Losing the Royal Dynasty
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 1ሳሙኤል 13 ዛሬ ፍሬ ነገራችን ስለ ጊዜ (ወቅት) ነው ፡፡ በመረዳት በእግዚአብሄር ፍቃድ ትጠብቃላችሁ ? በእግዚአብሄር ፍቃድ ትናገራላችሁ ትጓዛላችሁስ ? በዚህ ምዕራፍ ነቢዩ፣ ካህኑ፣ ሌዋዊዉ እና ንጉስ ቀቡዉ ሳሙኤል አለን ፤ በተጨማሪም በተለይም በሰሜን ነገዶች መካከል በጣም ታዋቂ የነበረው ምክንያቱም ከቢኒያም ነገድ የነበረ ከይሁዳ ያልነበረው ንጉሱ ሳዖልም አለን ፡፡ ምንም እንኳን ሳዖል የእግዚአብሄር ምርጫ እና ለንግስና የተቀባ ቢሆንም ጉዳይ ነበረው ፤ አንዳንድ ማብራሪያዎች ሳዖል የእግዚአብሄር የተመረጡት ህዝቦች ምልክት እንደ ነበር ይናገራሉ ፡፡ በምዕራፍ 13 ሳዖል አንዳንድ መጥፎ ምርጫዎችን አደረገ ፤ በድንገት ሳያስበዉ አለመታዘዝ ዉስጥ አልወደቀም አቅጣጫዉን በመምረጥ አደረበት እንጂ ፡፡ ሳዖል የሚመጣዉ አደጋ በማወቅ በፍርሀት ጠበቀ ነገሮችን ወደ እጁ ለማስገባት በመጥፎ ሁኔታ መረጠ ፡፡
የታሪኩ መነሻ ሀሳብ በ 1ሳሙ (10፡ 8) ላይ የሚገኝ ነው ፤ ሳሙኤል የሳዖልር ራስ በዘይት በመቀባት ሳዖል ንጉስ እንደ ሚሆን አወጀ ፤ ከዚያም ሳሙኤል ሳዖልን የሚቃጠል መስዋዕት በማቅረብ የህብረት መስዋዕት እንዲሰዋ እርሱን እንዲጠብቀዉ ወደ ጌልጌላ ላከው ፡፡ ሳሙኤል እስኪደርስ ሰባት ቀን እንዲጠብቁ እና ምን ማድረግ እንዳለበት እንደ ሚያሳየዉ ሳዖልን ነገረው ፤ እነዚህ ሊታወሱ የሚገባቸዉ ትንቢታዊ ቃል ነበሩ ፡፡ ምሁራን በምዕራፍ 13 ሰዎስት አመታት አልፈዉ እንደ ነበር እና ሳዖል እንደ ገና በጌልጌላ እንደ ነበር ይገምታሉ ፡፡ የተለመደ እንደ ሚሰማው ያውቃል እንዲሁም ደግሞ የሳሙኤልን መምጣት እየጠበቀ እንደ ነበርም ያውቃል ፡፡
ትምህርት
1-ሳሙኤል (13፡ 1-4)፡ ምን ያክሉ የሳዖል የስልጣን ዘመን አስቸጋሪ እንደ ሆነ ለማወቅ ይሞከራል ምክንያቱም ትክክለኛው የአመታት ቁጥር በዕብራዊያን ፅሁፍ ደብዛዛ ስለ ነበር ፡፡ ምሁራን ምዕራፍ 13 ከሳዖል ዘመን ቀድሞ ምናልባትም በአንደኛዉ እና በሰዎስተኛዉ አመት መካከል እንደ ተከናወነ ይስማማሉ (ቁጥር 1) ፡፡ ሳዖል 2,000 ጦር ከእርሱ ጋር እንዲሁም ደግሞ 1,000 ጦር ከዮናታን ጋር የሚሆኑ መመልመል ጀመረ (ቁጥር 2) ፤ ሳሙኤል እስራኤልን ነገስታቶች የሚጠብቃቸዉ ጦር እንደ ሚያስፈልጋቸዉ ነግሮአቸዉ ነበር ይህም መጀመሪያዉ ነበር ፡፡ እነዚህ እንደ ሰዉ ጠባቂ እና ለሳዖል ጥቃት ባስፈለገ ጊዜ ፍልስጤማዉያን ላይ ጉዳት ማምጣት የሚችሉ ልዩ ኃይል ነበሩ ፤ ፍልስጤማዉያን ጦርነት የሚያዉጁ ከሆነ 3,000 ምልምል ወታደሮች የሚበቁ አልነበሩም ፡፡ ይህ በራሱ ከተማ ሳዕል የተደገፈበት የዮናታን መጀመሪያ መጠቀስ ነው ፡፡
ዮናታን ፍልስጤማዉያንን መታቸው ምክንያቱም በናስብ ማለፊያዉን ዘግተዉት ስለ ነበር ዋጋዉም ለሳዖል ተሰጠ (ቁጥር 3) ፡፡ በሁሉም የዮናታን መፅሀፍ ቅዱሳዊ መግለጫዎች አስተዋይ እና የተከበረ እንደ ሆነ ነው ፡፡ ሳዖል በበግ ቀንደ መለከት በመንፋት የዚህን ዉጊያ ድል አበሰረ ይህም ወደ ቤታቸዉ ሄደዉ ለነበሩት ለሚዋጉት ለሁሉም ሰዎችሰ ለንጉሱ እርዳታ ተመልሰዉ እንዲመጡ የማገገሚያ ጥሪ ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ ጌልጌላ ለእስራኤላዊያን በኢያሱ ዘመን ጊዜ የማገገሚያ እና ቅዱስ ስፍራ ነበረች በሳሙኤል ጊዜም ቀጠለች (ሆሴ 4፡ 15፣ 9፡ 15፣ አሞ 5፡ 5) ፤ ይሁን እንጂ ጌልጌላ ለእስራኤላዊያን ጥሩ መከላከያ ስፍራ አልነበረችም ፡፡
1-ሳሙኤል (13፡ 5-9)፡ ከትንሽ ቀን በፊት በ 1ሳሙኤል 7-8 ላይ ስላስተማርኩት ማስተጋገያ ማድረግ ያስፈልገኛል ፤ በዚያ የተሰበሰበዉ የፍልስጤም ኃይል ከዚህ በፊት ከነበረዉ በጣም ብዙ ነበር ብያለሁ ነገር ግን ወደ ፊት እራሴ አገኘሁት ፤ ይህ ኃይል ግዙፍ ነበር - 3,000 ሰረገሎች፣ 6,000 ፈረሰኞች እና ለመቁጠር የሚያስቸግር የእግረኛ ወታደሮች ነበሩት (ቁጥር 5) ፤ ሰረገላው የቀድሞዉ አለም ታንክ ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን እንዳዩአቸው በጣም ፈሩ በዋሻ ዉስጥ እና በአለቶች መካከል ተሸሸጉ (ቁጥር 6) ፤ ሳዖልም ሳሙኤል እስኪመጣ በጌልገላ ሰባት ቀን ጠበቀው (ቁጥር 7-8) ፡፡ እየጠበቀዉ ሳለ ወታደሮቹም እየከዱ ነበር፣ ፍርሀት እየጨመረ ነበር እንዲሁም ጭንቀት እየወጣ ነበር ፤ ሳዖል ሳሙኤል እስኪመጣ መጠበቅ እንደሚያስፈልገዉ ያዉቃል ምክንያቱም ለእርሱ ከመታዘዙ በፊት የአመታት ትንቢታዊ ቃል እንዲነገረው ፤ ሆኖም ግን ይህ ለሳዖል እና ለህዝቡ መቅሰፍት ሆነባቸው ፡፡ ይህ ለሳዖል የፈተናዉ አደገኝነት ነበር ለሌሎች ንጉሶችም አደገኛ ፈተና ይሆንባቸዋል ፡፡ ሰባተኛዉ ቀን ላይ ሳዖል ከዚ በላይ መጠበቅ አልቻለም ትግስቱና እምነቱ አበቃ ፤ ሳዖል የሚቃጠለዉን መስዋዕት እና የደህንነት በመጥራት(በማምጣት) በመጥራት ለእግዚአብሄር አቀረበ (ቁጥር 9) ፡፡ ይህ ለሳዖል እድሉን የሚያበላሽ ዉሳኔ ነበር ምክንያቱም ሌዋዊያን ካህናቶች መስዋዕትን የማቅረብ ኃላፊነት ነበራቸዉ እንጂ ነገስታቶች ስላልነበሩ ፡፡
1-ሳሙኤል (13፡ 10-12)፡ ሳዖል መስዋዕት ማቅረቡን እንደ ጨረሰ ሳሙኤል ደረሰ (ቁጥር 10) ፤ ሳዖል ወደ ሳሙኤል በመሄድ ያደረገዉን ነገረው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ለሳዖል የዚህን ክስተት ትርጉም ማስረጃ ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው ፤ የሳዖል ድርጊት ለኛ አላሳፈላጊ ይመስለናል ነገር ግን አስፈላጊነታቸዉ በጣም ትልቅ እና ከፍ ያለ ስለ ነበር ፡፡ የሳሙኤል ጥያቄ “ ምንድን ነዉ ያደረከው ?” ሳዖል በመደንገጡ የጥፋቱ ስሜት ወዲያዉኑ ተገለጠ ፤ ራሱን ለመከላከል እና ድርጊቱን ለመሸፈን መዋሸት ጀመረ ፡፡ ሳዖል ድርጊቱን በብዙ “ እኔ “ በሚል ንግግር በመግለፅ መስዋዕቱን ለማቅረብ እንደ ገፋዉ ተናገረ (ቁጥር 11-12) ፤ ሳዖል ድርጊቱን በምክንያት በማብራራት በመዘግየቱ ሳሙኤልን ተጠያቂ አደረገ ፤ ሳሙኤል የደረሰዉ በትክክለኛዉ ጊዜ ነዉ አልዘገየም አልፈጠነምም ፡፡ ሮሜ (5፡ 6) የሚለው “ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢዓኞች ሞቶአልና “ ፤ ኒቭ “ በትክክለኛዉ ጊዜ እንደ መጣ “ ነዉ የሚናገረው ፡፡ ሳዖል የሚረዳ አልነበረም ሳሙኤልም በትክክለኛዉ ጊዜ ደረሰ ፤ በትክክለኛው ጊዜ ላይ ክርስቶስ ለእኛ ሞተ ፡፡ ጭንቀት የለም ምክንያቱም ክርስቶስ በትክክለኛዉ ጊዜ ስለመጣ ፤ በእግዚአብሄር ላይ ትግስት በማጣት ሳንጠብቅ ምርጫችንን ምን ያክል ጊዜ አድርገናል ?
1-ሳሙኤል (13፡ 13-14)፡ በቀሩት በትንሽ በሚንቀጠቀጡ ጦሩ ፊት ሳዖል በአደባባይ አፈረ ፤ እምነት የጉደለ አለመታዘዙ ንግስናዉን እና ስረዉ መንግስቱን ያሳጣዉ ነበር ፤ መንግስቱና ዘሩም አይቀጥልም ፡፡ ሳዖል የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ገፋ(ሳይቀበል ቀረ) እግዚአብሄርም ሳዖልን በመተዉ የእግዚአብሄር የራሱን ልብ የሚከተል አንድ ሰዉ ተመለከተ (ቁጥር 14) ፡፡ ንጉስ ሳዖል እንደ ህዝቡ ልብ ነበር ንጉስ ዳዊት ደግም እንደ እግዚአብሄር ልብ ነበር ፤ የተሰጠ ቀን ወይም ጊዜ አልነበረም ፤ ምናልባትም ይህ ንግግር ዳዊት ከመወለዱ በፊት የተደረገ ነበር በመዝሙር 139 ከመወለዱ በፊት እንኳን እግዚአብሄር እንደ ሚያዉቀዉ ወደ ተናገረዉ ወደ ዳዊት ንግግር ትኩረት ያመጣሉ (መዝ 139፡ 13-16) ፡፡
የእግዚአብሄር እቅድ በፍፁም የሚሰናገል አይደለም ! የእግዚአብሄር እቅድ አካል እንድንሆን እድል የተሰጠን እኛ ካልታዘዝን እግዚአብሄር ሌላ ይጠቀማል ፡፡
1-ሳሙኤል (13፡ 15-22)፡ ሳዖል ልጁ ዮናታን በነበረበት ወደ ጊቢዓ ተመለሰ ፤ በዚያን ጊዜ ከእርሱ ጋር የቀሩ ሳዖል 600 ሰዎች ብቻ ነበሩት (ቁጥር 15-16) ፡፡ ዮናታን የሳሙኤልን መግለጫ ሰማ በፍፁምም የሳዖልን ዙፉን እንደ ማይወርስ አወቀ ፡፡ ፍልስጤማዉያን እስከ መጨረሻዉ ሳዖልን ሊያጠፉ ወታደሮቻቸዉን በሰዎስት ትልቅ ክፍሎች አሰማሩ (ቁጥር 17-18) ፤ የሳዖል ጦር መሳሪያ አልነበረውም ምክንያቱም ፍልስጤማዉያን በምድራቸዉ ብረት ቀጥቃጭ እንዲኖር አልፈቀዱላቸዉም ነበር (ቁጥር 19) ፡፡ ጦሩ ለሚመጣዉ ዉጊያ የጦር መሳሪያቸዉን ከማረሺያ፣ ከዶማ እና ከማጭዶች አዘጋጀ (ቁጥር 20-22) ፡፡
1-ሳሙኤል (13፡ 23)፡ በምዕራፍ 13 በዚህ መጨረሻ ቁጥር ላይ ፍልስጤማዉያን ለዉጊያዉ ተዘጋጁ ፡፡
መደምደሚያ
ከእናንተ “ምክንያታዊ “ የጊዜ ሰሌዳ ጋር እግዚአብሄር ባልተገናኘ ጊዜ ምንድን ታርጋላችሁ ? አስታዉሉ እግዚአብሄር በፍፁም አይዘገይም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ የመጨረሻዋ ደቂቃ(በእኛ እይታ) እስክታልፍ ድረስ በመጠበቅ ታማኝነታችንን እና መታዘዛችንን ይፈትናል ፡፡ ለመጠበቅ ፍቃደኞች ናችሁ ? የምናደርጋቸዉ ምርጫዎች አስደናቂ ዉጤት ሊኖራቸዉ ይችላል ፤ ነገሮችን በራሳችሁ እጅ ለመዉሰድ በተፈተናችሁ ጊዜ የተገለጠዉን የእግዚአብሄር ፍቃድ ለመታዘዝ ምረጡ ቀጥሎም ስለሚመጣዉ በእርሱ ታመኑ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በቁጥር 4 እስራኤላዊያን ለፍልስጤማዊያን የተጠሉ ይሆኑ ነበር ለምን አለ ? እንደ ክርስቲያን በአሁን ጊዜ የምንታገለዉ ከማን ጋር ነው ? (ኤፌ 6፡ 12)
-
በቁጥር 4 የሳዖልን ደህንነት አለመኖርን እንዴት ታዩታላችሁ ? በትክክል ጭፍራዉን ያጠቃዉ (የመታዉ) ማነው ?
-
የእስራኤል ሰዎች ለምን ነበር የተበታተኑት ? ሳዖል የሳሙኤልን ቃል ለምን እንዳላመነ ምን ታስባላችሁ ? (1 ሳሙ 10፡ 8)
-
በቁጥር 13 ሳዖል ለእግዚአብሄር እንዴት ነበር የማይታዘዝ የሆነው ? ዉጤቱ ምን ነበር ? ይህ መጥፎ ዉጤት ወይም ምክንያታዊ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
ለእስራኤል እግዚአብሄር በንጉስ ላይ ምን አይነት ልብ ይፈልጋል ? (1ሳሙ 13፡ 14፣ መዝ 23፡ 1፣ 78፡ 72፣ ሐዋ 13፡ 22)
-
በ 1ሳሙኤል 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።