Historical Books 1 Samuel

The Victory is God's

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 232 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የተቀባ የሚለዉን የ 1ሳሙኤል ሀረግን አስታዉሱ ፤ የሳዖል ህይወት ወደ ዳዊት ህይወት ይመራል የዳዊት ህይወት ደግሞ ወደ መሲሁ ይመራል ፡፡ በ 1ሳሙኤል 13 ዮናታን በሳዖል ስር የእስራኤላዊያንን ጦር ወደ መጀመሪያቸዉ ድል መራቸው ፤ ከዚያም በአይነተኛ “ ዮናታን “ ስራ ዮናታን የድሉን ዋጋ ለሳዖል ሰጠው ፡፡ ቀድሞ ሳዖል የቅናት እና የኩራት ምልክቶች አሳይቷል ፡፡ ዮናታን ኃይለኛ ተዋጊ ነበር (2ሳሙ 1፡ 22) ፤ ዋይርስቤ ዮናታንን “ እንደ ጀግና ተዋጊ፣ እንደ ተወለደ መሪ እና የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ እንደ ሚመለከት ሰዉ ይገልፀዋል “ ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (14፡ 1-6)፡ ወደ ፍልስጤማዉያን የጦር ሰፈር ለመጓዝ ጋሻ አጃግሬዎቹን ወይም ጦር ተሸኪሚዋቹን ሲመራ ምንም ነገር እንዳልፈራ ያሳያል (ቁጥር 1) ፤ ምናልባትም “ ሳዖል የዮናታንን እቅድ እንደ ጥፋት ስለሚያስበዉ “ ዮናታን ለአባቱ አልነገረውም ፡፡ ሳዖል በሳዖል የትዉልድ ከተማ በሜግዶን አጠገብ በሮማኑ ዛፍ ስር ከ 600 ወታደሮች ጋር ተቀምጦ ነበር (ቁጥር 2) ፤ ነጩን የካህናት ልብስ ኢፉዱን ለብሶ የነበረው አኪያም በዚያ ነበር (ቁጥር 3) ፤ ይሁን እንጂ ወታደሮቹ ዮናታን ስለ መሄዱ አላወቁም ነበር ፡፡

ዮናታን በሚያልፍበት በሁለቱም በኩል በጉዞ አደጋን የሚግባቡባቸው ትርጓሜዉ የሚያንሸራትት የሆነዉ ስሙ ቦጼድ እና ትርጉሙ እሾካማ የሆነ ስሙ ሴኔ የሚባሉ ድንጋዮች ነበሩ (ቁጥር 4-5) ፡፡ በቁጥር 6 ዮናታን “ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሄርን አያስቸግረዉምና “ ብሎ በመናገር ለምን በጣም ደፋር እንደ ሆነ ገልጧል ፤ ዮናታን በድሉ እምነት ነበረው በዚያም ዉስጥ ለመጓዝ ዝግጁ ነበር ( ዘዳ 20፡ 1፣ መሳ 7፡ 7) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ከጉዳዮች ሁሉ አንዱ በመነሳት(በመንቃት) እንዲያደርጉት እግዚአብሄር የጠራቸዉን ለማድረግ ለመሄድ ሰዎች ከእምነት ዉጪ በሮማን ዛፍ ስር መቀመጣቸዉ ነው (1ሳሙ 9፡ 16፣ መዝ 147፡ 10) ፡፡ ይህን ድል ለማሸነፍ ሳዖል ይህ አስተሳሰብ አልነበረው ነገር ግን ይህ ሁል ጊዜ እምነት የነበረዉን ዮናታንን በመሆን ያበቃል ፡፡

1-ሳሙኤል (14፡ 7-14)፡ ዮናታን የጋሻ አጃግሬዉ ድጋፍ ነበረው (ቁጥር 7) ፤ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስም ከእርሱ ጋር አብረዉ የሚጓዙ በርናባስ፣ ጢሞቲዋስ፣ ቲቶ እና ሲላስ ነበሩት ፤ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር የሚጓዙ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ባላቸዉ ሰዎች ይከብበናል ፡፡ ዮናታን የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለመለየት ከእግዚአብሄር ምልክት ተመለከተ ፤ እርሱና ጋሻ አጃግሬው ቀርበዉ እንዲያዩዓቸዉ ፍልስጤማዉያንን ይፈቅዱላቸዋል ፤ ፍልስጤማዉያን ወደ እነርሱ ለመምጣት ጠብቁን ብለዉ ከነገሯቸው በዚያዉ ይቆማሉ ፤ ፍልስጤማዉያን ወደ እነርሱ እንዲመጡ ከነገሯቸው ይሄዳሉ “ ምክንያቱም እግዚአብሄር አሳልፎ ስለሚሰጣቸው “ (ቁጥር 8-10) ፡፡ ማክአርቱር ያመለከተው ይህ ለምልክት ከእግዚአብሄር ከጠየቀዉ ከጌዲዎን ጥያቄ ጋር እንደ ሚመሳሰል ነው (መሳ 6፡ 36-46) ፡፡ የፍልስጤም ወታደሮች ጠሩአቸው ዮናታንና የጦር ተሸካሚዉም ወደ እነርሱ ሄዱ (ቁጥር 11-12) ፤ እግዚአብሄር ዮናታንን ጠይቆት የነበረዉን ምልክት ሰጠው 20 ሰዎችንም መታቸው ጋሻ አጃግሬዉም ጨረሻቸዉ(ገደላቸዉ) (ቁጥር 14) ፡፡

1-ሳሙኤል (14፡ 15-17)፡ ፍርሀት በፍልስጤማዉያን ሰፈር ተሰራጨ ፤ “ ምድሪቱም እንኳን ተናወጠች ፤ ከእግዚአብሄርም ዘንድ ታላቅ ሽብር ሆነ “ (ቁጥር 15) ፡፡ ማክአርቱር “ የመሬት መናወጡ በፍልስጤማዉያን መካከል ለተፈጠረዉ ሽብር በዮናታን እና በጋሻ አጃግሬዉ ድንገተኛ ጥቃት መለኮታዉ ጣልቃ ገብነት እንደ ተጨመረበት የሚያረጋግጥ እዉነት እንደ ሆነ ይናገራል “ ፤ (መዝ 3፡ 8፣ ምሳ 21፡ 31) ፡፡ ወታደሮቹ የዮናታንን የእምነት ዝላይ እና የፍልስጤማዉያንን ሽብር አዩ (ቁጥር 16) ፤ ሳዖልም ማን እንዳልነበረ ለማየት ቆጠራ አደረገ ዮናታንና ጋሻ አጃግሬዉም አልነበሩም (ቁጥር 17) ፡፡

1-ሳሙኤል (14፡ 18-23)፡ ማክአርቱር ሳዖል “ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመመርመር “ ካህኑን አኪያን የእግዚአብሄርን ታቦት (ወይም ኤፉዱን) “ እንዲያመጣ ነገረው ፤ ነገር ግን ሳዖል እየተናገረ የፍልስጤማዉያን ጭንቀት ጨመረ ሳዖልም ካህኑን እንዳይጨነቅ ነገረው (ቁጥር 18-19) ፡፡ በታላቅ ዉዝግብ ዉስጥ እርስ በእርስ እየተዋጉ እነበሩት ፍልስጤማዉያን ላይ ሳዖል ጦሩን አቀና (ቁጥር 20) ፤ ፍልስጤማዉያንን ለመቀላቀል የሳዖልን ጦር ሸሽተዉ የነበሩትም ወታደሮች በመመለስ ከእስራኤላዊያን ጋር በመሆን አጠቁዓቸው (ቁጥር 21) ፤ እንዲሁም በፍርሃት ተደብቀዉ የነበሩት እስራኤላዊያንም የሳዖልን ጦር ተቀላቀሉ ምክንያቱም በግልፅ ድሉ ማሸነፍ ስለ ነበር (ቁጥር 22) ፡፡ በጦር ሜዳ የነበረ ሁሉም ሰዉ የእግዚአብሄርን ኃይል አየ እግዚአብሄርም እስራኤልን አዳነ (ቁጥር 23)፡፡

1-ሳሙኤል (14፡ 24-26)፡ ከዉጊያ የተመለሱት ወታደሮች ደክመዉም ተርበዉማል ነገር ግን ሳዖል ለአካላቸዉ የሚያስፈልጋቸዉን ሊሰጣቸዉ አልፈቀደም ፤ ከምሽት በፊት ምግብ እንዳይበሉ አስምሎአቸዉ ወይም የሚበላ የተረገመ ይሆን ብሎአቸዉ ነበር (ቁጥር 24) ፡፡ ሳዖል በራሱ ህዝብ ላይ እንዲህ አይነት አስቀያሚ ርግማን ለምን ያስቀምጣል ? የእግዚአብሄርን ሳይሆን የራሱን ቁጥጥር እየመሰረተ (እያቋቋመ ስለ ነበር ) ፡፡ ወታደሮቹ ወደ እንጨት ዉስጥ ሄዱ መሬት ላይ የሚፈስስም ማር አዩ (ቁጥር 25-26) ፤ የተስፋይቱ ምድር ወተት እና ማር የምታፈስስ ተብላ ስትገለፅ ምን ያክል ጊዜ አይተናል ? በዚያ በእነርሱ ፍት ማር ነበር ነገር ግን ወታደሮቹ በሳዖል ርግማን ምክንያት ምንም አልበሉም (ቁጥር 26) ፤ ይህ እግዚአብሄር ማን እንደ ሆነ የሳዖል የመረዳት እጥረት ተጨማሪ ማስረጃ ነው ፤ እግዚአብሄር ሰጥቶ የነበረዉን በመያዝ በእግዚአብሄር ላይ ያለዉን የመደገፍ እጥረት የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው ፡፡ ሳዖል የድሉን ዋጋ ለራሱ ለመዉሰድ ፈለገ እንጂ ለእግዚአብሄር አልሰጠም (መዝ 19፡ 9፣ 81፡ 16፣ 119፡ 103፣ ሕዝ 3፡ 3) ፡፡

1-ሳሙኤል (14፡ 27-33)፡ ዮናታን ማሩን አየዉ ወደ ማሩም ገባ ፤ በበላዉም ጊዜ የታደሰ ጥንካሬ ተቀበለ (ቁጥር 27) ፡፡ ዮናታን የእግዚአብሄርን ቃል ስለ ሚያዉቅ ማሩ ከእግዚአብሄር እንደ መጣ አዉቋል ፤ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለመለየት እግዚአብሄርን ቃል ማወቅ ያስፈልገናል ፡፡ ወታደሮቹ ዮናታንን ስለ አባቱ ርግማን በነገሩት ጊዜ ዮናታንም ሳዖል ለወታደሮቹ እንዲበሉ ባለ መፍቀዱ ምድሪቱ ላይ ችግር አምጥቷል አለ (ቁጥር 28-30) ፡፡ እስራኤላዊያን ፍልስጤማዉያንን አሸነፉዓቸዉ ነገር ግን በጣም ደክሟቸዉ ነበር ከማረኳቸዉም እንስሳቶች ለመዉሰድ ተጣደፉ በማረድም ስጋዉን እስከ ደሙ በሉት (ቁጥር 31-33) ፤ ወታደሮቹ በጣም በመራባቸዉ የእግዚአብሄርን ህግ (ዘሌ17፡ 10-14) በመተላለፍ ወደ እስራኤል ኃጢዓት አመጡ ፡፡ በቁጥር 30 ዮናታን እንደ ገለፀዉ “ ይልቅስ ካገኙት ከጠላቶቻቸው ምርኮ በልተዉ ቢሆን የፍልስጤማዉያን ይበልጥ ነበር !”

መደምደሚያ

የእግዚአብሄርን እቅድ በምትከተሉ ጊዜ ነፃነት አለ ፤ የሰዉን እቅድ በምትከተሉ ጊዜ ባርነት አለ ፡፡ ነፃነትን ለመቅመስ በእምነት መራመድ ይጠበቅባችኋል ፡፡ ዮናታን አሸናፊዉ እርሱ እንደ ነበር አምኗል በሂደቱም በብዙ የእግዚአብሄርን መገኘት መቅመስ ችሏል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: 1 Samuel (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 240.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 363.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 323.

  4. MacArthur, p. 323.

  5. MacArthur, p. 323.

  6. MacArthur, p. 323.

  7. MacArthur, p. 323.

ጥያቄዎች

  1. ሳዖል ባለማመን እየተጠራጠረ በነበረበት ጊዜ (ቁጥር 2) ዮናታን በእግዚአብሄር በመታመን እንዴት ነበር ወደ ፊት የተጓዘው ? ጠላቶቹን ለማጥቃት ዮናታን ስለ እቅዱ ለምን ለአባቱ እንዳልነገረዉ ምን ታስባላችሁ?
  2. በሮሜ (8፡ 31) ከተገለጸዉ ጋር ዮናታን ያለዉን ልብ እንዴት ታዩታላችሁ ? ቁጥር 6 እግዚአብሄር በጌዴዎን በኩል ካደረገዉ ጋር እንዴት ይወዳደራል ? (መሳፍንት 7)
  3. ሳዖል የእስራኤል ሰዎች ያስደረጋቸዉ መጥፎዉ መሀላ ምን ነበር ? የተሳሳተ የሆነዉን የሳዖልን ትኩረት እንዴት ታዩታላችሁ ?
  4. ሳዖል ፆም ጠርቶ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር ለሰራዊቱ እንዴት ሰጠ ? ማሩን የበላዉ ብቸኛዉ ሰዉ ማን ነበር ? ማሩን ከበላ በኃላ በእርሱ ላይ ምን ሆነ ?
  5. በ ቁጥር 37 የእግዚአብሄርን ምክር ሳዖል እየፈለገ የነበረዉ ለምን ነበር ? በሳዖል እና በዮናታን ህይወት ጨዋታ በመሆን 1ጴጥ (5፡ 5) እንዴት ታዩታላችሁ ?
  6. በ 1ሳሙኤል 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 14:6

“Jonathan said to the attendant who carried his weapons, ‘Come on, let’s cross over to the garrison of these uncircumcised men. Perhaps the LORD will help us. Nothing can keep the LORD from saving, whether by many or by few.’”

ዮናታንና አባቱ ሳኦል ሁለቱም የፍልስጥኤማውያንን የጦር ሰፈር ቢያውቁም ሳኦል ከስድስት መቶ ሰዎቹ ጋር በጊብዓ ዳርቻ ተቀምጦ ነበር ዮናታንና ገሻ ጃግሬው እግዚአብሔር ድርጊታቸውን ሲያፀናላቸው በእምነት በፍልስጥኤማውያን ላይ ጥቃት ይፈፅሙ ዘንድ ወጡ ፡፡ ዮናታንም ስለዚህ አልተናገረም ነበር እርሱም ለታማኝ ገሻ ጃግሬው “ ና እንሂድ” አለው ፤ ዮናታን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ከሆነ ድል እንደሚቀዳጁ አምኖ ነበር ፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን በእምነት ወጡ ድልንም ተቀዳጁ ፤ ሀያ ሰዎችንም ገደሉ ፡፡ ሰኦል በፍርሀት ውስጥ ሲቀር ዮናታን በእምነትና በመታዘዝ በመውጣት ነፃነትን አገኘ ፡፡

በህይወትህ ውስጥ በእምነት ልትወጣበት የሚገባ ጉዳይ አለ ? አሁንም ያ ድምጽ “ና እንሂድ “ ይልሀል ፡፡ በእግዚአብሄር ሀይል የምታምን ከሆነ በእምነት ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ስትወጣም መንገድህ ልክ መሆኑን እንድያስረግጥልህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፤ የዮናታንን መንገድ እንዳረጋገጠለት ሁሉ ያንተንም ያረጋግጥልሀል ፡፡ የማታውቀውን ከመፍራት ለማቆም ጊዜው ዛሬ ነው ፡፡ ምርጫው ያንተ ነው በእምነት ለመውጣትና ነፃነትን ለመለማመድ እንድሁም ደግሞ ከምታስበው በላይ የሆነ ነገርንም ለማግኘት ወይም ከመውጣት መቅረትና ሌሎች በነፃነት ውስጥ የሚያደርጉትን ጉዞ ማየት ፡፡

“ ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን ና ወደ እነዚህ ቄላፋን ጭፍራ እንለፍ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል ፡፡ “

- 1ኛ ሳሙኤል 14፡6

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤፌሶን 3፡20 –“ እንግድህ በእኛ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው ፡፡ “

ዕብራውን 11፤1 –“ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው ፡፡ “

ያዕቆብ 2፡14-17 –“ ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል ? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ? መንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብን ቢየጡ ከእናንተ አንዱም በደህና ሂዱ እሳት ሙቁ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል ? እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ ሞተ ነው ፡፡ “