋል ?
-
በ 2ሳሙ (12፡ 24-25) ስንመለከት እግዚአብሄር ሰለሞንን እንደ ወደደዉ ለማሳወቅ ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ለምን ላከው ለምንስ ለእግዚአብሄር ስሙን ይዲድያ ?
-
በ 2ሳሙኤል (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 12:12–13
“‘You acted in secret, but I will do this before all Israel and in broad daylight.’ David responded to Nathan, “I have sinned against the LORD.” Then Nathan replied to David, “The LORD has taken away your sin; you will not die.”
የዳዊት ሰዎች በጦር ሜዳ ሳሉ ዳዊት በኢየሩሳሌም መቆየቱን መረጠ ፡፡ ከወታደሩ ፣ ከቡድኑ ከስራው ርቆ ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳዊት ከኦርዮን ሚስት ቤርሳቤህ ጋር ዘሞተ ፡፡ ቤርሳቤህም ልጅን ወለደች ስለዚህም ዳዊት ኃጢአቱን ይሸፍን ዘንድ እቅድን አዘጋጀ ፡፡ ሆኖም ግን እቅዱ አልሰራም ፡፡ ስለዚህም በጦር ግንባር ይገደል ዘንድ ለኦርዮን አሴሬለት ፡፡ አንዷ ኃጢአት ወደ ሌላ ኃጢአት ትመራለች ፡፡ ምናልባት ዳዊት ቤርሳቤህን ስላገባትና ልጅንም ስለወለዱ በዙሪያው ያሉ ሰዎችን ማታለል እንደሚችል አስቦ ነበር ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር አይቶ ነበር ፡፡ አይቶ ነበር ዳዊት በድብቅ ያደረገውን ሁሉ ፡፡ ምንም እንኳ ለዳዊት የተገባለት ዘላለማዊ ኪዳን ባይሻርም ዳዊት ግን የኃጢአቱን ፍሬ መብላት ነበረበት ፡፡
በድብቅ የሰራኸውን ኃጢአት ማንም እንዳማያውቅ ልታስብ ትችል ይሆናል ፡፡ ከስራህ እረፍት ትወስዳለህ ፤ ከጓደኞችህ ከሰዎች ደግሞ ትርቃለህ እናም ፈተና ይገጥምሀል ፡፡ ጠላት ድካምህን ያውቃል በእግዚአብሔር መንግስትም ያለህን ሀይል ሊያሳጣህ ይፈልጋል ፡፡ በተደበቀ ኃጢአት ውስጥ ከሆንክ ይህን እወቅ እግዚአብሔር እያየህ እንደሆነ ፡፡ ምንአልባት እንደተደበክ ታስብ ይሆናል ግን ጌታ ያውቃል ፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ብትሰራም እንኳ ይወድሀል ፡፡ ልክ ከዳዊት ጋር የነበረውን ኪዳን እንዳላፈረሰ ሁሉ ካንተም ጋር ያለውን ኪዳን አያፈርስም ፡፡ ነገር ግን መደበቅ ልታቆም ጊዜው ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ሁልጊዜም አለ ምህረቱም ደግሞ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ፡፡ በተደበቀው የህይወት ክፍልህ ላይ ብርሀን እንድበራ ፍቀድ ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ተናዘዝ ፤ እንድሁም ደግሞ በህይወትህ ለምታምነው ሰው አካፍል ፤ እንደገናም ከኃጢአት መንገድ ራቅ ፡፡ ራስህን ከሚስጥር ነጻ አድርግ ከዚያም ህይወት በክርስቶስ ይበዛልሀል ፡፡
“ አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሀይ ፊት አደርገዋለሁ ፡፡ ዳዊትም ናታንን እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው ፡፡ ናታንም ዳዊትን እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሀል አትሞትም ፡፡
- 2ኛ ሳሙኤል 12፡12-13
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 68(69)፡5 –“ አቤቱ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም ፡፡ “
- ያዕቆብ 5፡16 –“ እርስ በእርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይፀልይ “
- 1ኛ ዮሐንስ 1፡9 –“ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያድነን የታመነና ጻድቅ ነው ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።