The Lord Was With David
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የፍልስጤማዉያንን ጎበዝ ጎልያድ እንደ ንጉስ በቅባቱ በመጓዝ ዳዊት ያለፋበትን ታሪክ ጨርሰናል ፡፡ ዳዊት በ 12 አመቱ ከቤተሱ በግሉ ተቀባ፣ በ 17 አመቱ ደግሞ በመግጠም ጎልያድን አሸነፈ ፤ ይሁን እንጂ ከ 10 አመታት በላይ ዳዊት እንደ ጊዜያዊ ንጉስ ሳዖል በማምለጥ ቆየ ፡፡ በእነዚህ ጊዜ ሳዖል ኃላፊነት ላይ ነበር ነገር ግን ህዝቡ የዳዊትን መሪነት ፈለገ ፡፡ ዋይርስቤ “ በእስር አመቱ ጊዜ ወይም ዳዊት ኮብልሎ በነበረበት እግዚአብሄር በተደጋጋሚ የሳዖልብ እቅድ ብቻ አልነበረም የሚያሰናክለዉ ዳዊትን የተሸለ በማድረግ ጀግና እና የእምነት ሰዉ ሊያደርገዉ የንጉሱን ጠላትነት ተጠቀመበትም እንጂ ፤ ሳዖል ዙፋኑን ሲጠብቅ ዳዊት ለዙፋኑ የተዘጋጀ እንደ ሆነ አመልክቷል “ ፡፡
ትምህርት
1-ሳሙኤል (18፡ 1-4)፡ የሳዖል ልጅ ዮናታን ከአባቱ ይልቅ ለዳዊት ራሱን አስገዛ (ቁጥር 1) ፤ ዮናታን ዳዊት ምናልባትም በእድሜ 25 አመት ያክል ይለያያሉ ፤ ዮናታን ሁለት ድሎች የነበሩት የወቅቱ ጦረኛ ነበር ፤ የዳዊት ብቸኛዋ ድል በጎልያድ ላይ በ 17 አመቱ ነበር ፡፡ በዚያም ቀን ሳዖል ዳዊትን ከእርሱ ጋር አደረገው ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስም አልፈቀደለትም (ቁጥር 2) ፡፡ ዮናታን ራሱን ለዳዊት በማስገዛት አንድ እንስሳ በመቁረጥ በዚያዉ ዉስጥ ሁለቱም በመጓዝ ከእርሱ ጋር ኪዳን አደረገ (ቁጥር 3) ፤ ዮናታን አባቱን እንደ ቀጣዩ ንጉስ ይከተለዋል ነገር ግን በዚህ ኪዳን ዉስጥ ዮናታን “ በዚህ ኪዳን ለቃሌ የምታመን ባልሆን እንደ ተቆራረጠዉ እንስሳ መጨረሻዬ ይሁን “ ብሎ እየገለፀ ነበር ፤ ከዚያም ዮናታን ዳዊትን የራሱን ልብሶች፡ ካባዉን፣ የጦር ልብሱን፣ ሰይፉን፣ ቀስቱን እና መታጠቂያዉን ሰጠው (ቁጥር 4) ፡፡ ዳቪስ “ ልብሶች ሰዉዬዉን እና ስልጣኑን እንዲሚገልፁ - ያ ማለት ዮናታን እንደ ልዑል የሆነዉን ዘዉድ ስልጣኑን በመተዉ አስተላለፈ በዚህም አሁንም ፍቃዱ ለዳዊት የስኬት መብት በመስጠት ፍቃደኛ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ድግራፍ “ ይህ ተግባር በእርሱ ላይ የእምነት አክት ነበር ፤ ያነስን ብቻ እንድንሆን ፍቃደኞች የሚያደርገን እምነት ብቻ ነው ፤ እምነት በእዉነት የእስራኤል ንጉስ በሆነዉ በክርስቶስ ላይ ያለንን ማስመሰል የሆነዉ መብታችንን እንድናስማርክ ምክንያት እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡
1-ሳሙኤል (18፡ 5-9)፡ ዳዊት ከሳዖል ጦር ጋር በመዝመት በሁሉም ተልዕኮዎች ሳዖል በሰጠዉ ስኬታማ ነበር ፤ ወታደሮቹ እና የሳዖል አገልጋዮች ዳዊት ኃላነት ላይ በመቀመጡ ደስተኞች ነበሩ (ቁጥር 5) ፤ ምሳ 3፡ 3-4) ፡፡ ወታደሮቹ ሲመለሱ ሴቶቹ በአቀባበላቸው ንጉስ ሳዖልን አገኙት ሳዖል ሺህ ገደለ ዳዊት ግን እልፍ ገደለ እያሉም ዘመሩ (ቁጥር 5-7) ፡፡ ሳዖል በቅሬታ በመናደድ ዳዊት ክሬዲቱን እና ክብሩን እየወሰደ ስለ ነበር ቀና (ቁጥር 8) ፤ ፑሪታን አገልጋይ ዮሐንስ ፍላቬል “ ኩራት የተሞላ ልብ ከሚያኮራ አንደበት ጋር በሚገናኝ ጊዜ አደገኛ ችግር እንደ ሆነ “ ተናግሯል ፤ በዚህም ሳዖል ዳዊትን በቅናት ሁኔታ ተመለከተው (ቁጥር 9) ፡፡
1-ሳሙኤል (18፡ 10-16)፡ በቀጣዩ ቀን ክፉ መንፈስ ሳዖልን ተቆጣጠረው ትንቢትም ይናገር ጀመር ፤ ዳዊት ለሳዖል በገና እየተጫወተለት እንደ ነበር ሳዖል ጦሩን በመዉሰድ ዳዊት ላይ ወረወረዉ ፤ ነገር ግን ዳዊት ሁለት ጊዜ ሸሸ (ቁጥር 10-11) ፡፡ የሳዖል ስሜታዊነት - ቀናተኝነቱ፣ ንዴቱ፣ ቅናቱ እና ፍራቱ እየጨመረ ነበር ፤ ሳዖል ዳዊትን እየፈራዉ ሄደ ምክንያቱም እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር እንጂ ከእርሱ ጋር ስላልነበር (ቁጥር 12) ፡፡ ዳዊት ስኬታማ መሆኑ ቀጠለ ፤ ሳዖልም ዳዊትን ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ሾመው (ቁጥር 13) ፡፡ ዋይርስቤ የሳዖልን እንደ ገና የመሾም ምክንያቱን፡ “ ዳዊት በዊጊያዉ የሚገደል ከነበር የጠላቶቹ ስህተት ነበር እንዲሁም ተርፎ ዉጊያዉን የሚሰነፍ ከሆነ ታዋቂነቱ ይወርዳል በሚል ነበር ፤ ነገር ግን እቅዱ አልሰራም ምክንያቱም ዳዊት ሁሉንም ዉጊያዎች ስላሸነፈ ! “ (ቁጥር 14-16) ፡፡ ሳዖል ዳዊት ተመልክቶባት ወደ ነበረችዉ ወደ ሴኬም ቀጠለ ፡፡
ዋይርስቤ የፃፈው “ ቅናት አደገኛና ቀስ በቀስ የሚጎዳ ጠላት ነው፣ የዉስጠኛዉ ህይወታችንን ቀስ በቀስ የሚበላው ካንሰር አስቸጋሪ ነገሮችን እንድንናገር እና እንድናደርግ ይመራናል … ቅናት የእኛ የሆነ ነገር ነዉ ብለን የምናስበዉን የሆነ ሰዉ በሚያሳካዉ ወይም በሚያገኘው ጊዜ የሚሰማን ስሜት እንደ ሆነ “ ይገልፃል “ ፤ (ምሳ 14፡ 30) ፡፡ ዋይርስቤ “ ቀናተኛ ሰዎች በእዉነት የማያስቡትን ሰዎችን ለማስደነቅ የማያስፈልጉዓቸዉን ነገሮች ለመግዛት የመጫወቻ ካርዳቸዉን የሚያወልቁ ሰዎች እንደ ሆኑ !“ ይገልፃል (መዝ 5፡ 12) ፡፡
1-ሳሙኤል (18፡ 17-30)፡ ጎልያድን በማሸነፉ ከሽልማቶቹ እንደ አንድ አካል ለጋብቻ የሳዖል ሴት ልጅ ዳዊት ቃል ተገብታለት ነበር ፤ በመጨረሻም ሳዖል ሴት ልጁን ሜሮብን ለዳዊት አቀረበለት (ቁጥር 17) ፡፡ በትህትና ዳዊት ወደ ሳዖል መለሳት ሳዖልም ለሌላ ሰዉ ዳራት (ቁጥር 18-19) ፤ ነገር ግን የሳዖል ሴት ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችዉ ከዚያም ሳዖል በትዳር ሜልኮልን ለዳዊት አቀረበለት (ቁጥር 20-21) ፡፡ እንዲሁም ሳዖል በዳዊት ምን ያክል ተባርኮ እንደ ነበር አገልጋዮቹ ዳዊትን እንዲነግሩት አዘዛቸው (ቁጥር 22) ፤ ነገር ግን እንደ ገና ዳዊት ሙሽራ ክፍያዉን ለመክፈል በጣም ድሀ እንደ ነበር አስተዋለ (ቁጥር 23፣ ዘጸ 22፡ 16) ፡፡ ንጉሱም የዳዊትን መልስ በሰማ ጊዜ ሳዖል ፍልስጤማዉያን ዳዊትን ይገድሉታል ብሎ ተስፋ በማድረግ ለሙሽራ ዋጋ የ100 ፍልስጤማዉያንን ሸለፈት ጠየቀዉ (ቁጥር 24-25) ፤ ዳዊት የሳዖልን ቃል በመቀበል 200 ፍልስጤማዊያንን በመግደል ሚልኮልን አገባ (ቁጥር 26-27) ፡፡ ሳዖል እግዚአብሄር ዳዊትን በደንብ እንደ ሚወደዉ አወቀ በጣምም ፈራው ፤ በዘህም ሳዕል የዳዊት ጠላት ሆነ (ቁጥር 28-29) ፡፡ ብዙ ነገር ሊያደርግ ሳዖል ቢሞክርም ዳዊት ከሌሎቹ ሰራተኞች ይልቅ በጣም ስኬታማ ነበር (ቁጥር 30) ፡፡
መደምደሚያ
በግልፅ የእግዚአብሄር እጅ በዳዊት ላይ ነበረች ፡፡ መዝ ( 92፡ 8-11) የሚለው “ አቤቱ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ ፤ አቤቱ እነሆ ጠላቶችህ ይጠፋሉና ዓመፃንም የሚሰሩ ሁሉ ይበተናሉና ፡፡ ቀንዴ አንድ ቀንድ እንዳለዉ ከፍ ከፍ ይላል ፤ ሽምግልናዬም በዘይት ይለመልማል “ ፡፡
ሮሜ (8፡ 28) የዳዊት ህይወት ሲጨመቅ ፡ “ እግዚአብሄርን ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናዉቃለን “ ፤ በእዉነታዉ ዳዊት በቅባቱ እየተጓ ስለሆነ እግዚአብሄር “ አገኘሁት “ አለው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Bible Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 255.
Dale Ralph Davis, 1 Samuel: Looking on the Heart (Fearn, Ross-shire, Great Britain: Christian Focus Publications, 2000, reprinted 2017), p. 194.
Davis, p. 194.
S. G. DeGraaf, Promise and Deliverance, v. 4 (Paideia, St. Catharines, 1978), 2:116; quoted by Dale Ralph Davis, p. 194.
Wiersbe, p. 257.
Wiersbe, p. 256.
Wiersbe, p. 257.
ጥያቄዎች
-
ዮናታን ራሱን እንደሚወደዉ ዳዊትን ወደደው ፤ በተለዬ ለምን ተሰማው (1 ሳሙ 15፡ 28) ? ማር (12፡ 13) አንብቡ ፤ ይህ ጥቅስ በዮናታን ላይ የምናየዉን ያንፀባርቃል ?
-
ዮናታን ከዳዊት ጋር ኪዳን በማድረግ ለዳዊት ካባዉን እና የጦር መሳሪያዉን ሰጠው ፤ በዚህ ከመጥን በላይ በሆነዉ ፍቅር ክርስቶስን እንዴት ልናየው እንችላለን ? (ኢሳ 61፡ 10፣ ሉቃ 15፡ 22፣ ኤፌ 6፡ 13-17)
-
በስዓቱ እንደ ንጉስ አያገልግል እንጂ ዳዊት አዲስ “ የተቀባ “ ነበር ፤ በምዕራፍ 18 ድርጊቱ እንዴት ክርስቶስን ያሳስበናል ? (1ሳሙ 18፡ 5፣ 10-13፣ ሉቃ 2፡ 52፣ ዮሐ 8፡ 29፣ 59፣ 10፡ 39፣ 11፡ 53-54)
-
በምዕራፍ 18 ለዳዊት ባለዉ በሳዖል አመለካከት ምን ለዉጥ ታያላችሁ ? (1ሳሙ 18፡ 8-9፣ 12፣ 15፣ 25፣ 29)
-
ዳዊት የንጉሱ ሴት ልጅ በቀረበችለት ጊዜ ለማግባት ፍቃደኛ ያልሆነዉ ለምን ነበር (1ሳሙ 18፡ 23-26) ? ሳዖል ልጁን ሜልኮልን ዳዊት እንዲያገባት ለምን ፈለገ ? (1ሳሙ 18፡ 21)
-
በ 1ሳሙኤል 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Samuel 18:9
“So Saul watched David jealously from that day forward.”
ምንም እንኳ ሳኦል የእስራኤል ንጉስ ቢሆንም የዳዊትን ስኬት ተመቅኝቶ ተመለከተ ፡፡ ሳኦልም በዳዊት ላይ በቅናት እየተመራያደርግና ይወስን ነበር ፡፡ በተጨማሪም ዳዊትን አንድ ጊዜ ሳይሆን ሁለት ጊዜ ለመግደል ሞከረ ፡፡ ይሁን እንጅ ሳኦል ቢጥርም የእግዚአብሄር እጅ በዳዊት ላይ ስለነበረ ዳዊት ስኬታማ መሆኑን ቀጠለ ፡፡
ቅናት ላንተ እንደሚገባ የምታስበውን ነገር ሌላ ሰው ሲያገኘው የሚሰማህ ህመም ነው ፡፡ ለትንስ ጊዜ ቆም በልና ስለ አባባሉ አስብ ፡፡ ስለ ቅናትና ምቀኝነት የ ልብህን መርምር ፡፡ በህይወትህ ስለ እርሱ ወይም ስለ እርሷ ሁኔታ ስታስብ ልብህ በስሜት የሚታወክበት ሰው አለ ይሆን ? በስጋ ስንኖር ቅናት ተፈትጥሯዊ ስሜት ነው ፡፡ ይህን ቅናት ለጌታ ተናዘዝና ተወው ፡፡ እግዚአብሔር በመንፈሱ አንድያድስህ ጸልይ ፡፡ በመንፈስ ሃይል ስትኖር መንፈስ ስጋን የምታሸንፍበትንና ነፃነትን የምትቀዳጅበትን ጥንካሬ ይሰጥሀል ፡፡ በመቅናትም ፈንታ ስለሌሎች ደስ ይልሀል በሌሎችም ስኬት ትደሰታለህ ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ በመንፈስህ አድሰኝ መንግስትህንም እገነባ ዘንድ ነፃነትን አቀዳጀኝ ፡፡
“ ከዚያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊትን ተመቅኝቶ ተመለከተው ፡፡ “
-1ኛ ሳሙኤል 18፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 24(25)፡4-5 –“ አቤቱ መነገድህን አመልክተኝ ፍለጋህንም አስተምረኝ ፡፡ አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ አስተምረኝም ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ፡፡ “
ገላትያ 5፡ ቁ16፡ ቁ19-20 ፡ ቁ22-23 –“ ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ፡፡ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት ፣ርኩሰት፣ መዳራት፣ ጣዖትን ማምለክ፣ ምዋርት ፣ጥል፣ ክርክር፣ ቅንዓት፣ ቁጣ፣ አድመኝነት፣ መለያየት ፣መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ መግደል፣ ስካር ፣ዘፋኝነት፣ ይህንንም የሚመስል ነው ፡፡ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር ፣ደስታ፣ ሰላም፣ ተዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው ፡፡ “
ያዕቆብ 3፡16 –“ ቅንዓትና አድመኝነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።