Historical Books 1 Samuel

Covenant Relationships

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 236 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለ 1ሳሙኤል ቃላችን የተቀባ ነው ፡፡ በ 1ሳሙኤል 19 ነገሮችን ተወሳስበዋል ፤ ሳዖል ልጁን ዮናታንን ዳዊትን እንዲገድል ነገረው (ቁጥር 1) ዮናታንም ለዳዊት ሳዖል ምን እንዲያደርግበት የነገረዉን ነገረው (ቁጥር 2-3) ፡፡ ዮናታን ወደ አባቱ ተመልሶ በመሄድ የዳዊትን መልካምነት ነገረው ሳዖልም ዳዊትን አልገድለዉም አለ ፤ ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳዖል መለሶ አመጣዉ አንደ ገናም ዳዊት ሳዖልን አገለገለዉ (ቁጥር 4-8) ፡፡ ነገር ግን ክፉዉ መንፈስ ወደ ሳዖል በተመለሰበት ጊዜ ሳዖል ዳዊትን ከግንቡ ጋር በጦር ሊያጣብቀዉ ሞከረ ፤ ዳዊት ስለ ህይወቱ ያመልጥ ነበር (ቁጥር 9-10) ፡፡ ሳዖል ለእርሱ የዳዊትን ቤት ፈለገው ነገር ግን ሚስቱ ሚልኮል ዳዊት ታሞ የተጋደመ እንዲመስል የቤት ተራፊም (ጣዖት) በአልጋዉ ላይ በማስቀመጥ እንዲያመልጥ እረዳችዉ (ቁጥር 11-14) ፤ ሳዖል አገልጋዮቹን ዳዊትን ከነአልጋዉ እንዲያመጡት ላካቸዉ ነገር ግን ተራፊዉን ብቻ አገኙ (ቁጥር 15-18) ፡፡ ሳዖል ዳዊት የት እንደ ሚገኝ በሰማ ጊዜ በዚያ መልዕክተኞችን ሰደደ ነገር ግን የነቢያትን ጉባኤ አገኙ ትንቢትም መናገር ጀመሩ ፤ ይህ ሰዎስት ጊዜ ሆነ (ቁጥር 19-21) ፡፡ ከዚያም ሳዖል ራሱ ሄደ የእግዚአብሄር መንፈስ እርሱ ላይ ወረደበት በብዙም ትንቢት መናገር ጀመረ (ቁጥር 22-23) ፤ ሳዖል ልብሶቹንም በማዉለቅ ወደቀ ቀኑን ሁሉ እና ምሽቱን ሁሉ እርቃኑን ተኛ (ቁጥር 24) ፡፡ ታሪኩ በምዕራፍ 20 ይቀጥላል ፡፡

ትምህርት

ዴል ራለፍ ዳቪስ በዚህ ምዕራፍ የተተገበሩ አራት ትዕይቶችን አጉልቶ ያሳያል፡

የመጀመሪያዉ ትዕይንት በዮናታን ፊት ነበር ፡፡ የመጀመሪያዉ እርምጃ ስለ አደጋዉ መከራከር ነበር (ቁጥር 1-4) ፤ ዳዊት ከነዋትዘራማ ሸሸ ዮናታንንም አገኘው ሳዖል ለምን ሊገድለዉ እየሞከረ እንደ ሆነም ጠየቀዉም (ቁጥር 1) ፡፡ ዳቪስ ዳዊት ወደ ዮናታን መሄድ የቻለው ኪዳናቸዉ ዳዊትን እርዳታ (ዋስትና) ስለሰጠዉ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ዮናታን ሳዖል ዳዊትን እንደ ማይገድለዉ ቃል ገብቷል አለው (ቁጥር 2) ፤ ነገር ግን ዳዊት ሳዖል ከዮናታን መረጃ እያገኘ እንደ ነበር ተከላከለው (ቁጥር 3) ፡፡ ዮናታን ከዳዊት ጋር ያለዉን ኪዳን አረጋገጠለት (1 ሳሙ 18፡ 1-5) ፤ “ ነፍስህ የወደደችዉን ሁሉ አደርግልሀለሁ አለው “ (ቁጥር 4) ፡፡ ኪዳኑ መታደስ ብቻ አልነበረም ጨመረም(ሰፋ) እንጂ ፡፡

ሁለተኛዉ እርምጃ ፈተና ማዘጋጀት ነበር (ቁጥር 5-7) ፡፡ ዳዊት ቀጣዩ ቀን አዲስ ጨረቃ የኃይማኖታዊ ስርዓት መጀመሪያ ስለ ነበር እራቱን በመዝለል ከንጉሱ ፊት ለሰዎስት ቀን እደበቃለሁ ለው (ቁጥር 5) ፤ የመባቻ በዓል ለአምልኮ ጊዜ ቤተሰቦች በአንድ ላይ በሚመጡ ጊዜ የሚሰዋ ምግብ ነበር (ዘኁ 10፡ 10) ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት የሳዖል ቤተሰብ አካል ስለ ነበር መገኘት ይጠበቅበታል ፡፡ ፈተናው ሳዖል የዳዊት መገኘትን በማጣቱ እንዴት በመቅረቱ እንደሚሆን ማየት ነበር (ቁጥር 5-6) ፤ ዳዊት በስፍራዉ ዮናታን ለሳዖል እንዲዋሽለት አስቀመጠው ፡፡ ፈተናው ሳዖል በዳዊት አለመገኘት ጥሩ ተሰማዉ ወይስ የተበሳጨ በመሆን ክፉ አሳብ ነበረዉ የሚለዉን ያሳያል (ቁጥር 7) ፡፡

ዮናታን ስለ ኪዳኑ ለመነ (ቁጥር 8-9) ፡፡ ዳዊት የተሳሳት ነግር አድርጌ ከነበር ዮናታንን ግደለኝ አለው ፤ “ በታማኝነት መነጋገር “(የማይወላዉል) የሚለዉ ቃል በመልካም እንደ መነጋገር ወይም በመተማመን መነጋገር መረዳት ይቻላል፡፡ በKJV ቃሉ እንደ “ ምህረት “ 250 ጊዜ የተተረጎመ ነው ፤ ዳቪስ የዚህን ሂደት ቅደም ተከተል፡ “ ፍቅር ራሱ በኪዳን ዉስጥ ስለሚሰጥ ደስተኛ የሆነ ቃል ኪዳን ለፍቅር የተሰጠ ነው ፤ የኪዳኑ አጋሮችም በዚያ ቃል ኪዳን በደህና በመኖር ዳዊትም በዚህ እንዳደረገዉ ስለ ኪዳኑ እንደ ሚፀልዩ “ ይገልፃል ፡፡ ዮናታን የዳዊትን ንግግር ተቃወመ ፤ ዮናታን ለዳዊት የታመነ በመሆን የሳዖልን አሳብ እንዲያዉቅ ፈቀደለት (ቁጥር 9) ፡፡

ዮናታን እንደ ገና የኪዳኑን ቃል ኪዳን አረጋገጠ (ቁጥር 10-17) ፡፡ ዳዊት እና ዮናታን የሳዖልን ምላሽ ምን እንደ ሆነ ለመነጋገር “ ልምምድ “ ለማድረግ ወደ ሜዳ ወጡ ፤ ዮናታን ሳዖል በዳዊት ደስተኛ ከነበር ለዳዊት ቃል እንደ ሚልክለት ቃል ገባ (ቁጥር 12-13) ፡፡ ኪዳኑ ለአልተለመደዉ መታመን ተሸከርካሪ(መሽከርከሪያ) ሰጠ ፤ ዮናታን ዳዊት ንጉስ እንደ ነበር እና ምን ይመጣ እንደ ነበር አስተዉሏል ፤ ዮናታን ዳዊትን ከዮናታን ሞት በኋላ ለእርሱና ለቤቱ ደግነትን እንዲያደርግ በጠየቀዉ ጊዜ የበለጠ(ተጨማሪን) ተመለከተ (ቁጥር 14-16) ፤ ልምድ የነበረው አንድ አዲስ ንጉስ ማንኙዉንም እና ለንጉሱ አገዛዝ አስፈሪ የሚመስሉ ቤተሰቦቻቸዉን ሁሉ ያጠፋል (1ነገ 15፡ 29) ፡፡ ዋይርስቤ “ ዳዊት በፍፁም ድፍረት አልነበረዉም ምክንያቱም ዮናታን በዉጊያ ተገድሎ ስለ ነበር ዳዊትም የሳዖልን ሴት ልጅ ሜልኮልን እንደ ሚስቱ ስላልተቀበላት ያለልጅ ሞተች ፤ ልጅ ኖሯት ቢሆን በንግስና መስመሩ ላይ ዉዝግብ ያመጣ እንደ ነበር “ አመልክቷል ፡፡ ዮናታንም እንደ ገና ዳዊትን ለመርዳት በፍቅሩ ማለለት (ቁጥር 17) ፡፡

ዮናታን እና ዳዊትም አስፈላጊ ምልክቶችን ይወስኑ ነበር (ቁጥር 18-23) ፤ ዮናታን ዳዊትን በሜዳዉ ላይ በአንድ ትላቅ አለት አጠገብ እንዲደበቅ ነገረው ፤ ዮናታን ሰዎስት ፍላፃዎች ወደ አለቱ ይወረዉራል ፤ ከዚያም ዮናታን ፍላፃዎቹን(ከአለቱ ወዲህ እንዲከት ወይም ከአለቱ አልፎ) እንዲፈልግ ለወጣቱ በሚሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ዳዊት ለመመለስ ደህና እንደ ሆነ ያውቃል ፡፡ በቁጥር 23 ዮናታን አሁንም እንደ ገና ኪዳናቸዉን አረጋገጠ ፡፡

ሰዎስተኛው ትዕይንት ሳዖል ገበታ ላይ ነበር (ቁጥር 24-23) ፡፡ የዳዊት ስፍራ በሳዖል ገበታ ላይ ለሁለት ቀን ቦዶ ሆነ ቆየ ፤ በሁለተኛዉ ቀን ሳዖል ዳዊት የት እንደ ነበር በጠየቀ ጊዜ ዮናታን ዳዊት ቤቴ ልሄም ስለመሄዱ ዉሸቱን ነገረው (ቁጥር 24-29) ፤ ሳዖል በንዴት በመመለስ ዮናታን ላይ ስድብ አወረደበት (ቁጥር 30) ፡፡ ሳዖል የዮናታን ታማኝነት ከዳዊት ጋር እንደ ነበር በማወቁ ለዳዊት የዮናታን ታማኝነት ዮናታንን ዙፋን እንደ ሚያስከፍለዉ(እንደ ሚያሳጣው) ገለፀ (ቁጥር 31) ፤ ዋይርስቤ “ ማንም የሳዖል ልጅ በፍፁም ዙፋኑን እንደ ማይወርሱ እና ዳዊት የእግዚአብሄር ምርጫ እንደ ነበር እግዚአብሄር በጣም ግልፅ አድርጎት ነበር ስለሆነም ሳዖል ከእግዚአብሄር ፍቃድ ጋር እየታገለ ነበር ዮናታንንም ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርግ እየጠየቀዉ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ዮናታን ለሳዖል ንዴት በእርሱ ላይ ዳዊት ምንድን እንዳደረገበት በመጠየቅ በመለሰለት ጊዜ ሳዖል በልጁ ላይ ጦሩን በመወርወር ሊገድለዉ ሞከረ (ቁጥር 32-33) ፡፡ ዮናታን “ በዳዊት ላይ በአባቱ አሳፋሪ ባህሪይ “ ተበሳጨ (ቁጥር 33) ፡፡ ዮናታን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጥላ ነው (ሉቃ 14፡ 26) ፡፡

አራተኛው ትዕይንት በሜዳዉ ላይ ነበር (ቁጥር 35-40) ፡፡ ዮናታን ለዳዊት መልዕክቱን ለማድረስ እቅዳቸዉን ተከተለ (ቁጥር 35-40) ፤ ዳዊት ወደ መሬት ተደፋ ፤ ከዚያም እሱ እና ዮናታን በአንድ ላይ አለቀሱ ምክንያቱም ዳዊት ሊሸሽ ስለነበር (ቁጥር 41-42) ፡፡ ዮናታን ዳዊትን እግዚአብሄር ጋሻህ ነው በማለት “ በደህና እንዲሄድ “ ወይም “ በሰላም እንዲሄድ “ ነገረው ፡፡

መደምደሚያ

በኪዳኑ ምክንያት ሰላም አለ ፤ በክርስቶስ ብቻ ሰላም ማግኘት እንችላለን፡

ሮሜ (5፡ 1፣ 3)፡ “ እንግዲህ በእምነት ከፀደቅን በእግዚአብሄር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ …. ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግስትን እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን “ ፡፡

ዮሐ (16፡ 33)፡ “ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ ! እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ “ ፤ በክርስቶስ ኪዳን ሊኖራችሁ ስለ ሚችል ብቻዉን ሰላም ይሰጣችኋል ፡፡

ቆላ (3፡ 15)፡ “ በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ ፤ የምታመሰግኑ ሁኑ ! “ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነታችሁ በህይወታችሁ ፤ በቅባት የመጓዝ ዉበት ይህ ነው ፡፡

  1. Dale Ralph Davis, 1 Samuel: Looking on the Heart (Fearn, Ross-shire, Great Britain: Christian Focus Publications, 2000, reprinted 2017), pp. 204–205.

  2. Davis, p. 205.

  3. Davis, p. 207.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Bible Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 262.

  5. Wiersbe, p. 263.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ (19፡ 5) የዮናታን ንግግር ማን ሲገለፅ ከተባለዉ ጋር ይመሳሰላል ? (ሉቃ 23፡ 4)
  2. በመስኮት ወርዶ እንዲያመልጥ ዳዊትን ማን ረዳው ? ዳዊት እንዲሄድ ስለ መፍቀዷ በጠየቃት ጊዜ ለአባቷ ምን ነገረችዉ ? (1 ሳሙ 19፡ 17)
  3. በ 1ሳሙ (19፡ 13) በማታለሉ የቤት ዉስጥ ተራፊም ጥቅም ላይ ዉሎ ነበር ፤ በዚያ ለምን ተራፊም(ጣዖት) እንደ ኖረ ምን ታስባላችሁ ? ይህ የተገኘዉ በማን ቤት ዉስጥ ነበር ?
  4. ሳዖል መልዕክተኞችን ዳዊትን መልሰዉ ከአርማቴ በነዋትዘራማ እናዲያመጡት ላከ በእያንዳንዷ ጊዜ ምን ተፈጠረ (1 ሳሙ 19፡ 20-21) ? ሳዖል ራሱ ወደ አርማቴ በሄደ ጊዜስ ምን ተፈጠረ (1ሳሙ 19፡ 22-24) ? በተወሰነ ቦታ የተለየ ቅባት ወይም የእግዚአብሄርን ኃይል ተመልክታችሁ ወይም ቀምሳችሁ ታውቃላችሁ ? (1 ሳሙ 10፡ 5-6)
  5. በምዕራፍ 19 እና 20 ሳዖል በተደጋጋሚ ዳዊትን ሊገድለዉ ሞከረ ዳዊት ፤ እንደ ንጉስ በሳሙኤል እንደ ተቀባ ያውቃል ? ዳዊትን ለመግደል የፍላጎቱ ስር መሰረቱ ምን ይመስላል (1 ሳሙ 20፡ 31) ? በ 1ሳሙ (15፡ 28) ሳሙኤል የነገረዉን ሳዖል አላመነም ነበር ?
  6. በ 1 ሳሙኤል (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 20:42

“Jonathan then said to David, ‘Go in the assurance the two of us pledged in the name of the LORD when we said: The LORD will be a witness between you and me and between my offspring and your offspring forever.’ Then David left, and Jonathan went into the city.”

ሳኦል ዳዊትን ለመግደል አልሞ በተደጋጋሚ ዳዊትን አጠቃው ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊትን አዳነው ፡፡ የሳኦል የራሱ ልጅ የሆነው ዮናታን ምንም እንኳ የራሱን ህይወትና ካባቱ ጋር ያለውን ግንኙነት አደጋ ላይ ቢጥልም ዳዊትን እንደ ወንድሙ ይወደው ስለ ነበር ዳዊትን ረዳው ጠበቀውም ፡፡ በተጨማሪም ዮናታን ዳዊት ከሳኦል ይሸሽ ዘንድ ለመርዳት ዕቅድን አዘጋጀ ፡፡ ዮናታንና ዳዊት ከመለያየታቸው በፊት እርስ በእርስ ለመጠባበቅ ቃልኪዳንን አደረጉ ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሚመጣው ምዘራቸው መካከል እንድሁ እንድሆን ተማማሉ ፡፡ ዮናታንም ዳዊትን እግዚአብሔር በመካከላቸው ስለነበረ “ በሰላም ሂድ “አለው ፡፡ ሁለቱም ሁልጊዜ ጓደኞች ሆኑ ፡፡

አንተንም እግዚአብሔር በዚያ አይነት ሰላም ይልክሀል ፡፡ እግዚአብሔር በሰላሙ ይጎበኝሀል ምክንያቱም አንተ ከእርሱ ጋር ኪዳን ስላለህ ፡፡በመንገድህ ምንም ይምጣ ኢየሱስ ሰላምን ይሰጥሀል ፡፡እርሱ አለምን አሸንፏልና የእርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም በጭንቅ መሀል ቢሆን እንኳ ጠንካራና ብርቱዎች ናቸው ፡፡እርሱ ይወድሀል እናም አንተ ስለ ፍቅሩ እርግጠኛ ሆነህ እንድትመላለስ ይፈልጋል ፡፡ በዚህ አለም ብዙ እርግጠኛ ያልሆኑ ነገሮች አሉ ነገረግን በክርስቶስ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ ምንም ነገር ቢሆን ፡፡

“ ዮናታንም ዳዊትን በደኅና ሂድ እነሆ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው ፡፡ ዳዊትም ተነስቶ ሄደ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ ፡፡ “

-1ኛ ሳሙኤል 20፡42

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 16፡33 –“ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንድህንላችሁ ይህን ተናግሬችኋለሁ ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ፡፡ “

ሮሞ 5፡1-3 –“ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክረስቶስ ሰላምን እንያዝ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ፀጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል በእግዚብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ነገር ግን መከራ ትዕግስትን እንድያደርግ ትዕግስትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንድያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፡፡ “

ቄላስያስ 3፡15 –“ በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ የምታመሰግኑም ሁኑ ፡፡ “