Historical Books 1 Samuel

God Is Faithful

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 26-27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 240 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና እግዚአብሄር የናባልን ሚስት አቢግያን መንገዱን ሊያሳጣዉ ድርጊት ላይ በጣም አትኩሮ በነበር ጊዜ በዳዊት ህይወት ላይ ጣልቃ ለመግባት እንዴት እንደ ተጠቀመባት ተምረናል ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (26፡ 1-4)፡ የዚፍ ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሳዖል በመሄድ ዳዊት የት ተደብቆ እንደ ነበር ነገሩት (1 ሳሙ 23) ፡፡ ሳዖል ዳዊትን ለመፈለግ ከ 3,000 ሰዎች ጋር ሄደ (ቁጥር 1-2) ፤ በዚህ ጊዜ የዳዊት ጠላቶች ዳዊት የት እንደ ነበር እየነገሩት ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄርም ከዳዊት ጋር እየተነጋገረ ስለ ነበር ሳዖል ቀርቦ እንደ ነበር ዳዊት እንዲያዉቅ አደረገው(ፈቀደለት) (ቁጥር 3) ፡፡ ዳዊት ሳዖል የት እንደ ነበር በትክክል እንዲያገኙት ሰላዮችን ላከ (ቁጥር 4) ፡፡ ለዳዊት እንደ ገና ከሳዖል ጋር በተመሳሳይ መንገድ መንገድ ትርጉም ይኖረዋል ፤ ስለ ዚህ ስሜቱን በመዝሙር 37 ተቀምጧል ፡፡

1-ሳሙኤል (26፡ 5-12)፡ ዳዊት የሳዖል ካምኘ የነበረበትን ባገኘዉ ጊዜ በዚያ በመሄድ ሳዖልን በ 3,000 ወታደሮቹ መካከል ተኝቶ አገኘው (ቁጥር 5) ፡፡ ዳዊት ኬጢያዊዉን አቢሜሌክንና የኢዮአብን ወንድም አቢሳን (የዳዊትን የአክስት ልጅ) ከእነርሱ መካከል ወደ ካምፑ ከእርሱ ጋር የሚሄድ እንዳለ ጠየቀ (ቁጥር 6) ፤ በዚያም ምሽት ዳዊት እና አቢሳን ሳዖል ተኝቶ ወደ ነበረበት ዘልቀዉ ገቡ (ቁጥር 7) ፡፡ አቢሳን ይህን ጠላቱን ለመግደል እንደ እድል በማየት ከእርሱ አጠገብ የነበረዉን ሳዖልን በራሱ ጦር ከመሬት ጋር እንዲያጣብቀዉ አቀረበ (ቁጥር 8) ፤ ዳዊት ጦሩን ያውቀዋል ምክንያቱም ሳዖል ሊገድለዉ በጦር ስለ ሞከረ ፤ አሁንም እንደ ገና ዳዊት እግዚአብሄር በቀባዉ ንጉስ ላይ እጁን ለማንሳት እምቢ አለ ፡፡ በጊዜዉ እግዚአብሄር ሳዖልን እንደ ሚጠብቀዉ አስተዋለ (ቁጥር 9-10) ፤ በዚያ ፋንታም ዳዊት ከሳዖል ራስ አጠገብ ያለዉን ጦርና ዉሃ መያዣ በመዉሰድ በዉስጡ የነበሩት ከእግዚአብሄር በሆነ ከባድ እንቅልፍ ስር የነበሩበትን ሰፈር ትተዉ ሄዱ (ቁጥር 11-12፣ ሉቃ 6፡ 27-36) ፡፡

1-ሳሙኤል (26፡ 13-16)፡ ዳዊት ወደ ሌላኛዉ ወደ ተራራዉ ክፍል ተሸገረ ከዚያም ወደ አቤነር ወደ ፍልስጤማዊያን ሰፈር ጮኸ (ቁጥር 13) ፡፡ ዳዊት መጀመሪያ አቤነርን ያገኘዉ ዳዊት የጎልያድን ራስ እንደ ያዘ ወደ ሳዖል ፊት የወሰደዉ ጊዜ ነበር (1 ሳሙኤ 17፡ 55-57) ፡፡ እንዲመልስለት አቤነርን ጠየቀው (ቁጥር 14) ፤ አቤነርም ዳዊትን ምን እያደረገ እንደ ነበር ጠየቀው ዳዊትም የሌልት ጠባቂዎች ተኝተዉ ስለ ነበር ማንም ሳያውቀው ወደ ሳዖል በኩል በቀስታ ወደ ካምፑ መግባት ችሎ እንደ ነበር ገለፀት ፤ ለማረጋገጫም ዳዊት አቤነርን የሳዖልን ጦር እና ዉሃ መያዣ እንዲመለከት ነገረው (ቁጥር 15-16) ፡፡

1-ሳሙኤል (26፡ 17-21)፡ አቤነር ወዲያዉኑ የዳዊትን ድምፅ ባያስተዉለዉም ሳዖል አስተዉሎታል (አዉቆታል) (ቁጥር 17) ፡፡ አስታዉሉ ሳዖል ለዳዊት እንደ ልጁ ሲጠቅሰዉ ዳዊት ለሳዖል እንደ ጌታዉ እና ንጉሱ ጠቅሶታል ፡፡ ዳዊት ለምን ይቅር ባለ ማለት ያለማቋረጥ እንደ ሚያሳድደዉ ጠየቀው ፤ ዳዊትም በእግዚአብሄር ላይ ክፉ አድርጎ ከሆነ ምን እንደ ነበር እንዲነግረዉ እና ለእግዚአብሄር መስዋዕት ማምጣት እንደ ሚችል ወይም ደግሞ ሳዖል ስለ ዳዊት ዉሸት እያመነ እንደ ከነበር እንዲነግረዉ ጠየቀው (ቁጥር 18-19) ፡፡ ዳዊት ለሳዖል እርሱን ለማግኘት 3,000 ሰዎች ጦርን መጠቀም የሚሸሽን እንደ ማሳደድ እንደ ነበር ወይም በተራሮች ዉስጥ ቆቅን ከኋላዉ እንደ ማባረር ነው አለው (ቁጥር 20) ፡፡ ዳዊት ወደ ሳዖል እዉነትን በመናገር ሳዖል ምን እያደረገ እንደ ነበር እንዲያስተዉል እየሞከረ ነበር ፤ ሳዖል ዳዊት ላይ እንደ ገና ኃጢዓት እንዳደረገ ተናዘዘ (ቁጥር 21) ፤ ይህ ሳዖል በዳዊት ላይ ስላደረገዉ ኃጢዓት ጥፋተኛ ሲሆን የመጀመሪያዉ አይደለም ፤ ዳዊት ሳዖልን ከመጉዳት ይልቅ የሳዖልን መጎናፀፊያ ከቆረጠዉ በኋላ ይህ ሆኗል ፤ ሳዖል ቢናዘዝም እንኳን አድርጎት ለነበረዉ በፍፁም ንስሀ አልገባም (2ቆሮ 7፡ 10) ፡፡

1-ሳሙኤል (26፡ 22-25)፡ ዳዊት ሳዖልን ከጎልማሶቹ አንዱን ጦሩን ለማግኘት እንዲልከዉ ነገረው (ቁጥር 22) ፡፡ ዳዊት የሳዖል ህይወት ዋጋ እንዳላት እንዳየዉ በማረጋገጥ የዳዊትንም ህይወት በተመሳሳይ እንዲያየዉ ሳዖል ጠየቀው (ቁጥር 23-24) ፡፡

መደምደሚያ

ዕብ (10፡ 23) እግዚአብሄር ሁልጊዜ ለተስፋዉ የታመነ እንደሆነ ይገልፃል ፤ እግዚአብሄር ለዳዊት የታመነ ነበር ዳዊትም ለእግዚአብሄር የታመነ ነበር ፡፡ ዳዊት ጎልያድን በገጠመ ጊዜ እግዚአብሄር የታመነ ነበር ፤ ዳዊት በዋሻዉ ዉስጥ ከሳዖል ጋር በነበረ ጊዜ እግዚአብሄር የታመነ ነበር ፤ ዳዊት ናባልን ባገኘዉ ጊዜ እግዚአብሄር የታመነ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ቅቦች(በእግዚአብሄር የተቀባን) ነን ሁልጊዜ ሊያድነን ለእኛ የታመነ ነው ፡፡

ዳዊት ምንም እንኳን ነገሮች በእርሱ ፍላጎት የሞሆኑ ባይመስሉም በጥሪዉ ተጉዟል ፤ ሁኔታዎችን ለማስታረቅ ከመሞከር ወይም የሆነ ነገር ከማድረግ ይልቅ ዳዊት ታምኖ ተቀመጠ ፡፡

የዳዊት ህይወት እንዴት ሊናገረን ይችላል ? ናባሎችን እና ሳዖሎችን በኑሮአችን በመዉሰድ መልካም እና ዉጤት ወዳለዉ ነገር ልናዞራቸዉ የምንችለዉ እንዴት ነው ? ለጠላቶቻችን እንዴት መፀለይ እንችላለን ? ጠላት ሰፈር ሄዳችሁ እግዚአብሄር በዚያ ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆን በማመን የእግዚአብሄር ቃል ትሰማላችሁ ? ከችግሮች ከመሸሽ ይልቅ እንዴት ወደ ችግሮቹ እንሄዳለን ? እግዚአብሄር በመሀከላችን እየተጓዘ መሆኑን በማመን የምናሳየዉ በምንድን ነው ?

በአሁኑ ጊዜ በህይወታችሁ ምንድን ነዉ እየሆነ ያለው ? የዚህ ምድረበዳ ኑሮ መቅመስ የጉዞዉ አንድ አካል ነው ፡፡ እግዚአብሄር ተስፋ ለገባላችሁ እና እንድታደርጉት ለጠራችሁ ለማንኛዉም ነገር የታመናችሁ ሁኑ !

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ(26፡ 11) ዳዊት እግዚአብሄር የቀባዉን አልነካም አለ ፤ በእግዚአብሄር የተቀባ ማለት ምን እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? ሌላ የት ይህን ቅባት ታዩታላችሁ ? (ሐዋ 4፡ 27፣ 10፡ 38፣ ሉቃ 4፡ 18)
  2. ዳዊት በጌት እያለ ብዙ ምድሮችን አጠቃ አንድም እንዲኖር አልተወም ነበር ፤ ይህን ለምን አደረገ ? በዚያን ጊዜ ከእግዚአብሄር ይሰማ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  3. በ 1ሳሙኤል (26-27) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 26:23–24

“May the LORD repay every man for his righteousness and his loyalty. I wasn’t willing to lift my hand against the LORD’s anointed, even though the LORD handed you over to me today. Just as I considered your life valuable today, so may the LORD consider my life valuable and rescue me from all trouble.”

ዳዊት እንደገና ሳኦልን መግደል የሚችበት አጋጣሚ ውስጥ እራሱን አገኘው ፡፡ ዳዊት ሳኦልን ካስወገደው ወድያውኑ የእስራኤል ንጉስ እንደሚሆን ያውቃል ቢሆንም ግን ዳዊት የእግዚአብሔር ሀሳብ ፉበራሱ እጅ ላለማድረግ መረጠ ፡፡ ዳዊት የራሱን ሰዎች ሳኦልን እንዳይገድሉ ተናገራቸው ፤ ይህ እርሱ በአምላኩ ያለውን እምነት ያሳያል ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር አሳብ በእግዚአብሔር ጊዜ አንደሚሆን ስለሚያምን ፡፡ ነገረ ግን ለሳኦል ነፍሱ እንደተተወች ለማሳየት ዳዊት የውኃውን መንቀልና ጦሩን ወሰደ ፡፡ የተሻለውን መንገድ በመምረጥ ዳዊት በድርጊቱ ሳኦልን የእምነት ቃሉን ለመስጠትና ኃጢአቱን ለመናዘዝ አበቃው ፤ በምላሹም ሳኦል ዳዊትን ባረከው አከበረውም ፡፡

በህይወትህ ወስጥ ሳኦል የሆነው ነገር ምንድን ነው ? አለ ይሆን ይፈጸም ዘንድ አንተ ተፅዕኖ የምታሳድርበት ነገር ፤ ከዚያም ኋላ የእግዚአብሔር አሳብ በቶሎ አንደሚሆን የተረዳኸው ? በሰዓቱ ቀላል ይመስል ይሆናል ነገሮችን በራስህ እጅ ውስጥ ማድረግ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ላንተ ህይወት እቅድና አሳብ አለው ፡፡ በልብህ ውስጥ ምንም አይነት ጥያቄ ካለ እሱን ተወው ፡፡ በቅንነት ስትኖር አሳብህ በእግዚአብሔር ይፈጸማልና ፡፡ መንገድን ጠይቀው ፡፡ አግዚአብሔር ስለወደፊቱ የተስፋን ቃል ከሰጠህ እርሱ ለመልካም ነገር እቅድ አለው ማለት ነው ይህንንም አርሱ ይፈጽመዋል ፡፡ አግዚአብሔር የልብህን ቅንነት ይባርካል ፡፡

“ ዛሬም እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶህ ሳለ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ አልወደድሁምና ለሁሉ እያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ጽድቁና እንደ እምነቱነ ፍዳውን ይክፈለው ፡፡ ነፍስህም ዛሬ በአይኔ ፊት እንደከበረች እንዲሁ ነፍሴ በእግዚአብሔር አይን ፊት ትክበር ከመከራም ሁሉ ያድነኝ ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 26፡23-24

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 40(41) ፡12 – “ እኔን ግን ስለ ቅንነቴ ተቀበልኸኝ በፊትህም ለዘላለም አጸናኸኝ ፡፡ “

ምሳሌ 4፡24-26 –“ የአፍህን ጠማማነት ከአንተ አውጣ ሐሰተኞቹን ከንፈሮችም ከአንተ አርቅ አይኖችህ አቅንተው ይዩ ሸፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ የእግርህን መንገድ አቅና አካሄድህም ሁሉ ይጽና ፡፡ “

ዕብራውያን 10፡23 –“ የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ “