The Shift in David's Leadership
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በትናትናዉ ጥናታችን (1 ሳሙኤል) ሳዖል ሳሙኤልን ከሞት የሚጠራ አንድ መናፍስት ጠሪ ነበረው እናም ሳሙኤል በቀጣዩ ቀን እርሱ እና ልጆቹ እንደ ሚሞቱ ሳዖልን መጥፎ ዜናዉን ለመስጠት(ለመናገር) ተነሳ ፤ ከዚያም ሳዖል መንግስቱ ከእርሱ ተወስዶ ወደ ዳዊት እንደ ተወሰደ አወቀ ፡፡ እስከዛዉ ድረስ ግን ዳዊት በፍልስጤም ምድር በመሆኑ ወደ ምድሪቱ ተጠርተዉ ከነበሩት ህዝቦች ከእስራኤል ጋር ከእነርሱ ጋር በመሆን የሚዋጋ እንዲሆን ስለጠበቁ ፤ በምዕራፍ 29 የፍልስጤም አዛዦች ዳዊት እና ሰዎቹ የጦራቸዉ አካል በመሆን እያደረጉ ስለነበረው መጠየቅ ጀመሩ ፤ እነዚህ አዛዦች ዳዊትን እና የእርሱን ሰዎች የተሰረዙ እንዲሆኑ ፈለጉ በዚህም አቅጣጫቸዉን አይቀይሩም በጦርነቱም ጊዜ ጠላቶቻቸዉ አይሆኑም (ቁጥር 1-5) ፡፡ ንጉስ አንኩስ የአዛዦቹን ማስጠንቀቂያ በማክበር ዳዊትን እና የእርሱን ሰዎች በማሰናበት ዳዊትን እና ሰዎቹን ወደ ቤት መለሳቸዉ ዳዊትም ላለመታመን ምን አድርጎ እንደ ነበር ጠየቀ (ቁጥር 6-8) ፡፡ አንኩስ ዳዊትን እንደ እግዚአብሄር መልዓክ አዉቅሀለሁ አለዉ ነገር ግን እርሱና የእርሱ ሰዎች ይመለሳሉ (ቁጥር 9-11) ፤ ይህ 1 ሳሙኤል 30 የምንጀምርበት ነው ፡፡
ትምህርት
1-ሳሙኤል (30፡ 1-4)፡ ዳዊት እና የእርሱ ሰዎች ተመልሰዉ በጺቅላግ እንደ ደረሱ አሜሌቃዊያን ከተማዋን አቃጥለዋት እና በዉስጧ የቀሩትን ሁሉንም አግተዋቸዉ አገኙ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ዳዊት እና የእርሱ ሰዎች ሁሉም የቤተሰብ አባሎቻቸው በመታገታቸው እምባቸዉ እስኪደርቅ ድረስ አለቀሱ (ቁጥር 3-4) ፤ ዳዊት እና የእርሱ ሰዎች ከተማቸዉ ተመሰቃቅላ ከማግኘታቸዉ በፊት በፍልስጤማዊያን በመሰናበታቸዉ የተበሳጩ ሆነዋል ፤ ማጣታቸዉ ከአቅም በላይ ስለ ነበር ማልቀስ ለመቀጠል አቅም አልቀረላቸዉም ነበር ፤ ይህ ሀዘን ከሰዉነት ማስወጣት እንደ ሚችል ማሳሰቢያ(ማስታወሻ) ነው ፡፡
1-ሳሙኤል (30፡ 5-6)፡ የዳዊት ሚስቶችም የተወሰዱ ቢሆንም ወታደሮቹ እርሱን ስለ መዉገር አወሩ ምክንያቱም ወንዶች እና ሴቶች ልጆቹ ተወስደዉ ስለ ነበር (ቁጥር 5-6) ፡፡ ዳዊት ወታደሮቹ በመመለሳቸዉ ኃይለቃ ጉዳት ዉስጥ ነበር ፤ ወታደሮቹም ለማዘን አቅም ስላልነበራቸዉ ምሬታቸዉ ዳዊትን ወግረዉ እንዲገድሉት አቅም ሰጣቸው ፤ “ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሄር ልቡን አበረታ (ቁጥር 6) ፡፡
1-ሳሙኤል (30፡ 7-8)፡ በዚህ ክስተት ዳዊት ወደ እግዚአብሄር በመዞር ወደፊቱን ለእርሱ ሰዎች እና ለመንግስቱ አዞረው ፡፡ ዳዊት ካህኑን አብያታርን ኤፉዱን እንዲሰጠው ጠየቀው ፤ ዳዊት ኤፉዱን በማጥለቅ በግልፅ በፀሎት እና በአምልኮ ልብሶቹን ራሱ ለበሳቸው ፤ ዳዊት ጺቅላግን በዘረፉት ላይ ምን ማድረግ እንደ ሚገባዉ እግዚአብሄርን ለመጠየቅ ልብሶቹን ተጠቀመባቸው ፡፡ እግዚአብሄር ዘራፊዎቹን በመከተል ሰዎቹን እንዲያስመልስ ነገረው (ቁጥር 7-8) ፤ እግዚአብሄር እኛን ድለኞች (ድል አድራጊዋች) እንድንሆን ፈጥሮናል ነገር ግን ጠላት ለተሳሳተ ነገር ሊያነሳሳን(ሊያጠነክረን) ነገሮችን የመረሩ በማስመሰል ሊጠቀም ይችላል ፡፡ ዳዊት በልቡ ካለዉ ህመም ይልቅ እግዚአብሄርን ተመለከተ ፡፡
የተቀባው ዳዊት ሰዎቹን ወደ ቤተሰባቸዉ መልሶ በማምጣት ለቅሶን እና ምሬትን ወደ ማቆም ተጓዘ (ተራመደ) ፤ ዳዊትም የተበሳጨ ነበር ምክንያቱም ሚስቶቹ ተወስደዉ ስለ ነበር ፡፡ ዳዊት ጥቃት አድራሾቹን በመድረስ ቤተሰቦችን እንዲታደግ እና መልሶ እንዲያመጣ የላከዉን እግዚአብሄርን ተከታተለ ፡፡
በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ የተቀባዉን ኢየሱስን የት ላይ ልናየው እንችላለን ? አይሁዶች ቀምሰዉት በነበረዉ ምርኮ በግብጢያን፣ በሶሪያዊያን፣ በባቢሎናዊያን እና በሮማዊያን ለረጅም አመታት በምሬት አልቅሰዋል በዚህም ምክንያት ሊታደጋቸዉ እና መልሶ የሚያቆማቸዉ አክል ተመለከቱ ፤ ኢየሱስ በዚያ ሁኔታ በመግባት ከአባቱ ተቀብሏቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ለመድረስ፣ ለመታደግ እና መልሶ ለማግኘት ሲሞክር አለቀሰ ፡፡ ኢየሱስቤተ ክርስቲያንን እንደ ሙሽራ ይመለከታል ስለ እርሷም ያለቅሳል ፡፡ አይሁዶች በረጅም ምርኮ ጊዜ ተስፋ ቢስ ሆነዉ ነበር ፤ ተስፋ ማጣት የሰዎችን ተስፋ፣ ህልም፣ የመንቀሳቀስ አቅምን መስበር ይችላል ፤ ኢየሱስን የደም ላብ ባላበበት በደብረ ዘይት ተራራ ተመልከቱ አብን “ ይህን ፅዋ ከእኔ ዉሰድ ? የሚወሰድበት ሌላ መንገድ አለን ? “ ብሎ ጠየቀ ይሁን እንጂ በዚያ ክስተት ኢየሱስ እግዚአብሄርን እየተከተለ ነው ፡፡
1-ሳሙኤል (30፡ 9-15)፡ ዳዊት ከ 600 ሰዎቹ ጋር ሄደ ነገር ግን 200ዎቹ በእነርሱ ላይ በሆነዉ ትልቅ ስሜት የተነሳ በጣም ደክመዉ ስለ ነበር በሶር ላይ ቀሩ (ቁጥር 9-10) ፡፡ ሳዖል ዙፋኑን አጥቶ የነበረበትን ምክንያት አስታዉሱ እግዚአብሄርን ባለመታዘዙ አማሌቃዊያንን አለማጥፋቱ እንደ ነበር ፤ ዳዊት በሰዓቱ በዚያ ከማይሆን ከዚህ ቡድን ጋር እየተነጋገረ ነበር ፡፡ ሲዘምቱ በሰዎስት ቀን ዉስጥ ምግብ ባለመብላቱ በሜዳ ላይ መሞት ብቻ ቀርቶት የነበረዉን አንድ ግብፃዊ አገኙ ፤ የዳዊት ጦር ህይወት መዝራቱ ከምግብ የነበረዉን ግብፃዊዉን መገቡት (ቁጥር 11-12) ፡፡ ዳዊት ግብፃዊዉ አሜሌቃዊያን ጺቅላግን ባቀጠሉ ጊዜ ከእነርሱ ጋር በመሆን የአሜሌቃዊያን አገልጋይ እንደ ነበር ሰማ (ቁጥር 13-14) ፤ ዳዊትም ጎልማሳዉን ሰዉዬ ወደ አማሌቃዊያን እንዲመራቸዉ ጠየቀው ሰዉዬዉም ላይገድሉት ቃል የሚገቡለት ከሆነ ተስማማ (ቁጥር 15) ፡፡
1-ሳሙኤል (30፡ 16-19)፡ ጎልማሳዉ ሰዉዬ ከፍልስጤም እና ከይሁዳ ምድር ንብረቶቹን በመዝረፍቸዉ በዳንስ እና በመጠጠ ወደ ሚያከብሩት አማሌቃዊያን ጋር ወሰዳቸው ፤ ዳዊት “ ከማታ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ቀን ምሽት ድረስ “ በመምታት ሁሉንም ገደላቸዉ ነገር ግን በግመል ላይ የነበሩ 400 ሰዎች ማምለጥ ቻሉ (ቁጥር 16-17) ፡፡
“ ከማታ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ምሽት ድረስ “ የሚለዉ ሀረግ መልሶ ወደ ክርስቶስ ትኩረት ይሰጣል፡
ከማታ ጀምሮ - የመጨረሻዉ እራት እና የኢየሱስ ተላልፎ መሰጠት በይሁዳ
እስከ - በመስቀሉ ላይ ቆይታዉ
የቀጣዩ ቀን ምሽት - በመስቀል ላይ ሞቱን ፡፡
የተቀባዊ ዳዊት ሁሉንም ቤተሰቦቹን መልሶ አገኛቸዉ ታደጋቸዉም ይህ የክርስቶስ ጥላ ነው (ቁጥር 18) ፡፡ ቁጥር 19 የሚለው “ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ከወሰዱትም ምርኮ ሁሉ ታላቅም ሆነ ታናሽም ሆነ ምንም የጎደለባቸዉ የለም ፤ ዳዊትም ሁሉን አስጣለ “ ፤ ይህ በመስቀለል ላይ ያለቀዉ ስራ ማስታወሻ ነው ፡፡ በጠላት ስልጣን የቀረ ምንም ነገር አልነበረም (ቁጥር 20) ፡፡ ኢየሱስ ሁሉን ነገር አስመለሰ ኃዘንንም እንኳን አስወገደው ፡፡
1-ሳሙኤል (30፡ 21-31)፡ በተመለሱም ጊዜ በቦሰር የነበሩት 200ዎቹ ዳዊትን እና ከእነርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገናኘት ወጡ ፤ ዳዊትም በመቅረብ ሰላም አላቸው (ቁጥር 21) ፡፡ ከ 400 ሰዎቹ ዉስጥ ክፉዎቹ እና ምናምንቴዎቹ ከኃላ ቀርተዉ የነበሩትን 200 ሰዎች ካስጣሉት ምርኮ ከሚስቶቻቸዉ እና ከልጆቻቸዉ ዉጪ እንዲቀበሉ አልፈለጉም (ቁጥር 22) ፤ በምሬት እና በብስጭት የተሞሉ ክፉዎች ስለራሳቸዉ ብቻ ማድረግ በሚችሉት የሚናገሩ የግላቸዉን አስተያየት የሚሰጡ ነበሩ ፡፡ ዳዊት ድሉ ከእግዚአብሄር የመጣ እንጂ ከሰዉ ድርጊት እንዳልሆነ መለሰ ስለዚህ ሁሉም ይካፈላሉ ( ቁጥር 23-24) ፤ በተጨማሪም ዳዊት ከኃላ ቀርተዉ የነበሩት ተልዕኮዉን እንደ ፈፀሙ እዉቅና ሰጠ - የጦሩን አቅርቦት ሲጠብቁ ስለ ነበር ፡፡ ዳዊት ይህን መረዳት ከየት አገኘው ? በእግዚአብሄር ራሱን በማበርታት ፤ በዳዊት መሪነት ይህ አስፈላጊ ክስተት ነበር - የእግዚአብሄርን ልብ በማየት ህዝቡን በጦርነት ሳይሆን በፀሎት በጌታ ድል መራ ፡፡ በወይን ስፍራ ስላሉት ሰራተኞች ኢየሱስ በዚህ አሳብ ላይ አስተምሯል (ማቴ 20፡ 1-6) ፤ ቁጥር 25 ሁሉም ተመሳሳይ መጠን ይቀበላሉ የሚለዉ ፍልስፍና ለእስራኤል ትዕዛዝ እንደ ሆነ ይናገራል ፡፡ ዳዊት ሌሎችን እንዴት ማየት እንዳለባቸው የእግዚአብሄርን ልብ በሚያሳይ ትዉልድ አይነት ወደ እስራኤል እየተጓዘ ነበር (ቁጥር 25) ፤ ከዚያም ዳዊት ምርኮዉን ከይሁዳ ሽማግሎዎች ጋር እና በእስራኤል ካሉ ሌሎች ነገዶች ጋር ማካፈል ጀመረ (ቁጥር 26-31) ፡፡
መደምደሚያ
በምዕራፍ 30 ዳዊት ጦርነትን በሚዋጋበት በተመሳሳይ ጊዜ ሳዖል እና ልጆቹ በፍልስጤማዊያን በጦርነት ተይዘዉ ነበር (1ሳሙ 31፡ 3-4) ፡፡ ሳዖል በቀስት በኃይለኛዉ ቆሰለ ጋሻ ጃግሬዉንም በሰይፍ እንዲገድለዉ ጠየቀው ፤ ጋሻ ጃግሬዉም እምቢ አለው ሳዖልም በራሱ ሰይፍ ላይ በመዉደቅ ራሱን ገደለ ፡፡ ምዕራፍ 30-31 ላይ ብንመለከት መርዳት አንችልም ነገር ግን በእነዚህ ምዕራፎች እና በኢየሱስ መካከል ተመሳሳዩነቱን እናስታውላን ፤ ጠላት ኢየሱስን በሰቀለበት ቀን በራሱ ሰይፍ ላይ ወደቀ ፡፡
ኢየሱስ የተቀባ ነው ፤ በኤደን ገነት የሰዉ ልጅ ያጣዉን ተከታተለ፣ መልሶ ያዘ ሁሉንም ነገር አስተካከለ ፡፡ ኢየሱስ ያደረገዉ ነፃ ስጦታ ነው ፡፡ ሁሉም ሰዉ መደ መስቀሉ በመሄድ ተጠቅሟል ፡፡ ዳዊት እርሱን ለሚያነሳሳዉ ህመም ከመፍቀድ ይል እግዚአብሄርን ተመለከተ ፤ በዚህ ሁኔታ የዳዊት ድል በቅባቱ አነሳሳዉ ፡፡ በጥሪዓችን በምንጓዝ ጊዜ ሁሉም ሰዉ ይጠቀማል ፡፡
ጥያቄዎች
-
ሊሰርቅ፣ ሊገድል እና ሊያጠፋ የሚመጣ ጠላት አለን (1ሳሙ 30፡ 3፣ ዮሐ 10፡ 10) ፤ በ 1ሳሙኤል በቁጥር 8 ዳዊት ተሰጥቶት እንደ ነበረዉ ተመሳሳይ የድል ተስፋ እንዳለን ለማወቅ እንዴት ትግልን መዉሰድ እንችላለን ? (ማር 12፡ 36፣ ሉቃ 1፡ 71)
-
ዳዊት ሰራዊቱ ቤተሰቦቻቸዉ ስለ ተወሰዱባቸዉ በኃዘናቸዉ እና ጦሩ እርሱን ሊገድሉ በመፈለጋቸዉ መካከል በነበር ጊዜ ዳዊት መጀመሪያ ትኩረቱን የት ላይ አደረገ ? በኃይለኛ ሁኔታ ወይም ችግር በሆናችሁ ጊዜ መጀመሪያ የምትፈልጉት ማን ወይስ ምንድን ነው ? “ ራሳችሁን ለማጠንከር(ለማበረታታት) “ ስትሉ ተስፋ በቆረጣችሁበት ወይም በተጨነቃችሁበት ጊዜ ምን ታደርጋላችሁ ?
-
በችግሩ ጊዜ ለማበርታት እግዚአብሄር ለዳዊት ያደረጋቸዉ ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (1 ሳሙ 30፡ 10-20፣ መዝ 37፡ 5)
-
ክፉዎች እና ምናምንቴ ሰዎች ስላስመለሱት ምርኮ ስለ ተናገሩት እና ዳዊት ስለ እነርሱ ባለዉ መካከል ልዩነቱ ምን ነበር ? ከፊት መስመር ላይ ያልሆኑ ከሩቅ የሆኑ ነገር ግን ከሩቅ የሚያግዙን (በገንዘብ ወይ በፀሎት ወይም ደግሞ በማበረታታት) እንደ ሌሎቹ ዋጋ አላቸው ?
-
በ 1ሳሙኤል 31 የሳዖል ህይወት ወደ ሚያሳዝን መጨረሻ መጣ ፤ ሳሙኤል ከአንድ ቀን በፊት ሳዖልን በእርሱ ላይ እና በልጆቹ ላይ ምን እንደ ሚሆን ነገረው (1ሳሙ 28፡ 19) ? ለመኖር አንድ ቀን እንደ ቀራችሁ ብታዉቁ ምን ታደርጋላችሁ ? እግዚአብሄርን እንዴት ታከብሩታላችሁ ?
-
በ 1ሳሙኤል (30-31) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Samuel 30:6b, 8
“But David found strength in the LORD his God. . . . and David asked the LORD: ‘Should I pursue these raiders? Will I overtake them?’ The LORD replied to him, ‘Pursue them, for you will certainly overtake them and rescue the people.’”
ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ አማሌቃውያን በደቡብ አገር ለይ ዘምተው ጺቅላግንም መትተው በእሳትም አቃጥለዋት አገኙ ፡፡ ሁሉም ነገር ብቻ አልነበረም የወደመው ነገር ግን ሚስቶቻቸው ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው ተወስደው ነበር ፡፡ ዳዊትና ሰዎቹም ለማልቀስ ኃይል እስኪያጡ ድረስ አለቀሱ ፡፡ ዳዊት ስላጣው ነገር ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሳለ በአምላኩ በእግዚአብሔር ብርታትን አገኘ ፡፡ ዳዊትም መንገድንና ቀጥሎም ምን ማድረግ እንዳለበት ለማወቅ ጥበብን ከእግዚአበሔር ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም አላሳፈረውም ነበር ፡፡ ዳዊትን ግልጽ የሆነ አቅጣጫን ሰጠው ድልን እንደሚያቀዳጀውና የተወሰደውም ሁሉ እንደሚመለስ ተናገረው ፡፡
የዳዊትን የሀዘን ታሪክ ስታነብ ጥሩ አጋጣሚ ነው በታሪኩ ውስጥ ያለውን ህመም ለመረዳት ምክንያቱም አንተም እንዲህ ባለ ህመምና ሀዘን ውሰጥ ስላለፍክ ፡፡ ማስታወስ ትችላለህ ባጣም ጮኸህ ለረጅም ሰዓት ያለቀስክበትን ጊዜ እንባ ከአይንህ ማውጣት እስኪያቅትህ ድረስ ፡፡ ምናልባት አሁንም በከባድ ሀዘን ውስጥ እያለፍክ ይሆናል ፡፡ እርሱ በድካምህ እንደሚያበረታህ ተናግሯልና በመከራም ውስጥ ብትሆን እንኳ እግዚአብሔር ብርታትን እንድሰጥህ ወደ እርሱ ፀለይ ፡፡ እርሱ ከተሰበረ ልብ ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ያዘኑትንም ያፅናናል ፡፡ መንገድን ጠይቀው እርሱም የምታደርገውን ይነግርሀል ፡፡ በኢየሱስ እግዚአብሔር ድልና ምርኮ አለው ፡፡
“ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ ፡፡ ዳዊትም የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን ? አገኛቸዋለሁን ? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ እርሱም ታገኛቸዋለህና ፈጽመህ ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት ፡፡ “
- 1ኛ ሳሙኤል 30፡6-8
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 22(24)፡4 –“ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል ፡፡ “
መዝሙር 32፡8 –“ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሳ ይደንግጡ ፡፡ እርሱ ተናግሮአልና ሆኑም እርሱ አዘዘ ጸኑም ፡፡ “
መዝሙር 72(73)፡26 –“ የልቤ አምላክ ሆይ ልቤና ስጋዬ አለቀ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።