Rejection, Retaliation, and Refocus
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
13ተኛዉን የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ልንጨርስ እየቀረብን ነው ይህ 240ኛዉ ክፍል ነው ፤ ያ ማለት በዚህ መፅሀፍ ቅዱስ መንገድ ላይ አንድ ሰዎስተኛዉ ላይ ነን ማለት ፡፡ ይህ ልክ እንደ ተግባር ሊሰማ ይችላል ፤ እንደ ምናገኘዉ እንደ ሌላ ቀን ትምህርት ፤ ወይም ደግሞ ሁል ጊዜ እግዚአብሄርን ዛሬ ምን እንድንማር የፈለገዉን በመጠየቅ መቅረብ እንችላለን ፡፡ ለ 1ሳሙኤል ቃላችን የተቀባ ነው ፤ ሁል ጊዜ የተቀባ በማይመሳሰል ጊዜ ይራመዳል(በአዲስ መልክ) ይጓዛል ፡፡
ትምህርት
1ሳሙኤል (25፡ 1-3)፡ ሳሙኤል ሞተ በዚያ የነበሩ ሁሉም እስራኤላዊያን አዘኑ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት (ቁጥር 1) ፤ ለሳሙኤል ካዘኑት ዉስጥ አብዛኞቹ አይወዱትም፣ ያለዉን አይታዘዙም ነበር ነገር ግን በሞቱ አከበሩት፡፡ ዳዊት እና ሰዎቹ ከደቡብ የሴሞን ወደ ዓረባ ምድረበዳ 100 ማይል ያክል ተጓዙ ፡፡ ቁጥር 2 በማዖን የሚኖረዉን እና በቀርሜሎስ አጠገብ ስራ የነበረዉን ናባልን ያስተዋዉቃል ፤ ወደ ፊት እና ወደ ኃላ በመሄድ በራሱ መልካም የገንዘብ ግብይትን የሚያደርግ ሀብታም ሰዉ ነበር ፡፡ ቀርሜሎስ ምርጥ ዝና አልነበራትም ፤ ሳዖል ለራሱ መታሰቢያ የሰራበት ስፍራ ነበር (1ሳሙ 15፡ 12) እንዲሁም ሳሙኤል ሳዖልን የእስራኤልን መንግስት መምራት በቤተሰቡ እንደ ማይቀጥል በነገረዉ ጊዜ ሳሙኤል ለመሄድ እምቢ ያለበት ስፍራ ነበር (1ሳሙ 15፡ 26) ፡፡ ሰዉዬዉ ናብል ነበር ሚስቱም አቢግያ “ አባቴ ደስታ ነው “ የሚል የስም ትርጉም ያላት የተዋበች እና አስተዋይ ሴት ነበረች ፤ ከካሌብ ወገን የነበረው ናባል የስሙ ትርጉም “ ሞኝ “ ማለት የሆነ ባለጌ እና ክፉ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ እዚህ ጋር አቢግያል ሚናዉን እንደ ተቀባ ትጫወታለች ፤ በቁጥር 25 አቢግያ ባሏን ናባልን “ በዚህ ምናምንቴ ሰዉ….እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው “ ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 4-8)፡ ዳዊት ናባል 3,000 በጎቹን እየሸለተ እንደ ነበር ሲሰማ ለናባል ሰላምታ የሚወስዱ አስር ጎልማሳ ሰዎችን ላከ (ቁጥር 4-6) ፤ ናባል በጎቹን እየሸለተ እንደ ነበር እንደ ሚያዉቁ በተጨማሪም እረኞቹ ከዳዊት ጋር በነበሩ ጊዜ ከድካም የተጠበቁ እንደ ነበሩ ይነግሩታል (ቁጥር 7) ፡፡ የፆም ቀን ስለነበር ጎልማሶቹ የናባልን የመለገስ እርዳታ ይጠይቁ ነበር (ቁጥር 8) ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 9-13)፡ የዳዊት ጥያቄ ትክክለኛ እና ተገቢ ነበር ፤ ጎልማሶቹ ሰዎች ዳዊት እንዳዘዛቸዉ አደረጉ (ቁጥር 9) ፤ ናባል በእግዚአብሄር የተቀባዉን ዳዊትን የኮበለለ ባሪያ ነበር በማለት መለሰ (ቁጥር 10) ፡፡ ናባል የእምቢተኝነት መንፈስ ስለነበረው ለመስጠት ፍላጎቱን አስተጓጎለው ፤ ሁሉም ሰዉ ዳዊትን ያውቀዋል ፤ አቢግያም እንኳን ታውቀዋለች ፡፡ ናባል ዳዊትን የዘለፈዉ አስቦት ነበር ፡፡
በዚህ ሂደት ዳዊት እምቢ ተባለ (ቁጥር 10-12) ፤ የእርሱ ሰዎች በተመለሱ ጊዜ ዳዊትን ናባል ተናግሮት የነበረዉን ነገሩት ዳዊትም ተበቀለው (ቁጥር 12-13፣ 21-22) ፡፡ ዳዊት በመበሳጨት 400 ወታደሮችን አሰለፈ (ቁጥር 13) ፤ በቁጥር 21-22 እምቢ ተብሎ ስለ ነበር ዳዊት ለበቀል እየሄደ ነበር ፡፡
የዳዊት ድርጊት(ምላሽ) ከዚህ በፊት አድርጎት ከነበረዉ በተቃራኒ ሄደ፡
- 1 ሳሙ (17፡ 28) - ዳዊት በወንድሙ በኤሊያብ ተገፍቶ ነበር ፡፡
- 1 ሳሙ (17፡ 32-33) - ዳዊት ጎልያድን ለመዋጋት ትልቅ እና ጠቃራ አይደለህም ባለዉ በሳዖል ተገፍቶ ነበር፡፡
- 1 ሳሙ (17፡ 37) - ዳዊት ለሁለቱም ተቃዉሞ (እምቢ መባል) በእምነት መለሰ ….” እግዚአብሄር ያድነኛል “ በማለት ፡፡
ምናልባት የናባል እምቢ ማለት ዳዊት በደከሙ፣ በራበዉ እና እየሸሸ በነበረ ጊዜ ስለ መጣ ከእነዚህ ሁለቱ የተለዬ ይመስላል ፤ ይህ ዳዊት ሁል ጊዜ የሚመልስበት መንገድ አልነበረም ፡፡ ሳዖል ዳዊትን ሊገድለዉ ከሞከረ በኋላ (1 ሳሙ 18፡ 11) ዳዊት በቀልን አልተቀበለም (1 ሳሙ 24፡ 10) ፡፡
መናቅ በማስደንገጥ እና ዉስጣችን መጥፎ ነገር በማምጣት ሊወስደን ይችላል ፤ ሰይጣን ማን እንደ ሆንን ዉሸጽ ለመናገር መናቅን እንደ እድል ይጠቀምበታል (1ጴጥ 5፡ 8) ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 14-19)፡ ከናባል ሰዎች አንዱ አቢግያን በናባል ምን እንደ ሆነ እና የዳዊት ወታደሮችን እንዴት በደህና ራሳቸዉን ተከላክለዉ እንደ ነበር ነገራት (ቁጥር 14-16) ፤ አገልጋዩ ናባል እርሱ ምናምንቴ ሰዉ ስለሆነ ማንም ሊናገረዉ አይችልም “ አለ (ቁጥር 17) ፡፡ ምናምንቴ የሚለዉን እንደ ባለጌ ሰዉ ወይም የማይረባ ልጅ ተብሎ መረዳት ይቻላል ፡፡ በምላሹ አቢግያ ብዙ ምግቦችን አከማችታ በመሰብሰብ በአዮች ላይ ጫነች (ቁጥር 18) ፤ በፊቷም እንዲሄዱ አገልጋዮቿን ላከቻቸዉ ነገር ግን ለባሏ ምንም አልነገረችዉም (ቁጥር 19) ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 20-31)፡ በተራራው ማለፊያ በኩል ስትወርድ አቢግያ ዳዊትን እና ሰዎቹን ከሩቅ ሲቀርቧት አየቻቸዉ (ቁጥር 20) ፤ አቢግያ ዳዊትን በመቅረብ በእርሱ ፊት በተደፋች ጊዜ ዳዊት እንደ ገና ለበቀል እቅዱን ተናግሮ ነበር (ቁጥር 21-23) ፡፡ በአቢግያ የትህትና ድርጊት የእርሷ ያልነበረዉን ጥፋት በመዉሰዷ ዳዊት እንደ ገና አሰበ ፤ አቢግያ ዳዊትን “ እንደ ጌታዋ “ ተቀበለችዉ ፤ በምዕራፍ 25 15 ጊዜ ዳዊት የተቀባ ንጉስ እንደ ነበር እዉቅና ሰጠች፣ ያለ ግብዣ ንጉሱን እንደ ምትቀርበዉ አስቴር ተመሳሳይ በቀጥታ እርሱን ለማናገር ጠየቀች ፡፡ “ ማዳመጥ “ የሚለዉ ቃል በብሉይ ኪዳን ዉስጥ 1,100 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ትርጉሙም መስማት ወይም መታዘዝ ነው ፤ ማክአርቱር “ አድማጩ ለሚናገረዉ ለአንዱ ሙሉ ትኩረቱን ይሰጠዋል እንደ ማለት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ዳዊት ናባል ባላደረገዉ ላይ ከማተኮር ይልቅ እግዚአብሄር የነበረዉን ትልቅ እቅድ ሊያስተዉል ይገባዋል (2ቆሮ 4፡ 15) ፤ በቁጥር 28 አቢግያ ስለ ዳዊት ስሮዉ መንግስት ከእግዚአብሄር የተመሰረተ እንደ ሚሆን ትንቢት ተናገረች ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን ጥበቃ እንደ ሚሰጠዉ በመግለፅ ቀጠለች (ቁጥር 30-31) ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 32-35)፡ ዳዊት አቢግያን ወደ እርሱ ስለላከለት እግዚአብሄርን አመሰገነ ፡፡ እግዚአብሄር የዳዊትን ድርጊት ለመቀየር አቢግያን ተጠቀመ የናባልን ነፍስ እና የሰዎቹንም አዳነ (ቁጥር 32-34) ፤ ከዚያም ዳዊት አቢግያን በሰላም ቤቷ ሰደዳት (ቁጥር 35) ፡፡ ዳዊት ተበቃይ እግዚአብሄር እንደ ሆነ እንጂ እርሱ እንዳልሆነ አወቀ ፡፡
1-ሳሙኤል (25፡ 36-44)፡ ናባል አቢግያ ያደረገችዉን በሰማ ጊዜ ድንጋጤም ወደቀበት የደነዘዘም በመሆን ከአስር ቀን በኋላ ሞተ ፡፡ አቢግያ ወደ ዳዊት ሄደች ተጋቡም ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ ተገፍቶ ነበር በፍፁም ግን አልተበቀለም ሀሳቡን በእግዚብሄር ላይ አደረገ እንጂ ፡፡ መገፋት (መናቅ) በሚገጥመን ጊዜ ተመልሰን እግዚአብሄር ላይ ማተኮር ያስፈልገናል ፤ ለእግዚአብሄር የሆነዉ በሰራዉ እንጂ በሰራነዉ ስላልሆነ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 275.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 377.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 340.
ጥያቄዎች
-
የሳሙኤል ሞት ማስታወሻ የሚሆን ይመስላል ፤ ለምን ? (1ሳሙ 8፡ 4-8)
-
ከዚህ ምዕራፍ ከናባል ምን እናዉቃለን ? በ 1ሳሙ (25፡ 10) መሰረት ናባል ከሳዖል ወይስ ከዳዊት በኩል ለመወገን ተከሰተ ?
-
ለናባል እምቢታ ለማጥቃት እና ነባልን እና በስሩ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ ለመግደል በማቀዱ የዳዊት ምላሽ ትክክል ነበር (1ሳሙ 25፡ 13፣ 22) ? ከእርሱ በተቃራኒ ለሆኑት ያልተለመደዉ የዳዊት ምላሽ ፅናት ነበር (1ሳሙ 17፡ 37፣ 24፡ 10) ? ለሁኔታዉ ከመመለስ ይልቅ በሁኔታዉ ምክንያት መልስ እንድትሰጡ እንዲያደርጋችሁ ፈቅዳችሁለት ታውቃላችሁ ?
-
በ 1ሳሙ (25፡ 33-34) ለምን ዳዊት አቢግያን ባረካት ? እግዚአብሄር እናንተን ለማስተካከል ወይም ኃጢዓት እንዳታደርጉ ለመከልከል ወደ እናንተ ሰዉ አምጥቶ ተጠቅሞ ያውቃል ? አዎ ከሆነ እንዴት አድርጋችሁ ምላሽ ሰጣችሁ ? (ምሳ 10፡ 17፣ 12፡ 1፣ ያዕ 5፡ 19-20)
-
ለፍላጎቱ እና ለእርሱ ሰዎች ፍላጎት በማገልገሏ እና በሂደት ከኃጢዓት ስለጠበቀችዉ አቢግያ ከዳዊት የመጨረሻ(ዋና) ሽልማት ምን ተቀበለች (1ሳሙ 25፡ 40-42) ? እንዴት ከክርስቶስ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ይሆናል ? (ኢሳ 61፡ 10፣ 62፡ 5፣ ራዕ 19፡ 7፣ 21፡ 9)
-
የተቀባዉን ባለመቀበሉ ናባል ላይ ምን ሆነበት (1ሳሙ 25፡ 38) ? በተመሳሳይ መቀባቱን ያልተቀበሉትን ጌት እንዴት ያደርግባቸዋል ? (ዮሐ 3፡ 18፣ 36፣ 12፡ 48፣ ዕብ 10፡ 31)
-
በ 1ሳሙኤል 25 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Samuel 25:32–33
“Then David said to Abigail, ‘Praise to the LORD God of Israel, who sent you to meet me today! Your discernment is blessed, and you are blessed. Today you kept me from participating in bloodshed and avenging myself by my own hand.’”
እስራኤላውያን ለሳሙኤል ሞት ካለቀሱ በኋላ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ በዚያም ናባል የተባለ ሀብታም የንግድ ሰው አገኘ ሰውየውም በጎቹን የሚሸልትበት ወቅት ላይ ነበር ፡፡ ምንም እንኳ ዳዊትና ሰዎቹ ለናባል እረኞች መልካምነትን ቢያሳዩም ናባል ግን ዳዊትና ሰዎቹን ለመባረክና ለእነርሱም ምግብን ለመስጠት እምቢ አለ ፡፡ ናባል የዳዊትን ጥያቄ ውድቅ ካደረገ በኋላ ዳዊት ናባልን ለመበቀልና ለማጥቃት ሰዎቹን በኃይል አስታጠቀ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የናባልን ሚስት አቢጊያን ተጠቅሞ ጣልቃ ገባ ፡፡ እግዚአብሔር የዳዊትን ትኩረት ወደ አምላኩ ለመመለስ የአቢጊያን ብልህነትና ቁርጠኝነት ተጠቀመ ፡፡ እግዚአብሔር ለዳዊት ታማኝ መሆኑን አሳየው እንድሁም ደግሞ ለዳዊት የሚያስፈልገውን ነገር ሰጠው ፡፡
በጣም ውስጥህን የሚነካ እምቢታ ገጥሞሀ ያውቃል ? ያናድዳል አይደል ፡፡ ምናልባት ነጉሩን ለማሳየት ለማስተካከል ወይም ደግሞ ሰዎች የሚገባቸውን ነገር ለመስጠት መበቀል እንዳለብህ ሊሰማህ ይችላል ፡፡ ሌላ ጊዜ እነዲህ ሲሰማህ በረጅሙ ተንፈስ ከዚያም እግዚአብሔር ማስተዋልን እንድሰጥህ ጠይቅ ፡፡ እግዚአብሔር ነገሩን ያያል ያውቅማል ፡፡ እርሱ አንተን ለማገዝ የሆነን ሰው ይልካል ወይም በዙሪያህ ያለን ሰው ሀሳብ ይቀይራል ፡፡ በንዴት ከምትመልስና ነገሮችን በራስህ ከምትወስን ይልቅ ልብህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል ሰላምም ይሸፍንሀል ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ስትታመን ከእርሱም ስትጠበቅ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ ለመጥፎ ሳይሆን ለበጎ ያደርግ ዘንድ እርሱ ያውቃል ፡፡ እርሱ ይታደግሀል ፡፡
“ ዳዊትም አቢግያን አላት ዛሬ እኔን ለመገናኘት አንችን የሰደደ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ ወደ ደም እንዳልሄድ በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን አንቺም የተመሰገንሽ ሁኚ ፡፡ “
- 1ኛ ሳሙኤል 25፡32-33
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 20፡22 –“ ክፉ እመልሳለሁ አትበል እግዚአብሔርን ተማመን እርሱም ያድንሀል ፡፡ “
1ኛ ተሰሎንቄ 5፡15 –“ ማንም ለሌላው በክፉ ፈንተ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ ነገር ግን ሁሉጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ ፡፡ ”
1ኛ ጴጥሮስ 3፡9 –“ ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።