Historical Books 1 Samuel

God's Anointed King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 233 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ሳሙኤል ለመሲሁ ሀረጉ(ቃሉ) የተቀባ የሚል ነው ፤ ያን በግልፅ የሚያሳይ ፅሁፍ አለ እርሱም 1 ሳሙኤል 16 ይሆናል ፡፡ ሳዖል የመጀመሪያዉ የተቀባ የእስራኤል ንጉስ ነበር ነገር ግን መሪነቱን እንዲወስድ ለልጁ ዮናታን እየፈቀደ ነበር ፤ ይህን በምዕራፍ 14 አይተነዋል እንዲሁም ደግሞ አሁን በምዕራፍ 15 ፡፡ በ 1ሳሙ (15፡ 1-3) ሳዖል ሁሉንም አማሌቃዊያንን ሴቶቹን፣ ልጆቹን እና ከብቶቻቸዉን እንዲያጠፋ ተነገረው ነገር ግን በቁጥር (4-9) ሳዖል ንጉስ አጋግ እና ለምርጥ ምርጥ ከብቶች እንዲኖሩ ፈቀደ ፤ እግዚአብሄር ሳዖልን ንጉስ በማድረጉ ተፀፀተ (ቁጥር 10-15) ፡፡ ባለመታዘዙ ምክንያት ሳዖል በእግዚአብሄር እና በሳሙኤል በሁለቱም ተናቀ (ቁጥር 16-23) ፤ ሳዖል ሳሙኤል ይቅር እንዲለዉ ለመነው ሳሙኤልም ከእርሱ ዞር ባለ ጊዜ ሳዖል ካባዉን(ቀሚሱን) ያዘዉ ተቀደደም ፤ ሳሙኤልም መንግስት ከሳዖል እንዲሁ ተቀደደች አለ (ቁጥር 24-30) ፡፡ ቁጥር 28 መንግስቱ ቀድሞ ለሳዖል ጎረቤት ለዳዊት ተሰጥቶ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ሳሙኤል የእግዚአብሄርን ፍርድ በማድረግ አጋግን ቆራረጠው ፡፡ ሳዖልን በፍፁም ደግሞ አላየውም (ቁጥር 32-35) ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (16፡ 1)፡ እግዚአብሄር ሳሙኤልን አዲስ ንጉስ እንዲቀባ ወደ ቤቴ ልሄሙ ወደ እሴይ ላከው (ቁጥር 1) ፡፡ የእስራኤልን ንጉስ ምርጫ እግዚአብሄር አደረገ ፤ ይህ አዲስ ንጉስ በዘፍ (3፡ 15) እና ዘኁ (24፡ 17) የተተነበዬ ነበር ፡፡ በመፅኀፍ ስለ ሚመጣዉ ንጉስ ስለ ሚመጣዉ መሲህ እነዚህ ብቻ አይደሉም የተተነበዩት ፤ ሁሉም ከእስራኤል ስለ ሚመጣዉ የእግዚአብሄር ምርጫ ስለ ሆነዉ ያመለክታሉ ፡፡ 1ሳሙ (2፡ 10) የሚለው “ ከእግዚአብሄር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ ፤ በሰማይም ያንጎደጉድዳቸዋል ፤ እግዚአብሄር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል ፤ ለንጉስም ኃይል ይሰጣል ፤ የመሲሁንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል “ ፡፡ ይህ ቅባት ከእስራኤል መንግስት እንደሚመጣ እናዉቃለን ፤ እግዚአብሄር ንጉስ እንዲሆን ለልጁ እቅድ አለው (መዝ 2፡ 1-4፣ 7-9) ፤ ደግሞም ሩት (4፡ 12) እና 22 ንጉሱ ከይሁዳ ነገድ እንደ ሚመጣ ይገልፃል ፡፡ ሳሙኤል መፅሀፍን ስለሚያዉቅ ቀጣዩ ንጉስ እግዚአብሄር ተስፋ የገባዉ እንደ ሚሆን ይህ ያስተዉላል (ዘፍ 49፡ 10፣ ሚክ 5፡ 2) ፡፡

1-ሳሙኤል (16፡ 2-5)፡ በሚያስገርም ሁኔታ የሳሙኤል የመጀመሪያዉ ምላሽ ፍርሀት ነበር ፤ ሳሙኤል እግዚአብሄርን ፈርቶት ከነበረዉ ይበልጥ ሳዖልን ፈራ (ምሳ 29፡ 25) ፡፡ እግዚአብሄር ሳሙኤልን እንደ መስዋዕት ከእርሱ ጋር ጊደር በመዉሰድ ወደ መስዋዕቱ እሴይን እንዲጠራዉ ነገረው ፤ ከዚያም ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግ እግዚአብሄር ይነግረዋል (ቁጥር 2-3) ፡፡ እንደ ገና 1 ሳሙ (2፡ 10) አንብቡ ፤ ምንድን እንደ ሚያደርግ ይህን ትንቢት ለእናቱ ለሀና መሰጠቱን ሳሙኤል ይሰማል ፤ አስቡት ወደ ቤቴ ልሄም እየተጓዘ ያንን ትንቢት እየፈፀመ እንደ ሆነ ያውቃል ! ለዚያ ነዉ ፍርሀቱ በጣም አስገራሚ የሆነው (2 ሳሙ 2፡ 7፣ 5፡ 3) ፡፡ ሳሙኤል በደረሰ ጊዜ ሽማግሌዎቹ በዚያ ምን ሊሰራ እንደ ነበር አስበዉ በመፍራት ለምን እንደ መጣ ጠየቁት (ቁጥር 4) ፤ ማክአርቱር ሳሙኤል በአጋግ ላይ አድርጎት የነበረዉን ሰምተዉ ስለ ነበር ምን ሊሰራ በዚያ እንደ ተገኘ እንደ ጠየቁት ይናገራል ፡፡ ሳሙኤልም ለሽማግሌዎቹ ለእግዚአብሄር ሊሰዋ በሰላም እንደ መጣ መለሰላቸው ራሳቸዉንም በመቀደስ ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ አዘዛቸው ፡፡ ማክአርቱር “ የያህዌ አምልኮ ሁል ጊዜ ዉጨኛዉን ልብስ እና ዉስጠኛዉን ሰዉ ከመንፃት እና ከመታጠብ ቀጥሎ የሚመጣ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፤ ዘጸ (19፡ 10፣ 14፣ 1ዮሐ 1፡ 9) ፡፡ ሳሙኤል የቀረ አንድ ወንድ ልጅ እንደ ነበር ሳያዉቅ እሴይን እና ልጆቹን በመቀደስ እንዲሰዉ ጋበዛቸዉ (ቁጥር 5) ፡፡

1-ሳሙኤል (16፡ 6-13)፡ ሳሙኤል የእሴይን ልጅ የስሙ ትርጉም “ አምላኬ አባቴ ነው “ የሚለዉን ኤሊያብን ባዬ ጊዜ የተቀባዉ በፊቱ እንደ ነበር አሰበ (ቁጥር 6) ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ሳሙኤልን በልጆቹ መልክ ላይ እንዳያተኩር ግን በልባቸዉ ላይ እንዲመለከት ነገረው (ቁጥር 7) ፡፡ ማክአርቱር “ በዕብራዊያን አስተሳሰብ ስሜትን፣ ፍቃድን፣ ሀሳብን እና ፍላጎትን እንደ ሚይዝ ፤ የሰዉ ህይወቱ ልብን እንደ ሚያንፀባርቅ ይገልፃል “ ፡፡ ኤር (17፡ 10፣ ማቴ 12፡ 34) ፤ በቁጥር 8-10 እያንዳንዶቹ ልጆች ለሳሙኤል ቀረቡ ነገር ግን እግዚአብሄር አልመረጣቸዉም ፡፡ በመጨረሻም ሳሙኤል የቀረ ሌላ ልጅ እንዳለ ጠየቀ እሴይም ትንሹ ልጁ በግ በመጠበቅ በዉጭ እንዳለ ተናገረ ፤ ሳሙኤልም እሴይን ከመብላታቸዉ በፊት እስኪመጣ ስለ ሚጠብቁት እንዲያስመጣው ነገረው (ቁጥር 11) ፡፡ ዳዊት በደረሰ ጊዜ እግዚአብሄር “ እርሱ ነዉ ቀባዉ “ አለው (ቁጥር 12) ፡፡ ቅባት በእግዚአብሄር ከፍ ተደርጎ የሚሰጥ እንጂ በሰዉ አይደለም ፡፡ ሳሙኤል በወንድሞቹ ፊት ዳዊትን ቀባው “ የእግዚአብሄርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ “ (ቁጥር 13) ፤ ቆይቶም ዳዊት በይሁዳ ነገድ ፊት ሁለተኛ ጊዜ ይቀባል ለሰዋስተኛ ጊዜ ደግሞ በመላዉ እስራኤል ፊት ይቀባል ፡፡

ያዕቆብ፣ ጌዴዎን እና ዮሴፍም ሁሉም የቤተሰቦቹ ታናናሽ ልጆች ነበሩ ፤ እንደ እረኛ በመጀመር ንጉስ የሆነዉ ዳዊት የእስራኤል በኩር በመሆን ተገልጧል (መዝ 78፡ 70-72) ፤ ዳዊት የክርስቶስ አይነት ነበር ፡፡ ዳዊት ዋጋ እንደ ሌለ አይተዉት በነበሩት በራሱ ወንድሞች የተገፋ ነበር ፤ የኢየሱስ ቤተሰብ አይምሮዉን አጥቷል ብለዉ አሰቡ (ማር 3፡ 21) ፡፡

ብሉይ ኪዳን ሰዎችን ስላስነሳዉ የእግዚአብሄር መንፈስ ብዙ ምሳሌዎች አሉት፡ ሳሙኤል/ሳዖል - 1ሳሙ 10፡ 6፣ 10፣ ሳዖል - 1ሳሙ (11፡ 6)፣ የሳዖል ወኪሎች - 1ሳሙ (19፡ 20፣ 23)፣ ዳዊት- 2ሳሙ (23፡ 2)፣ አዛሄል- 2ዜና 20፡ 14፣ የዳዊታዊ ንጉስ - ኢሳ 61፡ 1፣ ሕዝቄል - ሕዝ 11፡ 5፣ 37፡ 1 ፡፡ በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ሲጠመቅ መንፈስ በእርሱ ላይ መጣበት (ማቴ 3፡ 13-17) በአባቱ በተቀባ ጊዜ በመንፈስ ኃይል ተሞላ (ሐዋ 1፡ 8) ፡፡

1-ሳሙኤል (16፡ 14-17)፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ሳዖልን በተወዉ ጊዜ እግዚአብሄር ክፉ መንፈስ እንዲያሰቃየዉ ላከበት (ጥር 14) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በክፉ መንፈስ መጠቃት አራት ምንጮች እንደሚኖሩት ያመለክታል፡ “ 10 እንደ መለኮታዊ ቅጣት ክፉ ተቆጣጠረው፣ 2) ሰይጣናዊ ተፅዕኖ ወይም ጥቃት፣ 3) አካብን እንዲይዘዉ ተልኮ እንደ ነበረዉ ክፉ መልዕክተኛ እና 4) በሳዖል ልብ በእግዚአብሄር የተፈጠረ ደስተኛ ያለ መሆን መንፈስ “ ፤ ምንም ይሁን ምክንያቱ የሳዖል አገልጋዮች አዉቀዋል (ቁጥር 15) ፡፡ በጥቃት ስር በሚሆን ጊዜ ለማረጋጋት ለእርሱ በገና ለሚጫዎት ሰዉ ለማገኘት አቀረቡ (ቁጥር 16-18) ፤ ዳዊት ወደ ንጉሱ ከእሴይ ቤት ከስጦታ ጋር ተላከ (ቁጥር 19-20) ፡፡ ዳዊት የሳዖል ጦር ተሸካሚ ሆነ በትህትናም የዳዊት አገልግሎት ምልክት ነበር (ቁጥር 21-22) ፡፡

መደምደሚያ

ለመዝጋት ዳዊት በእግዚአብሄር የተቀባ አንድ ሰዉ የነበሩት ሁሉም ባህሪያት ነበሩት፡

  • ለእግዚአብሄር ልብ ነበረው ፡፡
  • በሰዉ የተገፋ ነበር ፡፡
  • በእግዚአብሄር ከፍ ያለ ነበር ፡፤
  • በእግዚአብሄር መንፈስ ኃይል የተሞላ ነበር ፡፡
  • የሙሉነት ሰዉ ነበር ፡፡
  • የእምነት ሰዉ ነበር ፡፡
  • በትህትና ተጓዘ ፡፡

ዳዊት በትህትና ሲጓዝ እግዚአብሄር በተሻለ አስቀመጠዉ(ሾመዉ) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 327.

  2. MacArthur, p. 327.

  3. MacArthur, p. 327.

  4. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 366.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ ( 15፡ 3) እግዚአብሄር በህይወት ያለዉ ሁሉ እንዲጠፋ ለምን እንዳዘዘ ምን ታስባላችሁ ?
  2. ሳዖል እግዚአብሄርን ባለመታዘዝ ንጉሱ እና ከብቶቹ እንዲኖሩ በፈቀደ ጊዜ በመጨረሻ ምን ተፈጠረ ? እግዚአብሄርን ያልታዘዛችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
  3. በ 1ሳሙ (16፡ 7) እግዚአብሄር ሳሙኤልን ወደ ቤቴ ልሄም እንዲሄድ ነገረው ፤ ለምን ሳሙኤል ለመሄድ አልፈለገም ? ለምን አላማ ነበር የሚሄደው ?
  4. 1 ሳሙ (16፡ 7) ስታነቡት ስለ እግዚአብሄር ለእናንተ ምን ይነግራችኋል (ምሳ 21፡ 2፣ 1ጴጥ 3፡ 4) ? አንዳንድ ጊዜ ዉጪ ላይ በመመልከት ብቻ ጥፋተኞች ነን ? (ዮሐ 7፡ 24፣ 2ቆሮ 10፡ 7)
  5. በ 1ሳሙኤል (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 16:7

“But the LORD said to Samuel, ‘Do not look at his appearance or his stature, because I have rejected him. Man does not see what the LORD sees, for man sees what is visible, but the LORD sees the heart.’”

ሳኦል አማሌቃውያንን በወጋ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሙሉ ትዕዛዝ ባለመፈጸም ሀጥያት ሰራ ፡፡ ስላለመታዘዙም እግዚአብሔር ሳኦልን የእስራኤል ንጉስ እንዳይሆን ነቀው ፡፡ ሳሙኤል ስለ ሳኦል ሀጥያትና ንግሥናውም በእግዚአብሄር መናቅ ሲያዝና ሲያለቅስ ሳለ እግዚአብሔር ሳሙኤልን አድሱን የእስራኤል ንጉስ ይቀባ ዘንድ እንድዘጋጅ አዘዘው ፡፡ እግዚአብሔርም በግ እረኛ የነበረውንና ከሁሉም ታናሽ የሆነውን ያልታሰበውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን መረጠ ፡፡ እግዚአብሔር በዳዊት ልብ ውስጥ የነበረውን ትሁት ማንነት ስላየ ዳዊትን መረጠ ፡፡ ሳሙኤልም በመታዘዝ ዳዊትን ቀባ ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ ዳዊትን ተቆጣጠረ ፡፡

እግዚአብሔር በዳዊት ውስጥ ማንም ያላየውን አየ ፡፡ ሰዎች ፊትን ሲያዩ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል ፡፡ ኢየሱስ የህይወት ምንጭ ልብ እንደሆነና ልበ ንፁሆች ደግሞ እግዚአብሔርን እንደምያዩት ይናገራል ፡፡ አንተ ስለ ውጫዊው አቋምህ ብቻ ከሆነ የምትጨነቀው ተሳስተሀል ማለት ነው ፡፡ ውበት ይመጣልም እንደገናም ደግሞ ይሄዳል ነገር ግን እግዚአብሔር እርሱን የሚፈሩትን ያከብራቸዋል ፡፡ እውነተኛ ውበት ከውስጥ ነው ሚመነጨው ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ልክ እንደ ዳዊትአንተም ለእግዚአብሔር መንግስት ተቀብተሀል ፡፡ እግዚአብሔር ልብህን ብቻ ነው ሚፈልገው ፡፡ አሁን እርሱን ስትሻ እግዚአብሔር ልብህን ያድሳል ፡፡

“ እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ሰው እንድያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት ሰው ፊትን ያያል እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 16፡7

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ምሳሌ 4፡23 –“ አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና ፡፡ “
  • ምሳሌ 31፡30 –“ ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች ፡፡ “
  • ማቴዎስ 12፡34 –“ እናንተ የእፉኝት ልጆች ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና ፡፡ “