Historical Books 1 Samuel

On the Battle Lines

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 234 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ሳሙኤል መጓዝ ስንቀጥል እነዚህ ሁሉንም ነገሮች በአንድ ላይ መጥተዉ ማየት አስደናቂ ነው ፡፡ በምዕራፍ 4 ሀና ልጇ አንድ ቀን ንጉስ እንደሚቀባ ተነግሯት ነበር እናም በምዕራፍ 16 ሳሙኤል ያን አደረገ ፤ ትናትና ከቤቴ ልሄም ከይሁዳ ነገድ ከእሴይ ዘር ስለ ሚመጣዉ ንጉስ አተገባበር አዉርተናል ፤ በዚህን ጊዜ ዳዊት ለአባቱ በግ እየጠበቀ እና ክፉ መንፈስ በሳዖል ላይ በመጣበት ጊዜ መዝሙር እየተጫወተ ነበር ፡፡

ለምዕራፍ 17 መነሻዉ የዳዊት መቀባት ነዉ ነገር ግን በንጉስ ተግባር(ቦታ) ላይ እስከሚሆን የእግዚአብሄርን ጊዜ መጠበቅ ነበረበት ፤ በብዙ መጠበቅ የነበረባቸዉን እነዚህን ተመልከቱ ፡ ኖህ ጎርፉ እስኪመጣ ድረስ ለ10 አመታት ጠበቀ ፤ አብርሃም ይስሀቅ እስኪመጣ 25 አመታት ጠበቀ ፤ ሙሴ እግዚአብሄር ህዝቡን ነፃ እንዲያወጣለት ወደ ግብፅ ከመምራቱ በፊት እንደ እረኛ በመስራት 40 አመታትን አሳልፏል ፤ በመጠበቅ ጊዜ እግዚአብሄር ሰዎች በደንብ እርሱን እንዲመስሉ ማጥራቱን ይቀጥላል ፡፡ ሁሉም በቅባታችሁ የእግዚአብሄርን ጊዜ ስለ መያዝ ነው ፤ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ህይወትን ተቀብላለች ነገር ግን በዚያ እየተጓዝን አይደለም (ዮሐ 10፡ 10) ፡፡ በ 1ሳሙ (17፡ 1-16) ዳዊት ጠላቶቹ እየቀለዱበት እንኳን በቅባቱ በመንፈስ ቅዱስ ስር በመሆን ሲጓዝ እናያለን ፡፡ በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በፍፁም አይተወንም ፤ ሁላችንም በመቀባት በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል (2ቆሮ 1፡ 21-22) ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (17፡ 1-7)፡ የፍልስጤም ጦር እና የእስራኤል ጦር በዉጊያ አሰላለፍ በኤላ ሸለቆ ማዶ ለማዶ ላይ ተሰለፉ (ቁጥር 1-2) ፤ ሸለቆዉ ትልቅ ስላልሆነ በሸለቆዉ ማዶ ለማዶ ላይ መተያየት ይችላሉ የተጋጣሚዋቻቸዉን ፊት ያያሉ ፡፡ ሁለቱም ጦሮች ተራራዉ አናት ላይ ነበሩ (ቁጥር 3) ፡፡ ጎልያድ የስሙ ትርጉም “ ጉልህ “ እና ዘጠኝ ጫማ ከዘጠኝ ኢንች እርዝመት ነበር (ቁጥር 4) ፤ የጎልያድ የጦር ልብስ 125 ፓዉንድ ይመዝን ነበር ፤ የብረት ጦሩ ብቻዉን 15 ፓዉንድ ይመዝናል (ቁጥር 5-7) ፡፡ ኮንስታብል “ ብብሉይ ኪዳን ይህ ለአንድ ግለሰብ የተደረገ ረጅም ገለፃ እንደ ሆነ ይናገራል ፤ ጸሀፊዉ በማስረጃነት የጎልያድን አስደናቂ ኃይል እና በአንባቢዎቹ ላይ አይበገሬነቱን ለማስገረም እንደ ፈለገ ይናገራል “ ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 8-11)፡ ጎልያድ እስራኤላዊያን ላይ በመጮኽ አንድ ጎበዛቸዉን ከእርሱ ጋር እንዲዋጋ እንዲልኩ ገፋፋቸው ፤ ጎልያድም የእስራኤላዊያን ጎበዝ ካሸነፈ ፍልስጤማዊያን የእነርሱ አገልጋይ እንደ ሚሆኑ ቃል ገባ ፤ ጎልያድ እስራኤላዊዩን ጎበዝ ከገደለዉ ደግሞ እስራኤላዊያን ፍልስጤማዉያንን ያገለግላሉ (ቁጥር 8-10) ፡፡ ጠላት ያለማቋረጥ ለይቶ ይወስደና፣ ዉሸት ይነግረናል ከዚያም የምናዉቀዉን እዉነት የሆነዉን ያጠቃዋል(ያጠፋዋል) ፤ ሳዖል እና የእስራኤል ጦር የጎልያድን ቃል በሰሙ ጊዜ በዉሸቱ በመወሰድ ፈሩ (ቁጥር 11) ፡፡ቤተ ክርስቲያን በአለም ዉስጥ በመኖር ደህና በሆነች ጊዜ፣ ወደ ዉጊያ ካልገባን በጣላቶቻችን ዉሸት ዉስጥ እየተገዛን ነው ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 12-16)፡ የእሴይ ትልቆቹ ሰዎስቱ ልጆች ወደ ጦርነት ሳዖልን ተከተሉት ትንሹ ልጅ ዳዊት ግን እንደ እረኛ በዘወትር ስራዉ እና ለንጉስ ሳዖል በኃላፊነቱ መካከል ይመላለስ ነበር (ቁጥር 12-15) ፡፡ ሁልጊዜ በሁሉም ጥዋት እና በሁሉም ምሽት ለ40 ቀናት ጎልያድ በመምጣት እስራኤላዊያንን ለግጥሚያ ይጠራቸዉ ነበር (ያስፈራራቸዉ)(ቁጥር 16) ፡፡ የጠላት ዉሸት ምን ያክል ረፍት የለሽ ሊሆን እንደ ሚችል አስታዉሉ ! ጠላት በሚያታልለን (በሚያጃጅለን) ጊዜ በጠላታችን ላይ መጀመር እና ዉሸቱን መስማት ማቆም ይጠበቅብናል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በፊተኛዉ መስመር ስለሆነች ስለ ወጊያዉ የሆነ ነገር ለማድረግ በስፈራዉ ነን ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 17-19)፡ በቤቴ ልሄም እሴይ አቅርቦቶቹን በአንድ ላይ ወደ እስራኤላዊያን ሰፈር እንዲያደርስ ዳዊትን አዘዘው ፤ እሴይ ያካተታቸዉን አስር እንጀራዎችን አስታዉሉ (ቁጥር 17) ፤ ቤቴ ልሄም ማለት “ የእንጀራ ቤት “ ማለት ነው ፡፡ እሴይ በተጨማሪም ለጦር አዛዡ አይብ በመላክ ዳዊትን በወንድሞቹ ላይ ያለዉን እንዲያረጋግጥ ነገረው (ቁጥር 18) ፤ ወንድሞቹ “ ከፍልስጤማዉያን ጋር እየተዋጉ “ ከሳዖል ጋር ነበሩ (ቁጥር 19) ፡፡ በእዉነቱ እየተዋጉ አልነበረም በእስራኤል በኩል በመሆን የዉጊያዉን መስመር እየጠበቁ እንጂ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እየተዋጋን እንዳለን እናስባለን ነገር ግን አይደለም ፤ ወደ ዊጊያዉ መስመር አልፈን መጓዝ ይጠበቅብናል ፤ በሪቫይ ት/ቤት ዉስጥ ለማነቃቃት የጊዜዉ አላማ ያ ነው ! ለመነሳሳት በመፈለግ እናዘነብላለን ነገር ግን ይህ እንዲያደርግ እግዚአብሄር ሌላ ሰዉ እንዲጠቀም እንፈልጋለን ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 20-29)፡ ወደ ጦርነቱ ለመግባት የፊተኛዉን መስመር አልፎ ለመጓዝ ዝግጅት ይወስዳል (ይጠይቃል) ፤ በማለዳ በመነሳት ከአቅርቦቱ (ከሚይዘዉ ምግብ) ጋር ከቤቴ ልሄም ከመሄዱ በፊት በጎቹ ጥበቃ ተደርጎላቸዉ መሆኑን እርግጠኛ ይሆናል ፡፡ በዉጊያ አሰላለፍ ፍት ለፊት የሚተያዩትን ጦሮች ለማየት በጊዜው ደረሰ (ቁጥር 20-21) ፤ ዳዊት ተቀብሎት በነበረዉ ሀላፊነት ምክንያት እቃዎቹን በመተዉ ወደ ጦሩ በመሮጥ የወንድሞቹን ደህንነት አረጋገጠ (ቁጥር 22) ፡፡ ጎልያድ እንደ ገና በመምጣት ለጦርነት በመጋበዝ ጮኸ (ቁጥር 23) እስራኤላዊያንም ሸሹ (ቁጥር 24) ፤ ዳዊት ጎልያድን የገደለ ሽልማቱ ምን እንደ ሆነ ጠየቀ (ቁጥር 25-27) ፤ ሽልማቱ ሀብት እና የሳዖል ሴት ልጅ በማግባት በሳዖል ቤተሰብ ስፍራን ያካትታል ፡፡ በጦርነት በምንዋጋ ጊዜ ለእኛም ሽልማት አለን (ማቴ 5፡ 10-12፣ 6፡ 20) ፤ ከካምፑ ዉስጥ ለሚመጣዉ ተቃዉሞ መዘጋጀት ነው ፡፡ የዳዊት ወንድም ኤልያብ የዳዊትን ሀቀኝነት እና ኃላፊነት የመወጣት ስሜትን (መዝ 78፡ 72) (ቁጥር 28) የተሳሳተ ነገር ለምንድን አደረክ ብሎ በመጠየቅ አጠቃ (ቁጥር 29) ፡፡

ዋይርስቤ የሚለው “ መቼም ቢሆን ጠላታችሁን ለመዋጋት በእምነት ስትራመዱ ሁል ጊዜ በዙሪያችሁ ተስፋ የሚያስቆርጣችሁ አካል አለ አንዳንድ ግዜም ከቤታችሁ እንደ ይጀምራል “ ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 30-39)፡ በራሱ ፍላጎት መሰረት ዳዊት ወደ ሳዖል ተወሰደ (ቁጥር 31) ፤ እግዚአብሄር ቀድሞ ዳዊት ለዉጊያ በግ በመጠበቅ ዉስጥ አሰልጥኖት ነበር ( ቁጥር 32-36) ፡፡ ዳዊት ድሉን እንደሚቀዳጅ አመነ (ቁጥር 37) ፤ የሳዖል የጦር ልብስ ዳዊት አልሆነዉም ነገር ግን ዳዊት አላስፈለገዉም (ቁጥር 38-39) ፡፡ በእግዚአብሄር እርግጠና ስለ ነበር ቄንጠኛ መሳሪያዎች አላስፈለጉት ፤ ዋይርስቤ የሚለው “ ሳዖል እግዚአብሄር አዲስ ነገር ማድረግ እንደ ሚችል እምነት ስለሌለው የተከበረዉን የዱሮ ጊዜ ፋሽንን የጦርነት ስልት መከረ “ ፡፡ ከተቀባ ከአምስት አመት በኋላ ዳዊት የ17 አመቱ ዳዊት በጥሪዉ ለመጓዝ ዝግጁ ነበር ፡፡

1-ሳሙኤል (17፡ 40-58)፡ ዳዊት አምስት ድንጋዮች በመምረጥ ከወንጭፉ ጋር በእጁ በመያዝ ወደ ጎልያድ ቀረበ (ቁጥር 40) ፡፡ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ለአዲስ የወይን አቁማዳ ጊዜዉ ነው (ሐዋ 11፡ 19-26) ፤ ባህል አንቀይረም ፡፡ እንዴት ያ ልዩነት ማድረግ እንደሚችል ለማየት መነጠቅ ወይም መቀየር እንድንችል አንድ ትንሽ ነገር ለማግኘት እንፀልይ ፡፡ በመጨረሻም ዳዊት ዉጊያዉ ላይ መግባት ቻለ (ቁጥር 41-47) ፤ ዳዊት ድሉ የእግዚአብሄር እንደ ነበር ያውቃል ፤ ጎልያድ ወደ ፊት እንደ መጣ ዳዊት ወደ እርሱ በመሮጥ በአንድ ድንጋይ እና በአንድ ወንጭፍ አሸነፈው (ቁጥር 48፡ 50) ፡፡ ዳዊት ራሱን ለመቁረጥ የራሱን የጎልያድን ሰይፍ ተጠቀመ (ቁጥር 51) ፤ የእስራኤል ጦር ፍልስጤማዉያንን በማባረር ገደሉዓቸዉ ሰፈራቸዉንም ዘረፉ (ቁጥር 52-53) ፡፡

መደምደሚያ

እስራኤላዊያን ለቀናት በዉጊያ በፊት መስመር ላይ ቆመዉ ነበር ፤ ነገር ግን ዳዊት በመጣ እና በጥሪዎ፣ በቀረባቱ በተጓዘ ጊዜ ህይወትን በይበልጥ በተትረፈረፈ መቅመስ(መልመድ) ቻሉ ፡፡

1ዮሐ (2፡ 20፣ 27)፡ “ እናንተም ከቅዱስ ቅባት ተቀብላችኋል ሁሉንም ታውቃላችሁ .....እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁትን ቅባት በእናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም ፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ እዉነተኛም እንደ ሆነ ዉሸትም እንዳልሆነ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ “ ፡፡

በተሰጠነዉ በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ልክ እንደ እስራኤላዊያን በምንሄድ ጊዜ ለእናንተ እና ለእኔ ማድረግ የሚፈልገዉን የእግዚአብሄር ሙሉነት መቅመስ እንችላለን ፡፡ ጥያቄዉ ኮኮብ የሆኑ ወታደሮች ወይም በጥሪዉ እንደ ተጓዘዉ እንደ ዳዊት መሆን ትፈልጋላችሁ ?

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 367.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Samuel, p. 88; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1samuel.pdf.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Bible Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 252.

  4. Wiersbe, p. 253.

ጥያቄዎች

  1. ዳዊት የአባቶቹን በጎች ሊመግብ ይሄድ ነበር (ቁጥር 15) ፤ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ በጎችን ስለ መመገብ ሲናገር የት ላይ ሰምታችኋል (ዮሐ 21፡ 17) ? በእነዚህ በጎች መካከል ምን ልዩነት ልታዩ ትችላላችሁ ?
  2. የሳዖል ጦር የጎልያደን ጦር ለምን ነበር የፈራው (ቁጥር 4-7) ? እግዚአብሄር ስለ ፍራት ምን ይላል (ኢያ 1፡ 9፣ ኢሳ 41፡ 10፣ 2ጢሞ 1፡ 7) ? በእግዚአብሄር እርዳታ ፍራትን አሸንፋችኋል ? እንዴት ? (1ዮሐ 4፡ 18)
  3. የዳዊት ወንድም በእርሱ ላይ ለምን ተበሳጨ ? (1ቆሮ 1፡ 27-29፣ ያዕ 3፡ 14፣ 16፣ 4፡ 11) ዳዊት ለወንድሙ ለኤልያብ ባደረገዉ(በዚያ) መንገድ ለምን እንደ መለሰለት ምን ታስባላችሁ ? (1ሳሙ 17፡ 29)
  4. ወጣቱ ዳዊት በእግዚአብሄር በጣም ብዙ በተማመን ስለ ነበረው በጥቂት ድንጋዮች ብቻ አንድ ግዙፉን(ጎልያድን) ለመግጠም ሄደ ፤ ከምን አይነት ግዙፎችን(ኃይለኞችን) ጋር በእግዚአብሄር እርዳታ ገጠማችሁ ? እንዴትስ ተመለሱ (ጠፉ) ?
  5. በ 1ሳሙኤል 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 17:37

“The LORD who rescued me from the paw of the lion and the paw of the bear will rescue me from the hand of this Philistine. Saul said to David, ‘Go, and may the LORD be with you.’”

ዳዊት የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ በሳሙኤል ተቀብቶ ሳለ እርሱ ግን በጎቹን ወደ መስክ ያሰማራ ነበር ፡፡ ዳዊት ሰልፈኛ ለነበሩት ወንድሞቹ ምግብ በሚያደርስበት ጊዜ ስለ ጎልያድ ሰማ እስራኤላውያንም እርሱን ፈርተው ሲጨነቅ አየ ፡፡ ነገር ግን ዳዊት ይህንን ግዙፍ ተዋጊ ለመፋለም አልፈራም ነበር ፡፡ ዳዊት ያ ከአንበሳና ከድብ መንጋጋ ያስጣለው እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊም እጅ እንደሚያስጥለው አውቆ ነበር ፡፡ እርሱ በእምነት ወጣ በእርሱም ላይ ባለው ቅባት ወጣ እንድሁም በእግዚአብሔር እንደተፈጠረ የእግዚአብሔርም መንፈስ አብሮት እንዳለ በማመን ወጣ ፡፡ ዳዊት ለአመታት በጎቹን ሲጠብቅ የለመደውን መሳሪያ በመጠቀም በአንድ የወንጭፍ ድንጋይ ጎልያድን በመጣል ድልን ተቀዳጀ ፡፡

እንደ ዳዊት ሁሉ ጠላትህን ልትገጥም ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ምንድን ነው ካቅምህ በላይ የሆነው ጭንቀትህ ወይም ጣላትህ በጊዜ ሂደት ከባድ እየሆነብህ የመጣው ነገርስ ? እግዚአብሔር ካንተ ጋር እነደሆነና ድሉም የእርሱ አንደሆነ ለማወቅ ጊዜው ነው ፡፡ አንተ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተቀብተሀል በእርሱም ሀይል ጠላቶችህን ማሸነፍ ትችላለህ ፡፡ ዳር መቆም ይብቃህ ሂድ ተከተል ውጊያው የእግዚአብሔር ነውና ፡፡

“ ዳዊትም ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ ፡፡ ሳኦልም ዳዊትን ሂድ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሆናል አለው ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 17፡37

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ሳመኤል 17፡45-47 –“ ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአቤኔር አቤኔር ሆይ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው ? አለው ፡፡ አቤኔርም ንጉሥ ሆይ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ አላውቅም አለ ፡፡ ንጉሡም ይህ ብላቴና የማን ልጅ እንደሆነ አንተ ጠይቅ አለ ፡፡ ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ አበኔር ወሰደው ወደ ሳኦልም ፊት አመጣው የፍልስጥኤማዊውንም ራስ በእጁ ይዞ ነበር ፡፡ “

መዝሙር 17(18)፡39 –“ ለሰልፍም ሀይልን ታስታጥቀኛለህ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ ፡፡ “

1ኛ ዮሐንስ 2፡27 –“ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ፡፡ “