Historical Books 1 Samuel

David's Journey Through Israel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 237 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ሳሙኤል 21 በማጠቃለል እንጀምራለን ፤ በቁጥር 1-6 ዳዊት በሰሜን በኩል ወደ ሚገኘዉ ወደ ኖብ ካህን ወደ አቢሜሌክ ሸሸ ፤ ዳዊት እርቦት ስለ ነበር ለካህኑ ተለይቶ የነበረዉን እንጀራ ጠየቀ ፤ በዚያም ዳዊት የጦር መሳሪያ ጠየቀ የጎልያድም ሰይፍ ተሰጠው ፡፡ ከሳዖል አገልጋዮች አንዱ የእረኞች አለቃ በዚያ ለመሆን ተከሰተ ምን እንደሆነም አየ (ቁጥር 7-9) ፤ ዳዊት ከዚያም በመሸሽ ወደ ጌትም ንጉስ አንኩስ ሄደ ፤ ዳዊት አንጉስን ፈራው የታመመም በመሆን አስመሰለ (10-15) ፡፡ ከምዕራፍ 21 ለእኛ የሚጠቅም የምንወስደው አቢሜሌክ ዳዊትን ሁለት ነገሮች - የተቀደሰዉን እንጀራ እና የጎልያድን ሰይፍ እንደ ሰጠው ነው ፡፡ የሳዖል አገልጋይ ኤዶማዊዉ ዶይቅም ሁሉንም ተመለከተ ፡፡ በምዕራፍ 21-22 የታሪኩ መስመር አካል የዳዊት ጉዞ ነው ፤ ዳዊት የተቀባ ነው የእግዚአብሄርም መንፈስ ሳዖልን በመተዉ ወደ ዳዊት ላይ መጣ ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (22፡ 1-2)፡ ዳዊት ከጌት በመሄድ በዓዶላማ ዋሻ ተደበቀ (ቁጥር 1) ፤ ለዳዊት በጥሪዉ መጓዝ ጉዞ ነው፡፡ የመቀባት ሂደት ተዓምራዊ እንደ ሆነ እና የተቀባ ሁሉም እንዳለዉ ለማሰብ እናዘነብላለን (እንሞክራለን) ፤ እዉነታው ግን ሂደት እና ጉዙ መሆኑ ነው ፡፡ የዳዊት ቤተሰቦች በዚያ እንደ ነበር ሰሙ ተቀላቀሉትም (ቁጥር 2) ፡፡

በወንድሞቹ መካከል ችግር እንደ ነበር አስታዉሱ ነገር ግን አሁን እንደ ቤተሰብ ሁሉም በአንድ ላይ መጡ ፤ ከእናንተ መካከል አንዳንዶቻችሁ በእግዚአብሄር የማይጓዙ እና ጥሪያችሁን የማይደግፉ የቤተሰብ አባላት ይኖሯችኋል ፤ በጊዜዉ የዳዊት ቤተሰቦች ካሉበት መጡ የእናንተም እንዲሁ ሊመጡ ይችላሉ ፡፡

ዋሻዉ ከኤላ ሸለቆ በስተደቡብ ሁለት ማይል፣ ከጌት ደቡብ ምስራቅ 10 ማይል እና ከቤቴ ልሄም ሰሜን ምስራቅ 10 ማይል ላይ ይገኝ ነበር ፡፡ በአካባቢዉ “ ተስፋ የቆረጡ፣ ብድር ያለበት ወይም ቅር የተሰኙ “ እና እንዲመራቸዉ ዳዊትን የመረጡትን 400 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ ትልልቅ ዋሶች ናቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ኮንስታብል ስለ እነዚህ ሰዎች “ ዳዊት በተለያዩ ምክንያቶች በሳዖል መንግስት ተስፋ የቆረጡ የነበሩ እና ለዉጥ ይፈልጉ የነበሩ ሰዎች ስብስብ መሪ እንደ ሆነ “ ይናገራል ፤ ዳዊት መዝሙር 57 እና 142 ከዋሻዉ ዉስጥ በመሆን በዚህ አሳብ ፅፏል ፡፡ ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ሲጮህ እግዚአብሄር እርሱን በሚረዱት ሰዎች ይከብበዉ ጀመረ ፤ ቆይቶ እነዚህ 400 ሰዎች “ ኃያላን “ ተብለዉ ይጠራሉ (1ዜና 11፡ 16-18) ፡፡

ዋይርስቤ ዳዊት በሚረዱት ከይሁዳ እና ከቢኒያም ነገድ በሆኑ ለእርሱ ሊዋጉ በመጡ ሰዎች ክልል ዉስጥ እንደ ነበር አመልክቷል ፤ ዳዊት በተጠማ ጊዜ ከይሁዳ ነገድ ሰዎስት ሰዎች ከቤቴ ልሄም ጉድጓድ ዉስጥ ዉሃ ለመስጠት ህይወታቸዉን አደጋ ላይ ጥለዋል ፤ ይህ ዳዊት በቀላሉ ሊወስደዉ እና ሊቀበለዉ የማይችለዉ ነበር ስለሆነም ለእግዚአብሄር እንደ ሚጠታ መስዋዕት ዉሃዉን አፈሰሰው ፡፡ ዳዊት ለእርዳታ የቡድኑን አባላት አልወሰደም ፤ ጊዜዉ ሲጨምር የዳዊት 400 ሰዎች ወደ 600 ጨመረ (1ሳሙ 23፡ 13) ፤ ይህ ሳዖል ከነበረው በጣም የሚያንስ ኃይል ነበር ነገር ግን ይህን ጉዞ ከዳዊት ጋር ለመጓዝ ፈቃደኞች ነበሩ ፡፡

1-ሳሙኤል (22፡ 3-5)፡ ዳዊት ወደ ዳዊት ቅድም ሴት አያቱ ወደ ሩት ቤት ወደ ሞዓብ ሄደ ፤ ዳዊት ለደህንነታቸዉ ቤተሰቦቹ በሞዓብ እንዲቆዩ እንዲፈቅድለት ንጉሱን ጠየቀው (ቁጥር 3) ፡፡ ያረጁ ቤተሰቦቻችንንየሚበልጡንን) መጠበቅ እና መዉደድ አስፈላጊ ነው ፤ በዳዊት ጥሪ ርዝመት ዉስጥ ዳዊት ቤተሰቦቹ ደህና እንደ ሆኑ አደረገ ፡፡ “ ምሽግ “ ወይም በዕብራዊያን መሱዳ የሚለዉ ቃል በቁጥር 4-5 ትልቅ ምሽግ በማለት ተጠቅሷል ፤ አንዳንድ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ሙሁራን ከጨዉ ባህር ምዕራብ በኩል የሚገኘዉን መሳድን እንደ ሚጠቅስ ያመለክታሉ ፡፡ መሱዳ “ በምድረበዳ ተፈጥሮአዊ መደበቂያ ስፍራ “ የሚለዉን ሊያመለክት ይችላል ፡፡ ይህ የትም ይሁን ዳዊት በዚያ እንደቆየ ቤተሰቦቹ በሞዓብ ነበሩ ፤ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጣና ወደ ይሁዳ እንዲመለስ ነገረው ፤ ዳዊትም ወደ ሄሬት ወይም “ ጥሻ “ ሄደ (ቁጥር 5) ፡፡ በዳዊት ህይወት በስልጣን ዘመኑ ዉስጥ ጋድ ትንቢታዊ ድምፅ ተናጋሪ ነበር (2ሳሙ 24፡ 11) ፡፡ ነቢዩ ዳዊትን ቀጣዩን እርምጃ እንዲራመድ ነገረው ፤ ሳዖል በፍፁም የትንቢታዊ ቃል ድምፅ ምሪት አልነበረውም ፡፡ ጋድ የንጉሱ ትንቢት ተናጋሪ ነበር እንዲሁም “ ለእግዚአብሄር መቅደስ የሙዚቃ መሪያዎች አገልግሎት እንዲተክል(እንዲረዳ) ዳዊትን ያዘዉ ነበር “ ( 2ዜና 29፡ 25) ፡፡ ይህ ትንቢታዊ ድምፅ ለምን ነበር ለዳዊት በጣም ያስፈለገው ?ዳቪስ ራልፍ ዴል “ ተስፋ መቁረጥ ቀልድ አይደለም ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ እና ዝምታ ሊታገሱዓቸዉ የማይችሉ እንደ ሆኑ ይናገራል “ ፡፡ ትንቢታዊ ቃል በመንፈስ ቅዱስ በኩል ከእግዚአብሄር ብቻ ነዉ ሊመጣ የሚችለው (2ጴጥ 1፡ 19-21) ፤ ለትንቢታዊ ቃል የማንከፍት ከሆነ እግዚአብሄር ለእኛ የሚናገረንን እንስተዋለን ፡፡

1-ሳሙኤል (22፡ 6-10)፡ ሳዖል ወደ ዳዊት ስለ ሄዱት ሰዎች ሰማ ፈራም ፤ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለእነርሱ ለታማኝነታቸዉ ይከፍላቸዉ እንደ ነበር ጠየቃቸው (ቁጥር 6-8) ፤ የሳዖል አገልጋይ ዶይቅ ዳዊት እንጀራ እና ሰይፍ በተሰጠዉ ጊዜ አቤሜሌክ ላይ አይቶት የነበረውን ተናገረ (ቁጥር 9-10) ፡፡

1-ሳሙኤል (22፡ 11-23)፡ ሳዖል ካህኑን አብሜሌክን እንዲሁም ካህናት የነበሩትን ቤተሰቦቹን በመሰብሰብ በእርሱ ላይ ከዳዊት ጋር ለምን እንዳሴሩበት ጠየቀው (ቁጥር 11-13) ፤ ይህ ህጋዊ ያልሆነ ፍርድ መጀመሪያ ነበር ፡፡ ሳኦል በአቢሜሌክ ላይ የሀሰት ክስ አደረገ አቢሜሌክም ክሱን አለተቀበለም (ቁጥር 14-15) ፤ ዳቪስ ራልፍ ደል ይህ “ መሸፈኛዉን በማዉለቅ ሳዖል የእግዚአብሄርን ካህን በአስጨኳይ በግፍ እንደ ሚገድል ሀሰተኛዉ ክርስቶስ የሚመስለዉን በእዉነት በማሳየት “ በራሱ በእግዚአብሄር ካህናት ላይ እንደ ሄደ አመልክቷል ፡፡ ሳዖል ጠባቂዎቹን ከዳዊት በጉል ወግነዉ የነበሩትን ካህናት እንዲገድሉ አዘዛቸው ነገር ግን አገልጋዮቹ የእግዚአብሄር ካሃናቶች አልገደሉም (ቁጥር 17) ፤ ሳዖልም ዶይቅን ካህናቱን እንዲገድል ላከው ፤ ዶይቅም የካህናት ልብስ የለበሱ 85 ሰዎችን ገደለ ከእነርሱም ጋር ሁሉንም ወንዶች፣ ሴቶች፣ልጆች፣ የሚጠቡትን እና እንሰሳቶች በኖብ ከተማ ያሉትን ሁሉ ገደለ (ቁጥር 18-19) ፡፡ ከካህናቱ አንድ ብቻ በማምለጥ ምንድን እንደ ሆነ ለዳዊት ሊናገር ሮጠ (ቁጥር 20) ፤ ዳዊት ስለ ሞቱ ተመለከተ ምክንያቱም አቢሜሌክ እርሱን በረዳበት ጊዜ ዶይቅን በዚያ አይቶት ስለ ነበር ዶይቅን ምንድን ተፈጥሮ እንደ ነበር ለሳዖል ከመናገር የሚከለክለዉ ስለሌለ (ቁጥር 22-23) ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት ኃያላን ሰዎች ተብሎ የሚጠራ ቡድን ነበረው ፤ በዛ ቡድን ዉስጥ እግዚአብሄር የንጉሱን ስም የዳዊትን፣ የነቢዩን ስም የጋድን እና የካህኑን ስም አቢሜሌክን ከፍ ማድረግ ቀጠለ ፡፡ እግዚአብሄር በግልፅ ለህዝቡ አዲስ የወይን አቁማዳ በማምጣት ስራ ላይ ነበር ፤ ዛሬም የእግዚአብሄርን እቅድ የሚሸከሙ(የሚያደርጉ) ቅሬታዎችን እያዘጋጀ ነው ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Samuel, p. 201; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1samuel.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1st Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 266.

  3. Wiersbe, p. 266.

  4. Wiersbe, p. 267.

  5. Dale Ralph Davis, 1 Samuel: Looking on the Heart (Fearn, Ross-shire, Great Britain: Christian Focus Publications, 2000, reprinted 2017), p. 223.

  6. Davis, p. 226.

ጥያቄዎች

  1. ሰዉዬዉ ራሱን ከሴት ጠብቆ ባይሆን ኖሩ የተቀደሰዉን እንጀራ መብላት ለምን ነበር ስህተት የሚሆነው (ዘሌ 15፡ 18) ? በአጠቃላይ የተቀደሰ እንጀራ መብላት ተቀባይነት ያለዉ ነበር ? (ማቴ 12፡ 3-4)
  2. ዳዊት በጌት ንጉስ ፊት እብድ በመሆን ለምን አስመሰለ ?
  3. ሰዎቹን ከጉዳያቸዉ ጋር ወደ ዳዊት እንዲመጡ ያደረጋቸዉ ምን እንደ ሆነ ታሳባላችሁ (1 ሳሙ 22፡ 2) ? በነገራችሁ በምትታገሉ ጊዜ የሄዱ(የመጡ) የሆኑ ሰዎች ነበራችሁ ? ከሰዎቹ ዉስጥ በእግዚአብሄር ቅባት የተጓዘዉ እሱ ወይስ እርሷ ? ያን ሰዉ ለመጥራት የሆነ ጊዜ በመዉሰድ በዚህ ሳምንት ለምን አመሰግናለሁ አትሉትም ?
  4. ሳዖል አቤሜሌክን እና ቤተሰቦቹን እንዲሁም የኖብን ሰዎች ለምን ገደለ (1 ሳሙ 2፡ 30-33) ?
  5. በ 1ሳሙኤል (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 22:5

“Then the prophet Gad said to David, ‘Don’t stay in the stronghold. Leave and return to the land of Judah.’ So David left and went to the forest of Hereth.”

ዳዊት ሳኦል ሊገድለው እንደሚፈልገው አውቆ ነፍሱን ከሳኦል እጅ ለማዳን ሸሸ ፡፡ እግዚአብሔር የተለያዩ ሰዎችን ተጥቅሟል ለዳዊት ህይወት ለመናገርና ዳዊትን ወደ ቀጣዩ አቅጣጫ ለመምራት ማለትም ዳዊትን ከኖብ ወደ ጌት ከዚያም ደግሞ ወደ ዓዶላም ዋሻ እንደገናም ወደ ይሁዳ ምድር ፡፡ ዳዊት በህይወቱ ላይ የንግስና ቅባት ነበረው ነገር ግን ወደ ንግስና የሚወሰደው መንገድ ቀላልና ቀጥ ያለ አልነበረም ፡፡

ስለራስህ መንገድ አስበህ ታውቃለህ ? መንፈስ ቅዱስ የተቀባውን ይመራል እግዚአብሔርም ለአንተ ህይወት ለመናገር ሰዎችን ይጠቀማል ፡፡ ምናልባት መንገዱ አንተ እንደጠበከው ላይሆን ይችላል መቆም አንዳንዴም ደግሞ መጠማዘዝ ሊኖር ይችላል ፡፡ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ ማድረግን እንዳትረሳ ፡፡ አርሱ በመንግስቱ ውስጥ እንድታገለግል ወደ ሚፈልገው ስፍራ ይወስድሀል ፡፡ ስትወጣ ክእርሱ ጋር ተነጋገር እርሱንም እመነው ፡፡

“ ነብዩ ጋድም ዳዊትን ተነስተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአምባው ውስጥ አትቀመጥ አለው ዳዊትም ተነስቶ ወደ ሔሬት ዱር መጣ ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 22፡5

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙር 118(119)፡105 –“ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሀን ነው ፡፡ “

ምሳል 3፡5-6 –“ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሀል ፡፡ “

ዕብረውያን 12፡1-2 –“ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙርያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን የእምነታችንን ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ ፡፡