Historical Books 2 Samuel

David's Grace to Mephibosheth

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 247 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 2ሳሙኤል የዳዊት ቤት በዘሩ ለዘላለም እንደ ሚገዣ የእግዚአብሄር ቃል ኪዳን የሆነዉን ጠዳዊት ኪዳን ላይ ተመልክተናል (መዝ 78፡ 70-72) ፤ በ ሉቃስ 1 ያ ዘር መሲሁ ኢየሱስ ሆኖ የተለዬ ነው ፡፡ በ 2ሳሙኤል 8 እግዚአብሄር ዳዊትን በፍልስጤማዊያን ላይ፣ በሞዓባዊያን ላይ፣ በአሞራዊያን ላይ እና በኤዶማዊያን ላይ ድልን ሰጠው ፡፡

ትምህርት

ዋይርስቤ ይህን ምዕራፍ ስለ ዳዊት ድርጊት ወደ ሰዎስት ክፍል ይከፍለዋል፡ “ ሜሚፊቦስቴን ማግኘት “ (ቁጥር 1-4) ፣ “ ሜሚፊቦስቴን መጥራት “ (ቁጥር 5-8) ፤ “ ሜሚፊቦስቴን ማዳበር “ (ቁጥር 9-13) ፡፡

2-ሳሙኤል (9፡ 1-4)፡ ዮናታንና ዳዊት ዳዊት ንጉስ በሚሆን ጊዜ የዮናታንን ቤተሰብ ሊንከባከብለት ኪዳን አድርገዉ ነበር ፤ ዳዊት ንጉስ ከሆነ በኋላ በጣሚ ከሚወደዉ ከጓደኛዉ ከዮናታን የተገናኘ የተረፈ የቤተሰብ አባል እንደ ነበር ጠየቀ (ቁጥር 1) ፡፡ እንደ ሰዉ በቃሉ ይህ የዳዊትን ሀቀኝነት ሌላ ስዕል ነው - እርሱን ለማግኘት ለመጡት ቤተሰቦችን አልጠበቀም ፡፡ ሲባ የሳዖል “ የንብረት ኃላፊ “ ተጠራ ዳዊትም ርህራሄን የማሳየዉ የቀረ ሰዉ እንደ ነበር ጠየቀው ፤ ሲባም ሁለቱም እግሮቹ የተጎዱ የዮናታን ልጅ ተርፎ እንደ ነበር አጋራው (ቁጥር 2-3) ፡፡ ሲባ ንጉሱን የዮናታን ልጅ በሎዶባር እንዴት ሊያገኘዉ እንደሚችል ትዕዛዝ ሰጠው (ቁጥር 4) ፡፡

2-ሳሙኤል (9፡ 5-8)፡ ዳዊት ወደ ቤቱ የዮናታን ልጅ ሜሚፊቦስቴ አስመጣው (ቁጥር 5) ፤ ሜሚፊቦስቴ በዳዊት ፊት በመደፋት እጅ ነሳ (ቁጥር 6) ፡፡ ዳዊት ስለ ሳዖል ቤተሰቦቹ ማንኛዉንም ጠይቆ ነበር የዮናታንንም ወንድ ልጅ አገኘ ፡፡ ሜሚፊቦስቴ አባቱ በጦርነት በተገደለ ጊዜ የአምስት አመት ልጅ ነበር አንካሳም ሆኖ የተወለደ አልነበረም ፤ ነገር ግን የዮናታን ሞት ከተሰማ በኋላ ለመሸሽ በትርምሱ ሞግዚቱ ጣለችዉ በዚህም ተሰበረ (2 ሳሙ 4፡ 4) ፡፡ ምሁራን ሜሚፊቦስቴ ወደ ዳዊት የመጣ ጊዜ 20 አመት እንደሚሆነዉ ይገምታሉ በተጨማሪም አንድ ወንድ ልጅ ሚካ ነበረው (ቁጥር 12) ፡፡ ሜሚፊቦስቴ ራሱን ለዳዊት እንደ በሪያ ሰጠ ምክንያቱም “ በመካከለኛዉ ምስራቅ አዲስ ስርዉ መንግስት አግኝዎች የቀድሞዉ አስተዳዳሪዎች ልጆችን በቤተሰቦቻቸዉ ስም ዙፋንን እንደ ገና ለማግኘት እንዳይሞክሩ ለማድረግ መግደል የተለመደ ስለ ነበር “ ፤ ሜሚፊቦስቴን እንዳይፈራ ነገረው ምክንያቱን ሁሉንም የሳዖልን ምድር ለሜሚፊቦስቴ ስለ ሚመልስለት (ቁጥር 7) ፤ በተጨማሪም ዳዊት መሚፊቦስቴን እንደ ቤተሰቡ በገበታዉ ላይ ስለ ሚያስተናግደው (ቁጥር 7) ፡፡ ሜሚፊቦስቴ ዳዊት ይህን ቸርነት “ የሞተ ዉሻ “ ለምመስል ለምን ያሳየኛል በማለት ተደነቀ (ቁጥር 8) ፡፡ ዉሾች “ እንደ እርኩስ ጥንብ አንሳዎች የሚታዩ ነበሩ በአጠቃላይ በርካሽነት የሚታዩ ነበሩ “ ስለሆነም አገልለፁን መጠቀም የሜሚፊቦስቴን “ ለራሱ ያለዉን ዝቅተኛ አመለካከት እና በፀጋዉ ለእርሱ የታየ በመሆኑ መደነቁን ያሳያል “ (ምሳ 26፡ 11) ፡፡ ሜሚፊቦስቴ ራሱን ዋጋ እንደ ሌለዉ ተመለከተ ፡፡

2-ሳሙኤል (9፡ 9-13)፡ ዳዊት ሲባን በመጥራት ለሜሚፊቦስቴ መልሶለት የነበረዉን ገለፀለት (ቁጥር 9) ፤ በተጨማሪም ዳዊት ሲባን ከ አስራ አምስት ልጆቹ መካከል እንደሚሆን እና አሁን የእርሱ 20 አገልጋዮች ምርት በመሰብሰብ ለሜሚፊቦስቴ እንደ ሚሰሩ ነገረው ፡፡ ሜሚፊቦስቴ የዳዊት ቤተሰብ አካል እና በዳዊት ገበታ ላይ እንዲበላ የተደረገ ሆነ (ቁጥር 10-11) ፤ የሉቃስ ወንጌል በገበታዉ ላይ መቀመጫ የመኖርን አስፈላጊነት ይገልፃል (ሉቃ 13፡ 29-30፣ 14፡ 12-24፣ 22፡ 29-30) ፡፡ እግዚአብሄር በገበታዉ ላይ ለሁሉም ሰዉ ስፍራን አዘጋጅቷል ፡፡ ቁጥር 13 ምዕራፉን መሚፊቦስቴ ሁሉንም ምግብ ከንጉሱ ገበታ በላ በሚል ንግግር ያጠቃልላል ስለዚህም ርስቱ ወደ ልጁ ይሄዳል ፡፡

መደምደሚያ

ችክ ስዊንዶል የፃፈው “ በእኔ የግል አስተያየት ይህ በብሉይ ኪዳን የጸጋ ትልቅ ማሳያ ነው “ ፤ እንዴት ሜሚፊቦስቴ እንደ ተነሳ አስቡ ፤ ለአመታት ሽባ ነበር “ በባዶነት ስፍራ ተደብቆ ነበር ንጉሱንም በመፍራት ዉስጥ ነበር….” አለመወደዱ ቢኖርም ዳዊት ሜሚፊቦስቴን ለመፈለግ በመነሳት ወደ ቤቱ እና ወደ መገኘቱ አመጣ እንደ ራሱም ልጅ ተቀበለው “ ፤ (መዝ 23፡ 6) ፡፡ በተመሳሳይ በራሳችን ምንም ነገር ሳናደርግ በትክክል የተባረክን ነን ፤ ሁላችንም “ በሎዶባር “ ሁኔታ ዉስጥ ነን ራሳችንን ለመርዳት ምንም ነገር ማድረግ በማንችልበት ፤ ሁላችንም በባዶነት ሁኔታ ዉስጥ ነን ሁሉም በክርስቶስ በኩል መሰራት በሚቻልበት ሁኔታ ውስጥ ፡፡

ይህን መብት ሊያደርግ የሚችል ሌላ ኃይማኖት የለም ምክንያቱም እያንዳንዳቸዉ ከተከታዮቻቸዉ ከመጥፎ የሚበልጥ መልካም ይፈልጋሉ ፤ ያ ግን ወደ እርሱ የጠራን የክርስቶስ ጉዳዩ አይደለም፡

  • ሮሜ (9፡ 16)፡ “ እንግዲህ ምህረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም ከሚምር ከእግዚአብሄር ነዉ እንጂ” ፤ በጥረታችን(በልፋታችን) አይደለም ፡፡

ገላ (5፡ 2)፡ “ እነሆ ! እኔ ጳዉሎስ እላችኋለሁ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም “ ፤ በስራችን አይደለም ፡፡

ሐዋ (13፡ 39)፡ “ በሙሴ ህግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን “ ፤ ሁሉንም ህግ ስለ መከተል አይደለም(የመከተል ጉዳይ አይደለም) ፡፡

ገላ (2፡ 16)፡ “ ነገር ግን ሰዉ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ስራ እንዳይሆን አዉቀን ስጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ስራ ስለማይፀድቅ እኛ ራሳችን በሕግ ስራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል “ ፤ በምታደርጉት የሚገባችሁን አታገኙም ፡፡

2 ጢሞ (1፡ 9)፡ “ ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሄር ነዉና ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነዉ እንጂ እንደ ስራችን መጠን አይደለም ፤ ይህም ፀጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን “ ፤ በስራችን አይደለም ፡፡

ቲቶ (3፡ 4-5)፡ “ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሄር ቸርነትና ሰዉን መዉደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅደስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ስራ አይደለም “ ፤ ሁሉም ነገር ከእግዚአብሄር ነዉ እንጂ ከእኛ አይደለም ፡፡

ሜሚፊቦስቴ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተቀበልነዉን “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ፤ ይህም የእግዚአብሄር ስጦታ ነዉ እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም “(ኤፌ 2፡ 8-9) ከዳዊት ተቀበለ ፡፡ ስለዚህም ለእኛ ዘላለም ስጦታ ነው ፤ በገበታዉ ላይ መቀመጫ ተሰጥቶናል “ እኛ ፍጥረቱ ነንና ፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሄር አስቀድሞ ያዘጋጀዉን መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን “ (ኤፌ 2፡ 10) ፡፡

ሜሚፊቦስቴ የንጉስ ዳዊት እንደ ልጅ ሆነ በፍፁምም ብቸኝነት እንደ ገና ወይም ፍላጎትን አላወቀም ፡፡ ሮሜ(8፡ 15) “ አባ አባት ብለን የምንጮኽበት የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋል እንጂ እንደ ገና ለፍርሃት የባርነት መንፈስ አልተቀበላችሁምና ! “

5 Charles R. Swindoll, David: A Man of Passion and Destiny. Great Lives from God’s Word series. (Dallas: Word Publishing, 1997), p. 169; quoted in Thomas Constable, Constable’s Expos- itory Bible Study Notes: 2 Samuel, p. 72, available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2samuel.pdf.

  1. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003),

  2. Wiersbe, pp. 328–329.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary: 2 Samuel (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 402.

  4. Nelson’s Commentary, p. 402.

  5. Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: 2 Samuel, p. 74; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2samuel.pdf.

ጥያቄዎች

  1. ለሳዖል ዘር ለዮናታን ልጅ ሲል ርህራሄ ማሳየቱ ለዳዊት ለምን አስፈላጊ ነበር ? (1 ሳሙ 18፡ 1-4)
  2. ዳዊት ለሜምፊቦስቴ እንዳይፈራ ለምን ነገረው ? (2 ሳሙ 9፡ 7)
  3. ዳዊት የሳዖል የሆነዉን ምድር ሁሉ ለሜምፊቦስቴ ለምን ሰጠው ? (ዘኁ 36፡ 7)
  4. ሐኖን አሞናዊያንን ለማዋረድ ፂማቸዉን መላጨት እና ልብሳቸዉን የመቅደድ ዘዴ እንዲጠቀም ያደረገዉ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል ?
  5. በ 2ሳሙኤል (9-10) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 9:6b–7

“David said, ‘Mephibosheth!’ ‘I am your servant,’ he replied. ‘Don’t be afraid,’ David said to him, ‘Since I intended to show you kindness because of your father Jonathan, I will restore to you all your grandfather’s Saul’s fields, and you will always eat meals at my table.’”

ዳዊት ስለ መልካም ጓደኛው ስለ ዮናታን ቸርነት ያደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው መኖሩን ጠየቀ ፡፡ የሳኦልም ባሪያ ሲባ በሎዶበር የሚኖረውን የሳኦልን የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ እንዳለ ተናገረ ፡፡ ዳዊት ሜምፊቦስቴን አመጣው ሜምፊቦስቴም ዳዊት የእርሱን መኖር ስለ መጠየቁ ፈራ ፡፡ ዳዊትም እንዳይፈራ ነገረው ፡፡ ከእርሱም ገበታ ሁልጊዜ እንጀራን እንደሚበላ እንድሁም ደግሞ የአባቱን የሳኦልን ምድር ሁሉ እንደሚመልስለት ነገረው ፡፡ ይህ እንደ ሜምፊቦስቴ ሽባ ለነበረ ሰው ያልተጠበቀና ያልተለመደ ሰጦታ ነው ፡፡

ዳዊት ለሜምፊቦስቴ ጥቅም አልባ ደግነንት ከእግዚአብሔር የሆነ ስጦታን አደረገለት ፡፡ ሜምፊቦስቴ ይህ ይገባው ዘንድ ምንም ነገር አላደረገም ነገር ግን ዳዊት እርሱን ተመለከተው ከፍቅር የሆነውንም ደግነት በእርሱ ላይ አደረገ ፡፡ ጓደኞቼ ይህ እውነት ለእናንተም ይሰራል ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ፍቅሩ ሊያስገባህ ይከተልሃል ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ስለ መልካም ስራህ የሆነ ሳይሆን እግዚአብሔር አባት ስላየህና ልጄ ብሎ ስለ ጠራህ እንጂ ፡፡ በነጻነትና ሙሉ በሙሉ ወደ መንግስቱ ተቀላቅለሃል ወደ እርሱም ገበታ ቀርበሃል ፡፡ እንዲሁ እንዳለህ ፍጹም ሳትሆን ይወድሀል እንድሁም ጥሩውንና መልካሙን ስጦታ ያደርግልሀል ፡፡ ዛሬ ስጦታውን ተቀበል ፡፡ እርሱ በገበታው ላንተ መቀመጫን አዘጋጂቷል ፤ተቀመጥ እና የእርሱን መገኘት በየለቱ አጣጥም ፡፡

“ ዳዊትም ሜምፊቦስቴ ሆይ አለ እርሱም እነሆ ባሪያህ አለ ፡፡ ዳዊትም ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሀለሁና አትፍራ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው ፡፡ “

  • 2ኛ ሳሙኤል 9፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሞ 8፡15 –“ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነትን መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና ፡፡ “

ኤፌሶን 1፡5 –“ በበጎ ፈቃዱ እንደወደደ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን ፡፡ “

ቲቶ 3፡4-5 –“ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመነረፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አልነበረም ፡፡ “