Historical Books 1 Samuel

When Faced With a Dilemma

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 28-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 241 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በትክክል 1ሳሙኤል 28 ለመረዳት 1 ሳሙኤልን 27 ለመከፋፈል እፈልጋለሁ ፤ ዳቪስ ራልፍ ደል ምዕራፍ 27 ወደ አራት ክፍል ይከፍለዋል፡ የዳዊት እቅድ (27፡ 1-4)፣ የዳዊት ከተማ 927፡ 5-7)፣ የዳዊት ተግባር(ድርጊት) (27፡ 8-12) እና የዳዊት አጣብቂኝ (28፡ 1-2) ፡፡

የዳዊት እቅድ፡ በቁጥር (1-4) ሳዖል በዚያ አያስድደኝም ብሎ በማሰብ ወደ ጠላቶቹ ምድር ወደ ፍልስጤማዊያን ሸሸ ፤ የዳዊት 600 ሰዎች እና ቤተሰቦቹ ሁሉም ወደ ፍልስጤም ምድር ጌት ሄዱ ፡፡ ዳዊት ከእርሱ ጋር ሁለት ሚስቶች ነበሩት አኪናሆምና አቢግያ (የናባል ሚስት የነበረችዉ) ነበሩ ፡፡ ሳዖል ዳዊት የት እንዳለ በሰማ ጊዜ መፈለጉን አቆመ ፤ እዚህ ጋር የዳዊት እቅድ የሰራ ይመስላል ነገር ግን በጠላት ሰፍር ዉስጥ ነበር ፡፡

የዳዊት ከተማ፡ በግልፅ ዳዊት (የተቀባዉ ንጉስ) በዚያ ለመቀመጥ ፍቃደኛ ነበር ምክንያቱም የሚኖርበትን ከተማ የፍልስጤም ንጉስ አንኩስ እንዲሰጠዉ ጠይቆት ስለ ነበር ፤ አንኩስ ጺቅላግን ሰጠዉ ዳዊትም ለ አንድ አመት ከ አራት ወር በዚያ ተቀመጠ (ቁጥር 5-7) ፡፡

የዳዊት ተግባር(ድርጊት)፡ በዚያን ጊዜ የዳዊት ተግባር የጠላት ከተማዎች ለመያዝ ሁሉንም መግደል ነበር ነገር ግን ሁሉንም እንስሳቶች እና ልብስ መዉሰድ ነበር ፡፡ አንኩስ “ ዛሬ በየት ዘመትክ ብሎ ጠየቀው “ ዳዊት በእያንዳንዱ ከተማ ያለዉን ሁሉንም ሰዉ ስለገደለ ለሳዖል ምን እያደረገ እንደ ነበር መናገር አይችሉም ፤ ዳዊት የደቡብ ይሁዳንም አገር ወሮ (ይዞ) ነበር ፡፡ አንኩስ ዳዊት ለእስራኤል ህዝብ ራሱን የተጠላ አድርጎ ስለ ነበር ለዘላለም የአንኩስ አገልጋይ ይሆናል ብሎ አመነ ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (28፡ 1-2)፡ አንኩስ እስራኤልን ለመዋጋት ጦሩን ባመጣ ጊዜ እና አንኩስ ዳዊት እና ሰዎቹ ከእርሱ ጋር ለመዋጋት እንደሚወጡ በጠበቀ ጊዜ የዳዊት አጣብቂኝ መጣ (ቁጥር 1) ፡፡ አንኩስ ዳዊት የጠላቶቻቸዉን ከተሞች እንዴት አድርጎ እንደያዘ አይቶ ስለ ነበር ዳዊት ከዋና ጠላታቸዉ ከእስራኤል ጋር ከእነርሱ ጋር ይዋጋል ብሎ ጠበቀ ፡፡ የዳዊት ምላሽ ለአንኩስ አወዛጋቢ ነበር ፤ ለመዋጋት ቃል አልገባለትም ነገር ግን እንደ ሚያደርገዉ መነሳሳት ሰጠው (ቁጥር 2) ፡፡ ዳዊት እቅዱን አልገለጠም ወይም በጊዜዉ እቅድ አልነበረው ፡፡

1-ሳሙኤል (28፡ 3)፡ ሳዖልም እንዲሁ አጣብቂኝ ነገር ዉስጥ ገባ ፤ ሳሙኤል ሞቶ ስለነበር ሁሉም እስራኤላዊያን ለእርሱ አዝነዉ እያሉ ሳዖል የፍልስጤማዊያንን መምጣት ሰማ (ቁጥር 3) ፡፡ ሳዖል ከምድሪቱ መናፍስት ጠሪዎችን እና ጠንቋዮችን አስወገደ (ዘዳ 18፡ 9-12) ፤ ሳዖል የእግዚአብሄርን ቃል ያዉቀዋል ይከተለዉማል ፡፡ ኮንስታብል “ መናፍስት ጠሪዎች ከሞቱ ሰዎች ጋር የሚነጋገሩ ሰዎች እንደ ሆኑ እና ጠንቋዮች ደግሞ ከክፉ መንፈስ ጋር የሚነጋገሩ ሰዎች እንደሆኑ “ ይገልፃል ፡፡ ጠንቋዮች የመናፍስት አካል ነበሩ (ኢሳ 8፡ 19) ፡፡

1-ሳሙኤል (28፡ 4-8)፡ ፍልስጤማዊያን በሱነም ሰፈሩ እስራኤላዊያን ደግሞ በኤዝራኤል ሸለቆ በሌላኛዉ በኩል ጊልቦዓም ላይ ሰፈሩ (ቁጥር 4) ፤ ሳዖል ፍልስጤማዊያንን ሰፍር ተመለከተና ፈራ ፡፡ አገልጋዮቹንም ታማክረዉ ዘንድ አንዲት መናፍስት የምትጠራ ሴት ሊያገኝ እንደ ሚሄድ ነገራቸው ፤ አገልጋዮቹም በዓይንዶር አንዲት መናፍስት የምጥጠራ ሴት እንዳለች መለሱለት (ቁጥር 7) ፡፡ ሳዖል በፍልስጤማዊያን የጦር ሰፈር አቅራቢያ በማለፍ ወደ ዓይንዶር አስር ማይል ጉዞ ለማድረግ ሁሉንም ንጉሳዊ ልብሶቹን አዉልቆ አገልጋዮቹ ጋር በመተዉ ራሱን ደበቀ ፡፡ ሳዖልም አገልጋዮቹን ለእርሱ የተነገረዉን እንዲያደርጉ ጠየቃቸው (ቁጥር 8) ፤ ሳዖል ነገሮችን በራሱ እጅ በማድረግ እንዲያከብረዉ ተብሎ በተማረዉ ትምህርት ላይ በተቃራኒ ሄደ ፡፡ መፅሀፍት ለኃጢዓት እና ለምኞት በምንሰጥ ጊዜ ሞት ይገጥመናል(ይደርስብናል) (ያዕ 1፡ 13-15) ፡፡

1-ሳሙኤል (28፡ 9-14)፡ መናፍስት ጠሪዋ ሳዖል መናፍስት ጠሪዎችን እንደ ገደለ ስለምታዉቅ በእርሷ ላይ ወጥመድ እያደረጉባት እንደ ነበር ተናገረች (ቁጥር 9) ፤ በምላሹ ሳዖል ለእርሷ ምንም ነገር እንደ ማይደርስባት “ በእግዚአብሄር “ ማለላት (ቁጥር 10) ፡፡ እግዚአብሄር እንድትኖር አይፈልግም ነገር ግን ሳዖል ጥሪዉን እንድታደርግለት እርሷን ለማግኘት ስሙን ተጠቀመ ፤ ሳዖል ከሳሙኤል ጋር እንድታገናኘዉ ፈለገ (ቁጥር 11) ፡፡ ሳሙኤል በተከሰተ ጊዜ በመደንገጥ ሳዖል ለምን እንዳታለላት ጠየቀችዉ (ቁጥር 12) ፤ ሳዖል ችግር ዉስጥ እንደ ማትሆን ቃል በመግባት ሳሙኤል ምን እንደ ሚመስል ጠየቃት (ቁጥር 13) ፤ ያየችዉን “ የመንፈስ አይነት “ ነገረችዉ (ቁጥር 13) ፤ ይህ መንፈስ መለኮታዊ ፍጥረት ወይም የታላቁ ዳኛ ዳኞች ሊሆን ይችላል ፡፡ በ 1ሳሙ (15፡ 27-28) ሳሙኤል የሳዖልን ዘርፍ መቅደድ እና የሳሙኤልን ዘርፍ መቀደድ የሚያስታዉስ መጎናፀፊያ ለብሶ ነበር (ቁጥር 14) ፡፡

1-ሳሙኤል (28፡ 15-25)፡ ሳሙኤል ለምን ሳዖል እንደ ሚያስቸግረዉ ጠየቀው ሳዖልም እግዚአብሄር ከእርሱ ዞር እንደለ ገለፀለት (ቁጥር 15) ፡፡ ይህ እግዚአብሄር አላማዉን ለመፈፀም ማንኛዉንም መንገድ ሊጠቀም እንደ ሚችል ምሳሌ ነው ፤ በዚህ ጊዜ ሳዖል ላይ ትንቢታዊ ቃል ለመናገር ክፉን ተጠቀመ ፡፡ ሳሙኤል ሳዖልን እግዚአብሄር ሊያደርግ የተናገረዉን እንዳደረገ እና ሳዖል እና ልጆቹ በቀጣዩ ቀን በፍልስጤማዊያን እንደ ሚገደሉ ነገረው (ቁጥር 16-19) ፤ ሳዖልም መሬት ላይ ወደቀ ፈራም ምግብም በማጣቱም(ባለመብላቱ) ደከመ (ቁጥር 23-25) ፤ ይሁን እንጂ ሴትየዋ እና አገልጋዮቹ እንዲበላ ቢገፋፉትም እምቢ አለ ፡፡ የሰባች አንዲት ላም በመግደል ሳዖልን በመጨረሻዉ እራት አገለገለችዉ (ቁጥር 23-25) ፡፡

መደምደሚያ

ምዕራፍ 29 መጀመሪያ ላይ ዳዊት ፍልስጤማዊያንነ እንዴት ማድረግ እንዳለበት ለማቀድ እየሞከረ ነበር ፤ ሳዖል ደግሞ በቀጣዩ ቀን እርሱና ልጆቹ በሚገደሉበት ዜና ላይ ለመነጋገር እየሞከረ ነበር ፡፡ ሳዖል ተስፋ አልነበረውም ፤ ከክርስቶስ ተለይቶ ነበር ፤ ይሁን እንጂ በክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ነን ፡፡ ከዚህ በኋላ ከእግዚአብሄር አንርቅም ከእርሱ ሊያርቀን የሚችል ትልቅ ኃጢዓት የለም (ኤፌ 2፡ 12-13) ፡፡ ኢየሱስ ነፃ አዉጥቶናል ፡፡

ምስራቅ ከምዕራብ እንደ ሚርቅ እንደ ቆሸሽን እዉቅና በሰጠን ጊዜ እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን ከእኛ አስወግዶታል (መዝ 103፡ 12) ፡፡ ከሳዖል ግዛት ወደ ዳዊት ግዛት እንሄዳለን ፤ ሳዖል እግዚአብሄር እንደ ማያስፈልገዉ ያስባል ፡፡

በአሁኑ ስዓት ይህ በማዳመጥ እና በማወቅ ከሌሎች የደበቃችኋቸዉ -ትንሽ ነገሮች እና ትልቅ ነገሮች አሉ ? የተደበቀዉን ስላገኛችሁ ለምትይዙት ነገር አታስቡ ፡፡ ኃጢዓታችሁን ብትናዘዙ እግዚአብሄር የታመነ እና ፃድቅ ስለሆነ ኃጢዓታችሁን ይቅር በማለት ቅዱስ ካልሆነዉ ነገር ሁሉ ያነፃችኋል (1ዮሐ 1፡ 9) ፤ እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን ወደ መንፃት እንድንመጣ እድል ሰጥቶናል ፡፡

  1. Dale Ralph Davis, 1 Samuel: Looking on the Heart (Fearn, Ross-shire, Great Britain: Christian Focus Publications, 2000, reprinted 2017), p. 279.

  2. Thomas Constable, Dr. Constables Expository Bible Study Notes: 1 Samuel, p. 201; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1samuel.pdf.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 287.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ (28፡ 6) ሳዖል ከእግዚአብሄር ጠየቀ መልስ ግን አላገኘም ፤ በእግዚአብሄር ለምን እንዳልተሰማ ምን ታስባላችሁ ? (ምሳ 1፡ 28-33)
  2. ሳዖል መናፍስት ጠሪዎችን እና ጠንቋዮችን ከምድሪቱ ለምን አስወጥቶ አስቀመጣቸው ? (ዘሌ 19፡ 31፣ 20፡ 6፣ ዘዳ 18፡ 10-11) ካደረገዉ በኋላ ሳዖል መናፍስት ጠሪዋን በመፈለግ ለምን እንደ ጎበኛት ምን ታስባላችሁ ?
  3. በ 1ሳሙ (29፡ 4) የፍልስጤም አለቆች ዳዊትን ወደ ሰፈሩ እንዲመለስ ለምን አደረጉ ?
  4. በ 1ሳሙኤል (28-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 28:5–8a

“When Saul saw the Philistine camp, he was afraid and trembled violently. He inquired of the LORD, but the LORD did not answer him in dreams or by the Urim or by the prophets. Saul then said to his servants, ‘Find me a woman who is a medium, so I can go and consult her.’ His servants replied, ‘There is a woman at En-dor who is a medium.’ Saul disguised himself by putting on different clothes and set out with two of his men. They came to the woman at night.”

ፍልስጥኤማውያን አስራኤልንና ንጉስ ሳኦል ለመውጋት በአንድነት ተሰበሰቡ ፡፡ ሳኦልም የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ባየ ጊዜ በፍርሀት ተንቀጠቀጠ ፡፡ ሰኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ ነገር ግን እግዚአብሔር አልመለሰለትም ነበር ፡፡ ስለፈራና ስለተጨነቀ ሳኦል መንገድን መፈለጉን ቀጠለ ፡፡ ሳኦልም ራሱን ለውጦ በሌሊት ወደ መናፍስት ጠሪ ቤት ሄደ ፡፡ ሳኦል መናፍስት ጠሪን መፈለግ ኃጢአት መሆኑን ቢያውቅም ግን አደረገው ፡፡ የሰማውም ነገር መልካም አልነበረም ይህም ነገር የበለጠ ተሰፋ አሰቆረጠው ፡፡

በህይወት ውስጥ እግዚአብሔር ዝም የሚልባቸው እንደገናም ቶሎ ምላሽ የማይሰጥባቸው ጊዜያት አሉ ፡፡ በዝምታም ውስጥ ቢሆን እንኳ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው ፡፡እርሱ በዝምታ ጊዜያትም አንተን የሚያሰተምረው ነገር አለው ፡፡ የእግዚአብሔርን ጊዜ ጠብቅ እርሱን መፈለግህንም ቀጥል ፡፡ እንደ ሳኦል ከሌላ ቦታ መልስን ለመፈለግ ትፈተን ይሆናል ፡፡ ይህንን ፈተና በእግዚአብሔር ላይ በመጽናት ተቋቋም ፡፡ነገር ግን እራስህን ደብቀህ በሌሊት ከእግዚአብሔር ወጭ የሆነን ነገር ወይም የሆነን ሰው እየፈለክ ከሆነ አሁን ጊዜው ነው ማስመስልን ልታቆም እንደሁም ንስሀ ልትገባ ፡፡ እርሱም የትኛውንም ሀጢአት ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ እንድሁ ያርቃል ፡፡ እርሱ ነፃ ያወጣሀል ውጊያህንም ይወጋ ዘንድ ካንተ ጋር ነው ምክንያቱም እርሱ ላንተ ያለው ፍቅር አያልቅምና ምህረቱም ማለዳ ማለዳ አድስ ነው ፡፡

“ ሳኦልም የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ባየ ጊዜ ፈራ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀተ ፡፡ ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ እግዚአብሔርም በህልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም ፡፡ ሳኦልም ባሪያዎቹን ወደ እርስዋ ሄጄ እጠይቅ ዘንድ መናፍስትን የምትጠራ ሴት ፈልጉልኝ አላቸው ባሪያዎቹም እነሆ መናፍስትን የምትጠራ አንድት ሴት በዓይንዶር አለች አሉት ፡፡ሳኦልም መልኩን ለውጦ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 28፡5-8

ተጨማሪጥቅስ

  • ሰቆቃወኤርምያስ 3፡22-23 –“ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሣ ነው ርኅራኄው አያለቅምና ፡፡ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ታማኝነትህ ብዙ ነው ፡፡ “

መዝሙር 102(103) ፡12 –“ ምሥራቅ ከምዕራብ አንደሚርቅ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ ፡፡ “

ያዕቆብ 1፡14-15 –“ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል ፡፡ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወላዳለች፡፡ “