Historical Books 1 Samuel

Cutting Saul's Robe

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 238 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለማስታወስ ያክል በ 1ሳሙኤል ለኢየሱስ ቃላችን የተቀባ ነው ፤ መፅሀፉ ሳዖልን የተቀባ በማድረግ ይጀምራል ነገር ግን ከንጉስ ሳዖል ወደ ዳዊት ተንቀሳቅሷል ፡፡ ዳዊት ምን ይመጣ እንደ ነበር ቢያዉቅም ምንም ነገር ሰዎቹን ከመንገር ዝም አለ ምክንያቱም ገና የእርሱ ጊዜ አልነበረምና ፤ ለምዕራፍ 23 እስከ 24 በጠቅላላ ፍሬ ነገሩ ይህ ነው - ገና የዳዊት ጊዜ አልነበረም ፤ ለክርስቶስ እንደ ግምባር ቀደም በመሆን የዳዊትን አስደናቂ መልክ ያሳያል ፡፡

በምዕራፍ 23 ዳዊት ፍልስጤማዊያንን ተዋጋ (ቁጥር 1-6) ፤ በቁጥር (7-8) ሳዖል ዳዊትን ለመያዝ ጦሩን ወደ ቅዒላ ወሰደ ነገር ግን ዳዊት የአብያታርን ኤፉድ ሳዖል ምን ላይ እንደ ነበር ለመወሰን ተጠቀመበት ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊትን በነገረዉ መሰረት ከቅዒላ ሄደ ከቦታም ቦታ ተንቀሳቀሰ (ቁጥር 9-14) ፡፡ በቁጥር (15፡ 18) ዳዊት እና ዮናታን እንደ ገና ኪዳናቸዉን አደሱ ዮናታንም የዳዊት ሁለተኛዉ አዛዥ ስፍራ ላይ እንደሚሆን ገመተ ፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ዚፋዊያን ሳዖል ዳዊት የት ተደብቆ እንደ ነበር ነገሩት ፡፡ ሳዖል ፍልስጤማዊያን እስኪያጠቁት ድረስ ዳዊትን አሳደደዉ ፤ ዳዊት እንደ ገና አመለጠ (ቁጥር 19-29) ፡፡

ትምህርት

በምዕራፍ 24 ዋይርስቤ ዳዊት የነበሩት አራት ልምዶች ያጋራል፡

የመጀመሪያዉ የዳዊት ጉጉት (ቁጥር 1-4) ፡፡ የዳዊት 600 ሰራዊት በዓይንጋዲ ምድረበዳ በሳዖል 3,000 ጦር(1 ለ 5 ንፅፅር ማለት ነው) የተሳደዱ ነበር (ቁጥር 1-2) ፤ በጉዞዉ መካከል ላይ ሳዖል ወገቡን ሊሞክር ወደ ዋሻ ሄደ ፤ ይህ ሲሆን ዳዊትና ሰዎቹ በዛዉ ዋሻ ዉስጥ ተደብቀዉ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ የሳዖል ወገቡን መመሞከር የማስፈለጉ ሁኔታ የዳዊትን መብሰላ ለማየት እድል የፈጠረ ነበር ፡፡

የሙሴ ህግ አንድ ሰዉ ወገቡን መሞከር በሚያስፈልገዉ ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት የተወሰነ ነበር ፤ ሰዉዬው ከሰፈሩ ዉጪ በመሄድ ጉድጓድ በመቆፈር ስላደረገዉ ጥንቃቄ በማድረግ እንደ ገና ጉድጓዱን ይሸፍናል ፤ ዘዳ (23፡ 12-13) ፤ ምክንያቱ “ አምላክህ እግዚአብሄር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነዉረኛ ነገር እንዳያይብህ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን “ (ዘዳ 23፡ 14) የሚል ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ሳዖል ከሰፈር ዉጪ በመሆኑ በራሱ ላይ በኃል ሊጎዳ የሚችል እንደ ሆነ ያመለክታል ፤ ማንኛዉም የሳዖል ሰላይ ብቁ አልነበሩም ለዚህ ሁኔታ ወይም ይህ አጋጣሚ በእግዚአብሄር ስር ነበር ፡፡ “ ማስታገስ “ የሚለዉ ቃል እግርን መሸፈን ማለት ነዉ ምክንያቱም ካፓ የለበሰ አንድ ሰዉ በዉጨኛዉ ልብሱ በእግሩ ዙሪያ በማድረግ ስለ ሚያደፍጥ (ስለ ሚቀመጥ) ፡፡ ሳዖል ራሱን እያስታገሰ(ወገቡን እየሞከረ) በነበረበት ጊዜ ዳዊት እና መሪዎቹ ለዳዊት ሳዖልን እግዚአብሄር አሳልፎ የሰጠበት ቀን እንደ ነበር እየተነጋገሩ ነበር ፡፡ የትም በመፅሀፍ ላይ ይህ ቃል ኪዳን የተመዘገበ አልነበረም ፡፡ በቁጥር 4 ዳዊት ሳዖል ወደ ነበረበት በቀስታ በመዉረድ በቀስታ የሳዖልን የመጎናፀፊያ ዘርፍ ቆረጠ ፤ (መዝሙር 26፡ 1) ፡፡

ሁለተኛዉ የዳዊት የፀና እምነት (ቁጥር 5-7) ፡፡ ዳዊት ሳዖል በአደገኛ ሁኔታ በነበረበት ጊዜ የዘርፉን አካል በመቁረጥ ሳዖልን በማዋረዱ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማዉ (ቁጥር 5) ፤ ዋይርስቤ “ ከዘርፉ ቁራጭ በመቁረጡ ዳዊት መንግስቱ ወደ እርሱ እየተላለፈ እንደ ነበር እያወጀ እንደ ነበር “ እናም በዚያ “ ዳዊት ንጉሱን ሊገድለዉ እንዳልፈለገዉ “ ይጠቅሳል (1ሳሙ 15፡ 27-28) ፡፡ ዳቪስ ራልፍ ደል የዳዊት ድርጊት “ በእግዚአብሄር ፍቃድ ወይስ በጉጉት “ የተመሰረተ ነበር ወይ በማለት ይጠይቃል ፡፡ የዳዊት ህሊና አስጨነቀዉ ምክንያቱም በ 1ሳሙኤል ስላለዉ ሳዖል የሳሙኤልን ካባ በቀደደዉ ጊዜ እና ለእግዚአብሄር የተቀባዉን አለማክበር አሳይቶ የነበረውን አጋጣሚ ስለ ሚያዉቅ (ዘጸ 22፡ 28) ፡፡ በሆነ ያክል ደረጃ ዳዊት በሳዖል ላይ የተሸለ እድል ለመዉሰድ ወደ ጉጉት ተሰጥቶ ነበር እናም ከዚያም ጉጉት ዳዊት በአሁኑ ሰዓት ዙፋን ላይ ባለዉ በእግዚአብሄር ንጉስ ላይ ጥፋት ማድረጉን አሰበ ፡፡ ምኞት ከእግዚአብሄር እንደ ማይመጣ እናዉቃለን (ያዕ 1፡ 13-15) ፡፡ ዳዊት መስመር እንዳለፈ ስላወቀ ሰዎቹ ሳዖልን እንዲገድሉት አልፈቀደም (ቁጥር 7) ፡፡

ሰዎስተኛዉ የዳዊት ነፃ መዉጣት (ቁጥር 8-15) ፡፡ ዳዊት በመነሳት ከዋሻዉ ዉስጥ ወጣ ፤ ሳዖልንም “ ጌታዬ ንጉሴ ሆይ !“ ብሎ በመጮኽ በማክበር ወደ መሬት ተደፋ (ቁጥር 8) ፤ በ 1ሳሙኤል ዳዊት ለሳዖል የተለያዩ ቃሎችን ተጠቅሟል ሁሉም ደግሞ በማክበር ተጠቀመ፡ አባቴ (24፡ 11)፣ የተቀባ (24፡ 6፣ 10)፣ የኔ ጌታ (24፡ 6፣ 10) እና ንጉስ (24፡ 8፣ 14) ፡፡ ዳዊት ሳዖልን የመጉዳት እቅድ እንዳል ነበረው ገለፀ (ቁጥር 9-15) ፤ ዳዊት ሳዖልን ለመግደል ያልወሰዳቸዉ ሁለት እድሎች ነበሩት ( 1ሳሙ 26፡ 2፣ 7-12፣ ሮሜ 13፡ 1-2) ፡፡ ዳዊት ማድረግ ያስፈለገዉ እያደረገ እንደ ነበር እንዴት እናዉቃለን ? ባሳየዉ ባህሪይ የተነሳ (ማቴ 7፡ 16-20) ፤ ዳዊት በመዝ (54፡ 1) የእምነት ፅናቱን ተናገረ ተናገረ ፡፡

አራተኛዉ የዳዊት ማረጋገጫ (ቁጥር 16-24) ፡፡ ዳዊት መናገሩን ከጨረሰ በኋላ ሳዖል አለቀሰ ፤ ዋይርስቤ ሳዖል “ ከዚህ በፊት እንዳደረገዉ ጊዜያዊ ስሜታዊነትን አሳየ ነገር ግን በፍፁም ስለ ንስሃ እና ስለ ልብ መቀየር በፍፁም እንዳልመጡ “ አመለከተ ፡፡ ሳዖልም የእግዚአብሄር ጥሪ በዳዊት ላይ እንደ ሆነ ወሰነ(አረጋገጠ) (ቁጥር 20) ፤ ዳዊት ሳዖልን እንደ ማይጎዳዉ ማለለት ዳዊት ወደ ምሽጉ ስሄድ ሳዖልም ተመልሶ ወደ ምሽጉ ሄዱ (ቁጥር 21-22) ፡፡

መደምደሚያ

እዚህ ትልቅ ስዕል አለ ፤ 1ጴጥ (2፡ 23)፡ “ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም ነገር ግን በፅድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ “ ፤ ዳዊት እንደ ተቀባ እንደ ተቀባ አይነት አገለገለ ፡፡

ኢሳ (53፡ 7)፡ “ ተጨነቀ ተሰቃየም አፉንም አልከፈተም ፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደ ሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም “ ፤ ይህ የሚመጣዉን የተቀባዉን ከሚያመለክተው ከዳዊት የህይወት አኗኗር ጋር ተመሳሳይ እሳቤ ይመስላል ፤ ብቸኛዉ ልዩነት በፍፁም ምኞት ዉስጥ አልወደቀም የኛ ሞደል ሊሆን የሚገባዉ ያ ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), pp. 272–274.

  2. Wiersbe, p. 273.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ (23፡ 9) ዳዊት ካህኑን አቢያታርን ኤፉዱን እንዲሰጠዉ መጠየቁ አስፈላጊነቱ ምን እንደ ነበር ምንታስባላችሁ ? (ዘጸ 28፡ 30፣ ዘኁ 27፡ 21)
  2. በ 1ሳሙ ( 23፡ 18) ዮናታን እና ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት ኪዳን አደረጉ ፤ ይህ ኪዳን ስላካተተው (ስላጠቃለለው) ምን ታስባላችሁ ? ዮናታን እና ዳዊት ከዚህ በፊት በመካከላቸዉ አላደረጉም ? ( 1ሳሙ18፡ 3፣ 20፡ 16)
  3. በ 1ሳሙ (23፡ 17) ዮናታን ስለ ዳዊት ወደፊት ትንቢት እየተናገረ ነበር ? (1 ሳሙ 16፡ 13)
  4. ዳዊት እድል ሲያገኝ ለምን ሳዖልን አልገደለዉም (1 ሳሙ 24፡ 4) ? ዳዊት የሳዖልን መጎናፀፊያ ዘርፍ በመቁረጡ መጥፎ ስሜት ለምን ተሰማው ? (1 ቆሮ 16፡ 22፣ መዝ 105፡ 15)
  5. በ 1ሳሙኤል (23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 24:5

“Afterward, David’s conscience bothered him because he had cut off the corner of Saul’s robe.”

ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትን በመፈለግ ላይ ሳሉ ሳኦል ወገቡን ይሞክር ዘንድ ከአንድ ወሻ ገባ ፡፡ ይህም ወሻ ዳዊትና ሰዎቹ የተደበቁበት ዋሻ ነበር ፡፡ ሳኦልም ያለ ጠባቂዎቹ በዋሻው ውስጥ ሳለ ዳዊት በዚያ እንዳለ አላወቀም ነበር ፡፡ የዳዊትም ሰዎች ዳዊት እንድገድለው በነገሩት ጊዜ ዳዊት ተነስቶ የሳኦልን መጎናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቄረጠ ፡፡ ነገር ግን ወድያውኑ ዳዊት ይህን እንዳደረገ እግዚአብሔር በቀባው ለይ እጁን በማንሳቱ ህሊናው ወቀሰው ፡፡ ስለዚህም ዳዊት ሰዎቹን ምንም እንኳ ንጉሡ በፊታቸው ቢሆንም በእርሱ ላይ እንዳይነሱ ከለከላቸው ፡፡ ሳኦልም ከዋሻው ከሄደ በኋላ ዳዊት ተከተለውና በታማኝነት ያደረገውን ነገረውና ህሊናውን አነፃ ፡፡ በሰዓቱም ሳኦልና ዳዊት ሰላም ነበሩ ፡፡

እግዚአብሔር የሚከተሉት በንጹህ ህሊና እንድከተሉት ያዛል ይህም ማለት ከጥፋተኝነት ስሜት ነጻ በመሆን ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰው ጋር መደባበቅ የሌለው ግንኙነት እንድኖረን ማለት ነው ፡፡ አንዴ ቆም በልና እግዚአብሔርን ጠይቅ ምናልባት ልትናዘዘው የሚገባ ድርገት ወይም ነግግር ካለ ፡፡ እግዚአብሔርን ጠይቅ እንዴት ነገሮችን ማስተካከል እንደምትችል እንድገልፅልህ ፡፡ምናልባት እንድትሄድና ይቅርታ እንድትጠይቅ ይመራህ ይሆናል ፡፡ ህሊናህን ንጹህ ለማድረግ ድፍረቱ ሲኖርህ እግዚአብሔር ደግሞ ከተሸከምከው ሸክም ያሳርፍሀል ፡፡ ነጻነትን ያቀዳጅሀል ደግሞም በእርሱ ስትታመን ነገርን ሁሉ ለበጎ ያደርግ ዘንድ እርሱ ያውቃል ፡፡እግዚአብሔር በታማኝነትህ ጊዜ በማያልቅ ፍቅሩና ፀጋው ያገኝሀል ፡፡

“ ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለ ቄረጠ የዳዊት ልብ በኃዘን ተመታ ፡፡ “

-1ኛ ሳሙኤል 24፡5

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኢሳያስ 53፡7 –“ ተጨነቀ ተሣቃየም አፉንም አልከፈትም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሻላቶቹም ፊት ዝም አእንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈትም ፡፡”

ሐዋርያት ስራ 24፡16 –“ ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ ፡፡

1ኛ ጴጥሮስ 3፡16 –“ በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁነ የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንድያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ ፡፡ “