Historical Books 1 Samuel

A Brand New King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 230 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ስንጀምር ትንሽ የሆነ መረዳት ለማምጣት እፈልጋለሁ ፤ 1ሳሙኤል በጣም በፍጥነት እንጓዛለን ፤ በምዕራፍ 8 ላይ ሳሙኤል አርጅቶ ነበር ፡፡ በመፅሀፍት ያሉን ዋና ዋና ነገሮች ናቸው ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (11፡ 1)፡ አሞናዊዉ ናዖስ በእስራኤል ላይ መጣ ፤ አሞናዊያን እነማን ነበሩ ? ከሎጥ ትንሽ ሴት ልጅ ዘር ደስ በማይል ሁኔታ(ከቅርብ ዘመድ ግንኙነት) ጋር የመጡ ነበሩ ፡፡

በተለይም በኢያቢስ ገለዓድ በጋድ ነገዶች ላይ መጡባቸው ፤ በኢያቢስ ገለዓድ ላይ ለምን ይመጣሉ ? ወደ መሳፍንት 20-21 ተመልሰን ስንሄድ የኢያቢስ ገልዓድ ሰዎች በሀይል በቁጥር የቀነሰ ነበር ምክንያቱም ከቢኒያም ጋር በነበረዉ ጦርነት ላይ የተቀላቀሉ ስላልነበር ፤ ይህ ለመረዳት በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በዚህ ምዕራፍ የእግዚአብሄር ሰዎች “ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ ሲሉ “ የምናየዉ የመጀመሪያዉ ነገር ስለ ነበር ፤ ለምን ? ጦር አልነበራቸዉም ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 2)፡ አሞናዊያን ኪዳን ከማድረጋቸዉ በፊት የእያንዳንዳቸዉን የቀኝ አይን ማዉጣት ፈለጉ ፤ ለምን ቀኝ አይን ፈለጉ ? ብዙ ምሁራን ቀይ አይን ጠባብ ነገር ለማየት ይጠቅም ስለነበር እንደሆነ ያምናሉ ፡፡ አሞናዊያን እስራኤላዊያንን ለማዋረድ ይህን ለማድረግ ፈለጉ ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 3)፡ መሪዎቹ እስራኤላዊያን ያሸንፏቸዉ እንደሆነ የፍቃድ ጊዜ ለሰባት ቀን እንዲጠብቁዓቸዉ ጠየቁ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 4-5)፡ መልዕክተኞች ወደ ሳዖል ሄዱ ፤ በእነዚህ ቁጥሮች የወንድማማችነት ሀሳብን ታያላችሁ ፡፡ ሰዎቹም ስለ ጋድ ሁኔታ በሰሙ ጊዜ አዘኑ ፤ መልዕክቱ መጀመሪያ በሚሰራጭ ጊዜ ሳዖል በማሳ ነበር ፤ በተመለሰም ጊዜ “ ሁሉም ለምንድን ነዉ የሚያለቅሱት “ ብሎ ጠየቀ ሳዖልም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ታሪኩ ተነገረው ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 6-7)፡ የእግዚአብሄር መንፈስ በሳዖል ላይ በኃይል መጣበት “ ቁጣዉም በኃይል ነደደ “ (ቁጥር 6)፡፡ ሳዖል ሁለት በሬዎችን በመግደል ወደ ቁርጥራጭ ቆረጣቸው ፤ ከዚያም ለእያንዳንዱ ነገድ በማስፈራት(በዛቻ) ቁራጮቹን ሰዎች በማስያዝ ላካቸዉ ፡፡ ዛቻዉ (ማስፈራቱ) ከሳዖል እና ከሳሙኤል ጋር የኢያቢስ ገለዓድ ወንድሞችን ለመታደግ መዝመት የማይመጡ ከሆነ በሮቻቸዉ በተመሳሳይ መንገድ እንደ ሚታረዱ ነበር ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 8-11)፡ 330,000 ሰዎች ለመዋጋት እንደ ሚመጡ ቃል ገቡ ፤ ወንድማማችነት ተመሰረተ ! የሚሰራበትንም እቅድ ሳዖል ነደፈ እስራኤልም አሞናዊያንን አወደሙዓቸው ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 12-13)፡ ይህ ድል ሳዖልን እንደ ንጉስ ከፍ አደረገው ፡፡ ሳሙኤል እድሉን በመመልከት በነገዶቹ አንድነትን ለማምጣት ሰበሰባቸው ፡፡ እግዚአብሄር የሳዖልን እግዚአብሄራዊ ንዴት እና ብስጭት በመጠቀም ድልን ሰጠ ፤ ወዲያዉኑም ሳዖል ከፍ ያለ ሆነ ፡፡ “ እግዚአብሄር ይህን አደረገ “ ብሎ የነበረዉ ሳዖል አንዱ ነበር ፤ እግዚአብሄር ከተበላሸዉ የክህነት አገልግሎት እንደ ንጉስ ወደ ሳዖል እንዲሄድ ሳሙኤልን እንደ ድልድይ ተጠቀመበት ነገር ግን እስራኤል ንጉስ እንዲኖረዉ በፍፁም የእግዚአብሄር አሳብ አልነበረም ፡፡

1-ሳሙኤል (11፡ 14)፡ ሕዝቡም በአንድ ላይ ወደ ጌልጌላ መጡ ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስለ አንድነት እናወራለን ነገር ግን በአንድ ላይ እንዋጋለን ? ለምክንያቱስ በአንድ ላይ እንመጣለን ? አንዱ ሌላዉን ይይዘዋልስ ? “ በእናንተ ህይወት ላይ በሚሆነዉ ኃጢዓት መደሰት አልፈልግም ፤ በህይወታችሁ በመምጣት የሚያድናችሁ ወኪል መሆን እፈልጋለሁ እንላለን ?” በተሰበሩት ዙሪያ እግዚአብሄር ማህበረሰብን መስራት ይችላል ፡፡ በእኛ ዙሪያ ያሉት በትግል ዉስጥ እያሉና በጦርነት ጠፍተዉ በእኛ ኑሮ ላይ ምን እየተካሄደ እንደ ሆነ ለመለየት ቀላል ነው ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ አዳኝ ሊያስነሳ ይችላል ፡፡ ሁላችንም ከኢያቢስ ገለዓድ ማገገም ያስፈልገናል ሁላችንም ችግር አለን ፤ የምንረዳዉ ነገር በዚህ እንዳለ አምናለሁ ፤ ምንም እንኳን ሳሙኤል ተስፋ ቢቆርጥም ህዝቡን ወደ እግዚአብሄር ለቀቃቸዉ(ተዋቸዉ) ፡፤

1-ሳሙኤል (12፡ 1-12)፡ በምዕራፍ 12 ሳሙኤል የራሱን አፈፃፀም ከለሰ ፤ ወደ እስራኤል በሚያደርገዉ ተግባሩ የተጠነቀቀ ነበር ፡፤ እነዚህን ጥያቄዎች ለምን እየጠየቀ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር እንዲያደርግ ጠይቆት የነበረዉን ጥሪዉን እንደ ፈፀመ ለማመልከት ፈለገ ፤ በሚያናድድ ሁኔታ ሕዝቡ የፈለገዉን በተቀበለ ጊዜ ስለ እግዚአብሄር የሚረሱ መሰሉ ፡፡

1-ሳሙኤል (12፡ 13-21)፡ ችግር የነበረው ሳሙኤል ተናገረ ፤ እስራኤላዊያን ንጉስ ነበራቸዉ ነገር ግን ንጉስ በራሳቸዉ ምርጫ ፈልገዉ እንጂ በእግዚአብሄር አልነበረም ፡፡

1-ሳሙኤል (12፡ 22)፡ ይህ የእስራኤል ንጉስን ምርጫ ከእግዚአብሄር ፍላጎት ዉጪ አልነበረም ፤ ሳሙኤል ህዝቡን እግዚአብሄር ህዝቡን አይተዉም ወደ ሚለዉ አንድ እዉነት ጠራቸው ፡፡

1-ሳሙኤል (12፡ 23-25)፡ ሳሙኤል ለእስራኤላዊያን መፀለይ በማቆም እግዚአብሄርን እንደ ማይበድል ቃል ገባ ፤ አሁንም መልካሙን እና ትክክለኛዉን መንገድ ሊያስተምራቸዉ የተሰጠ ነበር ፡፡ እስራኤላዊያንን እግዚአብሄርን እንዲፈሩ እና በሙሉ ልባቸዉ እንዲያመልኩት አዘዛቸው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ታላቅ ነገርም እንዲያስታዉሱ ፡፡ ሳሙኤል እነርሱና ንጉሶቻቸዉ ክፉ ነገር ማድረግ ከቀጠሉ እንደ ሚጠፉ እስራኤላዊያንን አስጠነቀቃቸው ፡፡

መደምደሚያ

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የህዝቡን የኃጢዓተኝነት ባህሪይ በሞት እና በጥፋት ፈርዷል ፤ በዚህም በእዉነቱ ኃጢዓት ምን ያክል መጥፎ እንደ ሆነ እና በኑሮአችን የኃጢዓት መሞት አስፈላጊ መሆኑን መረዳት እንችላለን (ሮሜ 7፡ 12-13) ፡፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር ማለት ቢዝነስ(ስራ) እንደ ሆነ አዉቀዋለል ፤ ኃጢዓት መስማት ያልቻለዉ ኤሊ እንድንሆን ወይም ቆይቶ መስማት ያልቻለዉ እና ከመስመር የወጣዉ ንጉስ ሳዖል እንድንሆን ምክንያት ይሆንብናል ፡፡ በስጋ ነገሮች የተያዝን በመሆን ከእግዚአብሄር እቅድ እንዳንወጣ ጠንቃቆች መሆን አለብን ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት በቅድስና እንጓዝ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ናዖስ ለኢያቢስ ገለዓድ የሰጠዉ ንግግር ምን ነበር ? የገለዓድ ነገዶችም ይህን ንግግር ለምን ተመለከቱት ?
  2. የእግዚአብሄር መንፈስ በሳዖል ላይ በመጣ ጊዜ ምን ተፈጠረ ? ፍቃዱን እንድንፈፅም መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳናል ? (ሉቃ 4፡ 1፣ ሮሜ 8፡ 14)
  3. በ 1ሳሙ (11፡ 15) ቀድሞ እንደ ንጉስ ቀብቶላቸዉ በነበረ ጊዜ በእግዚአብሄር ፊት ሳዖልን ንጉስ አድርግልን ለምን አሉት ? (1 ሳሙ 10፡ 1፣ 24)
  4. በ 1ሳሙ (12፡ 13) ለህዝቡ እግዚአብሄር ምን አመለከታቸው ? ከፈሩት እና ካከበሩት እግዚአብሄር ምን እንደ ሚሆን ነገራቸው ? ካላከበሩት ምን ይፈጠራል ?
  5. 1ሳሙ (12፡ 23) አንብቡ ፤ ለሌላ ሰዉ አለመፀለይ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት እንደ መስራት አስባችሁታ ታዉቃላችሁ ? ለሆነ ሰዉ መፀለይ ማቆም ለምን እንደ ኃጢዓት ይታያል ? (ሐዋ 6፡ 4፣ ሮሜ 1፡ 9፣ ኤፌ 6፡ 17-18)
  6. በ 1ሳሙኤል (12፡ 23) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 12:22, 24

“The LORD will not abandon His people, because of His great name and because He has determined to make you His own people . . . Above all, fear the LORD and worship Him faithfully with all your heart; consider the great things He has done for you.”

ሳኦልና ሳሙኤል ባንድነት እስራኤላውያንን ከአሞናውያን ጋር በተደረገ ውጊያ ከመሩ በኋላ እስራኤላውያን ሳኦል ንጉሳቸዉ እንድሆን ተስማሙ ፡፡ ይህም ጊዜ ሳሙኤል የሚያርፍበት ሳኦል ደግሞ እንደ መሪ መንግስቱን የሚጀምርበት ጊዜ ነበር ፡፡ ሳሙኤልም በመጨረሻ የህዝብ ንግግሩ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን እንድፈሩ ፤ እርሱንም በሙሉ ልባቸው እንድያመልኩ እንድሁም ደግሞ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረጋቸዉን ታላላቅ ነገሮች እንድያስታውሱ አስጠነቀቃቸው ፡፡ ምንም እንኳ ለህዝቡ ምድራዊ ንጉስን መሾም የእግዚአብሔር አሳብ ባይሆንም እግዚአብሔር ህዝቡን ፈጽሞ ላይተው ቃል ገባ ፡፡

በአመታትም ሁሉ ህዝቡ አይኖቻቸውን በእርሱ ላይ እንድያደርጉ አግዚአብሔር ይናገር ነበር ፡፡ ያንተስ ? ያንተስ አይኖች በነገስታት ንጉስ በጌቶቸ ጌታ በሆነው በኢየሱስ ላይ ናቸው ? ወይስ የራስህ ህይወት መሪ ሆነህ ነው የምትኖሪው ? ጠላት አንተን ለማደናቀፍ ለመጣል ያሴራል ፤ ዓለም በጥፋት የተሞላች ናት ህይወትም ፈተናዎች አሉአት ፡፡ በነዚህ ጥፋቶችና ፈተናዎች ውስጥ እግዚአብሔር አለ ፡፡ እርሱ ፈጽሞ አይተውህም ፤ አንተ በስጋህ በምትወስንባቸው ጊዜያት ሳይቀር እርሱ ፈጽሞ አይተውህም ፡፡ ምንም ነገር ብትሰራ እግዚአብሔርን ካንተ ርቆ አይሄድም ፡፡ ዛሬ አይኖችህን ወደ ኢየሱስ ወደ ንጉሱ አንሳ እና እንደምትወደው ንገረው እርሱን ብቻ እንደምትወድ ፡፡ ወደ እርሱ ለመመለስ ፍርሀት ወይም ጭንቀት እስኪያሸንፍህ እስኪይዝህ አትጠብቅ ፡፡ አሁን ወደ እርሱ ተመለስ ፡፡

“ እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ወድዶአልና እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም ፡፡ ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አስተምራችኋለሁ እንጅ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ ፡፡ ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት ፡፡ “

-1ኛ ሳሙኤል 12፡22-24

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 28(29)፡10 –“ እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉስ ሁኖ ይቀመጣል ፡፡ “

ዕብራውያን 13፡5 –“አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን ያላችሁ ይብቃችሁ እርሱ ራሱ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና ፡፡ “

ራዕይ 15፡3 –“ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላከ ሆይ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው ጌታ ሆይ የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማነ ነው ? አንተ በቻ ቅዱስ ነህና የጽድቅም ስራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ ፡፡ “