The Assassinations of Abner and Ish-Bosheth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ሳሙኤል 1-2 ዳዊት በይሁዳ ነገድ ላይ የተቀባ ንጉስ ነበር ፤ መጀመሪያ ጊዜ ዳዊት ጎልማሳ ልጅ እንደ ነበር እንደ ንጉስ ተቀብቶ ነበር ሳሙኤልም በእግዚአብሄር እንደ ተመረጠ የእስራኤል ንጉስ ቀብቶታል ፡፡ ይህ በእስራኤል ክፍል እንደ ንጉስ ሁለተኛ ቅባቱ(መቀባቱ) ነበር ፡፡
ትምህርት
2-ሳሙኤል (3፡ 1-5)፡ ረጅም ጦርነት በሳዖል ቤት እና በዳዊት ቤት መካከል ተካሄደ ፤ የሳዖል ቤት እየደከመ ሲሄድ የዳዊት ቤት እየበረታ ሄደ (ቁጥር 1) ፡፡ በ 2ሳሙ (2፡ 8) አበኔር የሳዖልን ልጅ ኢያቡስቴን ሁሉም “ እንደ እስራኤል በተለዩት “ በገልዓድ፣ በአሴር፣ ኤዝራኤል፣ ኤፍሬም እና ቢኒያም ምድር ላይ ንጉስ አደረገው ፡፡ ጦርነቱ እስራኤልን ሚያስተዳደር - በሳዖል ቤተሰብ ወይም በዳዊት ነበር ፤ ለዙፋን ይህ ዉጊያ በቀጣዮቹ በ 2ሳሙኤል ስድስት ምዕራፍ ዉስጥ ይቀጥላል ፡፡
የሳዖል ቤት እየደከመ ሲሄድ የዳዊት ቤት እየበረታ የነበረዉ ለምን ነበር ? እዚህ ጋር ዳዊት ለቤተሰቡ ተጨማሪ ሚስቶችን እና ልጆችን ጨምሮ ነበር (ቁጥር 2-5) ፤ የእግዚአብሄር እጅ ዳዊት ላይ ነበረች ፡፡ በሳዖል ቤት ድንጋጤ እና ምስቅልቅልነት ነበር (1 ሳሙ 13፡ 14) ፡፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን ልብ ያገኘ እና የእግዚአብሄርን ፍቃድ የተመለከተ በድፍረት እና በኃቀኝነት የተጓዘ አንድ ሰዉ ነበር ፤ ሳዖል ግን በፍርሀትና በድንጋጤ አደረገ (ድርጊት ፈፀመ) ፤ ይህ በጥበብ ይመራ ወደ ነበረው ያመጣል ፡፡
ሰለሞን ከእስራኤል ንጉሶች ጥበበኛ የሆነ እንደሚሆን የተለየነ ነው ፤ ጥበቡ ከየት የመጣ ነበር (ያዕ 3፡ 13-18) ? ከአባቱ ከዳዊት ፤ ሰለሞ በአባቱ ዉስጥ ሲጓዝ ጥበብን አይቷል ፤ ለዚያም ነው ሰለሞን በመረዳት እግዚአብሄርን ጥበብ የጠየቀዉ ፡፡
2-ሳሙኤል (3፡ 6-11)፡ በሳዖል ቤት እና በዳዊት መካከል ያለዉ ጦርነት ሲቀጥል የሳዖል አጎት እን የጦር አዛዡ አበኔር በኃይል መበርታት ቀጠሉ (ቁጥር 6) ፡፡ ኢያቡስቴ አበኔርን ከሳዖል ቁባቶች ከአንዷ ጋር በመተኛት ከሰሰው (ቁጥር 7) ፤ አበኔር በኃይል በመበሳጨት እኔ ለይሁዳ አባል የሆንኩ የዉሻ እራስ ነኝን በማለት ጠየቀው ፤ በብሉይ ኪዳን ሁል ጊዜ ዉሾች በመጥፎ ሁኔታ ይጠቀሱ ነበር ፡፡ አበኔር ለእስራኤል ይሰራ የነበረ አመንዝራ ወንድ የሚል አሳብ ስለነበር እየጠየቀ ነበር ፡፡ አበኔር ተበሳጨ ምክንያቱም ለኢያቡስቴ መንግስት ቸርነትን አድርጎ የነበረ አንዱ ስለ ነበር (ቁጥር 8) ፤ አበኔር እግዚአብሄር ዳዊትን ተስፋ ገብቶለት እንደ ነበር እያወቀ ከዳዊት አስተዳደር ጋር ተዋግቶ ነበር ፤ ነገር ግን በዚህ ክስ ምክንያት የአበኔር ታማኝነት ወደ ዳዊት ዞረ (ቁጥር 9-10) ፤ ኢያቡስቴም አበኔርን ፈራው (ቁጥር 11) ፡፡
2-ሳሙኤል (3፡ 12-16)፡ አበኔር ዳዊትን አሁን የዳዊትን የዙፋን ጥያቄ እንደደገፈ እንዲያዉቅ ፈቀደ (ቁጥር 12) ፡፡ ዳዊት በአበኔር እቅድ - አበኔር የሳዖልን ልጅ ሚልኮልን ከእርሱ ጋር እንዲያመጣት ከሚለዉ ዉጭ ተስማማ (ቁጥር 13) ፤ ዳዊት ለኢያቡስቴ (ለሳዖል ልጅ) የ 100 ፍልስጤማዊያንን ሸለፍ ላመጣለት ለመጀመሪያ ሰዉ “ ሳዖል ሸጧት” በነበር ጊዜ ለማግባት አጭቷት የነበረችዉን ሚልኮልን መልሶ እንዲሰጠዉ ቃል ላከለት (ቁጥር 14) ፡፡ ኢያቡስቴ ሚልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፈልጢኤል በመዉሰድ ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 15-16) ፡፡
2-ሳሙኤል (3፡ 17-21)፡ ከዚያም አበኔር የእስራኤልን ሽማግሌዎች በማግኘት ዳዊትን እግዚአብሄር ለእነርሱ የቀባላቸዉ ንጉስ እንደ ሆነ አቀረበላቸው (ቁጥር 17-18) ፤ አበኔር በተጨማሪም የሳዖል ነገድ ከሆነዉ ከቢኒያማዊያን ጋር በመገናኘት የቀሩት እስራኤላዊያን ዳዊት በእነርሱ ላይ ንጉሳቸዉ እንደ ሆነ እንደ ተስማሙ ነገራቸው (ቁጥር 19)፡፡ አበኔር 20 ሰዋችን ወደ ዳዊት አመጣ ዳዊትም ለሰዎቹ እና ለእርሱ ሰዎች ግብዣ አዘጋጀ (ቁጥር 20) ፤ አበኔር ሁሉንም እስራኤል በዳዊት ፊት አንደ ሚሰበስባቸዉ ቃል ገባ ዳዊትም አበኔር በሰላም ላከው (ቁጥር 21) ፤ እነዚህ የቀድሞ ላቶች አሁን ሰላም ነበሩ ፡፡
2-ሳሙኤል (3፡ 22-27)፡ አበኔር ከሄደ በኋላ ኢዮአብና የዳዊት ወታደሮች ከዘመቻ በምርኮ ተመለሱ (ቁጥር 22) ፤ ኢዮአብ የዳዊት የወንድም ልጅ ነበር አበኔር ደግሞ ከኢዮአብ ወንድሞች አንዱን ገሎ ነበር (2 ሳሙኤል 2) ፡፡ ኢዮአብ ዳዊት እና አበኔር ሰላም እንዳደረጉ በሰማ ጊዜ ዳዊትን ከአበኔር ጋር ያደረገዉን ዉሳኔ ጠየቀው ፤ ኢዮአብ አበኔርን በዳዊት ላይ ሊሰልል እንደ መጣ አሰበ (ቁጥር 23-25) ፡፡ ከዳዊት እዉቅና ዉጪ ኢዮአብ አበኔርን ከሴይርም ጉድጓድ እንዲመልሱት መልዕክተኞችን ላከ (ቁጥር 26) ፤ ኢዮአብ አበኔርን ወደ ጎን በመገተት የወንድሙን ሞት ለመበቀል በሆዱ ወጋዉ (ቁጥር 27) ፤ የኢዮአብ ድርጊት በጥበብ የተፈፀመ ሳይሆን በበቀል እና በራስወዳድነት የተፈፀመ ነበር፡፡
2-ሳሙኤል (3፡ 28-39)፡ ዳዊት ለኢዮአብ ደም አፍስሰዉ ለነበሩት በመለሰበት አልመለሰለትም ፤ ዳዊት በአበኔር መገደል ምንም ነገር እንዳላደረገ ሁሉም እስራኤል በማወቅ እርግጠኛ እንዲሆኑ አደረገ (ቁጥር 28-29) ፡፡ ዳዊት ኢዮአብን እና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎቹ በአበኔር መገደል በአደባባይ እንዲያዝኑ በማዘዝ ዳዊት በቀብር ስነስርዓቱ ሂደት ተጓዘ (ቁጥር 31-32) ፡፡ በአበኔር ሞት ዳዊት አዘነ ፡፡
2-ሳሙኤል (4፡ 1-12)፡ ከአበኔር ሞት በኋላ ኢያቡስቴ ድፍረቱን አጣ እስራኤልም ሁሉ ደነገጡ (ቁጥር 1) ፤ አሁንም የሳዖል ልጅ በራስ ፍላጎት (ጉጉት) ተይዞ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ ለሳዖል ልጅ ይሰሩ የነበሩ ሁለት ሰዎች እንቅ ልፍ እንደ ወሰደው በራሱ ቤት ኢያቡስቴን ገደሉት (ቁጥር 5-7) ፤ ሰዎቹም የኢያቡስቴን ራስ በመቁረጥ ለዳዊት ወሰዱለት (ቁጥር 8) ፤ ዳዊት ገድለዉ የነበሩትን እነዚህን ሰዎች በኬብሮን ዉሃ መቆሚያ አጠገብ ለሁሉም እንዲታይ ሰዉነታቸዉን ሰቀለው ፡፡ የኢያቡስቴም ራስም በአቤኔር መቃብር ተቀበረ (ቁጥር 9-12) ፡፡
መደምደሚያ
የሚነሳዉ ጥያቄ ዳዊት ለምን እነዚህን ሰዎችን ገድሎ ኢዮአብን እንዲሄድ ፈቀደለት የሚለው ነው ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሰለሞን ቆይቶ ከኢዮአብ ጋር ይነጋገራል ፤ በዳዊት ታሪክ ዉስጥ ኢዮአብ ትልቅ ሚና ተጫዉቷል በመንገዱ ላይ የራስ ወዳድነት ጉጉት አገኘዉ ኑሮን በመዉሰዱም በአቤኔር አልቆመም ፡፡ ኢዮአብ ዳዊት አድርጎበት በነበረዉ ተመሳሳይ ልብ አልሄደም ፤ ዳዊት እንደ (በራሱ በእግዚአብሄር) እግዚአብሄር ልብ ተጓዘ ፡፡
ለእኛ ይህ ምን ማለት ነው ? በጥሪዓችን ስንጓዝ ከጥሪዓችን አስወጥተዉ ከሚመሩን ሰዎች ጋር ስንገጥም ልንጠነቀቅ ይገባናል ፡፡ እግዚአብሄር ጥበብን ሰጥቶናል ነገር ግን ኢዮዐብ እንደ ነበረበት በተሳሳተ ጥበብ ቁመና ከሆንን ያ ጥበብ አያድነንም ፡፡ በሰላም እና በእዉነት እንደ እግዚአብሄር እንደ ሚመልሰዉ ልክ እንደ ዳዊት ልብ አለን ፤ የእግዚአብሄር ልብ በነበረዉ በአንዱ የተመሰረተዉን ዘላለማዊዉን የእግዚአብሄርን ዙፋን እያየን ነው ፡፡
ጥያቄዎች
-
በ 2ሳሙ (3፡ 11) ኢያቡስቴ አበኔርን ሊመልስለት አልቻለም ምክንያቱም ስለ ፈራው ፤ ኢያቡስቴ የሚፈራው በምን ምክንያት ነበር ?
-
በ 2ሳሙ (3፡ 9-10) አበኔር እግዚአብሄር መንግስቱን ለዳዊት እንደሚሰጠዉ ምሎለት እንደ ነበር እንዴት አወቀ ? እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር እንደ ነበር (1ሳሙ 15፡ 28፣ 18፡ 14፣ 28) እንዲሁም ደግሞ ዳዊት የሳዖልን ነፍስ ሁለት ጊዜ እንዳዳነ (1ሳሙ 24፣ 26) ስላስተዋለ ነበር ?
-
በ 2ሳሙ (4፡ 4) የዮናታን አንካሳ ልጅ ለምን ተጠቀሰ በዚህ ምዕራፍስ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው ? (2 ሳሙ 9፡ 3)
-
በ 2ሳሙኤል (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Samuel 4:11
“How much more when wicked men kill a righteous man in his own house on his own bed! So now, should I not require his blood from your hands and wipe you off the earth?”
ኢዮአብ አቤኔርን ገደለው እንደገናም ሬካብና በዓና ኢያቡስቴን ገደሉት ፡፡ ሰዎቹ በመሞታቸውና ከእንግድህ ለንጉሱ ስጋት ስላልሆኑ ያመሰግናቸው ዘንድ እነዚህ ሶስቱ ወደ ዳዊት ቀረቡ ፤ ዳዊት ግን ተቃራኒ ምላሽ ነበረው አላመሰገናቸውም ይልቁንም የንፁሀን ደም ስለ ፈሰሰ አዘነ እንጂ ፡፡ ዳዊት ፍለጎታቸውን ስለተረዳ ኢዮአብን ረገመ ሬካብና በዓናም እንድገደሉ አዘዘ ፡፡
መግደልን ለምን መረጡ ? ዳዊት እነዚህ ሰዎች ቀድሞ በተደረገ ነገር ልባቸው መጎዳቱን አወቀ ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔር ልባቸውን ይፈውስ ዘንድ አልፈለጉም ከዳዊትም ምክርን አልሻቱም ነበር ፡፡
ምናልባት በተሳሳተ መንገድ ካንተ ጋር የሚጋጩ በተጨማሪም ስሜትህን የሚጎዱ ሰዎች ልታገኝ ትችላለህ ፡፡ አንድ ሰው ቢጎዳህ የተጎዳው ልብህ እንድያኮርፍ እንድያቄም አትፍቀድለት ፡፡ ወድቀህ በሰውነትህ ላይ አካለዊ ጉዳት ቢያጋጥምህ ኖሮ ልታጸዳው ልታክመው ትፈቅድ ነበር በተጨማሪም ኢንፌክሽን አለመፍጠሩንና እየሰፋ አለመሄዱን ታረጋግጥ ነበር ፡፡ ሌሎችም ልብህን በጎዱት ጊዜ እውነቱ ተመሳሳይ ነው ፡፡ የተጎዳ ልብ ካልታከመ እንደ ኢንፌክሽን ቅንዓትና መራራነት ይከማችበታል፡፡ በኢዮአብ በሬካብና በበዓና ጊዜ የሆነው ይህ ነበር ነገር የያዘው ያቄመው ልባቸው ግድያን እንድፈጽሙ አድርጓቸዋል ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ህመምህን መፈወስ ይችላል በየትኛውም ሁኔታ ውስጥም ደግሞ ተስፋን ሊሰጥህ እንድሁ ፡፡
“ ይለቁንስ በቤቱ ውስጥ በምንጣፉ ላይ ንጹሑን ሰው የገደላችሁትን እናንተን ኃጢአተኞችንማ እንዴት ነዋ ? ደሙን ከእጃችሁ አልሻውምን ? ከምድርም አላጠፋችሁምን ? “
- 2ኛ ሳሙኤል 4፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ዜና 7፡14-15 –“ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ በሰማይ ሁኜ እሰማለሁ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ፡፡ “
ኤርምያስ 33፡6 –“ እነሆ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ እፈውሳቸውማለሁ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ ፡፡ “
ያዕቆብ 3፡14-16 –“ ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ ፡፡ ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም ነገር ግን የምድር ነው የስጋም ነው የአጋንንትም ነው ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።