Bringing the Ark to Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 1ሳሙ (16፡ 12-13) ዳዊት በሳሙኤል ፊት መጥቶ የእስራኤል ቀጣዩ ንጉስ እንደ ሚሆን በእግዚአብሄር ተመርጦ ነበር ፤ ቁጥር 13 “ የእግዚአብሄርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ “ ብሎ ይናገራል ፡፡ በ 1ሳሙኤል እንደ ቀሪ እግዚአብሄር ዳዊትን መባረክ በመጀመር በእስራኤል ዙፋን ላይ ለሚቀመጥባት አንድ ቀን አዘጋጀው ፤ ይሁን እንጂ ዳዊት የወደፊት ንጉስ ተደርጎ በመቀባቱ እና በሳዖል የአሁን ንጉስነት መቀባት መካከል በማያቋርጥ ትግል እና ዉጥረት ዉስጥ ነበር ፡፡ በ 2ሳሙኤል በመጀመሪያዉ ክፍል ዳዊት የይሁዳ ንጉስ ተደረገ በምዕራፍ 5 ደግሞ መላዉ እስራኤል ዳዊትን በላያቸዉ ላይ እንደ ንጉስ ሊሾሙ በአንድ ላይ መጡ ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን በጎቹን ይጠብቅ እንደ ነበረዉ አሁን ህዝቡን እንዲጠብቅ እና በእስራኤል ላይ እንዲያስተዳድር ነገረው ( 2ሳሙ 5፡ 1-3) ፡፡
እስራኤል እንደ ተቀባ ለዳዊት የእርሱ ደም እና ስጋ እንደ ነበሩ የተቀባዉ የሚመጣዉ የኢየሱስ ጥላ እንደ ሆነ ነገሩት ፤ ኢየሱስ ለእኛ ደም እና ስጋ ሆኖልናል ፡፡ በተጨማሪም በሳዖል እንደ መጀመሪያ ንጉስ እና በአዳም እንደ መጀመሪያዉ ሰዉ፣ በዳዊት እንደ ሁለተኛ ንጉስ እና በኢየሱስ እንደ ሁለተኛዉ ሰዉ መካከል የሚያስደንቅ ተመሳሳይነት አለ ፡፡
አንዳንዶቻችሁ በእናንተ ላይ ተነግሮ የነበር ትንቢታዊ ቃል አላችሁ ምናልባትም በዚያ በጥሪአችሁ ዉስጥ ስትጓዙ በጭንቀት ዉስጥ ትሆናላችሁ ፤ በህዝብ ፊት ያልሆነ ቅባት (ሹመት ) አይኖራችሁ ይሆናል ፤ ነገር ግን ማንም ለእናንተ የሆነዉን ያን ቅባት እዉነቱን ዋጋ አያሳጣዉም ፡፡ ዳዊት በጥሪዉ ሲጓዝ በሂደቱ ተግቶ መስራትን እና ሀቀኝነትን አዳበረ ፡፡ ዳዊት ንጉስ በሆነ ጊዜ 30 አመቱ ነበር ፤ ይህ ያስደንቃል ኢየሱስም አገልግሎቱን ሲጀምር 30 አመቱ ነበር ፡፡
በምዕራፍ 5 እንደ ቀሪ ኢየሩሳሌምን ከኢያቡሳዊያን ላይ ለመዉሰድ ዳዊት ወታደሮቹን መራ ፤ እስራኤላዊያን ለተስፋይቱ ምድር በሚዋጉ ጊዜ ኢያቡሳዊያንን እንደ ሚጠብቁዓቸዉ አስበዉ ነበር ፤ ያ ባለመሆኑ ዳዊት በስትራቴጂክ እንቅስቃሴ ይህንን ወሰደ ፡፡ ኢየሩሳሌምን እንደ አዲስ ዋና ከተማ በመመስረት ዳዊት በደቡብ እስራኤል እና በሰሜን እስራኤል መካከል ጥምረት ፈጠረ ፡፡ ኢያቡሳዊያን ከተማዋ በኃይል እንደ ተመሸገች በማመን ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት እዉሮችን እና አንካሳዎቹን በምሽግጉ ላይ አስቀመጡዓቸው ፤ ዳዊት እና የእርሱ ሰዎች በዉኃ መሹለኪያ በኩል በመግባት ከተማዋን ያዙአት ፡፡ ይህ እንደ ንጉስ የዳዊት የመጀመሪያዉ ዉጊያ ነበር ፡፡ ዳዊት ንጉስ እንደ ነበር ፍልስጤማዊያን በሰሙ ጊዜ ሊያሰንፉት በማቀድ ከኃላዉ ተከተሉት ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ፍልስጤማዊያንንም ለዳዊት ሰጠው ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (6፡ 1-5)፡ ዳዊት ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በአንድ ላይ የተመረጡ 30,000 ሰዎችን አመጣ (ቁጥር 1-2) ፤ ዳዊት እና ወታደሮቹ ለ50 አመት ከተቀመጠበት ከአሚናዳብ ቤት ታቦቱን ለማምጣት ሄዱ ፡፡ ፍልስጤማዊያን ታቦቱን ማርከዉት ነበር ነገር ግን በመካከላቸዉ በመገኘቱ በአካላቸዉ ላይ እብጠቶች ማደግ ጀመረባቸው (1 ሳሙኤል 6) ፤ ለህመማቸዉ ታቦቱ ምክንያት እንደ ነበር ለማየት በአዲስ ሰረገላ ላይ በማድረግ መልሰዉ ላኩት ላሞቹም መልሰዉ ወደ ቤተሳሚስ ሳቡት ፤ በዚያ የነበሩ ሰዎች ታቦቱን በአምልኮ አላስተናገዱትም እግዚአብሄርም 70 ሰዎችን ገደለ ፡፡ ታቦቱም ተቀምጦበት በነበረው ወደ አሚናዳብ ቤት ተወስዶ ነበር (1 ሳሙኤል 7) ፤ ታቦቱ በአዲስ ሰረገላ ወደ እነርሱ ተመልሶ ስለ ነበር ዳዊት እና ወታደሮቹ በሌላ አዲስ ሰረገላ ላይ አስቀመጡት (ቁጥር 3) ፡፡
2-ሳሙኤል (6፡ 6-11)፡ ሰረገላዉን እና ታቦቱን ሲከተሉ በሬዉ ስላደናቀፈዉ ታቦቱ ተወዛወዘ ፤ ዖዛ ታቦቱ ላይ ደረሰ ስለዚህም ታቦቱ አይወድቅም (ቁጥር 6) ፤ በዖዝ አምልኮ(አክብሮት) ማጣት ላይ የእግዚአብሄር ቁጣ ነደደ ዖዝንም ስለ ቀሰፈዉም በዚያዉ ሞተ (ቁጥር 7) ፤ በእስራኤል ህግ ታቦቱን ሰዎች በአምልኮት እና በአክብሮት ያስተናግዱታል ፡፡ ታቦቱ በትክክል አልተያዘም ነበር ፤ ዳዊት ተበሳጨ በተፈጠረዉም ነገር እግዚአብሄርን ፈራ (ቁጥር 8-9) ፡፡ በኢየሩሳሌም ፋንታ ታቦቱ ወደ አቢዳራ ቤት ተወሰደ በዚያም ለሰዎስት ወር በመቀመጡ የአቢዳር ቤት ተባረከ (ቁጥር 10-11) ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በመካከላችን በሚኖር ጊዜ ነገሮች መቀየር ይጀምራሉ በመኖሩም ፍሬ ይመጣል ፡፡ በራሴ ህይወት በአገልግሎቴ ፍሬ የማላፈራበትን ጊዜ የማይባቸዉ ብዙ ጊዜዎች አሉ በዚህም በማቆም ለምን እንደ ሆነ እግዚአብሄርን መጠየቅ እፈልጋለሁ ፡፡
2-ሳሙኤል (6፡ 12-19)፡ ሰዎች በታቦቱ መገኘት ምክንያት እግዚአብሄር የአቢዳር ቤት እየተባረከ እንደ ነበር ዳዊትን ነገሩት ዳዊትም በደስታ ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት ሄደ (ቁጥር 12) ፡፡ ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋዊያን የእግዚአብሄርን የአፈጣጠር ሂደትን የሚወክለዉን ስድስት እርምጃ ከሄዱ በኋላ ታቦቱ ይቆማል ዳዊትም አንድ በሬ እና የሰባ ጥጃ ይሰዋ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ዳዊት ንጉስ ነበር በተጨማሪም የበፍታ አፉዱን በመልበስ እና በአምልኮ በመጨፈር የካህኑ ቁመና(ድርሻ) ላይ ቆመ፤ ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ሲያመጣው እስራኤል ሁሉ ከዳዊት ጋር በመምጣት ጮኹም የመለከት ቀንድም ነፉ (ቁጥር 15) ፡፡ የሳዖል ልጅ እና የዳዊት ሚስት ሚልኮል በመስኮት ስትመለከት ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት ሲጨፍር አየችዉ “ በልቧም ናቀችዉ “ (ቁጥር 16) ፡፡ ያለ ገደብ እግዚአብሄርን በድርጊታችን ለማምለክ ፍቃደኛ ባለመሆናችን እደነቃለሁ ምክንያቱም ሌሎች ስለ እኛ ምን እንደ ሚያስቡ ያተኮርን ስለሆነ ፡፡ በዚህ ፅሁፍ ሚልኮል ለእግዚአብሄር የዳዊትን ምላሽ እና ግብረ መለስ ግራ የሚያገባ መሆኑን የግሏን አስተያየት እንደ ሰጠች አያለሁ ፡፡ ታቦቱ ዳዊት አዘጋጅቶለት በነበረዉ ስፍራ ተቀመጠ ዳዊትም ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት እና የደኅንነት መስዋዕት አቀረበ (ቁጥር 18) ፡፡
የሚቃጠለዉ መስዋዕት ሙሉ መስዋዕት ነበር ይህ ማለት የሚሰዋዉ እንሰሳ የማይቃጠለዉ ብቸኛዉ አካል ለሌዋዊያን ተሰጥቶ የነበረው ቆዳዉ ብቻ ነበር ማለት ነው ፡፡ የደህንነት መስዋዕት የእግዚአብሄር ሰላም ለእግለሰብ ወይም ለቡድን መምጣቱን የሚያሳዉቅ ነበር ፤ የደህንነት መስዋዕት እንደ መስዋዕት አካል በመሆን በዛዉ የሚበላ እንጂ ቤት የሚወሰድ አልነበረም ፡፡ ሁሉም እስራኤላዊያን እና የዉጪ ሰው ከደህንነት መስዋዕቱ አካል ይቀበላሉ ፤ ይህ ሰላም ለሁሉም እንደ መጣ የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋትነት የሚያምር መልክ ነው ፡፡ ከመስዋዕቶቹ በኋላ ዳዊት ህዝቡን በእግዚአብሄር ስም ባረካቸው ፤ በተጨማሪም ዳዊት ለእያንዳንዱ በእስራኤል ላለዉ ማህበረሰብ ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም አንድ እንጀራ፣ አንድ ቁራጭ ስጋ እና አንድ የዘቢብ ንጣፊ ሰጣቸዉ ሁሉም ወደራሱ ቤት ሄደ (ቁጥር 19) ፡፡ ከዚያም ዳዊት የራሱን ቤተሰብ ሊባርክ ወደ ቤቱ ሄደ በ 1ዜና ቤተሰቡን እንዳገለገለ የተገለፀ ነው ፡፡ ዳዊት የራሱን ቤተሰቦች እና የህዝቦቹን አከበረ ፡፡
2-ሳሙኤል (6፡ 20-23)፡ ዳዊት ቤት በገባ ጊዜ የሳዖል ልጅ ሚልኮል በድርጊቱ በመቆጣት ራሱን አጋልጦ እንደ ነበር እና እንደ ባለጌ አድርገሀል አለችዉ (ቁጥር 20) ፡፡ ዳዊት የሚልኮልን ቁጣ ባለመቀበል እንዲያስተዳድር በሚልኮል ቤተሰቦች ላይ በመረጠዉ አምልኩ ፊት እየጨፈረ እንደ ነበር ነገራት ፤ “ ስለዚህም በእግዚአብሄር ፊት እጫወታለሁ ፤ አሁንም ከሆንኩት ይልቅ የተናቅሁ እሆናለሁ በዓይንሽም እዋረዳለሁ ፤ ነገር ግን በተናገርሽዉ ቆነጃጅት ዘንድ እከብራለሁ አላት “ (ቁጥር 21-22) ፡፡ በመሰረቱ ዳዊት ሚልኮልን ከእርሷ ጋር ነገሩን እንደ ፈፀመ እየነገራት ነበር ፤ ቁጥር 23 ይህን ያረጋግጣል “ የሳዖልም ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም “ ፡፡
መደምደሚያ
ዳዊት ዋና ከተማ እንዲሆነዉ በኢየሩሳሌም ቦታን መሰረተ ፤ እንዲሁም ከሁሉም በላይ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ እዉነተኛ ንጉስ እንዲሆን መፈለጉን አሳዬ ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄር ከእርሱ በላይ እንዲያስተዳድር ፈለገ ስለሆነም ታቦቱና የእግዚአብሄር መገኘት በዋና ከተማዉ ይኖረዋል ፤ ለዚህ ነው እግዚአብሄርን የንገስታት ንጉስ እና የጌቶች ሁሉ ጌታ ብለን የምንጠራው ፡፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን መገኘት በማክበር መገኘቱን በትክክለኛ ስፍራ አስቀመጠ - ከሁሉም ነገር እና ከሁሉም ሰዉ በላይ በሆነው ፡፡
አንድ የመጨረሻዉ አሳብ ስለ ዘላለማዊ ዙፋን ፍሬ ነገር ነው ፡፡ እስራኤል ታቦቱን በሰረገላ ላይ ባስቀመጡት ጊዜ አንድ ሰዉ ሞተ ስለዚህም ተመልሰዉ በመምጣት በሌዋዊያን ትካሻ ላይ አስቀመጡት ፤ ኢሳ (9፡ 6) “ አለቅነትም በጫንቃዉ ላይ ይሆናል “ ይላል ፤ ኢየሱስ “ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነዉና “ ብሏል (ማቴ 11፡ 30) ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በትካሻችን ላይ በማረፍ ከዚያ ስፍራ ከፍ እንድንል ምክንያት ይሆናል ፡፡ በትካሻቸዉ ላይ ታቦቱን ማስቀመጣቸው የእግዚአብሄርን መገኘት በትካሻዉ የተሸከመዉ የኢየሱስ ጥላ እንደ ነበር አምናለሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
አንዳንድ ጊዜ “ የዉሃ መሄጃ እያለ “ (2 ሳሙ 5፡ 8) ወይም ለአደጋ የሚያጋልጥ ቦታ ወይም በኑሮአችሁ ድካም ቢኖርም በምድራዊ ሀብት፣ ሁኔታ ወይም እዉቀት ደህንነታችን እንደ ተጠበቀ በማመን ኢያቡሳዊያንን እንመስላለን ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በ 2 ሳሙ (5፡ 13) ኢያቡሳዊያን በቁጥር 6 እንዳደረጉት ተመሳሳይ ነገር ዳዊት እያደረገ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ (ያለበትን ስልጣን እንደ ጥቅም በመዉሰድ) ?
-
ዳዊት የኪዳን ታቦቱን ከመሸከም ይልቅ በአዲስ ሰረገላ ላይ አስቀምጧል (ዘኁ 4፡ 5-6፣ 15፣ 2 ሳሙ 6፡ 3) ? ይህን ሀሳብ ከየት አገኘው ( 1ሳሙ 6፡ 7-8) ? ነገሮችን በዚህ አለም መንገድ ከማድረግ ይልቅ እግዚአብሄር ለመፈለግ ከዳዊት መዉደቅ ስህተት ምን ልንማር እንችላለን ?
-
በ 2ሳሙ (6፡ 20) ሚልኮል ስለ ዳዊት አለባበስ እና በእግዚአብሄር ፊት እንዴት እንደ ጨፈረ ቅር ተሰኝታ ነበር ፤ የመጣባት ዉጤት ምን ነበር ( 2ሳሙ 6፡ 23) ? አምልኮአቸዉን እንዴት እንደ ሚገልፁ በሌሎች ላይ ሳትስማሙ ወይም ፈርዳችሁ ታውቃላችሁ ? ዳዊት እንዳደረገበት ተመሳሳይ ሁኔታ ራሳችሁን ለመግለፅ ሰዎች ምን ያስባሉ በማለት ተሰናክላችሁ ታውቃላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልተሰናከላችሁም ?
-
በ 2ሳሙኤል (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 6:21–22
“David replied to Michal, ‘I was dancing before the LORD who chose me over your father and his whole family to appoint me ruler over the LORD’s people Israel. I will celebrate before the LORD, and I will humble myself even more and humiliate myself. I will be honored by the slave girls you spoke about.’”
ዳዊት የቀልኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም መለሰ ፡፡ ሌዋውያኑ ታቦቱን በትከሻቸው በተሸከሙ ጊዜ ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽል ያመሰግኑ ነበር ፡፡ ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይዘፍን ነበር ፡፡ የዳዊት ሚስትም ሜልኮል ባሏ በእግዚአብሔር ፊት ሲዘፍን አይታ ናቀችው ፡፡ ነገር ግን ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት በመዝፈኑና በመዝለሉ አላፈረም ነበር ፡፡
እግዚአብሔር አምሎክህን ይናፍቃል ፡፡ ሌሎች ሊያስቡ ስለሚችሉት ነገር ራስህን አታስጨንቅ ፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ መገኘት በደስታ የተሞላ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሔርን ማምለክ እንድትዘል እንድትሽከረከር ካሳኘህ አድርገው ፡፡ አምልከው ምክኝያቱም ሀዘንህን በደስታ ስለለወጠ ! ሌሎች ስለሚሉት ነገር አትጨነቅ ፡፡ እርሱ ሁሉም ነገር ይገባዋል መመስገንም እንድሁ ፡፡ ለእግዚአብሔር ህይወትህን ስጥ ምክንያቱም እርሱ የማቅ ልብስህን አውልቆ ደስታን አጎናጽፎኃልና ! ዘምር ደግሞም ዝም እንዳትል ! ዛሬ በነጻነት እግዚአብሔርን አምልክ !
“ ዳዊትም ሜልኮልን በእግዚአብሔር ፊት ዘፍኛለሁ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ ፡፡ አሁንም ከሆንሁት ይልቅ የተናቅሁ እሆናለሁ በዓይንሽም እወረዳለሁ ነገር ግን በተናገርሽው ቆነጃጅት ዘንድ እከብራለሁ አላት ፡፡ “
- 2ኛ ሳሙኤል 6፡21-22
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 15(16)፡11 –“ የሕይወትን መንግድ አሳየኸኝ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ ፡፡ “
መዝሙር 29(30)፡11-12 –“ ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ ማቄን ቀደድህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ አቤቱ አምላኬ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ ፡፡ “
2ኛ ቆሮንቶስ 3፡17 –“ ጌታ ግን መንፈስ ነው የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።