David's Kingdom is Forever
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
2 ሳሙኤል 7 የተለየ እና በብሉይ ኪዳን ዉስጥ አንዱ አስፈላጊ ምዕራፍ ነው ፡፡ እዚህ ጋር ዳዊት መሮጥ በማቆም እንደ ተቀባ የእስራኤል ንጉስ በአዲስ ተግባር ተቀምጦ ነበር ፤ ምዕራፍ 7 ዘላለማዊዉ ዙፋን ( ለ2 ሳሙኤል ቃላችን) እንዴት እንደ ሚጓዝ ያተኩራል ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (7፡ 1-3)፡ ዳዊት በቤተ መንግስቱ ዉስጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ እግዚአብሄርም ዳዊትን ከጠላቶቹ አሳረፈው (ዘጸ 33፡ 14) ፤ ይህ እረፍት በተስፋ የተተነበየ እና በእግዚአብሄር ብቻ ሊገኝ የሚችል ነበር ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃጠል የምንናገረው በእርሱ እዉነተኛ እረፍት ለማግኘት ስንል ነው ፡፡ አሁን እንደ ንጉስ የዳዊት ፍላጎት እግዚአብሄርን ማክበር ነበር ፤ በጥድ ቤቱ ላይ በመመልከት ለእግዚአብሄር ቋሚ ማደሪያ የማይኖረዉ ለምን ትክክል አይሆንም በማለት ጠየቀ ፤ ዳዊት ነቢዩ ናታንን ስለዚህ በተሟገተዉ ጊዜ ናታን እግዚአብሄር ከአንተጋር ስላለ በልብ ያለዉን አድርግ ብሎ ነገረው (መዝ 132፡ 1-5) ፡፡
ነቢዩ ናታን “ ትክክለኛ ሰዉ አልነበረም “ ፤ በርግጥ በ 2ሳሙኤል 12 ዳዊትን በኃጢዓቱ የተጋፈጠ ሰዉ ነበር ፤ ናታን የእግዚአብሄርን ቃል ዳዊትን ሊነግረዉ መጣ ፤ ይሁን እንጂ በዚህ በምዕራፍ 7 የእግዚአብሄርን ምሪት ሳይጠይቅ በግልፅ ወዲያዉኑ ተናገረ (ቁጥር 3) ፡፡ ዳቪስ ራልፍ ደል “ ናታን ዳዊት እያሰበ የነበረዉን ያውቃል ፤ ተከበረ፣ ጥሩ አሳብ እና ትክክለኛ አሳብ ነበር ፤ ሁለት ጊዜ ስለ ሀሳቡ ማሰብ አያስፈልገውም ፤ ናታንም እንዲሰራ ዳዊትን እንዳነሳሳው “ ይገልፃል ፡፡
2-ሳሙኤል (7፡ 4-8)፡ ናታን የእግዚአብሄርን ቤት እንዲሰራ በፍጥነት እንዲቀጥል ዳዊትን ሰጥቶት ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር ሌላ እቅድ ነበረው - ወደ ሚመጣዉ መሲሁ የሚያመለክተዉ ዳዊታዊ ኪዳን ፡፡ እግዚአብሄር ለዳዊት ለምን “አትሰራም “ አለው ? እግዚአብሄር የዳዊትን ፍላጎት እምቢ ያለበትን ሰዎስት ምክንያቶች ኮንስታብል ይሰጣል፡ “ መጀመሪያ ለመስራት የሚጫን ፍላጎት አልነበረም ስለሆነም ከዘፀዓት ጀምሮ ታቦቱ በድንኳን ኖረ…. ሁለተኛ እግዚአብሄር ህዝቡን ቋሚ ቤተ መቅደስ እንዲሰሩለት አላዘዘም ነበር …. ሰዎስተኛ ብዙ ደም ስላፈሰሰ ዳዊት ቤተ መቅደሱን ለመስራት ትክክለኛዉ ሰዉ አልነበረም “ ፡፡ በቁጥር 4 እግዚአብሄር ናታን ለዳዊት የነገረዉን ቃል አስተካከለው ፤ እስራኤላዊያን ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ በሁሉም አመት እግዚአብሄር ስለ ቤት አልጠየቀም (ቁጥር 5-7) ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄር ዳዊትን የቤተ መቅደሱ ሰሪ እንዲሆን ሳይሆን ለህዝቡ መሪ እንዲሆን እንደ ጠራዉ ለማሳየት የእረኛ ንግግር እንደ ተጠቀመ ይገልፃል (ቁጥር 8) ፡፡ አሁንም ቢሆን “ የእግዚአብሄር አገልጋዮች የህይወትን ቅር መሰኘትን መቀበል መማር አለባቸው ኤ.ቲ. ፔይርዘን ቅር መሰኘቶች ሹመቶቹ ናቸዉ ለማለት ተጠቅሞበታል “ ፡፡ ኮንስታብል “ እግዚአብሄር ዳዊትን እየቀጣዉ እንዳልነበር ወይም የዳዊትን ጥሩ ሀሳብ በመከልከል ተቃዉሞት አልነበረም ፤ በቀላሉ እግዚአብሄር አገልጋዩን እያስተካከለዉ ነበር ፤ መሪ የሚሆን እንደ ነበር እንጂ ቤተ መቅደስ ሰሪ እንዳልነበር “ ይገልፃል ፡፡ በተመሳሳይ እግዚአብሄር እንድንሰራለት ያስፈልገዋል በለን ከምንሰራለት ነገሮች እንድንሰራለት ወደ ሚፈልገዉ ነገር የሚያስተካክልበት ጊዜያቶች አሉ ፤ ልንሰራለት ያስፈልገዋል የምንላቸዉን ነገሮች በእርሱ መስራት መቀጠል የለብንም ይልቁንስ ወደ ዳዊት ኪዳን ተመልሶ የመሄድ እቅድ እንዳለዉ በመቀበል በእርሱ እንረፍ ፡፡
2-ሳሙኤል (7፡ 9-13)፡ እግዚአብሄር ዳዊትን በእርሱ ዉስጥ በአብርሃም ኪዳን እየተጓዘ እንደ ነበር በማስታወስ የዳዊትን ስም ታላቅ አደርገዋለሁ አለ (ቁጥር 9) ፡፡ አንድ ቀን ከዳዊት ዘር አንዱ ለእርሱ ቤት እንደ ሚሰራለት እና እግዚአብሄርም ለዘላለም የመንግስቱን ዙፋንለዘላለም ይመሰርታል (መዝ 89፡ 4) ፤ ይህ ልጅ የዳዊትና የቤርሳቤህ ልጅ ሰለሞን እንደሚሆን እናዉቃለን ፡፡ እግዚአብሄር የዳዊትን እና የቤርሳቤህን ሁኔታ በመሲሁ የዘር መስመር ዋጀው (ቁጥር 12-13) ፡፡
2-ሳሙኤል (7፡ 14-17)፡ እግዚአብሄር ለእርሱ ልጅ ለሚሆነዉ ለዚህ ዘር አባት እሆነዋለሁ አለ ፤ ይህን ልጅ በሰዉ በትር ይቀጣዋል እንጂ ፍቅሩ በፍፁም ከልጁ አይርቅም ፡፡ የዳዊት ቤት እና መንግስቱ ለዘላለም ይገዛል ዙፋኑም ለዘላለም ይሆናል (ቁጥር 14-16) ፡፡ ናታን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለዳዊት ነገረው (ቁጥር 17) ፡፡
2-ሳሙኤል (7፡ 18-29)፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት በመቀመጥ “ ጌታዮ እግዚአብሄር ሆይ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማነኝ ? “ በማለት ጠየቀ (ቁጥር 18) ፡፡ የምዕራፉ ቀሪ የዳዊት የምስጋና ፀሎት ነው ፡፡
በዳዊት ኪዳን እግዚአብሄር ዳዊትን ቤቱ፣ መንግስቱ እና ዙፉኑ ለዘላለም እንደሚቆይ ቃል ገባለት ፡፡ ዳዊት የእስራኤል መብራት ነው ብርሃኑም በፍፁም አይጠፋም (2 ሳሙ 21፡ 17) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህን የተስፋ ቃል፡ “ 1) የዳዊት መስመር ወይም ቤት ሁል ጊዜ የነገስታት መስመር ይሆናል፣ 2) ሁል ጊዜ የማስተዳደር መብ የዳዊት ዘር መብት ይሆናል እና 3) የምድራዊዉ መንግስት አንድ በአንድ መብት ከዳዊት የልጅ ልጅ ዘር እንደ ማይወሰድ “ ይገልፃል ፡፡ይህ ማለት በዚህ አስተዳደር መቆም የለም ማለት አልነበረም (ሆሴ 3፡ 4-5) ፡፡
አአስተዳደሩ(መሪነቱ) ሁል ጊዜ በዳዊት ኪዳን በኩል ይመጣል (ሉቃ 1፡ 32-33) ፤ “ የዚህ ተስፋ ቃል የመጨረሻዉ መፈፀመ ክርስቶስ በህዝቡ ላይ ሊገዛ በሚመለስ ጊዜ በሁለተኛው ምጽዓት የሚታቅ ይሆናል “ (ራዕ 20፡ 1-6) ፡፡ 2 ሳሙኤል 7 ወደ ኢየሱስ መወለድ (ሉቃስ 1) እና ወደ መመለሱ (ራዕይ 20) ያመለክታል ፡፡
ዋይርስቤ የዳዊትን ምስጋና የመስጠትን ፀሎት በሰዎስት ክፍል ይከፍለዋል፡ የመጀመሪያው ዳዊት በሰዓቱ በህይወቱ ላይ ስለ ነበረዉ የእግዚአብሄር ሞገስ አመሰገነ (ቁጥር 18-21) ፤ ሁለተኛው ዳዊት በባለፈዉ ለእስራኤላዊያን እግዚአብሄር አድርጎት ስለ ነበረው አመሰገነ (ቁጥር 22-24) ፤ ሰዎስተኛዉ ደግሞ ዳዊት ስለ ወደፊቱ ገልጦለት ስለ ነበረዉ እግዚአብሄርን በማመስገን ተስፋዎቹም እንዲፈፀሙ ጠየቀ (ቁጥር 25 -29) ፡፡
መደምደሚያ
ከፓስተር ጃክ ዌልማን በዚህ ፅሁፍ ላይ ሰዎስት የሚያስደንቁ እይታዎች አሉ፡
- እግዚአብሄር የወደፊቱን ያያል (ኢሳ 46፡ 9-10) ፡፡
- የእግዚአብሄር መንገድ ከእኛ ይበልጣል (መዝ 33፡ 11፣ ኢሳ 55፡ 8፣ 9) ፡፡
- እናቅዳለን - እግዚአብሄር ያሳያል(ይመራል) (ምሳ 10፡ 9፣ 19፡ 21፣ 20፡ 24፣ ኤር 10፡ 23) ፡፡
በ 2ሳሙኤል 8 ዳዊት በእግዚአብሄር በማረፉ ምክንያት ዳዊት ድሎች ነበሩት፡ በፍልስጤማዊያን ላይ (ቁጥር 1)፣ በሞዓባዊያን ላይ (ቁጥር 2)፣ በአሞራዊያን ላይ (ቁጥር 5) እና በኤዶማዊያን ላይ (ቁጥር 13) ፤ “ ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሰ ፤ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድና ጽድቅን አደረገላቸው “ (ቁጥር 15) ፤ ዳዊት በጥሪዉ መጓዝ ጀመረ ምክንያቱም እግዚአብሄር በህይወቱ እንዲናገረው ስለፈቀደ ፡፡
Dale Ralph Davis, 2 Samuel: Out of Every Adversity (Geanies House, Fearn, Ross-shire, IV20 1TW, Great Britain: Christian Focus Publications, 1999), p. 84.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes, pp. 52-53; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2samuel.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 2 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 323.
Wiersbe, p. 323.
Charles R. Swindoll, David: A Man of Passion and Destiny. Great Lives from God’s Word series. (Dallas: Word Publishing, 1997), p. 162-68; quoted at Constable, p. 53.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 399.
Nelson’s, p. 399.
Wiersbe, p. 325.
ጥያቄዎች
-
ዳዊት ለእግዚአብሄር ታቦት ማደሪያነት ለምን የፅድ ቤት መስራት ፈለገ ? የእግዚአብሄር መልሻ ምን ነበር ? እግዚአብሄርን በሆነ ስፍራ አስቀምጣችሁ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? እንዴት ?
-
በ 2ሳሙ (7፡ 12-13) እና 16 እግዚአብሄር ከዳዊት ዘር መንግስትን እንደ ሚያስቀምጥ ተናገረ ፤ ይህ ወደ ኢየሱስ እና ወደ ዘላለማዊዉ ዙፋኑ እንደ ሚያመለክት ታስባላችሁ ? ኢየሱስ ከዳዊት የዘር ሀረግ ነዉ የመጣው ? (ማቴ 1፡ 1-17)
-
በ 2ሳሙ (8፡ 3) እግዚአብሄር ተስፋዉን ለመጠበቅ እንዴት ቀጠለ ? (ዘፍ 15፡ 18-21፣ 1 ዜና18፡ 3)
-
የእግዚአብሄር ቃል ሙሉ ድል የማድረግ ተስፋን ሰጥቷል ፤ እንደ እግዚአብሄር ልጆች ተስፋ የተገባልንን ሁሉንም ግዛት ወስደናል ወይስ አሁንም በጠላት የተያዘ ጥቂት አለ ? (ገላ 5፡ 13፣ ፊል 4፡ 19)
-
በ 2ሳሙኤል (7-8) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያሳያችኋል) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 8:14b–15
“The LORD made David victorious wherever he went. So David reigned over all Israel, administering justice and righteousness for all his people.”
ንጉስ ዳዊት የእስራኤል ንጉስ ሳለ በቤቱም ዕረፍትን ባገኘ ጊዜ የራሱን ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለዳዊት ራዕዩን ያካፍልና የምክርን ቃል ይሰጠው ዘንድ ነቢዩ ናታንን ተጠቀመ ፡፡ ዳዊትም ቃሉን ከናታን ከሰማ በኋላ ፤ በእግዚአብሔር ፊት ጊዜን አሳለፈ ፤ የእግዚአአብሔርንም ታማኝነት በማስታወስ እግዚአብሔርን አመሰገነ ፡፡ ዳዊት ቃልንና ምሪትን ከእግዚአብሔር ተቀበለ ፤ ከእግዚአብሔር ጋርም የነበረው ዘላለማዊ ኪዳን አስተዋለ ፡፡ ዳዊት ከራሱ አሳብ ይልቅ የእግዚአብሔርን ፍቃድ አሳብ ተከተለ ፡፡
በእግዚአብሔር ስትታመን እርሱ መንገድህን ያቀናልሀል ፡፡ እቅድ ይኖርህ ይሆናል ምናልባትም እርሱን ለመፈጸም መንገድ ጀምረህ ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሔር መንገድህን ያስተካክል ዘንድ ወይም እቅድህን ሊያራዝም ሰዎችን ወይም ደግሞ ሁኔታዎችን በመንገድህ ይልካል ፡፡ እግዚአብሔር የምትማርና የምትስተካከል እንድትሆን ይፈልጋል ፡፡ እልከኛደግሞም በራስህ መንገድ የጸናህ አትሁን ፡፡ የእግዚአብሔር መንገድ እንድመራህ ፍቀድ ፡፡ ደግሞም ስል እቅዱ መቀየር ጥያቄ ካለህ እግዚአብሔር እንድያሳውቅህ ጠይቀው ፡፡ ከዚያም ሳትወላውል በእምነት ጸንተህ ተራመድ ፡፡ እግዚአብሔርም መንገድህን ያቀናልሀል ፡፡ መንገዱ ከመንገድህ አሳቡም ከአሳብህ ከፍ ይላልና እቅዱ ይፈጸማል ፡፡ በክርስቶስ ውስጥ ድልን ትቀዳጃለህ ፡፡
“ እግዚአብሔርም ዳዊት በሚሄድበት ሁሉ ድልን ሰጠው ፡፡ ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው ፡፡
- 2ኛ ሳሙኤል 8፡14-15
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 16፡9 –“ የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል ፡፡ “
ኢሳያስ 55፡ 8-9 –“ አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር ፡፡ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደደሚል እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው ፡፡ “
ያዕቆብ 1፡6 –“ ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።