Historical Books 2 Samuel

David's Second Anointing

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Throne 2 Samuel 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 243 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በ 2 ሳሙኤል የመጀመሪያዉ ክፍላችን ነው ከ 1ሳሙኤል እንደ ሚቀጥል ታሪክ መጠቅለል እንደ ምንችለዉ ይሰማል ፤ እዉነታው 1 እና 2 ሳሙኤል መጀመሪያ ላይ እንደ አንድ መፅኀፍ የተፃ ነበር ፡፡ ነገር ግን ለየብቻቸዉ ስንመለከት ይህን እንደ ተለያየ መፅሀፍ ሁለቱም የ 1 ሳሙኤል ቀጥሎ የመጣ አድርገን ልናየዉ ያስፈልገናል ፤ የ 2 ሳሙኤል ፀሀፊ ሳሙኤል እንደ ነበር ይታመናል ነገር ግን ምናልባት በሰዎስት በተለያ ሰዎች (ሳሙኤል፣ ናታን እና ጋድ) ተፅፎ ከሳሙኤል በኃላ የተሰየመ ነበር (1ዜና 29፡ 29) ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀዶሞ ሳሙኤል ሞቶ ነበር ፤ ሁለቱም የሳሙኤል መፅሀፍ የ 135 አመት ጊዜን ይሸፍናል 2 ሳሙኤል 35 አመት ጊዜን ያክል ይሸፍናል ፡፡ ጎርደር ቫን ፖል የ 1ሳሙኤልን መፅሀፍ እንደ አንድ ሽግግር ይገልፃል፡ “ በሙሴ ስር ከተመሰረተው ቲዎሪይ በንጉስ ሳዖል ወደ ተጀመረው ንጉሳዊ አገዛዝ ያለዉን ለዉጥ ያስቀምጣል ፤ በተጨማሪም መፅሀፉ በእስራኤል የእግዚአብሄር ሀሳብ እንደ ሆነዉ ማዕከላዊ እቅድ ከካህናት ወደ ነቢያት ሽግግርን ያሳያል “ ፡፡ ሜንዲ በአንድ ሙሉ ስዕል ለእነዚህ ሁለት መፅሀፍት ሁለት ስዕሎችን አጣምራለች (በአርት የመፅሀስ ሽፋን ተብሎ የሚጠራ ነው) ፡፡ ለ 1ሳሙኤል ቃሉ የተቀባ ነበር ፤ ለ 2ሳሙኤል ቃሉ ዘላለማዊ ዙፋን ነው ፡፡

በ 1ሳሙኤል ሀና ሳሙኤልን እንደ ምትወልድ ተነግሯት ነበር ፤ “ ለንጉስም ኃይል ይሰጣል ፤ የመሲሁንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል “ (1ሳሙ 2፡ 10) ፤ በ 2ሳሙኤል በዚህ መፅሀፍ ዉስጥ ስንሄድ የምታዩዓቸው አራት ጭብጦች(ፍሬ ነገሮች) አሉ፡

  1. የዳዊት ኪዳን እና የሚመጣዉ ንጉስ (2 ሳሙ 7፡ 11-13፣ 16)፡ የተቀባው (ዳዊት) በትክክል ወደ ኢየሱስ ዘላለማዊዉ ዙፋን ይጓዛል ፤ ዙፋን ከዳዊት እንደ ሚመጣ እና መጨረሻ እንደ ሌለዉ የሚያወራዉን ሉቃ (1፡ 30-31) መመልከት ነው ፡፡ ይህን የተገለጠዉን ለማየት እዚህ እንጀማራለን ፡፡

ኢየሩሳሌም (2 ሳሙኤል 5)፡ዳዊት ከተማዋን በመያዝ ዋና ከተማ አደረጋት ፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ኢየሩሳሌም በመጥቀስ ያለን ብቸኛዉ መነሻ ኢያቡሳዊያን ገና ድል ባልተደረጉ ጊዜ በዘፍጥረት 14 እና መሳፍንት (1፡ 8) ላይ የሚገኙ ናቸው (መዝ 48፡ 1-2) ፡፡ በዚህ ጊዜ ኢየሩሳሌም እንደ ዳዊት ከተማ የምትታወቅ ነበረች ፡፡

የዳዊት ኃጢዓት እና ዉጤቱ (2ሳሙኤል 11-18)

የወደፊቱ ተስፋ ( 2ሳሙ 23፡ 5)፡

ትምህርት

2 -ሳሙኤል (1፡ 1-10)፡ አማሌቃዊያንን ካሸነፈ በኋላ ዳዊት ጺቅላግ በመመለስ በዚያ ተቀመጠ (ቁጥር 1) ፡፡ በጺቅላግ በሰዎስተኛዉ ቀን ከሳዖል ሰፍር የነበር አንድ ሰዉ ወደ ዳዊት በመምጣት አክብሮት ሰጠው (ቁጥርሰ 2) ፤ ሰዉዬው ዳዊትን ለማየት ከጊልቦ ተራራ ወደ ጺቅላግ 90 ማይል ተጎዙ የነበር ብቻዉን መዳን ችሎ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ ዳዊት ስለ ጦርነቱ ዉጤት ጠየቀው ሰዉየውም አብዛኞቹ ወታደሮች እንዲሁም ዮናታንና ሳዖልም እንደ ሞቱ ነገረው (ቁጥር 4) ፤ ዳዊት ሰዉዬዉ እንዴት ይህን መረጃ እንዳወቀ ጠየቀው (ቁጥር 5) ፤ ሰዉዬዉ ስለ ሳዖል ሞት የዓይን ምስክር ነበር ፡፡ የፍልስጤማዊያን ቀስተኞች እና ፈረሰኞች ሲቀርቡት (ቁጥር 6-8) ሳዖል በራሱ ጦር ላይ በማዘንበል ከልቡ በመቁሰሉ ላይ ቢሆንም “ አሁንም በህይወት ስላለ “ ማለትም ሳዖል ጣረ ሞት ላይ ስለ ነበር ሳዖል እንዲገድለዉ ጠይቆት እንደ ነበር ነገረው (ቁጥር 9) ፡፡ ሰዉዬው ሳኦልን በመግደል ዘዉዱን እና የክንዱንም ቢተዋ (የሳዖልን ንጉሳዊ አልባሳትን) ወደ ዳዊት ይዞ እንደ መጣ ዳዊትን ነገረው (ቁጥር 10) ፡፡

የሰዉዬዉ መግለጫ በ 1ሳሙኤል ከተመዘገበዉ የሳዖል አሟሟት ጋር የሚፃረር ይመስላል ፤ በ 1ሳሙ (31፡ 1-3) የፍልስጤም ቀስተኞች በኃይል ሳዖልን አቆሰሉት፣ በቁጥር 4-6 የሳዖል ጋሻ አጃግሬ ሳዖልን ለመግደል እምቢ አለዉ ሳዖልም በራሱ ሰይፍ ላይ ወደቀ ፡፡ አማሌቃዊዉ ሰዉዬ ሳዖል በራሱ ጦር ላይ እንዳዘነበለ መናገሩን አስታዉሉ ስለዚህ ሊሆን የሚችለው - ይህ አማሌቃዊዉ ሰዉዬ በሳዖል ላይ ጋሻ አጃግሬዉ ለማድረግ እምቢ ያለዉን በሚያደርግበት በተክክለኛዉ ጊዜ የመጣበት መንጠልጠል ነው ፤ ይህ ከአማሌቃዊያን የተለያየ አመለካከትን ያሳያል ፡፡

2-ሳሙኤል (1፡ 11-16)፡ ዳዊት በኃዘን ልብሱን ቀደደ ሰዎቹም ተመሳሳይ ነገር አደረጉ (ቁጥር 11) ፤ ለሳዖል እና ለዮናታን ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ ሞተዉ ለነበሩት እስራኤላዊያን ሁሉ ቀኑን ሙሉ አለቀሱ ፆሙም (ቁጥር 12) ፡፡ ይህ ለእኔ በዳዊት አካል የአንድነት ምልክንት ይመስላል ፡፡ ዳዊት ሳዖልን ለመግደል ሰዎስት እድሎች ነበሩት … አንድኛዉንም አልወሰደውም ፤ የተቀባ ንጉስ እንደ ነበር ያውቃል ነገር ግን ዙፋኑን ለመቀበል የራሱን ጊዜ ጠበቀ ፤ በሀቀኝነት ተጓዘ ፡፡ ዳዊት ሰዉዬውን ከየት እንደ ነበር ጠየቀዉ ከአማሌቅም እንደ ነበር ሰማ (ቁጥር 13) ፤ በቁጥር 14 ዳዊትም “ እግዚአብሄር የቀባዉን ለመግደል እጅህን ስትዘረጋ ለምን አልፈራህም ? “ አለው ፡፡ ዳዊት የመጨረሻዉን ሞት ለመስጠት ማንኛዉም እግዚአብሄር በቀባዉ በእስራኤል የመጀመሪያዉ ንጉስ ላይ እጁን እንዴት ሊያነሳ እንደ ቻለ ሊገባዉ አልቻለም ፤ ዳዊት አማሌቃዊዉን እንዲገድለዉ አንዱን አገልጋይ ጠራው (ቁጥር 15) ምክንያቱም ደሙ በእርሱ ራስ ላይ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡ ዳዊት የሳዖልን ዘርፍ በመንካቱ ጥፋተኛ ነበር ስለዚህ የዳዊት ድርጊቶች በአማሌቃዊዉ ላይ የማያሳምኑ ነበሩ ፡፡

2-ሳሙኤል (1፡ 17-27)፡ ዳዊት ለሳዖል እና ለዮናታን የሀዘን እንጉርጉሮ አዜመ በሁሉም ይሁዳ የሀዘን ለቅሶ እንጉርጉሮዉን እንዲማሩ አዘዘ (ቁጥር 17-18) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ እንጉርጉሮዉን “ በጣም ዜማዊ፣ በኃይል ግላዊ እና ስሜት ቀስቃሽ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ እንጉርጉሮዉ በንጉሱ ሞት ሀገራዊ ሀዘንን ይወክላል ፤ በእስራኤል ያሉት ንጉሳቸው የተመረጠ እንደ ነበር እና በእግዚአብሄር እንደ ተቀባ አውቀዋል እግዚአብሄርም በእነርሱ ላይ በረከቱን አፍስሷል ፡፡ የዳዊት እንጉርጉሮ በሰዎስት ስንኞች የተፃፈ ነው ፡፡

የመጀመሪያው ስንኝ (ቁጥር 19-24) ሳዖልን እና ዮናትንን ይታይ እንደ ነበር የእስራኤል ድምቀት ገልጧቸዋል ፤ ዳዊት ከእስራኤል ዉጪ ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር መረጃዉን መጋራት አልፈለገም ምክንያቱም በሳዖል ሞት ደስተኛ እንዲሆኑ ስላልፈለገ ፤ እንዲሁም በመካከላቸው በላዉ ችግር እያለም እንኳን ዳዊት፣ ሳዖል እና ዮናታን እርስ በእርሳቸዉ ስለሚዋደዱ እና ስለ ማይለያዩ ፡፡

ሁለተኛው ስንኝ (ቁጥር 25-26) ለወንድሙና ለጓደኛዉ ለዮናታን ወደ ዳዊት ፍቅር የዞረ ነው ፡፡ ሰዎስተኛዉ ስንኝ (ቁጥር 27) የቁጥር 19 እና 25 በመድገም ይጨርሳል፡ “ ኃያላንም በሰልፍ እንዴት ወደቁ ! “

2-ሳሙኤል (2፡ 1-4)፡ እነዚህ አራት ጥቅሶች በመጨረሻም የዳዊት ጊዜ መጥቶ እንደ ነበር ያመለክታሉ ፡፡ ዳዊት ቀጣይ ምን እንደ ሚያደርግ ለማወቅ እግዚአብሄር ን ተመለከተ ፤ እግዚአብሄርን ወደ ኬርያት አርብ ወይም “ የአራት ከተሞች “ ለመሄድ ጠየቀ ፤ ይህ በአካባቢው ትንሽ ከተሞችን አጧቅሷል ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊትን ኬብሮን እንዲሄድ ነገረው (ቁጥር 1) ፤ ኬብሮን እግዚአብሄር በፓትሪያሪኮች መካከል የተንቀሳቀሰባት ቁልፍ ከተማ ነበረች ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ 20 ማይል ላይ ትገኝ ነበር ፡፡ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ከአኪናሆምና ከአቢግያ ጋር ሄደ (ቁጥር 2) ፤ በተጨማሪም ዳዊት በኬብሮን ከተሞች አጠገብ ኖሩትን ሰዎቹን እና ቤተሰባቸዉን አመጣ (ቁጥር 3) ፡፡ በዚያ የይሁዳ ሰዎች መጥተዉ ዳዊት እንደ ይሁዳ ንጉስ ቀቡት - ሁለተኛ ጊዜ ዳዊት እንደ ንጉስ ተቀባ ፤ የመጀመሪያዉ ጊዜ ዳዊት ተቀብቶ የነበረዉ በሳሙኤል ነበር ( 1 ሳሙ 16፡ 13) ፡፡ ሁሉም እስራኤላዊያን የቅባቱ አካል በሚሆኑ ጊዜ ቆይቶም ሰዎስተኛ ጊዜ ይቀባል ( 2 ሳሙ 5፡ 3) ፡፡ የእስራኤልን የመጀመሪያ ንጉስ ሳዖልን ካከበረ በኋላ የዳዊት ቅባት እንደ ይሁዳ ንጉስ መጣ ፡፡

መደምደሚያ

በእግዚአብሄር መጠበቅ ምን ማለት እንደ ሆነ ዳዊት ያውቃል ፤ መዝ (37፡ 34) “ እግዚአብሄርን ደጅ ጥና መንገዱንም ጠብቅ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሀል ፤ ኃጢዓተኞችም ሲጠፉ ታያለህ “ ይላል ፤ ይህ የዳዊትን ህይወት ገልፃል ፡፡ በእግዚአብሄር በመታመን የእግዚአብሄርን ጊዜ ጠበቅ እንጂ የሰዉን አይደለም ሁሉም አልተደበቀም ፤ መዝ (21፡ 7) “ ንጉስ በእግዚአብሄር ተማምኖአልና በልዑልም ምህረት አይናወጥም “ ፤ ይህ የዳዊት ተግዳሮት ነበር ፡፡ በእግዚአብሄርን በምትጠብቁ ጊዜ አትናወጡም ፡፡ የዳዊት ዘላለማዊ ዙፋን አይናወጥም ፡፡

  1. Paul R. Van Gorder, The Old Testament Presents . . . Reflections of Christ; available at http://www.thebookwurm.com/ref-1sam.htm.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 388.

  3. Nelson’s Commentary, p. 389.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ሳሙኤል 1 የሳዖልን ሞት ሮፖርት ባደረገዉ ሰዉ ላይ ችግሩ ምን ነበር ? (1ሳሙ 31፡ 1-6፣ 1ዜና 10፡ 14)
  2. መልዕክተኛዉ አማሌቃዊ እንደ ሆነ ተናገረ ፤ እስራኤላዊያን በአማሌቃዊያን ላይ እንዲያደርጉ እግዚአብሄር ምን አዝዟቸዉ ነበር (ዘዳ 25፡ 17-19) ? ዳዊት በገደለዉ ጊዜ ሳዖል ለማድረግ ወድቆበት የነበረዉን በማድረግ እግዚአብሄር አዝዞት ለነበረው ታዛዥ ነበር ? ( 1ሳሙ 15፡ 8-9)
  3. በሀዘኑ እንጉርጎሮ ላይ አፅዕኖቱ(ዋናዉ አላማው) ምን ነበር ? በዚህ ዜማ ህዝቡ ምን እንዲያደርጉ ዳዊት ነገራቸው ?
  4. ከሳዖል ሞት በኋላ ዳዊት የት ነበር እየኖረ የነበረው ? 2ሳሙኤል መጀመሪያ ላይ ዳዊት በእግዚአብሄር ያለዉን እምነት እንዴት ነበር ያሳይ የነበረው ? ስለ ህይወታችሁ የጠለቀ ዝርዝር ያለማቋረጥ እግዚአብሄርን ትጠይቁታላችሁ ?
  5. በመጨረሻ ህዝቡ ዳዊት የይሁዳ ንጉስ አድርገዉ የት ቀቡት ? በዚያ(በተመሳሳይ)ኑ ጊዜ ንጉስ የተደረገዉ ማን ነበር ? ይህ ለእግዚአብሄር የታሰበ አለመታዘዝ ነበር ?
  6. በ 2ሳሙኤል (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Samuel 2:7

“Therefore, be strong and courageous, for though Saul your lord is dead, the house of Judah has anointed me king over them.”

ስለ ሳዖል ሞት ካለቀሰ ከፆመና ካዘነ እንድሁም ስለ ክብሩ የሀዘን ቅኔን ከተቀኘ የአይሁድ ልጆችንም ቅኔውን ካስተማረ በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር እንደተናገረው ወደ ኬብሮን ሄደ ፡፡ በኬብሮንም የይሁዳ ሰዎች መጥተው ዳዊትን በይሁዳ ቤት ላይ ብቻ ይነግስ ዘንድ ቀቡት ፡፡ ዳዊት እግዚብሔር የተናገረው በመላው እስራኤል ላይ ንጉስ እንደሚሆን መሆኑን ቢያውቅም እንኳ ዳዊት ሳኦልን በማክበር በትህትና እንድሁም ንግስናው በእግዚአብሔርን ጊዜ እንደሚፈጸም በማመን ጠበቀ ፡፡

መጠበቅ ….. ማንም ለምንም ነገር መጠበቅ አይፈልግም ፡፡ ሆኖም ግን ሁሉም ነገር ጊዜ አለው ፡፡ ሁሉም ጊዜ ምክንያት አለው ፡፡ እግዚአብሔር የመጠበቅን ጊዜያት አያባክናቸውም ፡፡ ማደግ የሚሆነው ስትጠብቅ ነው ፡፡ አንተ ማግኘት ወይም ቶሎ መርካትን ትፈልግ ይሆናል ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር መንገድ ቀስ ያለና ጊዜን የሚወስድ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር አሳብ በራሱ መንገድና ጊዜ ይሆን ዘንድ ፍቀድ ፡፡ በቶሎ እንድሆነልህ ሂደቱን ውደደው ደግሞም የተስፋውን ቃለ እመን ፡፡

“ አሁንም ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና እጃችሁ ትጽና እናንተም ጨክኑ ዳግም የይሁዳ ቤት በእነርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብተውኛል ፡፡ “

- 2ኛ ሳሙኤል 2፡7

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 20(21)፡7 –“ ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና በልዑልም ምህረት አይናወጥም ፡፡ “

መዝሙር 26(27) ፡14 –“ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፡፡

መዝሙር 36(37) ፡34 –“ እግዚአብሔርን ደጅ ጥና መንገዱንም ጠብቅ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሀል ኃጢአተኞችም ሲጠፉ ታያለህ ፡፡ “